ስህተትን ወደ ስኬት!
“ከተሳሳታችሁ በኋላ እንደገና መጀመርን አትፍሩ፡፡ እንደገና ስትጀምሩ እኮ የምትጀምሩት ከዜሮ ሳይሆን ከስህተታችሁ ትምህርትና ልምድ ካገኛችሁበት ደረጃ በመነሳት ነው - ካልታወቀ ምንጭ
ከትናንትናው ዛሬ አድጋችኋል፣ ተለውጣችኋል፣ በስላችኋል፣ ተሻሽላችኋል፣ ጥበብ አግኝታችኋል፣ በርትታችኋል፣ ነገሩ ገብቷችኋል . . . ፡፡
ከዛሬው ደግሞ ነገ የተሻላችሁ ሆናችሁ ማደጋችሁና መለወጣችሁ አይቀርምና ተነሱና ስሩ፣ ሞክሩ፣ ጀምሩ!
ብርቱ ነበራችሁ፣ አሁንም ብርቱ ናችሁ! ነገም ትበረታላችሁ!
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

የገንዘብ አቅም እጥረት ጉዳይ!
የገንዘብ አቅም እጥረት በራሱ ምንም ችግር የለበትም፡፡ ምክንያቱም ሁል ጊዜ በራሳችን ምርጫና ስህተት ችግር ውስጥ ስለማንገባ ማለት ነው፡፡
ይህ ማለት፣ ከቤተሰብ የወረስነው፣ የምንኖርበት ሃገራዊና ሕብረተባዊ ሁኔታ አንዳንድ አጋጣሚዎችና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የገንዘብ አቅማችን አናሳ እንዲሆን ሊያደርገው ይችላል፡፡
ችግር ያለበት . . .
• ላለብን የገንዘብ እጥረትና የኑሮ ትግል የምንሰጠውን ትክክለኛ ምላሽ አለማወቅ፣
• ባለብን የገንዘብ እጥረት ምክንያት የስሜት ቀውስ ውስጥ መግባት፣
• የኑሮ ደረጃን ከማንነት ዋጋ ጋር በማጣረስ በራስ ላይ ያለ አመለካከት መውረድ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ናቸው፡፡
እነዚህና መሰል ሁኔታዎች ላይ በሚገባ ከሰራንና በተረጋጋ ሁኔታ ከተንቀሳቀስን፣ የኑሮ ደረጃችን እስከሚሻሻል በሂደቱ እንጠነክራን፣ ጊዜው ሲደርስ ደግሞ ካለብን ጫና መላቀቃችን አይቀርም፡፡
ገንዘብን በትክክለኛው መንገድ ማግኘት (earning)፣ በሚዛዊነት ማዋል (spending)፣ በብቃት ማባዛት (multiplying)፣ በዲሲፕሊን ማጠራቀም (saving) እና በትክክለኛ መርህ መስጠት (giving) ካለንበት ከማንኛውም የገንዘብ ውጥረት ውስጥ እንድንወጣ መንገዱን ይጠርግልናል፡፡
በዚህ ርእስ ላይ ለመሰልጠን ፍላጎቱ ካላችሁ መረጃው ለእናንተ ነው፡፡
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo

ላለብን በኢኮኖሚ የማደግ ፍላጎት ከመጸለይና ፈጣሪን ከማን ባሻገር ማድረግ ያለብን . . .
በማንበብ፣ በመማር፣ በመሰልጠንና አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር ራስን ማሻሻል ነው፡፡
የተዘጋጀሎትን ስልጠና ለመከታተል መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል

ሶስቱ የስፍራችንን ትክክለኛነት የሚለዩ ጥያቄዎች
ስፍራ ማለት፣ የተሰማራንበት የስራ መስክ፣ ለመኖር የወሰነውን የመኖሪያ አካባቢ፣ የተቀላቀልናቸውን ጓደኝነቶችና ማሕበራዊ ግንኙቶች፣ እንዲሁም ሌሎችን የወደፊታችንን የሚወስኑ ሁታዎችን የሚወክል ጉዳይ ነው፡፡ ከተጠቀሱትና ከመሰል ሁኔታዎች አንጻር ውስጣችን ያመነበትን፣ ለእኛ ተስማሚና ትክክለኛ የሆነውን “ስፍራችንን” ማግኘት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ወደበለጠ ማብራሪያ ከመግባታችን በፊት፣ ያለንበት ስፍራ ትክክለኛ መሆኑንና አለመሆኑን ለመለየት መጠየቅ የምንችላቸው ጥያቄዎች አሉ፡፡
1. በዚህ ሁኔታና ስፍራ ውስጥ የአእምሮ ሰላም አለኝ ወይስ እረበሻለሁ?
2. በዚህ ሁኔታና ስፍራ ውስጥ በመቆየቴ የሕይወት ደረጃዬ እያደገ ይሄዳል ወይስ እያሽቆለቆለ?
3. ያለሁበት ሁኔታና ስፍራ ትክክል እንዳልሆነ እያወኩት በዚያ የቆየሁት ከፍርሃት የተነሳ ነው?
ትክክለኛውን ስፍራችንን ለይተን ያለማወቃችን ቀንደኛው አጉል ውጤት ቀስ በቀስ የስነ-ልቦና ቀውስ ከመግባታችንም ባሻገር፣ ያለንበት ስፍራ ምንም እንኳ ለወደፊት መሻሻልን የማይሰጠን ቢሆንም እንዲሁ ተቀብለን እዚያው የመክረማችን ጉዳይ ነው፡፡
ይህ ሲሆን፣ እድሜያችንን እንዲሁ እናባክናለን፣ በአንድ ስፍራ ተተክለን በመቅረታችን ምክንያት ትክክለኛና ለእኛ መሆን የሚገባቸው እድሎች ያመልጡናል፣ ውስጥጣችን ተስፋ ይቆርጣል . . . ፡፡ ስለዚህ ስፍራችንን ለይተን ለማወቅ ማድረግ ያለብንን ማድረግ የግድ ነው፡፡
ስፍራችንን ከለየን በኋላ እዚያ እስከምንደርስ ድረስ አሁን ባለንበት የመቆየታችን ሁኔታ ምንም ችግር የለበትም፡፡ ስፍራችንን ከለየን በኋላ ግን አሁን ያለንበት ቦታ ሆነን ካለማቋረጥ ወደትክክለኛ ስፍራችን የምንደርስብትን እቅድ ማውጣ አለብን፡፡ ያንን እቅድ ካወጣን በኋላ ደግሞ ጉዞ በመጀመር ካለማቋረጥ ወደዚያ መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ይህ እንቅስቃሴ የሚያስከፍለንን ሁሉ መስዋእትነት ከመክፈልም ወደ ኋላ አንበል፡፡
ሆኖም፣ ያለንበት ስፍራ ትክክለኛው እንዳልሆነ በመገንዘብና ወደ የት አልፈን መሄድ እንዳለብን ከለየን በኋላ፣ ለውጥ በማምጣት እዚያ መድረስ ከባድ መስዋእትነት እንደሚያስከፍል እስበን ያለንበት ከቀረን ግን የበለጠ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡
አንድ ነገር አንዘንጋ፡- ወደ ትክክለኛው ስፍራችን ለመራመድ ከምንከፍለው ዋጋ የበለጠ የምንከፍለው ትክክለኛ ስፍራችን ባልሆነ ቦታ በመቆየት ነው፡፡ በመንቀሳቀስ የአጭር ጊዜ ዋጋ እንከፍላለን፣ ያለንበት በመቅረት ግን የረጅም ጊዜ ዋጋ እንከፍላለን፡፡
ያለህበትን ስፍራ እንመልከት፣ ትክክለኛውን ስፍራችንን እንለይ፣ ከዚያም በጥንቃቄ እንወስንና ካለንበት ስፍራ የመቀየርን ጉዞ እንጀምር!

Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የገንዘብ አያያዛችን ጉዳይ!
በሚከተሉት አምስት የገንዘብ ዘርፎች መብሰል፣ ማደግና ሚዛናዊ መሆን የገንዘብ ነጻነትን ይሰጣል፡፡
1. ገንዘብን የማግኘት ክህሎት - የገንዘብ ገቢያችሁን ይጨምረዋል!
2. ገንዘብን ለጤናማ ዓላማ የመጠቀም ጥበብ - ገንዘብን በበጀት የመጠቀም ብልሃታችሁን ያሳድገዋል!
3. ገንዘብን ኢንቨስት በማድረግ የማባዛት ብቃት - በኢኮኖሚ ልቆ የመገኘትን መንገድ ይጠርግላችኋል፡፡
4. ገንዘብን የማጠራቀም ዲሲፕሊን - ለድንገተኛ ነገር ዝግጁ ያደርጋችኋል!
5. ገንዘብን የመስጠት ፈቃደኝነት - የሰብአዊነትና የእርካታ ስሜትን ይሰጣችኋል!
በእነዚህ ወሳኝ የገንዘብ ሂደቶች በበሰልንና ሚዛናዊ በሆንን ቁጥር የገንዘብ ነጻነትንና እድገትን እናገኛለን፡፡
ለዚህና ለመሰል ከገንዘብ ጋር ለሚገናኙ እውቀቶች የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
እናመሰግናለን!

የማስገባትና የማቆየት ሕግ
የማይለወጠው እውነታ፡- አንድን ነገር በእጃችን ባስገባንበት መንገድ ብቻ በእጃችን እናቆየዋለን!
እስቲ ቀድሞ የእኛ ያልነበረና አሁን ግን በእጃችን ላይ ያለ ማንኛውንም ነገር እናስብ፡፡ ከዚያም በእንዴት አይነት ሁኔታ በእጃችን እንዳስገባነውና የእኛ እንዳደረግነው እናስታውስ፡፡ ከዚያም ወደፊት ያንን ነገር በእጃችን ለማቆየት ያለንን ብቸኛ መንገድ ማወቅ ጊዜ አይፈጅብንም፡፡
በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ነገሮችን በእጃችን ለማስገባት እንጣጣራን፡፡ ያፈቀርነውን ሰው የእኛ ለማድረግ፣ ስራን ለማግኘት፣ ንግድን ለመጀመር፣ የተለያዩ ንብረቶችና ቁሳቁሶች ባለቤት ለመሆን፣ ስልጣንን ለመጨበጥ . . . ፍላጎታችን ዘርፈ-ብዙ ነው፡፡ ይህ ፍላጎት ሲጋጋል ደግሞ ምንም አይነት መንገድ ተጠቅመንም ቢሆን ያንን ነገር በእጃችን የማስገባታችንን ሩጫ ጥጉ ድረስ ይወስደዋል፡፡
አንድን ነገር የእኛ ለማድረግ የመፈለጋችንን ያህል፣ ያንን ነገር እጃችን ለማስገባት የምንጠቀምበትን መንገድ ጉዳይ አብረን ማሰቡ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ማንኛውንም ነገር በእጃችን ለማስገባት በተጠቀምንበት መንገድ ብቻ ነው ነገሩ እጃችን ከገባ በኋላ ማቆየት የምንችለው፡፡ ከጊዜያዊው ያላለፈ አይነት ሕይወት የመኖር ፍላጎት ካላደረብን በስተቀር፡፡
ሲተነተን . . .
• በኃይል እጃችን የገባን ነገር በእጃችን ለማቆየት ካለማቋረጥ ኃይልን መጠቀም አለብን፣
• በማታለል እጃችን የገባን ነገር ለማቆየት ካለማቋረጥ ማታለል አለብን፣
• በውሸት እጃችን የገባን ነገር ለማቆየት ካለማቋረጥ መዋሸት አለብን . . .
እያለ እውነታው ይቀጥላል፡፡ ከተርታው ሰው እስከ ተጽእኖ አምጪውና አልፎም እስከ አገር አመራሩ ድረስ እውነታው ፈጽሞ አይለወጥም፡፡
አንዲትን ሴት ለማግባት ካለው ፍላጎት የተነሳ የሌለውን ነገር እንዳለው የዋሸን አንድ ሰው ብናስብ፣ ተሳክቶለት ያችን ሴት ቢያገባት፣ ነኝና አለኝ ብሎ ያስተዋወቀው እንደሌለ እንዳይታወቅበት ምን አይነት ጡዘት ውስጥ እንደሚገባ ማስላት አያዳግትም፡፡ ቀድሞ ለማስታወቂያነት የተጠቀመበትን ድራማ እውን ማድረግ ሲያቅተው ግንኙነት መዛባት ይጀምራል፡፡
በስራውም መስክ ቢሆን እውነታው ይኸው ነው፡፡ የሌለንን ችሎታ እንዳለን፣ ያልሆንነውን ማንነት ደግሞ እንደሆንን አሳይተን በውሸት በገባንበት የስራ መስክ ውስጥ ለመቆየት ምን ማድረግ እንዳለብን መገመት አያስቸግርም፡፡ ካለማቋረጥ ስንሸፋፍንና ስንዋሽ ልንኖር ነው፡፡
መፍትሄው፣ አታላይነትን፣ ዛቻን፣ ኃይልንና ጉልበትን ተጠቅመን በወጣንበት የውሸት ከፍታ ላይ ለመቆየት እድሜ ልካችንን ስንታገልና ስንፍጨረጨር ከመኖር ይልቅ፣ ያለንንና የሆንነውን ትክክለኛውን ነገር አቅርበን በተረጋጋ ሁኔታ ውሎ ማደርና በልክ መኖር እጅግ የተመረጠ ነው፡፡

በገንዘብ አቅም የማደግ ትርጉም!
“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎቶች ማዳበር” ማለት ምን ማለት አይደለም
1. በሕብረተሰቡ መካከል ታወቂ ሃብታም የመሆን ፍላጎት ማለት አይደለም፡፡
2. እንደፈለግን የምናወጣው ገንዘብ ማካበት ማለት አይደለም፡፡
3. ገንዘብን ለማግኘት ካለልክ መሯሯጥና ምንም መንገድን ለመጠቀም ክፍት መሆን ማለት አይደለም፡፡
“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎቶች ማዳበር” ማለት ምን ማለት ነው
1. ትክክለኛ የገንዘብ ማግኛ መንገዶችን በመከተል በኢንቨስትመንት እያደጉ መሄድ ማለት ነው፡፡
2. ለእኛ እና ለቤተሰባችን በቂ የገንዘብ ገቢን በማግኝኘት መደላደል ማለት ነው፡፡
3. ገቢያችን እኛን እና ቤተሰባችን ካደረላደለ በኋላ ለድንገተኛ ሁኔታ እና ለተቸገሩትን ለመደገፍ የሚያስችለን የገንዘብ አቅም ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡
ይህንን ሚዛናዊ አመለካከት ስናዳብር፣ የሚያስፈልገንን ነገር (our needs) ከማሟላት አልፈን ከዓላማችን አንጻር ማድረግ ወደምንፈልገው ነገር (our wants) የማለፍ አቅም ይኖረናል፡፡
በዚህ ርእሰ-ጉዳይ ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማዳበር የሚጠቅማችሁ ስልጠና እደተዘጋጀላችሁ አትርሱ፡፡
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎቶች ማዳበር” ማለት ምን ማለት አይደለም
1. በሕብረተሰቡ መካከል ታወቂ ሃብታም የመሆን ፍላጎት ማለት አይደለም፡፡
2. እንደፈለግን የምናወጣው ገንዘብ ማካበት ማለት አይደለም፡፡
3. ገንዘብን ለማግኘት ካለልክ መሯሯጥና ምንም መንገድን ለመጠቀም ክፍት መሆን ማለት አይደለም፡፡
“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎቶች ማዳበር” ማለት ምን ማለት ነው
1. ትክክለኛ የገንዘብ ማግኛ መንገዶችን በመከተል በኢንቨስትመንት እያደጉ መሄድ ማለት ነው፡፡
2. ለእኛ እና ለቤተሰባችን በቂ የገንዘብ ገቢን በማግኝኘት መደላደል ማለት ነው፡፡
3. ገቢያችን እኛን እና ቤተሰባችን ካደረላደለ በኋላ ለድንገተኛ ሁኔታ እና ለተቸገሩትን ለመደገፍ የሚያስችለን የገንዘብ አቅም ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡
ይህንን ሚዛናዊ አመለካከት ስናዳብር፣ የሚያስፈልገንን ነገር (our needs) ከማሟላት አልፈን ከዓላማችን አንጻር ማድረግ ወደምንፈልገው ነገር (our wants) የማለፍ አቅም ይኖረናል፡፡
በዚህ ርእሰ-ጉዳይ ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማዳበር የሚጠቅማችሁ ስልጠና እደተዘጋጀላችሁ አትርሱ፡፡
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
“ሁል ጊዜ እንደተሳሳትኩ ነው … አንድ ቀን ትክክል ሆኜ አላውቅም … አመለካከቴ የተሳሳተ ነው … ብቃት የለኝም ... ሰዎች ወደፊት ሲገሰግሱ እኔ ግን ኋላ ቀርቻለሁ … አልቻልኩበትም … ዓላማየን አላውቀውም … እና የመሳሰሉት ስሜቶች ብዙ ሰዎችን የሚያጠቁ ስሜቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በተገቢው መንገድ ካልተያዙ ማንነትህን የማኮሰስና ወደኋላ የማስቀረት አቅም አላቸው፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እነዚህ ስሜቶች ሁሉም ሰው የሚጋራቸው ስሜቶች ናቸው፡፡ ሆኖም፣ እንደ ማንቂያ ደወል ከተጠቀምክባቸው መልካም ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እነዚህን ስሜቶች ለተስፋ መቁረጥ ከተጠቀምክባቸው ወደ ኋላ ይጎትቱሃል፡፡
ይህንን እውነታ አንድ ሰው በዚህ መልክ ይገልጽዋል፡-
በብልሽት ምክንያት ልክ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ የቆመ (አናሎግ) ሰዓትን ተመልከተው፡፡ ይህ ሰዓት ምንም እንኳን የቆመና ትክክል ያልሆነ ሰዓት ቢሆንም፣ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የቆመ ሰዓት በቀ ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል - ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ እና ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ፡፡ አየህ የተበላሸ ሰዓት እንኳን በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል፡፡ አንተ ደግሞ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
የቆመ ሰዓት በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ከሆነ፣ ምንም ያህል ስህተት የሰራህ ሰው ብትሆን፣ ምንም ያህል ወደፊት መራመድ እንዳቃተህ ብታስብ፣ ምንም ያህል የመሻሻል ነገር እንዳልታየብህ ብታምን፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!! የዛሬ አስር አመት፣ የዛሬ አምስት አመት፣ የዛሬ ሶስት አመት፣ የዛሬ አመት . . . የነበርክበትን አስብ፡፡ በትንሹም ቢሆን አሁን ከዚያ ትሻላለህ፡፡
ምናልባት፣ “እኔ ባለሁበት የቆምኩ ሰው ነኝ” ልትል ትችላል፡፡ ምናልባትም፣ “እኔ ባለፉት አመታት ከነበርኩበት ደረጃ የወረደ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት” በማለት ታስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሁኔታ እንኳን የተማርከውን ትምህርት አስበው፡፡ ሁኔታህ አለመሻሻሉ እየሰጠህ ያለውን የመንቂያ ደውል አስታውሰው፡፡ ማሰብ፣ ራስን መገምገም፣ ያለፈውንና የወደፊቱን ማስላት የመቻልህን ብቃት አስበው፡፡
ከዚህ አመለካከት ለመውጣት ከፈለክ፣ ከተሳሳትከው፣ ከማትችለው፣ ካልተሳካውና ካልሆነው አትነሳ፡፡ ምንም እንኳን ትንሽ ነው ብለህ ብታስብም፣ ከትክክለኛነትህ፣ ከተሳካልህና ከሆነልህ ነገር ተነሳ፡፡ በዚህ ስሜት ጫና ውስጥ ሆነህ ዘንግተኸው ነው እንጂ፣ ሌሎች ማድረግ የቻሏቸው ለአንተ ግን ያቀቱህ በርካታ ነገሮች የመኖራቸውን ያህል፣ ሌሎች ሰዎች ያቃታቸው አንተ ግን ማድረግ የምትችላቸው በርካታ ነገሮች እንዳሉ አትርሳ፡፡
ያም ሆነ ይህ፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
“ሁል ጊዜ እንደተሳሳትኩ ነው … አንድ ቀን ትክክል ሆኜ አላውቅም … አመለካከቴ የተሳሳተ ነው … ብቃት የለኝም ... ሰዎች ወደፊት ሲገሰግሱ እኔ ግን ኋላ ቀርቻለሁ … አልቻልኩበትም … ዓላማየን አላውቀውም … እና የመሳሰሉት ስሜቶች ብዙ ሰዎችን የሚያጠቁ ስሜቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በተገቢው መንገድ ካልተያዙ ማንነትህን የማኮሰስና ወደኋላ የማስቀረት አቅም አላቸው፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እነዚህ ስሜቶች ሁሉም ሰው የሚጋራቸው ስሜቶች ናቸው፡፡ ሆኖም፣ እንደ ማንቂያ ደወል ከተጠቀምክባቸው መልካም ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እነዚህን ስሜቶች ለተስፋ መቁረጥ ከተጠቀምክባቸው ወደ ኋላ ይጎትቱሃል፡፡
ይህንን እውነታ አንድ ሰው በዚህ መልክ ይገልጽዋል፡-
በብልሽት ምክንያት ልክ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ የቆመ (አናሎግ) ሰዓትን ተመልከተው፡፡ ይህ ሰዓት ምንም እንኳን የቆመና ትክክል ያልሆነ ሰዓት ቢሆንም፣ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የቆመ ሰዓት በቀ ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል - ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ እና ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ፡፡ አየህ የተበላሸ ሰዓት እንኳን በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል፡፡ አንተ ደግሞ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
የቆመ ሰዓት በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ከሆነ፣ ምንም ያህል ስህተት የሰራህ ሰው ብትሆን፣ ምንም ያህል ወደፊት መራመድ እንዳቃተህ ብታስብ፣ ምንም ያህል የመሻሻል ነገር እንዳልታየብህ ብታምን፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!! የዛሬ አስር አመት፣ የዛሬ አምስት አመት፣ የዛሬ ሶስት አመት፣ የዛሬ አመት . . . የነበርክበትን አስብ፡፡ በትንሹም ቢሆን አሁን ከዚያ ትሻላለህ፡፡
ምናልባት፣ “እኔ ባለሁበት የቆምኩ ሰው ነኝ” ልትል ትችላል፡፡ ምናልባትም፣ “እኔ ባለፉት አመታት ከነበርኩበት ደረጃ የወረደ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት” በማለት ታስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሁኔታ እንኳን የተማርከውን ትምህርት አስበው፡፡ ሁኔታህ አለመሻሻሉ እየሰጠህ ያለውን የመንቂያ ደውል አስታውሰው፡፡ ማሰብ፣ ራስን መገምገም፣ ያለፈውንና የወደፊቱን ማስላት የመቻልህን ብቃት አስበው፡፡
ከዚህ አመለካከት ለመውጣት ከፈለክ፣ ከተሳሳትከው፣ ከማትችለው፣ ካልተሳካውና ካልሆነው አትነሳ፡፡ ምንም እንኳን ትንሽ ነው ብለህ ብታስብም፣ ከትክክለኛነትህ፣ ከተሳካልህና ከሆነልህ ነገር ተነሳ፡፡ በዚህ ስሜት ጫና ውስጥ ሆነህ ዘንግተኸው ነው እንጂ፣ ሌሎች ማድረግ የቻሏቸው ለአንተ ግን ያቀቱህ በርካታ ነገሮች የመኖራቸውን ያህል፣ ሌሎች ሰዎች ያቃታቸው አንተ ግን ማድረግ የምትችላቸው በርካታ ነገሮች እንዳሉ አትርሳ፡፡
ያም ሆነ ይህ፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
የስልጠና እድል!
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል::

ጥያቄ፡-
ሰላም ዶ/ር
ከስንት አመታችን ጀምሮ ስራ መስራት አለብን? ከእድሜው እና ከጥቅሙ አብራራልኝ፡፡
መልስ፡-
ማንኛውም ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ ስራን መስራት መልመድ አለበት፡፡ እዚህ ላይ “ስራ” በምንልበት ጊዜ በሁለት ከፍለን መመልከት ይኖርብናል፡፡
1. ካለ ክፍያ መስራት
አንድ ልጅ መናገር እና በእግሮቹ መሄድ ከጀመረበት እድሜው ጀምሮ ከእድሜው ጋር የሚመጥን ስራን በቤተሰቦቹ ምሪትና አበረታችነት ቢሰራ ጥሩ ነው፡፡
ለምሳሌ፣ ከተመገበ በኋላ የበላበትን ሳህን ከጠረቤዛ ላይ ማንሳት አይነት ቀላል ስራ ጀምሮ፣ እድሜው እየጨመረ ሲሄድ ቀላላል የጽዳት ስራዎችን ቢሰራ መልካም ነው፡፡ እድሜው ወደ አስራዎቹ ሲገባ ደግሞ ቤተሰቦች የሚሰሩት የግል ስራ ካለ እሱ ላይ በተወሰነ መልኩ ሃላፊነትን እየተማረ ቢሄድ ተመራጭ ነው፡፡
ጥንቃቄ
• ልጆች የሚሰሩት ስራ በልጅነታቸው ሊኖቸው የሚገባን የጨዋታ ጊዜ እንዳይነካባቸው ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
• ልጆች ሲሰሩ ምንም እንኳን የገንዘብ ክፍያ ባይሰጣቸውም የመመስገን፣ የማድነቅና አንዳንድ ነገሮችን በመስጠት ማበረታታት መልካም ነው፡፡
• ልጆች ሲሰሩ በትንሹ ገንዘብ መስጠቱ ችግር ባይኖረውም ገንዘቡን ግን አጠራቅመው አንድ የግል ፍላጎታች ላይ እንዲያውሉት በመቆጣጠርና ማየት እፈላጊ ነው፡፡
2. ለክፍያ መስራት
አንድ ልጅ 18 ዓመት ከሞላው ጀምሮ ገንዘብን እየተከፈለው ቢሰራ የሚበረታታ ነው፡፡
ለምሳሌ፣ ራሱ የፈጠረውን ስራ፣ የቅጥር ስራ፣ ወይም የቤተሰቦቹን ንግድ ወይም ሌላ ስራ በማገዝ አቅጣጫ በክፍያ ቢሰራ የሚመከር ነው፡፡ ይህንን በማድረጉ ከልጅነት ወደ አዋቂነት፣ በሰው ላይ ከመደገፍ በራሱ ላይ ወደመደገፍ የመዘዋወርን ሂደት ቀስ በቀስ እንዲለምድ ያግዘዋል፡፡
ጥንቃቄ
• ወጣቶች ስራን ሲሰሩ በተቻለ መጠን የቤተሰብን ሃላፊነት ከመሸከም አንጻር ሁሉም ነገር በእነሱ ትከሻ ላይ ሊቀመጥ አይገባውም፡፡
• ወጣቶች ሲሰሩ ትኩረታቸው ገንዘብ ላይ ከመሆኑ የተነሳ ትምህርታቸውንና ለእድሜያቸው የሚመጥንን ሁኔታ ችላ እንዳይሉ መመልከትና ምሪት መስጠት የግድ ነው፡፡
• ወጣቶች ሲሰሩ ገንዘባቸውን በትክክለኛው ነገር ላይ ማዋላቸውንና ወደ ተላያዩ ሶሶች እንዳይገቡ ክትትል ያስለፍጋቸዋል፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ሰላም ዶ/ር
ከስንት አመታችን ጀምሮ ስራ መስራት አለብን? ከእድሜው እና ከጥቅሙ አብራራልኝ፡፡
መልስ፡-
ማንኛውም ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ ስራን መስራት መልመድ አለበት፡፡ እዚህ ላይ “ስራ” በምንልበት ጊዜ በሁለት ከፍለን መመልከት ይኖርብናል፡፡
1. ካለ ክፍያ መስራት
አንድ ልጅ መናገር እና በእግሮቹ መሄድ ከጀመረበት እድሜው ጀምሮ ከእድሜው ጋር የሚመጥን ስራን በቤተሰቦቹ ምሪትና አበረታችነት ቢሰራ ጥሩ ነው፡፡
ለምሳሌ፣ ከተመገበ በኋላ የበላበትን ሳህን ከጠረቤዛ ላይ ማንሳት አይነት ቀላል ስራ ጀምሮ፣ እድሜው እየጨመረ ሲሄድ ቀላላል የጽዳት ስራዎችን ቢሰራ መልካም ነው፡፡ እድሜው ወደ አስራዎቹ ሲገባ ደግሞ ቤተሰቦች የሚሰሩት የግል ስራ ካለ እሱ ላይ በተወሰነ መልኩ ሃላፊነትን እየተማረ ቢሄድ ተመራጭ ነው፡፡
ጥንቃቄ
• ልጆች የሚሰሩት ስራ በልጅነታቸው ሊኖቸው የሚገባን የጨዋታ ጊዜ እንዳይነካባቸው ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
• ልጆች ሲሰሩ ምንም እንኳን የገንዘብ ክፍያ ባይሰጣቸውም የመመስገን፣ የማድነቅና አንዳንድ ነገሮችን በመስጠት ማበረታታት መልካም ነው፡፡
• ልጆች ሲሰሩ በትንሹ ገንዘብ መስጠቱ ችግር ባይኖረውም ገንዘቡን ግን አጠራቅመው አንድ የግል ፍላጎታች ላይ እንዲያውሉት በመቆጣጠርና ማየት እፈላጊ ነው፡፡
2. ለክፍያ መስራት
አንድ ልጅ 18 ዓመት ከሞላው ጀምሮ ገንዘብን እየተከፈለው ቢሰራ የሚበረታታ ነው፡፡
ለምሳሌ፣ ራሱ የፈጠረውን ስራ፣ የቅጥር ስራ፣ ወይም የቤተሰቦቹን ንግድ ወይም ሌላ ስራ በማገዝ አቅጣጫ በክፍያ ቢሰራ የሚመከር ነው፡፡ ይህንን በማድረጉ ከልጅነት ወደ አዋቂነት፣ በሰው ላይ ከመደገፍ በራሱ ላይ ወደመደገፍ የመዘዋወርን ሂደት ቀስ በቀስ እንዲለምድ ያግዘዋል፡፡
ጥንቃቄ
• ወጣቶች ስራን ሲሰሩ በተቻለ መጠን የቤተሰብን ሃላፊነት ከመሸከም አንጻር ሁሉም ነገር በእነሱ ትከሻ ላይ ሊቀመጥ አይገባውም፡፡
• ወጣቶች ሲሰሩ ትኩረታቸው ገንዘብ ላይ ከመሆኑ የተነሳ ትምህርታቸውንና ለእድሜያቸው የሚመጥንን ሁኔታ ችላ እንዳይሉ መመልከትና ምሪት መስጠት የግድ ነው፡፡
• ወጣቶች ሲሰሩ ገንዘባቸውን በትክክለኛው ነገር ላይ ማዋላቸውንና ወደ ተላያዩ ሶሶች እንዳይገቡ ክትትል ያስለፍጋቸዋል፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (Trauma Bonding) ምንድን ነው?
በስነ-ልቦና ጤንነት ዘርፍ “Trauma Bonding” የተሰኘውን ሃሳብ ወደ አማርኛችን ለመመለስ ማብራራት የሚጠይቅ ጉይዳ ቢሆንም፣ የጉዳት (የስቃይ) የሚለው ትርጓሜ ለመነሻነት ያግዘናል፡፡ ሲብራራም በአንድ ሰው አመካኝነት አንድ የአእምሮ፣ የስሜት ወይም የስነ-ልቦና ጉዳት ሲደርስብን ከሁኔታው የተነሳ የሚከሰተውን መስመር የሳተ ሂደትንና ምላሽ ጠቋሚ ነው፡፡
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር የሚከሰተው የአእምሮ፣ የስሜት ወይም የስነ-ልቦና ክልላችን ሲጣስ ነው፡፡ ጥሰቱ የደረሰበት ሰው ቀስ በቀስ የደረሰበት ሁኔታ መብቱ ተጥሶ ሳይሆን ተገቢ ነገር እንደሆነ ወደማመን ሲመጣ ያለውን ሂደት የሚጠቁም ሃሳብ ነው፡፡ የሆነበት ነገር በአጋጣሚ እንደሆነና ጉዳቱን ያደረሰበት ሰው አውቆና ሆን ብሎ ሊጎዳው አስቦ እንዳላደረሰበት ወደማመን ሲመጣ ሂደቱ የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (Trauma Bonding) ይባላል፡፡
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (Trauma Bonding) በጓደኝነት፣ በፍቅር፣ በትዳርና በቤተሰብ ግንኙነቶች ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ ሲሆን ሰዎቹ ሆን ብለው እየጎዱንና ጥቃትን እያደረሱብን እንኳን ሁኔታውን እንደጉዳት ቆጥረን ተገቢውን ምላሽ የመውሰድ ፍላጎቱም ሆነ አቅሙ አይኖረንም፡፡
ለምሳሌ፡-
• የሆነብን ነገር ሁሉ በራሳችን ስህተት እንደሆነ አምነን እንድንቀበል (gas lighting) ያደርጉናል፡፡
• ከጎዳን ሰው ጋር ከተለያየን በኋላ ወደዚያው ጤና-ቢስና ጎጂ ግንኙነት ውስጥ እንደገና የመመለስ አዙሪት እንገባለን፡፡
• ሰዎቹ ለሚያደርሱብን ጉዳት ምክንያት በመፈላለግ እውነታውን ለመቀበል አለመፈለግ ያጠቃናል፡፡
• መርዛማና ጎጂ ከሆነ ግንኙነት ወስኖ ለመውጣት ያለመቻል ስሜት ይጫጫነናል፡፡
• ስለምናልፍበት ሁኔታ ለሌሎች ሰዎች ከተናገርን ሁኔታው ይፋፋማል በሚል ስጋት የጥቃቱን ሁኔታ ለሌሎች ሰዎች ለመናገር ድፍረት ማጣትና ዋጥ ማድረግ እናበዛለን፡፡
• እንደፈለጉ የሚያደርጉንንና የሚጎዱንን ሰዎች በግልጽነት ለመሞገት ፍላጎትና ድፍረት እናጣለን፡፡
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር” (“Trauma Bonding”) አስከፊ ውጤት
1. ውብ የሆነን ጊዜ ማባከን
ከነገ ነገ ይስተካከላል ብለን በምናስበው ሁኔታ ውስጥ እያለፍን አሁንም የማይስተካከል ከሆነና እኛም በዚያው ከቀጠልን፣ በጉዳት እና ራስን በማከም ሂደት ውስጥ ብዙ ልንሰራባቸውና ልንደሰትባቸው የምንችላቸውን አመታቶቻችንን እናባክናቸዋለን፡፡
2. የጤና ቀውስ
በተደጋጋሚ የስነ-ልቦና፣ የስሜትና የአካል ጥቃት የሚደርስት ሰው ብዙም ሳይቆይ ሊቀለበስ ለማይችል በሽታ ራሱን ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
3. የወደፊት ጸጸት
ዛሬ በዚህና በዚያ ያባከንናቸው አመታት፣ ያደከምነው የስሜት ሁኔታ፣ ያጣነው ጤንነትና መሰል ነገሮች ነገ እንደሚጸጽተን ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡
4. ሊረዱን ከሚችሉ ሰዎች እየተለያዩ መሄድ
በአሰቃቂ ትስስር ቁጥጥር ስር ስንውል ከሚያጋጥመን ሁኔታ አንዱ ከቅርብ ወዳጆቻችን መለየት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የሚከሰተው በአንድ በኩል በዚህ ውጣ ውረድ ውስጥ ስናልፍ ለማሕበራ ግንኙነት አቅም ስለምናጣ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሊረዱን የፈለጉ ሰዎችን ችላ በማለት ስለምናጣቸው ነው፡፡
ከተጠቀሰው ርእስ ጉዳይ እና በሌሎች የሕይወት አስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ጥያቄያችሁን ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ መላክ ትችላላችሁ፡፡
@DrEyobmamo
የዚህን ትምህርት ሁለተኛ ክፍል ዛሬ ከቀኑ በ6 ሰዓት ይጠብቁ፡፡
በሚቀጥለው ፖስቴ፣ “የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (“Trauma Bonding”) አስከፊ ውጤት” የሚለውን ሃሳብ እንመለከታለን፡፡