Telegram Web Link
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የጊዜ አጠቃቀማችሁ ጉዳይ!

⏱️ እናንተ ለጊዜያችሁ እቅድ ካላወጣችሁ፣ በእቅድ የሚኖረውን ሰው ዓላማ እንዳስፈጸማችሁ ትኖራላችሁ፡፡

⏱️እናንተ ጊዜችሁን በአግባቡ ካልተጠቀማችሁበት፣ ጊዜአቸውን በሚገባ በሚጠቀሙ ሰዎች ስር ጥገኛ እንደሆናችን ትኖላችሁ፡፡

⏱️ጊዜያችሁን በሚገባ ሳትጠቀሙ ስታባክኑት በእጃችሁ ያለውንም ሆነ ገና ልታስገቡት የሚገባችሁን ገንዘብ ታባክናላችሁ፡፡

⏱️የራሳችሁን ጊዜ ካላከበራችሁ፣ የሌሎችንም ሰዎች ጊዜ አታከብሩም፤ የሰዎችን ጊዜ ካላከበራችሁ ደግሞ ሰዎች እናንተን አያከብሯችሁም፡፡

⏱️ጊዜያችሁን በተደራጀ መልኩ ካልመራችሁት ራሳችሁንም ሆነ ስራችሁን በተደራጀ መልኩ መምራት አትችሉም፡፡

ኑሯችን የማያድገውና የማይሻሻለው አነዚህን የማይለወጡ ሕጎች ችላ ስለምንላቸው ነው፡፡

በዚህ ርእስ ላይ ነቃ ያለ ሕይወት መኖር ከፈለጋችሁ የተዘጋጀውን ስልጠና መውሰዳችሁን አትዘንጉ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
45👍17🔥2😱1
ጊዜ እንዳያመልጠን!

ጊዜ እያለን ልክ እንደሌለው የምንኖረው፣ ያንን ያለንን ጊዜ በሚገባ የማንጠቀምበት ከሆነ ነው፡፡

ጊዜያችን ሲባክን ደግሞ ባለን ጊዜ ሰርተን ማግኘት የሚገባንን ገንዘብም ሆነ ሌሎች የገንዘብ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች አብረው ይባክናሉ፡፡ ስለሆነም፣ ጊዜ ባከነ ማለት ሁሉም ነገር ባከነ ማለት ነው፡፡ ጊዜ አተረፍን ማለት ደግሞ ብዙ ነገር አተረፍን ማለት ነው፡፡

ማንኛውንም ነገር የምናተርፈው በቅድሚያ ጊዜያችንን ስናተርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ጊዜውን በትክክል ሲጠቀምና ጊዜ ሲተርፈው፣ ተጨማሪ ገንዘዝን ለማትረፍ የማሰቢያ እና የመስሪያ ጊዜ ያገኛል፡፡

የብዙ ነገራችን መዘባረቅ መነሻው ጊዜያችንን በትክክል ስለማንጠቀም ይሆን?

ጊዜያችሁን በውጤታማነት እንድትጠቀሙ የሚያግዛችሁ ወሳኝ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
57👍6🔥5
መላቀቅ! (Breaking free)
10👍2
መላቀቅ! (Breaking free)

ከአስቸጋሪ ሰዎች ለመላቀቅ ያልቻልንባቸው ምክንያቶች!

አንዳንድ ጊዜ በቅርባችን ያሉ ሰዎች በጣም የሚጎዳንን ተግባርና ባህሪይ እያሳዩና እየተጎዳን እንኳን ሁኔታውን ማረም ወይም ከሰዎቹ መለየት ያስቸግረናል፡፡

ይህ ሲሆን፣ ለምን እንደዚያ አይነት ባህሪይ እያንጸባረቅን እንደሆን መነሻውን ማግኘት አስፈላጊ ነው፡፡

1. የስሜት ትስስር

አንዳንድ ጊዜ ከሰዎች ጋር ብዙ ከተቀራረብንና ከእነሱ ውጪ መኖር የማንችል እስከሚመስለን ድረስ ራሳችንን ከሰጠን፣ ሁኔታው የስሜት ትስስር ይፈጥርና እየጎዱን እንኳን ከእነሱ መለየት ያስቸግረናል፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመፍታት ሰዎችን ስንቀርብ ራሳችንን እስከምናጣው ድረስ በእነሱ ላይ ከመደገፍ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡

2. አንድ ቀን ይለወጣሉ ብሎ መጠበቅ

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ደጋግመው አንድ አይነት አስቸጋሪ ባህሪይ እያሳዩን እንኳን እንደሚለወጡ በጭፍንነት የመጠባበቅ ዝንባሌ እናሳያለን፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመፍታት ሰዎች ማቆም በሚገባቸው እኛን የሚጎዳ ባህሪይና ተግባር አንጻር የቀይ መስመር ማበጀትና ጠንከር ማለት አስፈላጊ ነው፡፡

3. የምናገኘው ጥቅም እንዳይቀርብን

አንዳንድ ጊዜ ከሰዎች ከምናገኘው ጥቅም ውጪ መኖር እንደማንችል እናስብና እኛ የሚጎዳንን ባህሪያቸውን ከአቅም በላይ እንታገሳለን፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመፍታት በሰዎቹ ላይ እንደንደገፍ ያደረገንን ማንኛውም ድጋፍ ቀስ በቀስ እየቀነሱ በመሄድ ራሳችንን ወደመቻል መሸጋገር አስፈላጊ ነው፡፡

4. በራስ ላይ ያለ የወረደ አመለካከት

አንዳንድ ጊዜ የዝቅተኝነት፣ ራስን ያለመቀበልና በራስ ያለመተማመን ሁኔታዎች ሲያጠቁን አጉል ለሰዎች የመገዛትና ላመንንበት ነገር ያለመቆምን ሁኔታ ልናንጸባርቅ እንችላለን፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመፍታት ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ ራሳችንን የመቀበልን ስራ መስራት አስፈላጊ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የመፍትሄ ሃሳቦች በራሳችን የመተግባርን ብርታት የማዳበር አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንዳንድ ጊዜ ከአቅማችን በላይ ሲሆን ግን የአማካሪን እገዛ ማግኘት ወሳኝ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
73👍22🤩2😱1
ራሳችሁን ተከተሉ ብትባሉ ትከተሉታላችሁ?

ለመሪዎች . . .
በቤተሰብ፣ በድርጅት፣ በተቋም፣ በሕዝብም ሆነ በሃገር የአመራር ሂደታች፣ የአመራራችሁን ጤናማነት ለመገምገም ከፈለጋችሁ አንደኛውና ቀለል ያለው መንገድ ራሳችሁን ይህንን ጥያቄ መጠየቅ ነው፡፡

የግል ዲሲፕሊናችሁን፣ ለሰዎች ያላችን ርህራሄ፣ ከግል ጥቅም ይልቅ የምትመሩትህ ሕዝብ ጥቅም የማስቀደማችሁን ሁኔታ፣ ለዓላማችሁ ያላችሁን ጽንአትና የመሳሰሉትን ሁኔታዎቻችሁን ተመልከቱትና “ራሴን ከተከታዮቼ ቦታ ሆኜ ባየውና እኔ ራሴንው መከተል ቢኖርብኝ በእርግጥ የምከተለው አይነት ሰው ነኝ?” ብላችሁ ጠይቁ፡፡

ይህንን ጥያቄ ከልባችሁ ጠይቃችሁ ከመለሳችሁት ተከታዮቻችሁ በእናንተ ላይ ያላቸውን አመለካከት በመጠኑም ቢሆን ትደርሱበታላችሁ ብዬ አስባለሁ፡፡

ያንን ካያችሁ ደግሞ ተከታዮች ከመሪያቸው የሚፈልጉትን አይነት የተጽእኖ መሪ ለመሆን መስራትን አትዘንጉ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
52👍8😁1
ጊዜያችንን በትክክል ስንጠቀም!

⏱️ የበለጠ ገንዘብን ለመስራት የሚያስችል አደረጃጀት ይኖረናል፡፡

⏱️ ብዙ ስራ ለማከናወን በቂ ጉልበት ይኖረናል፡፡

⏱️ በትክክለኛው ነገር ላይ የማተኮር ብቃት ይኖረናል፡፡

⏱️ በማይሆን ስፍራና ሁኔታ ላይ ስለማናሳልፍ ስሜታችንን የመቆጠብ እድል ይኖረናል፡፡

ጊዜያችሁን በትክክል ተጠቀማችሁ ማለት ሕይወታችሁን በትክክል ተጠቀማችሁ ማለት ነው፡፡

በጊዜ አጠቃቀም ዙሪያ በቂ የሆነን ስልጠና ለማግኘት መመዝገባችሁን አትርሱ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
👍3225🎉6
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ሰዎች ስኬታማ የሚሆኑት!

አንዳንዶች እደዚህ ሲሉ ይደመጣሉ፡- “ስኬታማና ቢዚ ስሆን ጊዜዬን በሚገባ የማደረጃትን ስልት አዳብራለሁ”፡፡

ሁኔታው ግን የዚያ ተቃራኒ ነው፡፡ ስኬታማና ቢዚ የሆኑ ሰዎች እንደዚያ የሆኑት ጊዜያቸውን በትክክል መጠቀም ስጀመሩ ነው እንጂ ቢዜ ስለሆኑ አይደለም ጊዜያቸውን በትክክል መጠቀም የጀመሩት፡፡

የእነዚህን ሁለት ነገሮች ቅደም ተከተል ማዛባት፣ ፈጽሞ የማይመጣን ነገር ስንጠብቅ ጊዜያችንን እንድናባክን ያደርገናል፡፡
ጊዜያችሁን በሚገባ መጠቀም ስትጀምሩ ስኬታማ እየሆናችሁና ቢዚ እየሆናችሁ መሄዳችሁ አይቀርም፡፡ ስለዚህ፣ ጊዜያችሁን በሚገባ በማደራጀት አሁኑኑ ጀምሩ፣ የቀረው ተከትሎ ይመጣል፡፡

ይህንን ልምምድ ለማዳበር አቅጣጫ የሚያሳያችሁ ስልጠና ስለተዘጋጀ ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ሰልጥኑ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
47👍11😁1🎉1
እድገትና ምርጫ
11👍4
እድገትና ምርጫ
(“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

አንደኛው ምርጫህ ከዚህ በፊት ያስመዘገብካቸው ስኬቶች ላይ በመቆም እነዚያን ሲቆጥሩና ሲያወሩ መኖር ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ካለፈውና ከዛሬው የላቀ ሌላ ደረጃ እንዳለ በማመን ለአዲስ ነገር መነሳት ነው፡፡

ከ2 ሺህ አመታት በፊት አንድ ቲማንቲስ (Timanthes) የተሰኘ ወጣት የግሪክ ሰዓሊ ከታዋቂ አስተማሪ እግር ስር ተምሮ ነበር፡፡ ከብዙ አመት በኋላ አስተማሪው ተሳካለትና ተማሪው አስገራሚ ስእልን በመሳል አበረከተ፡፡ ይህ ጎበዝ ተማሪ ከዚህ በፊት የሚታወቀው በየቀኑ የሚስለው ስእል ላይ ትኩረቱን በመጣል ነበር፡፡ አሁን ግን ራሱ በሳለው ስእል እጅግ በመደነቁ ለብዙ ቀናት በየቀኑ እየመጣ የራሱን ስእል ፍጥጥ ብሎ በማየት ሲያደንቅ ይውል ነበር፡፡

አንድ ቀን ያንኑ በየቀኑ በመገረም ሲመለከተው የሚውለውን የራሱን ስእል እንደገና ለማየት በጠዋት ሲመጣ ግን ስእሉ በቀለም ተበለሻሽቶ አገኘውና በጣም ተበሳጨ፡፡ ወደ አስተማሪው ፈጥኖ በመሄድ ስእሉን አንድ ሰው እንዳበላሸበት ስሜታዊ ሆኖ ነገረው፡፡

አስተማሪውም ተማሪውን በማረጋጋት ያንን ያደረገው አስተማሪው ራሱ እንደሆነ ነገረው፡፡ በመቀጠልም “ይህንን ያደረኩበት ምክንያት ለአንተው ጥቅም ስል ነው፡፡ ይህ የሳልከው አስገራሚ ስእል እድገትህንና ወደፊት ልትፈጥር የምትችለውን አዲስ ስእል እንዳትስል እንቅፋት እየሆነብህ ነው፡፡ ሌላ የፈጠራ ስራ መስራት ስትችል በዚህ ስእል በመደመም እሱን ስታይ ነው የምትውለው፡፡ በል፣ እንደገና እንደ አዲስ ጀምርና የተሻለ ነገር ታከናውን እንደሆነ እስቲ ተመልከት” አለው፡፡ ተማሪው የአስተማሪውን ምክር ተቀበለና ወደ ስእል ስራው በመመለስ ከጥንታዊ ታዋቂ ስእሎች መካከል በውበቱ እጅግ የተመሰከረለትን አስገራሚ ስእል አበረከተ

አንዳንድ ጊዜ ያለፈው ስኬት ለነገው እድገት እንቅፋት የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያት ሰዎች ባለፈው ካከናወኑት ነገር የተነሳ በዚያ ላይ ሲረጉ ነው፡፡ ስለዚህም አሁን የደረሰበት ደረጃ ወደፊት ሊደረስበት ከሚችለው የላቀ ደረጃ ሲገድባቸው ይታያል፡፡

የትናንት ስኬት ለነገ እድገትህ መንገድ ሊጠርግ ሲገባው ካሰብነውና በውስጠ-ህሊናችን አይተን ከተነሳነው ፍጻሜ ካስቆመን የጥሩ ምርጫ ሰው አይደለንም፡፡ እኛ ያከናወንነውን ስናይና ስለእሱ ስናወራ ዙሪችን አልፎን እንደሚሄድና ወደላቀ ደረጃ ደርሶ እንደሚቆየን እንዳንዘነጋው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰዎች በኋላ ከእኛ ክንዋኔ የላቀና የሚደነቅ ነገር ይዘው ብቅ ሲሉ የሚኖርብን የስሜት ቀውስ ቀላል አይሆንም፡፡

አያችሁ፣ ያቃታቸው የመሰላቸው ሰዎች በተስፋ መቁረጥ ሲፈዙ፣ የተሳካላቸው የመሰላቸው ደግሞ “በማን ይደርስባኛል” ስሜት ሊፈዙ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ እስካሁን ከደረስንበት ደረጃና ካከናወንናቸው ታላላቅ ነገሮች የላቀ ነገር ይጠብቀናልና አልፈን እንሂድ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
58👍31🔥1
የጊዜ ውስንነት!

አንድ አሰልጣኝ ለስልጠና በአንድ ክፍል ውስጥ ለሞሉ ሰዎች እንዲህ አላቸው፣ “እስካሁን ለማድረግ ጊዜ ያላገኛችሁላቸውንና ጊዜ ቢኖራችሁ ማድረግ የምትፈልጉአቸውን ሶስት በጣም አስፈላጊ ነገሮች ጻፉ”፡፡

የተጠየቁትን እንዲያደርጉ ሶስት ደቂቃ ከሰጣቸው በኋላ በመቀጠል፣ “አሁን ደግሞ ለእነዚህ ማድረግ ለምትፈልጓቸው ሶስት ነገሮች ጊዜ እንድታገኙ አሁን በማድረግ ላይ ካላችሁት ነገሮች መካከል የምትቀንሷቸውን ሶስት ነገሮች ጻፉ” አላቸው፡፡

ይህኛው ጥያቄ ለብዙዎቹ ከባድ ነበር፡፡ አሰልጣኙ ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክት፣ ጊዜ እንደማንኛውም ቁሳቁስ ተጨባጭ የመሆኑን እውነታ ነው፡፡

አንድ ጢም ብሎ የሞላ ሻንጣ ውስጥ ሌላ ልብስ ለመጨመር፣ ከነበረው ውስጥ መቀነስ የግድ እንደሆነ ሁሉ፣ አንድ ተግባር ለመጀመር ሌላ ተግባር በመቀነስ ጊዜን ማመቻቸት የግድ ነው፡፡ ያገኘነውንና የፈለግነውን ልብስ ሁሉ በአንድ ሻንጣ ውስጥ እንደማንጨምረው፣ ያገኘነውንና የፈለግነውን ተግባር ባለችን ውስን ጊዜ ውስጥ መጨመር አንችልም፡፡

በጊዜ አጠቃቀም ላይ ሰፊና ተግባራዊ እውቀትን የሚሰጣችሁ ስልጠና ተዘጋጅቷል፡፡

ለመረጃው ፖሰትሩን ይመልከቱ!

ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

Have a great day!
66👍11
ጊዜና ትኩረት!

በሕይወታችን ጊዜያችንን በከንቱ ከሚያባክኑብን ስህተቶች መካከል፣ መለወጥ ወይም መቆጣጠር በማንችላቸው ሁኔታዎች ላይ የማተኮር ልማድ ቀንደኛው ነው፡፡

አያችሁ፣ አንዳንድ ሁኔታዎችነ ምንም ብናደርግና ብንጨነቅ ልንለውጣቸው አንችልም፡፡ አንዳንድ ሁኔታዎች ግን በማቀድ፣ በመደራጀትና ጊዜያችንን በትክክል በመጠቀ ልንለውጣቸውና መስመር ልናስይዛቸው እንችላለን፡፡

ጊዜያችሁን በተገቢው መንገድ በመጠቀም ለለውጥ ስሩ፡፡

በዚህ ርእስ ላይ የተዘጋጀላችሁ ስልጠናም አያምልጣችሁ፡፡ በርካቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡ እናነትም ዛሬው ተመዝገቡና ተሳተፉ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
45👍7
የ30 ቀናት Challenge!

እስኪ ለሚቀጥሉት 30 ቀናት የሚከተሉትን ልማዶች ለማዳበር ሙከራ አድርጉ፡፡ የግላችሁ የኑሮ እና የስራ ሁኔታ አስቸጋሪ የሚያደርጋቸውን ልምምዶች የመኖራቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የምትችሉትን አድርጉ፡፡

1. በየቀኑ በውስጣችሁ የሚብሰለሰሉ አዎንታዊም ሆኑ አሉታዊ ሃሳቦችና ስሜቶች ለመጻፍ ሞክሩ፡፡

2. በየቀኑ ገንዘብን ከማግኘትም ሆነ ከውስጥ እርካታ አንጻር አንድን ጠቃሚ ክህሎት በonline ራሳችሁን ለማሰልጠን ሞክሩ፡፡

3. በየቀኑ ቢያንስ የአንድ ጠቃሚ መጽሐፍ 3 ምእራፍ ለማንበብ ሞክሩ፡፡

4. በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት ወደ መኝታ ለመሄድና ጠዋትም በተመሳሳይ ሰዓት ለመነሳት ሞክሩ፡፡

5. በየቀኑ ቢያንስ ለአንድ ሰው የሚያበረታታ ንግግርን ለመናገር ወይም አንድን መልካም ተግባር ለማድረግ ሞክሩ፡፡

6. በየቀኑ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ለማድረግ ሞክሩ፡፡

7. በየቀኑ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ የሚሆን ጊዜ ለብቻችሁ በጸጥታ ለማሳለፍ ሞክሩ፡፡

8. በየቀኑ ቢያንስ የ30 ደቂቃ ጊዜ በመውሰድ ግቦቻችሁን መጻፍንና መገምገምን ለመለማመድ ሞክሩ፡፡

ነገ ይጀመር!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍10274🔥7🤩2
ትልቁ ሃብታችን!

ጤንነታችን እና በዙሪያችን የሚገኙ የሰው-ለሰው ግንኙነቶች እንደ ሃብት የመቆጠራቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሕይወታችን እንደ ሃብት የምንቆጥራቸው ሶስት ዋና ዋና ነገሮች አሉ፡፡

እነዚህም፣ 1) የገንዘብ ሃብት፣ 2) የእውቀት ሃብት እና 3) የጊዜ ሃብት ናቸው፡፡

ከእነዚህ ሶስት ሃብቶች አንዱ ኖሮን ሌላው ሲጎድለን፣ ካለን ሃብት በመነሳት ሌላውን ማምጣት እንችላለን፡፡

ማንኛውም ሰው ምንም እንኳን ገንዘብ እና እውቀት ባይኖረውም እንኳን ለሁሉም የተሰጠ እኩል ጊዜ ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን ጊዜ በትክክል በመጠቀም የገንዘብንም ሆነ የእውቀትን ሃብት ማምጣትና እያባዙ መሄድ ይቻላል፡፡

ይህንን ሂደት እንድትጀምሩ የሚያግዛችሁ ስልጠና ተዘጋጅቷል፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
65👍10🔥3🎉2
ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር!

ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በደረሰበት አንዲት ከተማ ውስጥ በተሰጠው እርዳታ ትንሽ አገገመ፡፡

የዚህን ሰው ጉዞ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው፡፡ ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ነበር? ምግብ ማጣት ነበር? አውሬ ነበር? ሽፍቶች ነበሩ? ወይስ . . . ?

የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር፡፡

የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡

“በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡

በርቱ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
171👍43🔥5😁3
ውድ የተባለው ነገር!

ውድ የተባለው ነገር ገንዘብ ሳይሆን ጊዜ ነው፤ ጊዜያችንን በአግባቡ ከተጠቀምን ገንዘብ ማግኘትና ማባዛት ስለምንችል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ፣ ብዙ ጊዜያችንን እየበላ ጥቂት ትርፍ ከሚሰጠን ስራ አልፎ በመሄድ ጥቂትን ነገር በጥበብ በመስራት ውጤታማ መሆን ይቻላል፡፡ ይህንን ልምምድ ለማዳበር ግን የጊዜን ትርጉም፣ አስፈላጊትና አጠቃቀም በማወቅ መብሰል የግድ ነው፡፡
ስልጠናው አያምልጣችሁ!

መረጃውን ከፖስተሩ ላይ ያገኛሉ

ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

Thank you!
69👍14😱1
የትምህርት ቤት ክፍያ
👍107
የትምህርት ቤት ክፍያ

አንዳንድ ሰዎች ለምን እንደማይማሩ ሲጠየቁ፣ “ትምህርት ቤት መማር ብዙ ዋጋ ያስከፍላል” ይላሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ልክ ነው መማር ያስከፍላል - ገንዘብን፣ ጊዜን፣ እንቅልፍን፣ ጉልበትን . . . ያስከፍላል! ነገር ግን መማር ከሚያስከፍለው ይልቅ አለመማር ያስከፍላል፡፡ መማር አሁን ያስከፍልና ነገ ይከፍላል፤ አሁን ያደክምና ነገ ያሳርፋል፡፡ አለመማር ግን፣ “አሁን ዘና በል” በማለት ነጻ ይለቀንና እድሜ ልካችንን እያስከፈለና እየገዘገዘን ያከርመናል፡፡

ከላይ የተጠቀሰው የመደበኛ ትምህርት ሂደት እውነታ መደበኛ ባልሆነው የየእለት የሕይወት ትምህርትም አንጻር ያው ነው፡፡ ለነገው ሕይወታችን ጥበብን፣ ልምድንና የሕይወት ተሞክሮ ተግባራዊ እውቀትን የምናገኝበት ብቸኛ መንገድ ዛሬ አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር ከምንሰራቸው ስህተቶች የተነሳ ነው፡፡ በሌላ አባባል ሲገለጽ፣ ስህተት ማለት ለነገ የሕይወት ስኬት ዛሬ የምንከፍለው የትምህርት ቤት ክፍያ ነው፡፡

“በሕይወታችን ሁለት ፍላጎቶች ብቻ ናቸው ያሉን፡፡ አንደኛው ሁል ጊዜ መማር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሁል ጊዜ ሳይሳሳቱ ትክክል መሆን” (Errol Gerson)፡፡ እነዚህን ሁለቱንም ነገሮች ግን በአንድ ላይ ማስኬድ አንችልም፡፡

ሁል ጊዜ ትክክል መሆን ከፈለግን አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እናቆማለን፡፡ ያን ጊዜ ሕይወት ይቆማል - ትልቁና የመጨረሻው ስህተት!፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሁል ጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ከሞከርን መሳሳታችን አይቀርም - ታላቁና ውጤታማው ስኬት መንገድ!
ሁል ጊዜ አዳዲስ ነገሮችን የመሞከርን መንገድ የመረጥን ጊዜ ሕይወት በብዙ ልምድ፣ ልምምድ፣ ጥበብና እውቀት ታሸበርቃለች፡፡

ዛሬ አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር የምንከፍለው ዋጋ ለነገው ሕይወታችን ስኬታማነት የሚከፈል ስለሆነ ማለት ነው፡፡

ተንቀሳቀሱ! ጀምሩ! ስሩ! ከተሳሳታችም ከስህተታችሁ በመማር ለነገ የተሻለ ማንነት ያዙ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
62👍25
የጊዜ አጠቃቀም ችግራችን መንስኤ ከሶስቱ አያልፍም!

1. ዓላማን አጥርቶ አለማወቅ

የምንኖርለትን ዓላማ በሚገባ ለይተን ካላወቅን ይህንና ያንን ስንከታተል ጊዜያችን ይባክናል፡፡

2. የዲሲፕሊን አለመኖር

ምንም እንኳን ዓላማችንን አውቅ ብንነሳም የመጀመርና የጀመርነውን እስክ ጥጉ የመቀጠል ዲሲፕሊን ከሌለን ጊዜያችንን በአግባቡ መጠቀም አንችልም፡፡

3. የክህሎት ጉድለት

ዓላማውን ያወቀና በጣም ዲሲፕን ያለው ሰው የአደራረግ ክህሎቱን ካላዳበረ ብዙ በመልፋትና ጥቂት ውጤት በማግኘት ጊዜውን የሚያባክን ይሆናል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀውን ስልጠና መከታተላችሁን እርግጠኞች ሁኑ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
56👍23🔥4
16👍4
2025/10/26 04:15:04
Back to Top
HTML Embed Code: