#የመስቀል_ክብረ_በዓላት_
#መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፤
#መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤
#መስከረም_10_ተቀጸል_ጽጌ_፤
#መጋቢት_10_መስቀሉ_የተገኘበት_በዓል፤
#ደመራ_፤ ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ያወቀችበት ዕለት ነው፡፡ ጥንተ ታሪኩም፤ ክርስቶስ በሞተ ጊዜ የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በጌታ መካነ መቃብር ጎልጎታ ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት የኢየሩሳሌሙ ኤጲስ ቆጶስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገው እነርሱም ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱ በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠዋትና ማታ በጎልጎታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተአምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ መፈወስ ጀመሩ፤ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ሳባቸው፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ በመውሰድ ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየተጣለበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆየ፡፡ በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጕዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንቱ ትዕምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ /በዚህ ምልክት ድል ታደርጋለህ/›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት ድል በማድረጉ ነው፡፡
የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመኾኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው እርሱም ሦስት ተራሮችን ጠቆማትና ከሦስት ተራሮች የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ግን በእግዚብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ /አስደምረሽ/ ዕጣን አፍስሺበትና በእሳት አያይዥው የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጭሽ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡ ደመራ ማለትም፤ ደመረ፣ ጨመረ፣ አንድ አደረገ፤ ከሚለው የግእዝ ቃል የተወረሰ ሲሆን መቀላቀልን፣ መገናኘትን፣ መሰብሰብን፣ መጣመርን፣ መዋሐድን በአጠቃላይ ሱታፌን፣ አንድነትን እና ኅብረትን ያመለክታል፡፡
#መስቀል_፤ መስከረም 17 ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት መስቀሉ እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽቦችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡
#ተቀጸል_ጽጌ_(#መስከረም_10_/#አፄ_መስቀል_/)፤ መስቀሉ ወደ ሃገራችን የገባባት ዕለት ነው፡፡
#መስከረም_21_፤ መስቀሉ መስከረም 10 ቀን ቀን ወደ ሃገራችን ከገባ በኋላ ‹‹መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ›› በተባለው ቃል መሠረት ከብዙ ፍለጋ በኋላ መስከረም 21 በግሸን ደብር ከርቤ ያረፈበት ዕለት ነው /ዝርዝሩን መስከረም 21 ይጠብቁ/፡፡
✤፠ንግስት እሌኒ በመስከረም 16 ቀን ደመራ አስደምራ፤ ፠፠✤✤መስከረም 17 ቁፋሮ አስጀምራ ፠፠፠✤✤✤በመጋቢት 10 ቀን ቁፋሮ ተጠናቅቆ መስቀሉ ተገኝቷል፡፡
(በደብራችን በአ.አ በብቸኝነት ከንግሥት ዘውዲቱ ጀምሮ በደብራችን የመስቀል ክብረ በዓል መስከረም 17ና መጋቢት 10 ይከብራል፤ ላልሰማው ያሰሙ፡፡ እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ ሙሉ ሥርዐተ ማኅሌቱን (ዘመድኀኔዓለምና ዘአደባባይ ብለን) አቅርበንላችኋል፡፡)
እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ፤ መስከረም 16ና 17፤ በደመራው (በርጥብ እንጨት ለሚደመረው ደመራ)፣ በዋይዜማው፣ በማኅሌቱ፣ በሰዐታቱ፣ በኪዳኑ፣ በቅዳሴው፣ በዑደተ ታቦተ ሕጉ፣ የመስቀሉን እምነት ግናባራችንን ለመቀባት በቀጨኔ ደብረ ሰላም እንገናኝ፡፡
፠ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን፤ የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡
፠ "በወንጌሉ ያመናችሁ፤ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፡፡"
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር
/ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ ባጭሩ የተወሰደ፡፡
https://www.tg-me.com/EOTC2921
https://www.tg-me.com/EOTC2921
https://www.tg-me.com/Ethio_Orthodox1

Telegram
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

🙏3❤2
✔✞ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ 2 ቁጥር 14
14-15 እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥
16 ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።
✔✞መዠመሪያዪቱ፡የሐዋርያው፡የቅዱስ፡ጳውሎስ፡መልእክት፡ ወደቆሮንቶስ፡ሰዎች። ምዕራፍ፡1፤
18፤የመስቀሉ፡ቃል፡ለሚጠፉት፡ሞኝነት፥ለእኛ፡ለምንድን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ኀይል፡ነውና።

👍3❤2
negere meskel.pdf
445.6 KB
https://www.tg-me.com/EOTC2921
🌾✞ #መስቀል ✞🌾
ስለመስቀል ሰፊ መረጀ በውስጡ፦
✔መስቀል በኢትዮጵያ
✔ማዕተብና ክታብ
✔የመስቀል ከማዕድናት አሰራር ትርጉም
✔መስቀሉ እንዴት ጠፋ?
✔ስለ ደመራ እና ሌሎችንም የሚያገኙበት
•
•
🌾✞ #መስቀል ✞🌾
ስለመስቀል ሰፊ መረጀ በውስጡ፦
✔መስቀል በኢትዮጵያ
✔ማዕተብና ክታብ
✔የመስቀል ከማዕድናት አሰራር ትርጉም
✔መስቀሉ እንዴት ጠፋ?
✔ስለ ደመራ እና ሌሎችንም የሚያገኙበት
•
•
❤4
Forwarded from የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
#መስቀሌን_በመስቀለኛ_ስፍራ_አኑር ✞
✞ መስቀሌን በመስቀለኛ ስፍራ አኑር በተባለበት ግሼን ደብረ ከርቤ ማርያም ተገኝተው ለማየት የቻሉ ሁሉ እጅግ የታደሉ ናቸው!!
➣ግሽን በጥንት ፍጥረት በመስቀል ቅርጽ ተፈጥራ ዙሪያዋን በአራቱም አቅጣጫ በገደል የተከበበችና አንድ መግቢያ ብቻ ያላት ድንቅ የሆነች ታሪካዊ ቦታ ነች፡፡ ግሸን ደብረ ከርቤ ዳግማዊ እየሩሳሌም የተቆረቆረችው በ517 ዓ.ም በንጉስ ካሌብ ዘመነ መንግስት ሲሆን የመሰረቷትም የአፄ ካሌብ ክርስትና አባት የሆኑት አባ ፍቃደ ክርስቶስ የተባሉ መናኝ ባህታዊ መነኩሴ እንደነበሩ ታሪክ ያስረዳል፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማሪያምንና የእግዚአብሄርአብን ጽላቶች ከሀገረ ናግራን /በዛሬው አጠራር የመን ከተባለውና በዚያን ዘመን የኢትዩጵያ ግዛት ከነበረው ቦታ ይዘው በዘመኑ አጠራር መቃድስ በአሁኑ ሞካድሾ/ሶማሊያ/ በኩል አድርገው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት የበሸሎን ወንዝ ተሻግረው እረጅም ጉዞ በማድረግ አቀበቱን ወጥተው ወደ መስቀለኛው አምባ ጥግ ሲደርሱ በተፈጥሮ የመስቀል ቅርፅ ካለው ይህ አስደናቂ አምባ መወጣጫ ሲፈልጉ በገደሉ ላይ ንብ ሰፍሮ ማር ተጋግሮበት በማየታቸው የአካባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ ሲያደንቁ ይህስ “አምባሰል ነው” በማለት ተናገሩ ይባላል፡፡
✞ አባፈቃደ ክርስቶስ በእግዚአብሄር ፈቃድ የእግዚአብሄር አብንና የእምቤታችን ጥላቶች ይዘው ወደ አምባው በመግባት ሁለት ትንንሽ የሳር ጎጆዎችን አስቀልሰው በመግባት በዚያው የብህትና ኑሯቸውን በማከናወን እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው እንደኖሩ ይነገራል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቦታው እግዚአብሄር ሲወደስና ሲቀደስ ከኖረ በኋላ በዘመኑ ለነበሩ የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ዘርያቆብ “አንበር መስቀል በዲበ መስቀል” መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ” የሚል ቃል በመንፈስ እግዚአብሔር ራዕይ ተገለፀላቸው፡፡
✞ አባታቸው አፄ ዳዊት ከግብፆች ተረክበውት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በመንገድ ላይ በመሞታቸው ምክንያት ከመንገድ ላይ እንዲቆይ የተደረገውም ቅዱስ መስቀል እና ልዩልዩ ንዋያተ ቅዱሳትን ከግብፆች ተረክበው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ በ1446ዓ.ም አጼ ዘርያቆብ መስቀሉን አስይዞ መስቀለኛ ቦታ ለማግኘት አያሌ የኢትዮጵያ ተራሮችን እየተዘዋወሩ ካዩ በኋላ በመጨረሻም የግሸን አምባን ስላገኙ ቅዱስ መስቀሉን አስይዘው ወደ አምባው ጥግ ከስፍራው እንደደረሱ ወደ ውስጥ ሳይገቡ ዙሪያውን ሦስት ጊዜ በመዞር ከውጭ አደሩ።
✟ በራዕያቸውም ተነስተህ በስተምስራቅ በኩል ግባ አላቸው እርሳቸውም ተናጋሪውን ሳይሆን ንግግሩን በማስተዋል እንደታዘዙት በብቸኛዋ መግቢያ ምስራቃዊ በኩል ገብተው አምባው እንብርት ወርዱና ቁመቱ አርባ ክንድ የሆነ ጉድጓድ አስቆፍረው የእየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀልን በወርቅና እንቁሳጥን ከዚያም በሸክላ ሳጥን አድርገው በመሬት ውስጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ብልሀት በተዘጋጀ ቦታ በክብር አስቀምጠው ከላዩላይ የእግዚአብሔር አብን ቤተክርስቲያንን በጥሩ ሁኔታ አሳንፀው እንደፈፀሙ መስከረም 21 ቀን 1449 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ በከፍተኛ ድምቀት እንዲከበር አድርገዋል፡፡ ደብሩንም ደብረ ከርቤ ሲሉ ሰየሙት ትርጉሙ ‹‹ደብር›› የተከበረ ቦታ ሲሆን ‹‹ከርቤ›› ደግሞ የተሰበረ የሚጠግን ማለት ነው፡፡ ይህ በእንድህ እያለ የንጉሱ እህት የሆኑት ንግስት እሌኒ ደግሞ የማርያም ቤተክርስቲያንን ከእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ትንሽ ራቅ ብለው አሰሩ፡፡
✞ በአጼ ዘርያቆብ ዘመነ መንግስት የነበሩት ሊቃነ ጳጳስ ሱባኤ ገብተው የተገለፀላቸውን መንፈሳዊ ሚስጥር ለማስረዳት እንዲህ በማለት የቦታውን ታላቅነት አረጋግጠው መስክረዋል፡፡መስቀሉ ያለበትን የግሽን ደብር የተሳለመ፤ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያስተማረባቸውን ቀራኒዮን፤ ጎለጎታንና፤ ደብረታቦርን እንደተሳለመ ይሆንለታል በማለት ተናግረዋል፡፡ የግሽን ደብረ ከርቤ ቅዱስ ቦታ በውስጡ አምስት አብያተ ክርስትያናትን የያዘ ነው፡፡
✞ በጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የግድግዳ ላይ ስዕሎችና ስለመስቀሉ አጠቃላይ ታሪክ የሚተርከዉ መፅሀፈ ‹‹ጤፉትም›› እዚሁ ቦታ ብቻ ይገኛል፡፡
✞ በሌላ በኩል በዚህ ቦታ በቅዱስ ጊዮርጊስ የተፈጥሮ ዋሻ ውስጥ የቅዱሳን አባቶች አጽም ይገኛል፡፡ የግሸን በዓል ከመስከረም 17 ጀምሮ የሚከበር ትልቅ ሚስጢርና በረከት የሚገኝበት ቦታ ነው፡፡ መንግስት በአሁኑ ጊዜ የአገሪቱን በጎ ገጽታ ለሌላው አለም በማስተዋወቅ ጥረት በማድረግ የቱሪስት መስህብ በሆኑ ታሪካዊ ቦታዋች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ በሚገኝበት ወቅት ላይ አለም አቀፍ ቅርስ ስለሆነው የክርስቶስ መስቀል ማረፊያነት የተመረጠችው፣ በመስቀል ቅርጽ የተፈጠረችውና በራሷም ቅርስ የሆነችው ግሽን ደብረ ከርቤ ለሀገራችን በተለይም ደግሞ ለአካባቢው ህዝብ ልታስገኘው የምትችለው የቱሪስት ገቢ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡
✞ በዚህም መስከረም እና በጥር 21 ቀናት የማርያም ንግስ በዓል በሚከበርበት ወቅት ከሰሜንና ደቡብ ፤ከምዕራብና ከምስራቅ የሚሰባሰቡት ምዕመናን ቁጥር በየአመቱ እየጨመረ ይገኛል፡፡
#እንኳን_ለግሼን_ማርያም_አመታዊ_ክብር_በአል_በስላም_አደረሰን_አደረሳችሁ✞
🙏 ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ ወላዲተ አምላክ በረከቷ ፍቅሯና አማላጅነቷ ከሁላችን ጋር ይሁን🙏
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🙏5🥰3👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌾🌻🙏✞ #መጽሐፉማ_ይላል ✞🙏🌻🌾
መጽሐፉማ ይላል ይቤሎ ይቤሎ /፪/
እመቤቴ ማርያም የወርቅ ሀመልማሎ
አማን በአማን
አማን በአማን /፬/
በወላዲተ አምላክ ሁሉም ሰው ይመን
አማን በአማን
ዕርም ዕርም ይላል ሲሄድ በፈረስ /፪/
ባሕርዳር ያለኸው ቅዱስ ጊዮርጊስ /፪/
አማን በአማን
https://www.youtube.com/EOTC2921
https://www.facebook.com/eotc2921
https://www.tiktok.com/@eotc2921
https://www.instagram.com/eotc2921
መጽሐፉማ ይላል ይቤሎ ይቤሎ /፪/
እመቤቴ ማርያም የወርቅ ሀመልማሎ
አማን በአማን
አማን በአማን /፬/
በወላዲተ አምላክ ሁሉም ሰው ይመን
አማን በአማን
ዕርም ዕርም ይላል ሲሄድ በፈረስ /፪/
ባሕርዳር ያለኸው ቅዱስ ጊዮርጊስ /፪/
አማን በአማን
https://www.youtube.com/EOTC2921
https://www.facebook.com/eotc2921
https://www.tiktok.com/@eotc2921
https://www.instagram.com/eotc2921
❤5🙏4👍2🥰2👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🌾🌻🙏✞ #ቅዱስ_ሚካኤል ✞🙏🌻🌾
ሚካኤል ሚካኤል
ያሳደከኝ ሚካኤል "
ጠባቂዬ ሚካኤል "
የዋህ መልአክ ባለሟል "
ሚካኤል ሚካኤል "
ስምክን ጠርተን ተሰደድን "
የዋህ መልአክ ታጋሽ ነህ "
ለኛ ፈጥነህ ትደርሳለህ "
➥ለተጨማሪ...
youtube.com/EOTC2921
facebook.com/eotc2921
tiktok.com/@eotc2921
instagram.com/eotc2921
ሚካኤል ሚካኤል
ያሳደከኝ ሚካኤል "
ጠባቂዬ ሚካኤል "
የዋህ መልአክ ባለሟል "
ሚካኤል ሚካኤል "
ስምክን ጠርተን ተሰደድን "
የዋህ መልአክ ታጋሽ ነህ "
ለኛ ፈጥነህ ትደርሳለህ "
➥ለተጨማሪ...
youtube.com/EOTC2921
facebook.com/eotc2921
tiktok.com/@eotc2921
instagram.com/eotc2921
👍3🙏3🥰2❤1
#ገብርኤል_ማን_ነው?
🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾
#ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” - የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን
ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን
አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ
ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ”
እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
#ይህ_ቅዱስ_ገብርኤል_ነው
ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
👉* ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ
👉*ገብርኤል ነው፡፡*
የአሸናፊና የኃይል መልአክ
*ገብርኤል ነው፡፡*
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
*ገብርኤል ነው፡፡
🙏"የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ረድኤት አይለየን"🙏
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921

🙏4👍2❤1🥰1
•••✞✞✞ #በዓለ_ስቅለት ✞✞✞••••
ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የፈጣሪያችን የመድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።
✔✞መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?
✔✞ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።
✔✞ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።
✔✞በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።
✔✞በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።
✔✞አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።
✔✞በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን

❤2👏2🙏2🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🌾🌻🙏✞ #መድኃኔዓለም ✞🙏🌻🌾
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
➥ለተጨማሪ...
youtube.com/EOTC2921
facebook.com/eotc2921
tiktok.com/@eotc2921
www.tg-me.com/EOTC2921
instagram.com/eotc2921
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
➥ለተጨማሪ...
youtube.com/EOTC2921
facebook.com/eotc2921
tiktok.com/@eotc2921
www.tg-me.com/EOTC2921
instagram.com/eotc2921
❤4🙏4🥰2👍1