Telegram Web Link
Forwarded from Anteneh Nurlign
የኢትዮጵያ ጤና ሙያ ተማሪዎች ማህበር ከሕጻናትና አቅመ ዳካማ አረጋዊያን ጋር የገና በዓልን አሳልፏል

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ጤና ሙያ ተማሪዎች ማህበር ባህር ዳር ቅርንጫፍ እንዲሁም ሌሎች በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚገኙ ክበባት እና ማህበራት በተጨማሪም የተማሪ ህብረቶች ከዝግባ ሕጻናትና አረጋዊያን መርጃ  በጎ አድራጎት ድርጅት በመረዳት ላይ ለሚገኙ ወገኖች የምሳ ግብዣ በማድረግ በዓልን አሳልፈዋል።

በዚህም ተግባር የብዙዎችን አረጋውያን ና ህፃናት ሳቅ ማየት ችለናል። በተጨማሪም በመርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ተገኝተው ድርጅቱን በመጎብኘት ለዚህ መልካም ተግባር ትኩረት ለሰጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች አድናቆታቸውን ችረዋል።

ለዚህ ተግባር መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ የኢትዮጵያ ጤና ሙያ ተማሪዎች ማህበር አባላት በሙሉ ጥልቅ ምስጋናየን ማቅረብ እወዳለሁ።

የኢትዮጵያ ጤና ሙያ ተማሪዎች ማህበር ባህር ዳር
👍5
EHPSA debremarkos had commemorated christmas with enat debre markos children village and EHPSA debremarkos had donated 32 inch TV to the organization and we spent a good memorable time with the children there.

Lead By Example Inspire With Action!

Ethiopian Health Profession Students Association-EHPSA Debremarkos Branch

Join Our Channel:👉🏻 https://www.tg-me.com/EHPSA
👍5🔥2👏2
Forwarded from Abebaw
📌ዝግባ የሕፃናት እና አረጋውያን መርጃ ድርጅት ለማሕበራችን EHPSA የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ።

ከዚህ በፊት እንደተገለፅነው ዝግባ የሕፃናት እና አረጋውያን መርጃ ድርጅት የገና በዓልን ምክንያት  በማድረግ ከ EHPSA እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ተማሪ አደረጃጀቶች ጋር ለነበረው በጐ ትብብር ዛሬ 04/05/2017 ዓ.ም ባዘጋጀው የምስጋና መርሐግብር አረጋውያን እና የተለያዩ አጋር አካላት በተገኙበት የምስጋና ሰርተፊኬት ለ EHPSA Bahir Dar ፕሬዝደንት አንተነህ ኑርልኝ አስረክቧል።
የድርጅቱ ኃላፊ አቶ ስለሺ ዝግባ ከ 16 ዓመት በላይ ጧሪ የሌላቸውን ሕፃናትና አረጋውያን (በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከ2600 በላይ የሚሆኑ) ሰብስቦ እያኖረ መሆኑን ገልጸው ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል በሚችለው መልኩ እንዲያግዝ እና የእኛንም(የEHPSA) የወደፊት አጋርነታችን አጠናክረን እንድንቀጥል ጠይቀዋል።

🔗በዚህ መልኩ እውቅና ለሰጠን እያመሰገንን:- ውድ የEHPSA Bahir Dar አባላቶቻችን ሆይ ማሕበራችን ለማሳደግ ወደፊት በተለያዩ ስራዎችን የምንቀጥል ስለሚሆን ቅንነታችሁ ትብብራችሁ እንዳይለይ እናሳስባለን።

#EHPSA_Bahir_Dar
👍61👏1
2025/07/09 21:59:36
Back to Top
HTML Embed Code: