🌾✞ #ደብረ_ታቦር ✞🌾
❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ክብር ይግባውና ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስምንቱን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አሥነስቶ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ መኾኑን ብርሃኑ የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9)
❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው። ምክያቱም ከምሥጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤ ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጽልን፡፡
❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት፦
መጀመሪያ አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 88፡12 ላይ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት ለመፈጸም ነው፡፡
❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ 4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች፤ በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን ተራራን መርጦታል፡፡
❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ
ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት ኹሉ በእውነት የሙሴና የኤልያስ ፈጣሪ መኾኑን ሲገልጽላቸው ሲኾን ሙሴና ኤልያስም ጌታቸው ፈጣሪያቸው ርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በተራራው ላይ መስክረዋል፡፡
ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡
❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት ሲያመለክተው ነው።
❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ ፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡
❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡
❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦
1⃣ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት
2⃣ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመን የነቢያትንና የሐዋርያትን ክብርና ምልጃ እንደምታስተምር ለማሳየት ነው፡፡
3⃣ ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ
4⃣ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት
5⃣ ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡
6⃣ ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም “በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡
7⃣ ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨
8⃣ ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ ነውና፨
9⃣ ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3 ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡
❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤ ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡
❖ ሌላው “ብሑዕ” ማለት የቦካ ማለትን ሲያመላክት በዚኽ ቀን የሚጋገረውን ሙሉሙል ዳቦ የሚያመለከክት ነው፡፡
❖ በዚህ በዓል የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ነሐሴ 12 ማታ ይበራል፤ ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡
❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ሄደዋልና የዚያ ምሳሌ ነው፡፡
[በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው]
✍መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞
www.tg-me.com/EOTC2921

Telegram
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

#በዓለ_ደብረ_ታቦር @EOTC2921.pdf
337.4 KB
🌾✞ #ስለ_በዐለ_ደብረ_ታቦር ✞🌾
በብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገሪማ (ዶክተር) የተሠጠ የሚያስደንቅ አስተምሮ ማንም ሳያነብ እንዳይቀር፤
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንኳን #ለደብረ_ታቦር በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!!!
እነሆ በዓሉን የሚመለከት ድንቅ ዝማሬ፦
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
☞ @EOTC2921 Channel
☞ @Orthodox2921 Group
እነሆ በዓሉን የሚመለከት ድንቅ ዝማሬ፦
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
☞ @EOTC2921 Channel
☞ @Orthodox2921 Group
🍀✞ #ቡሄ_በሉ ✞🍀
ቡሄ በሉ (2) ሆ ልጆች ሁሉ ሆ የኛማ ጌታ ሆ
የዓለም ፈጣሪ ሆ የሰላም አምላክ ሆ
ትሁት መሀሪ ሆ በደብረ ታቦር ሆ የተገለጠው ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ
ልብሱ እንደብርሃን ሆ ያንፀባ ረቀው ሆ
#ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና (2)
#የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን (2)
ያዕቆብ ዮሐንስ ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ
አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ
አባቱም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ
ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ
#ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና (2)
#የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)
ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ
ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ
ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ
#ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2)
#የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)
በተዋህዶ ልጆች ሆ
ወልድ የከበረው ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ
ወልደ ማርያም ነው ሆ
ቡሄ በሉ (2)
የአዳም ልጆች ሆ ብረሃንን ሆ ተቀበሉ ሆ
#ድምጽህን_ሰማና በብህሩ_ደመና(2)
#የቡሄው_ብርሃን ለኛ_መጣልን(2)
አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
አጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
አክስቴም አለኝ ለከት ሆ
ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ
#ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2)
#የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)
የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣው ሆ
ከተከመረው ሆ ከመሶቡ ይውጣ ሆ
ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ሰለመጣ ሆ
የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይምጣ ሆ
#ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2)
#የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)
ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ ያላችሁ ሆ
ባህላችሁን ሆ ያዙ ሆ አጥብቃችሁ ሆ
ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ
ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ
#ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2)
#የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)
አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ
የቡሄን ትርጉም ሆ ያሳወቁን ሆ
እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን ሆ
ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ
#ድምጽህን_ሰማና በብህሩ_ደመና(2)
#የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)
ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ
በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ
ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ
#ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2)
#የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)
ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነጽ ሆ
በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ
በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችን ይድረስ ሆ
#ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2)
#የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)
ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
#በጋሽዬ_ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
#በእማምዬ_ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና
#እንዲሁ_እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ
#ለዓመቱ_በሰላም በፍቅርያ ድርሳችሁ
#ክርስቶስ_በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ
#የመንግስቱ_ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ
#እንዲሁ_እንዳለን በፍቅር አይለየን
#ለዓመቱ_በሰላም በፍቅር ያድርሰን
#አማኑኤል_በቀኙ በፍቅር ያቁመን
#የመንግስቱ_ወራሽ በፍቅር ያድርገን
የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
#በሁሉም_ቤት (2) ይግባ በረከት
#በሁሉም_ቤት (2) ይግባ በረከት
እንቁም በሃይማኖት ፀንተንበትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
#ባህላችንን_የአባቶች_ትውፊት (3)

ደብረ ታቦር.pdf
391.5 KB
~~~✞ #ግጥም ✞~~~
https://www.tg-me.com/EOTC2921
🌾✞ #ደብረ_ታቦር ✞🌾
መለኮት ተገለጦ ብርሃንን አበራ፣
በተቀደሰችው የታቦር ተራራ።
የአብ አባትነት የወልድ ልጅነት፣
በግልጽ ታወቀ ተነገረ በእውነት።
ዮሐንስ ጴጥሮስ ያዕቆብን ጠርቶ
ሙሴን ከመቃብር ከሙታን አሥነስቶ
ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስን አምጥቶ
በአምላክነቱ ፍጹም አንጸባርቆ
በሕያው መለኮት በብርሃናት ደምቆ
አብም ተገለጠ በብሩህ ደመና፣
የምወደው ልጄ ክርስቶስ ነውና።
እርሱን ብቻ ስሙት እስከ ዘለዓለም፣
ሕይወትን በእርሱ እንጂ ያለርሱ አትድኑም።
ብሎ ስለልጁ በግለጽ መሰከረ፣
አምላክነቱንም በተግባር ነገረ።
"...ታቦርና አርሞንዔም በስምኽ ደስ ይላቸዋል፤ ክንድኽ ከኀይልኽ ጋራ ነው፤ እጅኽ በረታች ቀኝኽም ከፍ ከፍ አለች።" መዝ ፹፰፥፲፪

#የቅድስት_ድንግል_ማርያምን_እውነተኛ_ዕርገት_ክደው_ለሚያስክዱ_በዘመናችን_ለተነሡ_ሐሰተኞች_የተሰጠ_ምላሽ
☞❀ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ሥር በአደራ የተቀበለ ፲፭ ዓመት ከርሷ ጋር የኖረ በ፷፬ ዓመቷ የኾነ ዕረፍቷን፣ ፍልሰቷን፣ ትንሣኤዋን፣ ዕርገቷን በዐይኑ ያየው ቅዱስ ዮሐንስ አምላክን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ለመሸከም የበቃች የአምላክ ታቦት ካረገች በኋላም በሰማያት ያላትን ታላቅና ፍጹም ክብር በራእ ፲፩፥፲፱ ላይ
“በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት ከተናገረ በኋላ በተከታይነት አሕዛብንም ኹሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ የወለደች ርሷ በሰማይ ፀሓይን ተጐናጽፋ፣ ጨረቃን ተጫምታ፣ ከዋክብትን ደፍታ እንዳያት ጽፏል፡፡
☞❀ዮሐንስ የአምላክ ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያምን በዕርገቷ በሰማያት ያላትን ክብር በዐይኑ ዐይቶ “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት ሲጽፍልን፤ ሀብተ ትንቢት የተሰጠው ዳዊት ደግሞ አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ ታቦት” በማለት ክብር ይግባውና ልጇ በሥልጣኑ አስቀድሞ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ለዐይን ቅጽበት እንኳን ወዳልተለየው ወደ ጌትነቱ ዙፋን ወደ ሰማይ እንዳረገ ኹሉ ፱ወር ከ፭ ቀን
በማሕፀኗ የተሸከመችው ታቦቱ ቅድስት ድንግልም በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ እንደምታርግ ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡
☞❀በዚኽ አማናዊ ምስክርነት በሰማይ ዮሐንስ ያያት ታቦት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ ያረገችው የአምላክ ታቦት ንግሥተ ሰማያት ወምድር ቅድስት ድንግል ናትና ኢትዮጵያዊዉ ቄርሎስ ዐምደ ሃይማኖት
የተባለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በኆኅተ ብርሃን መጽሐፉ ላይ “ወታቦተ
ራእየ ምስጢረ ኅቡአቲሁ ለዮሐንስ አቡቀለምሲስ ረኣዬ ኅቡአት” (የተሰወረ
ነገርን የሚያይ የራእይ አባት የዮሐንስ የምስጢራቱ ምስጢር ራእይ ታቦት አንቺ
ነሽ) በማለት በትክክል ገልጾታል፡፡
☞❀ጌታችን እንኳን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን በዠርባዋ ያዘለችውን በክንዶቿ የታቀፈችውን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የኾነው ታቦቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን ትቅርና ያገለገሉት ወዳጆቹን እንኳን ሞትን ሳያዩ ወደ ሰማይ እንደወሰዳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስናነብብ፤ ለምሳሌ ሔኖክ ሞትን ሳያይ በሕይወቱ ሳለ እግዚአብሔር እንደወሰደው በዘፍ
፭፥፳፬ እና በዕብ ፲፩፥፭ ላይ ተጠቅሷል።
☞❀ነቢዩ ኤልያስም ሞትን ሳያይ በእሳት ሠረገላ ተነጥቆ ወደ ሰማይ እንደወጣ (፪ነገ ፪፥፲፩‐፲፪) ተጽፎልናል፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከእግረ መስቀሉ ሥር በጌታ ሥልጣን ስለተነሡ ቅዱሳን ማቴዎስ ሲጽፍ “መቃብሮችም ተከፈቱ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ” ይለናል (ማቴ ፳፯፥፶፪-፶፫)፡፡
☞❀ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና እንደምናገኘው በመቃብር ውስጥ
መፍረስ መበስበስ የኀጢአት ውጤት ሲኾን ትእዛዝን የጣሰውን አዳምን “ዐፈር
ነኽና ወደ ዐፈርም ትመለሳለኽና” በማለት ተረግሞ ነበር (ዘፍ ፫፥፲፱)፤ በዚኽም ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሥጋዊ ደማዊ የኾነው ኹሉ ወደ መቃብር ሲወድቅ፤ ርሷ ግን ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፣ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ይኽነን መርገም ከመስማታቸው በፊት ከነበራቸው ንጽሕና የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች
ናትና በመቃብር ፈርሶ መቅረት አይስማማትም።
☞❀አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽነን ንጹሕ ሥጋዋንና ነፍሷን
በመንሣት በተዋሐደው ሥጋ በመስቀል ተሰቅሎ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነሥቷልና
እናቱም በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ዐርጋለች፤ ርሱን በመፅነስና
በመውለድ ዕድፍ ጉድፍ ያላገኘው ያልተለወጠ ድንግልናዋ፤ የተሸከመው
ማሕፀኗ፤ የታቀፉት ክንዶቿና፣ የዳሰሱት እጆቿ፤ የሳሙት ከንፈሮቿ ያሳደጉት
ጡቶቿ፤ ከርሱ ጋር የተመላለሱ እግሮቿና፤ ያዘለው ጀርባዋ፤ ብሩሃት የሚኾኑ
ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ያላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች የሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ
በገብርኤል ቃል ብሥራትን የሰሙ ዦሮቿ ፈጽመው በመቃብር ፈርሶ በስብሶ
መቅረት የለባቸውም፤ ከርሷ ሥሮችንና ጸጒርን፣ ደምንና ዐፅምን ነፍስንና ሥጋን
ነሥቶ አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮቱ ጋራ አንድ ያደረገው ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ
ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡
☞❀የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የነበረ አስተምህሮ ሲኾን ይኽን ለመጀመሪያ ጊዜ የጻፈው በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ነው ብሎ መጻፍ የመጨረሻው የአለማወቅ ጥግ ነው ቢባል አያስከፋም፨
☞❀ዮሐንስም የዕረፍቷንና የዕርገቷን ነገር በዐይኑ በማየቱ ስለአምላክ እናት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰት የነባቤ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ
ምስክርነት (The Account of St. John the Theologian of the
Dormition of the Holy Mother of God) በሚል ርዕስ የጻፈው ሲኾን፤
ይኽም ጽሑፉ በእኛ በብራና በሚገኘው በነገረ ማርያም መጽሐፍ ላይና
በመጽሐፈ ፍልሰታ ላይ በቀደምት መተርጒማኖቻችን የተተረጐመልን በመኾኑ ይኽነን የተቀደሰ ታሪክ ቀደምት የኾነችው ቤተ ክርስቲያናችን አስቀድማ
አግኝታዋች፤ ይኽ በግሪክ ቋንቋ ተጽፎ የሚገኘው የዮሐንስ ምስክርነት አስቀድሞ በሱርስትና በዐረብኛ ቋንቋ የተተረጐመ ሲኾን በኋላም ወደ ተለያዩ የዓለም ቀደምት ቋንቋዎች ጽሑፉ ተተርጒሟል፤ በዚኹ ምዕራፍ በክፍል ኹለት ላይ ከጽርዕ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጐመውና ከኒቅያ ጉባኤ በፊት የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሥራ (Ante-Nicean Fathers, Vol. 8.) በሙሉ በያዘው በክፍል ስምንት ላይ ተጽፎ ያለውን ሙሉውን ምስክርነት ነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፌ ላይ ተርጉሜዋለኹና ያንብቡ።
☞❀የአርማትያሱ ዮሴፍም ከጌታ ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ያልተለየና ዐብሯቸው የነበረ በመኾኑ የቅድስት ድንግል ማርያምና ዕረፍትና ዕርገት በዐይኖቹ በማየቱ የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገትን ርሱም እንደ ዮሐንስ “ዮሴፍ ዘአርማትያስ የጻፈው የቡርክት ድንግል ማርያም ኅልፈት” (Joseph of Arimathea, The Passing of the Blessed Virgin Mary) በሚል ርዕስ ከእመቤታችን ዕርገት በኋላ የጻፈላት ሲኾን ይኽም አስቀድሞ በላቲንና በሱርስት ቋንቋዎች ተተርጒሞ ይገኛል፤ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጐመውና ከኒቅያ ጉባኤ በፊት የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሥራ (Ante-Nicean Fathers, Vol. 8.) በሙሉ በያዘው በክፍል ስምንት ላይ ያለውን የአርማትያሱ ዮሴፍን ሙሉውን ምስክርነት በነገረ ማርያም በሊቃውንት
መጽሐፌ ላይ በአማርኛ ቋንቋ አስፍሬዋለኊ፡፡

☞❀በ69 ዓ.ም. ያረፈው ከ72ቱ አርድዕት የኾነው የአንጾኪያ የመጀመሪያው ጳጳስ ቅዱስ ኢቮዲየስ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ስለነበረ በጥር ፳፩
የኾነ የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍትና በነሐሴ ፲፮ የተከናወነ በዓለ ዕርገቷን
በዐይኖቹ የተመለከተውን “ድርሳን ዘደረሰ አባ ኢቮዲየስ ሊቀ ጳጳሳት ዘአንጾኪያ
በእንተ ዕረፍታ ወፍልሰታ ለማርያም” (Evodius of Rome, Homily on the Dormition The falling asleep of Mary) በሚል ርዕስ ሲጽፍ የዚኽ መጽሐፍ ቅጂ በታችኛው ግብጽ ይነገር በነበረው በቦሃይሪክ ቅጅ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጻፈው ተገኝቷል፡፡ ይኽም መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ወደ አማርኛ ቋንቋ የተተረጎመው ነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፍ ላይ ያንብቡ፨
☞❀ቅዱስ ሚሊቶ በምዕራብ አናቶሊያ በሲሚርና አጠገብ በሳርዴስ
ጳጳስ የነበረ ሲኾን በግሪክ (Μελίτων Σάρδεων Melíton Sárdeon)
ሲባል ዕረፍቱም በ፻፹ (180) ዓ.ም ነው፤ ሊቁ ጀሮም የብሉይ ኪዳን ቀኖናን
ሚሊቶ ሠርቶ እንደነበር መስክሮለታል፡፡ የጻፋቸውም መጻሕፍት ዝርዝር
አውሳብዮስና ጀሮም ጽፈውት እናገኛለን፡፡ ብዙ መጻሕፍት ሲኖሩት በተለይም
የቅድስት ድንግል ማርያምን ኅልፈተ ሕይወትና አካላዊ ዕርገት አስመልክቶ
"የሳርዲሱ ቅዱስ ሚሊቶ የቡርክት ማርያም ኅልፈተ ሕይወት ትምህርት" The Passing of Blessed Mary) በሚል ርዕስ ርሱም እንደ ሐዋርያትና ሰባ
አርድእት ጽፏል፡፡ ይኽም መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ወደ ዐማርኛ
ቋንቋ በነገረ ማርያም በሊቃውንት ተተርጉሟል።
☞❀በ380 ዓ.ም በኢየሩሳሌም ጳጳስ የነበረው ጢሞቴዎስ (Timothy
of Jerusalem) ሲገልጽ “Wherefore the Virgin is
immortal…” (ድንግል እስካኹን ድረስ ሟች ያለመኾኗ ምክንያት በርሷ ውስጥ
ያደረው ጌታ ወደ ማረጊያ ክልሎች ስለወሰዳት ነው) በማለት ሞት በሌለበት
በዕረፍት ስፍራ ልጇ ያሳረጋት መኾኑን መስክሯል፡፡
☞❀በተጨማሪም ከ70 ዓ.ም. ጀምሮ ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ በነበረው ስደት በክርስቲያኖች ዘንድ ዐፅመ ቅዱሳን ከፍተኛ ስፍራ የነበረው ሲኾን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት በሙሉ እንደሚያስረዱን በዚያ የስደት ዘመን ክርስቲያኖች በድፍረትና ሐላፊነትን ተሸክመው በቈራጥነት የሰማዕታትን
ሰውነት ከመግደያው ስፍራ በመውሰድ ዐፅማቸውን በክብር ይጠብቁ የነበረ
ሲኾን ይኽነንም አጥብቀው በመጠበቃቸውና ለትውልድ በማስተላለፋቸው የከበረ ዐፅማቸው ባረፈበት ቦታ ላይ ዛሬ አብያተ ክርስቲያን ታንጸውበት እጅግ በርካቶች ጐብኚዎች እየጐበኙት ሲገኙ ለምሳሌ ያኽል የነቅዱስ ጴጥሮስ፣ የነቅዱስ ጳውሎስ፣ የነቅዱስ ቶማስ፣ የነያዕቆብ ወ.ዘ.ተ የከበረ ዐፅማቸው ስፍር ቊጥር በሌላቸው ሰዎች ከጥንት ዠምሮ እስከዛሬ ድረስ ሲጐበኝና ሲታይ
የቅድስት ድንግል ማርያምን አንድ የራሷን ጠጒርና የእጇን ጥፍር አገኘኊ
የምትል ምንም ሀገርና ቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ፈጽማ የለችም
ምክንያቱም አምላካችን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ያደረባት የአምላክ ታቦት ክቡር
ዳዊት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ
ታቦት” ብሎ ትንቢት እንደተናገረላት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ በዕረፍቱ
ስፍራ አለችና ነው፡፡
☞❀ይኸውም ሊታወቅ የዓለም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን በ400 ዓ.ም አካባቢ ነግሦ የነበረው ንጉሡ ማርሲያን የኢየሩሳሌሙን ፓትሪያርክ የቅድስት ድንግል ማርያም ዐፅም ካለ ወደ ቊስጥንጥንያ እንዲያመጣለት ቢጠይቀው ርሱ ግን እመቤታችን እንዳረገችና ምንም ዐይነት የርሷ ቅሪት እንደሌለ አስረድቶ ስለ ዕርገቷ ጽፎለታል።
☞❀የሚገርመው ቅሪቶች ከፍተኛ ዋጋ ስላላቸው ብዙ ሰዎች ወደ ከተማቸው
ጐብኚዎችን ለመሳብ ሲሉ አስመስለው ለመሥራት በመሞከራቸው ብዙዎች
ተከሰው የነበረ ሲኾን ለምሳሌ አክሊለ ሦኩን መስቀሉን አስመስለው ለመሥራት
ከበፊት ዠምሮ ቢሞክሩም ኾኖም ግን የቅድስት ድንግል ማርያም አካል አለን
የሚልና የሚሞክር ከጥንት ዠምሮ እስከ ዛሬ በዓለም ላይ ለምን ጠፋ? ቢባል
ማንም ሰው ይኽነን ሐሰት ስለማያምንና ከሐዋርያት ጊዜ ዠምሮ እስከ ቀደምት
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እስከ አኹንም ድረስ የቅድስት ድንግል ማርያም
አካል ፈጽሞ በምድር ላይ እንደሌለና ወደ ሰማይ በአካል እንዳረገች ስለሚታወቅ
ነው፡፡
☞❀በተጨማሪም ከመዠመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን-16ኛው መቶ ክፍለ
ዘመን ድረስም የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በቤተ ክርስቲያን፣ በነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ኹሉ ሙሉ በሙሉ የታወቀ በመኾኑ በዕርገቷ ዙሪያ ምንም ዐይነት የጥርጥር ጥያቄን ያቀረበ ማንም የለም፡፡
☞❀ዛሬ በጭፍኑ አንዳንዶች ከዕውቀት የራቁ መናፍቃን የካዱትን ይኽነን
እውነታ የእምነቶቻቸው መሥራቾች እንኳን ደፍረው አልተናገሩትም ለምሳሌ
የፕሮቴስታንት ሪፎርመር የኾነው ሄንሪች ቡሊነግር በ፲፭፻፴፱ (1539 ዓ.ም) ላይ
ጣዖታትን ተቃውሞ በጻፈው መጽሐፉ ላይ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ
ሰማይ ስለማረጓ ሲገልጽ፦
"Elijah was transported body and soul in a chariot of fire; ...he was not buried in any Church bearing his name,…It is for this reason, we believe, that the pure and immaculate embodiment of the Mother of God, the Virgin Mary, the Temple of the Holy Spirit, that is to say her saintly body, was carried up to heaven by the angel." (ኤልያስ በሥጋና በነፍስ ሳለ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ወጣ፤ በርሱ ስም በተሠየሙ ባንዳቸውም ቤተ ክርስቲያን አልተቀበረም፤ ይኽም ዘላለማዊነት እግዚአብሔር ለሚያምኑበት ለነቢያቱ ድንቅና ለማይነጻጸሩ ፍጡራኑ እግዚአብሔር እንዳዘጋጀ ያሳውቀናል … በዚኽ ምክንያት የአምላክ እናት የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ፣ አካሏ ንጹሕና ኀጢአት አልባ የኾነው የድንግል ማርያም ንጹሕ የተቀደሰ ሰውነቷ በመላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ እንዳረገ እናምናለን) በማለት ጽፏል (Heinrich Bullinger, cited in Thurian, page 89, 197, 198)
☞❀ዛሬ ደግሞ ጥቂቶች ይኽነን እውነት መቃወማቸው የእምነት መሪዎቻቸው
እንኳን ያስተማሩትን ትምህርትና የጻፏቸውን መጻሕፍት እንዳላነበቡ
ያጋልጥባቸዋል፡፡
☞❀ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በነሐሴ ፲፮ የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት
በዓል ብሔራዊ በዓል ተደርጎ በተለያዩ ሀገራት ሲከበር ዕርገቷ ከሚታሰብባቸው
ሀገራት ውስጥም ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ አንዶራ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ክሮሺያ፣
ኢኳዶር፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ሊባኖስ፣ ጣሊያን፣ ማልታ፣ ስሎቬኒያ፣ ፖላንድ፣
ፖርቹጋል፣ ሩማኒያ፣ ቺሊ፣ ሳይፕረስ፣ ሀይቲ፣ ሴኔጋል፣ ስሎቬኒያ፣ ስፔን፣ ካሜሩን፣ ጋቦን፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ፣ ኮትዲቭዋር፣ ማዳጋስካር እና ሌሎች በርካቶች የዓለም ሀገራት ይገኛሉ (Columbus World Travel Guide, 25th Edition)
🙏እመቤታችን ሆይ ከልጅሽ መንግሥት ለይቶ ሳጥናኤል ከሰራዊቱ ጋር ወደ
ሚገባበት ዘላለማዊ እሳት ውስጥ ከሚያስጥል የሃይማኖት ክሕደት እኛ
ልጆችሽን በምልጃሽ ጠብቂ አሜን🙏
[ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]

_ማርያም አርጋለች__ ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ(MP3_70K).mp3
Unknown Artist
https://www.tg-me.com/EOTC2921
🌾✞ #ማርያም_አርጋለች ✞🌾
ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪)
የሰማይ መላእክት እያረጋጒዋት
እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም
ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
ሐዋርያት አበው እንኩዋን ደስ አላችሁ
በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ
የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
🌾✞ #ማርያም_አርጋለች ✞🌾
ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪)
የሰማይ መላእክት እያረጋጒዋት
እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም
ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
ሐዋርያት አበው እንኩዋን ደስ አላችሁ
በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ
የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ = = = ✞✞✞ = = =
🌾✞ #ጳጉሜ ✞🌾
☞✞ ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine / በመባል ትታወቃች፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡
☞✞በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፡2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
☞✞ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት። ዮዲ 8፡2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
☞✞ የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነው፡፡
☞✞ ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡
❀✿ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✿❀
መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጷጉሜ) ይሁንልን፡፡
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞

🌻✞🕊 #ስርዓተ_በዓል_ወጾም_ዘኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ቤተ_ክርስቲያን 🕊✞🌻
❀✞ #ዓመተ_ምህረት፥ ፪፻፲፭(2015 ዓ.ም)
❀✞ #ወንጌላዊ፥ ሉቃስ
❀✞ #የዘመን_መለወጫ_ቀን፥ እሁድ(ሰንበት)
❀✞ #አበቅቴ፥ ፱(9)
❀✞ #መጥቅዕ፥ ፳፩(21)
❀✞ #ጾመ_ነነዌ፥ ጥር ፳፱(29)
❀✞ #ዐቢይ_ጾም፥ የካቲት ፲፫(13)
❀✞ #ደብረ_ዘይት፥ መጋቢት ፲(10)
❀✞ #ሆሣዕና፥ ሚያዝያ ፩(1)
❀✞ #ስቅለት፥ ሚያዝያ ፮(6)
❀✞ #ትንሣኤ፥ ሚያዝያ ፰(8)
❀✞ #ርክበ_ካህናት፥ ግንቦት ፪(2)
❀✞ #ዕርገት፥ ግንቦት ፲፯(17)
❀✞ #ጰራቅሊጦስ፥ ግንቦት ፳፯(27)
❀✞ #ጾመ_ሐዋርያት፥ ግንቦት ፳፰(28)
❀✞ #ጾመ_ድኅነት፥ ግንቦት ፴(30)
🌻🌼✞ #እንኳን_አደረሳችሁ ✞🌼🌻
🌻🌼✞ #እንኳን_አደረሰን❗ ✞🌼🌻
🌻🌻 #በእግዚአብሔር_ፈቃድ 🌻🌻
🌾መጪው ፳፻፲፭ ዓ.ም፦
🌻የተከፋ፣ የአዘነና የአለቀሰ፤ የሚደሰትበት።
🌻የተራበና የተጠማ፤ የሚጠግብበት።
🌻የተሰደደ፤ በሰላም ተመልሶ የሚኖርበት።
🌻ፍቅር፣ ዕምነትና ትዕግሥት፤ የምንጎናጸፍበት።
🌻ዕውቀቱን፣ ጥበብና ማስተዋሉን፤ የምናገኝበት።
🌻ከችግርና ከመከራ፤ ተላቀን በሐይማኖት በምግባር የምንጸናበት ዘመን ይሁንልን። ✞አሜን✞
🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞🙏
https://www.tg-me.com/EOTC2921
www.youtube.com/EOTC2921
www.tiktok.com/EOTC2921
www.facebook.com/EOTC2921
❀✞ #ዓመተ_ምህረት፥ ፪፻፲፭(2015 ዓ.ም)
❀✞ #ወንጌላዊ፥ ሉቃስ
❀✞ #የዘመን_መለወጫ_ቀን፥ እሁድ(ሰንበት)
❀✞ #አበቅቴ፥ ፱(9)
❀✞ #መጥቅዕ፥ ፳፩(21)
❀✞ #ጾመ_ነነዌ፥ ጥር ፳፱(29)
❀✞ #ዐቢይ_ጾም፥ የካቲት ፲፫(13)
❀✞ #ደብረ_ዘይት፥ መጋቢት ፲(10)
❀✞ #ሆሣዕና፥ ሚያዝያ ፩(1)
❀✞ #ስቅለት፥ ሚያዝያ ፮(6)
❀✞ #ትንሣኤ፥ ሚያዝያ ፰(8)
❀✞ #ርክበ_ካህናት፥ ግንቦት ፪(2)
❀✞ #ዕርገት፥ ግንቦት ፲፯(17)
❀✞ #ጰራቅሊጦስ፥ ግንቦት ፳፯(27)
❀✞ #ጾመ_ሐዋርያት፥ ግንቦት ፳፰(28)
❀✞ #ጾመ_ድኅነት፥ ግንቦት ፴(30)
🌻🌼✞ #እንኳን_አደረሳችሁ ✞🌼🌻
🌻🌼✞ #እንኳን_አደረሰን❗ ✞🌼🌻
🌻🌻 #በእግዚአብሔር_ፈቃድ 🌻🌻
🌾መጪው ፳፻፲፭ ዓ.ም፦
🌻የተከፋ፣ የአዘነና የአለቀሰ፤ የሚደሰትበት።
🌻የተራበና የተጠማ፤ የሚጠግብበት።
🌻የተሰደደ፤ በሰላም ተመልሶ የሚኖርበት።
🌻ፍቅር፣ ዕምነትና ትዕግሥት፤ የምንጎናጸፍበት።
🌻ዕውቀቱን፣ ጥበብና ማስተዋሉን፤ የምናገኝበት።
🌻ከችግርና ከመከራ፤ ተላቀን በሐይማኖት በምግባር የምንጸናበት ዘመን ይሁንልን። ✞አሜን✞
🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞🙏
https://www.tg-me.com/EOTC2921
www.youtube.com/EOTC2921
www.tiktok.com/EOTC2921
www.facebook.com/EOTC2921
Telegram
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
እንቋዕ እም ዘመነ ማርቆስ ኀበ ዘመነ
ሉቃስ በሰላም ወበጥዒና አዕደወክሙ፡፡
🌼 የ2015 ዓ.ም በዓላትና አጽዋማት
፩) ነነዌን መሠረት በማድረግ።
፩) ጥንተ ዮን
◦ 2015 ፥ 28 =71 ቀሪ 27
◦ ዓመተ ፀሓይ ➾ 27
◦ ምርያ ➾ 27
◦ ሠግር = 6
◦ ጥንተ ዮን = ምርያ + ሠግር
= 27 + 6
= 33/7 = 4 ቀሪ 5
ጥንተ ዮን = 5 ➾ እሑድ
#መስከረም 1, 2015 ዓ.ም ➾ #እሑድ
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
ወንጌላዊ = (5500+2015) / 4
= 7515/4
=1878 ቀሪ 3
#ዘመኑ ➾ ዘመነ ሉቃስ
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፫) ወንበር
◦ 7515 ፥ 19 = 395 ቀሪ 10
◦ ዓመተ አበቅቴ ➾ 10
◦ ወንበር = ዓመተ አበቅቴ - 1
= 10 - 1
#ወንበር = 9
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፬) አበቅቴ
◦ አበቅቴ = (ጥንተ አበቅቴ * ወንበር) /30
= (11* 9 )/30 = 3 ቀሪ 9
#አበቅቴ ➾ 9
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
🌷 መጥቅዕ + አበቅቴ = 30
፭) መጥቅዕ
◦ መጥቅዕ = 30 - አበቅቴ
= 30 - 9 = 21
#መጥቅዕ ➾ 21
መጥቅዕ ➾ መስከረም 21
ነነዌ የምትውለው #ጥር ውስጥ ነው።
ይህንን ለማረጋገጥ መጥቅዑ የዋለበትን ዕለት ተውሳክ ማወቅ ይኖርብናል።
#መስከረም 21, 2015 ዓ.ም መቼ ይውላል?
= አጽፈ አውራኅ + ዕለት + ጥንተ ዮን
= 2 + 21 + 5
= 28 ➾ 28/7 = 4
በጥንተ ዕለት = 7ኛ ቀን = ቅዳሜ
መጥቅዑ ( መስከረም 21, 2015 ዓ.ም)
የሚውለው ➾ ቅዳሜ ነው።
#የቅዳሜ_ተውሳክ ➾ 8
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
#መባጃ_ሐመር = መጥቅዕ + መጥቅዑ የዋለበት ዕለት ተውሳክ
= 21 + 8 = 29
#መባጃ_ሐመር = 29
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
በዓላት/አጽዋማት = ነነዌ + የበዓላት/ አጽዋማት ተውሳክ
፮) ጾመ ነነዌ ➾ [ጥር 17, የካቲት 21]
ጾመ ነነዌ ተውሳክ የላትም።
በመባጃ ሐመር ትገኛለች።
ነነዌ = መባጃ ሐመር = 29
#ነነዌ ➾ ጥር 29
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፯) ዐቢይ ጾም = ነነዌ + የዐቢይ ጾም ተውሳክ
= 29 + 14
= 43 ➾ 13
#ዐቢይ_ጾም ➾ የካቲት 13
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፰) ደብረ ዘይት= ነነዌ + የደብረ ዘይት ተውሳክ
= 29+ 11
= 40 ➾10
#ደብረ_ዘይት ➾ መጋቢት 10
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፱) ሆሳዕና = ነነዌ + 2
= 29 + 2
= 31 ➾ 1
#ሆሳዕና ➾ ሚያዝያ 1
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፲) ስቅለት= ነነዌ + የስቅለት ተውሳክ
= 29 + 7
= 36 ➾ 6
#ስቅለት ➾ ሚያዝያ 6
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፲፩) ትንሣኤ = ነነዌ + 9
= 29 + 9
= 38 ➾ 8
#ትንሣኤ ➾ ሚያዝያ 8
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፲፪) ርክበ ካህናት = ነነዌ + 3
= 29 + 3
= 32 ➾ 2
#ርክበ_ካህናት ➾ ግንቦት 2
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፲፫) ዕርገት = ነነዌ + 18
= 29 + 18
= 47 ➾ 17
#ዕርገት ➾ ግንቦት 17
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፲፬) ጰራቅሊጦስ = ነነዌ + 28
= 29 + 28
= 57 ➾ 27
#ጰራቅሊጦስ ➾ ግንቦት 27
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፲፭) ጾመ ሐዋርያት = ነነዌ + 29
= 29 + 29
= 58 ➾ 28
#ጾመ_ሐዋርያት = ግንቦት ➾ 28
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▬
፲፮) ጾመ ድኅነት = ነነዌ + 1
= 29 +1
= 30
#ጾመ_ድኅነት ➾ ግንቦት 30
#ማስታወሻ፦ የበዓላትና የአጽዋማት ተውሳክ ማለት ከጾመ ነነዌ ማግስት እስከ በዓሉ/ጾሙ ድረስ ያለው ርቀት ነው።
▣▪️▣▪️▣▪️▣▪️▣▪️▣▪️
፪) ትንሣኤን መሠረት በማድረግ
በቅድሚያ የ2015 ዓ.ም በዓለ ፍሥሕን ማግኘት አለብን፡፡
ፍሥሕ = መጥቅዕ + 10
= 21 +10
= 31 ➜ 1
1 ማለት ሚያዝያ 1 ነው።
◦ ፍሥሕ ➜ [መጋቢት 25, ሚያዝያ 23]
ሚያዝያ 1, 2015 ዓ.ም መቼ ይውላል?
ሠ.ዕ = አ.አውራኅ + ዕለት + ጥንተ ዮን
= 16 + 1 + 5 = 22
= 22/7 = 3 ቀሪ 1
በጥንተ ዕለት 1 ማለት እሑድ ነው።
በዓለ ፍሥሕ ➜ እሑድ ሚያዝያ 1, 2015 ዓ.ም
ትንሣኤ በዓለ ፍሥሕ ከዋለበት ቀጥሎ ያለው እሑድ ነው፡፡ ሚያዝያ 1 እሑድ ከዋለ ቀጥሎ ያለው እሑድ የሚውለው ሚያዝያ 8 ነው፡፡ በመኾኑም የ2015 ዓ.ም ትንሣኤ ሚያዝያ 8 ይውላል።
በዓል/ጾም = ትንሣኤ + የበዓሉ/ጾሙ ኢየዐርግ
▪️ ነነዌ = ትንሣኤ + የነነዌ ኢየዐርግ
= 8 + 21 = 29
#ነነዌ ➳ ጥር 29
▪️ዐቢይ ጾም = ትንሣኤ + ኢየዐርግ
= 8 + 5
= 13
#ዐቢይ_ጾም ➳ የካቲት 13
▪️ ደብረ ዘይት = ትንሣኤ + ኢየዐርግ
= 8 + 2
= 10
#ደብረ_ዘይት ➳ መጋቢት 10
▪️ሆሳዕና = ትንሣኤ + የሆሳዕና ኢየዐርግ
= 8 + 23
= 31➳ 1
#ሆሳዕና ➳ ሚያዝያ 1
▪️ስቅለት = ትንሣኤ + የስቅለት ኢየዐርግ
= 8 + 28
= 36 ➳ 6
#ስቅለት ➳ ሚያዝያ 6
▪️ርክበ ካህናት = ትንሣኤ + ኢየዐርግ
= 8 + 24
= 32 ➳ 2
#ርክበ_ካህናት ➳ ግንቦት 2
▪️ዕርገት = ትንሣኤ + የዕርገት ኢየዐርግ
= 8 + 9
= 17
#ዕርገት ➳ ግንቦት 17
▪️ ጰራቅሊጦስ = ትንሣኤ + ኢየዐርግ
= 8 + 19
= 27
#ጰራቅሊጦስ ➳ ግንቦት 27
▪️ጾመ ሐዋርያት = ትንሣኤ + ኢየዐርግ
= 8 + 20
= 28
#ጾመ_ሐዋርያት ➳ ግንቦት 28
▪️ጾመ ድኅነት = ትንሣኤ + የጾመ ድኅነት ኢየዐርግ
= 8 +22
= 30
#ጾመ_ድኅነት ➳ ግንቦት 30
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
ግዛቸው ደጀኑ መኰንን
መስከረም ፩፣ ፳፻፲፭ ዓ.ም
🌼 ሠናይ ሐዲስ ዓመት ይኩን ለኵልነ

#አቤቱ_ደግ_ሰው_አልቋልና_አድነኝ
መዝ 11፥1
#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን_ግርማ
“አድህነኒ እግዚኦ እስመ አልቀ ሄር” እንዲህ አይነት 3ቱም ምህረት ጠፍቷል ነው የሚለው ቅዱስ ዳዊት 3ቱ ምህረት በምድር ላይ ጠፍቷል እና አድነኝ “በውህደ ሃይማኖት እም እጓለ መሕያው” ከሰው ልጆች ሃይማኖት ጠፍቷል ማለት ከሰው ልጆች ከምድርም ሐይማኖት ጠፍቷል ይላል ምድር ያለው ሰው ነው ሰው ከአፈር ስለተፈጠረ ከሰው ልጆች ሁሉ ማለት ነው ባለው ጳጳሱም ምድር ነው ካህኑ ምድር ነው ዲያቆኑ ምድር ነው መነኩሴው ምድር ነው ባህታዊው ምድር ነው ሰው ሁሉ ምድር ነው ስለዚህ ምን ማለት ነው ከምድር ላይ ባለ ጊዜ ከሁሉም ሰው ማለት ነው ከተማረውም ካልተማረውም ሃይማኖት ጠፍቷል እና አድነኝ በዚህ ዘመን ከተማረውም ካልተማረውም ሃይማኖት የጠፋበት እንደዚህ ዘመን ያለ የለም ሃይማኖት የጠፋው ከእኛ ቤት ነው ከእኛ ከካህናቱ ከደቀ መዛሙርቱ ከሊቃውንቱ ነው የጠፋው በእውነት የተማረውና ያልተማረው ማንኛውም ሰው ትምህርት ሲማር ቅኔ ሲማር አቋቋም ሲማር ቅዳሴ ሲማር መፃህፍት ሲማር ቅጠል በጥብጦ ቢማር ደስ ይለዋል ቅጠል በጥብጦ ጠጥቶ ትምህርት ቢገለጥለት ደስ ይለዋል። ከዚያ ጎዶሎነታችን የተነሳ እንኳን በቤተክርስቲያን የተሻለ እውቀት ያለው ሰው ካየን አይ የኔታ እገሌማ የቀመሷት ነገር አለ ማለት ነው ጎዶሎ ነዋ ጠማማ ነዋ ራሱ ጠማማ ስለሆነ እንደጠማማ ነው የሚያስበው ራሱ ጎዶሎ ህፁፅ ጎዶሎ ስለሆነ ሰውን ሁሉ እንደዛ ስለሚለው ማለት ነው አንድ እንኳን በዚህ ዘመን እግዚአብሄርን ማን ያምነዋል በዚህ ዘመን በእውነቱ ማለት ነው እነ እገሌን ያወጣቸው እግዚአብሄር ነው ብፁዕ አቡነ እገሌን ያወጣቸው እግዚአብሄር ነው የኔታ እገሌን እግዚአብሄር አወጣቸው ቄስ እገሌን እግዚአብሄር አወጣቸው አይባልም እሳቸውማ ያገኙት ነገር አለ መድሃኔዓለም ይሄንን ጠማማ ትውልድ ቢቻል ይመልሰው ባይቻል ግን ይንቀለው በእውነቱ እንዲህ ያለ ጠማማ በእግዚአብሄር መንግስት የሚከለክልበት ቸርነት የሚከለክልበት የውዳሴ ማርያምን አቅም የሚጠራጠር የቅዳሴ ማርያምን የዳዊትን የቅዱሳንን ገድል የሚተራጠር ሰው ስጋውን ደሙን ለማጥራት አቅም እስከ ማሳጣት የሚደርስ ስጋ ወደሙን ደካማ የሚያደርጉ ስጋ ወደሙ እውቀት እንደሚገልጥ የማያምኑ ጠማማች ስር በጣሾች ስር ማሾች ቅጠል በጣሾች ለምንም የማይጠቅሙ በእግዚአብሔር ፊት ርስት የሌላቸው እንዲህ ያሉት ናቸው በእውነቱ እንዲህ ያሉትን ነው እግዚአብሄር ይንቀላቸው ብሎ ቅዱስ ዳዊት የተናገረው ልብ በልብ ይትናገር ይሴርር እግዚአብሄር ለከናፍር ስር እየማሱ ቅጠል እየበጠሱ ስመ አጋንንትን ሸ ጨ ጀ እያሉ እየጠሩ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን እየተሰደበች አንዱ እግዚአብሔር እንዳይሰማን ምህረት እንዳናገኝ ከቤተ መንግሥት ከቤተ ክርስቲያን እንድንታመስ ያደረገን እኛ ቤት ያለው ጥንቆላ ነው በጥንቆላ ተተብትበን ወይ መስቀሉን መምረጥ ነው ወይ ስሩን መምረጥ ነው ወይ ስመ እግዚአብሔርን መምረጥ ነው ወይ የአጋንንትን ስም ያን ጨ ጀ የምትለውን መምረጥ ነው “እይህክል አሐዱ ገብር ተቅኔየ ለክልኤ አጋእዝት” አንድ ባርያ እንዴት ለሁለት ባርያዎች መገዛት ይችላል አንደኛው ቆላ ሲልከው አንደኛው ደግሞ ደጋ ይልከዋል አንዱ ተራራ ውጣ ይለዋል አንዱ ቁልቁለት ውረድ ይለዋል ወደ የትኛው ትሄዳለህ 2 እግር አለኝ ተብሎ 2 ዛፍ ላይ በአንድ ጊዜ መውጣት ይቻላል አይቻልም ጥንቆላና ሐይማኖት ስርቆትና ምፅዋት ተባብረው የተቀመጡበት የእኛ ቤት ነው ይሄ ባለመጥፋቱ ምክንያት ነው ምህረት የጠፋው ዘረኝነቱ ያለው እኛው ቤት ስርቆቱ ጥንቆላው ያለው እኛው ቤት እግዚአብሔር ከእንዲህ ያለ መተት ይሰውረን በእውነት፡፡ አንዳንዱ ይመጣና ለማጥናት አንዳንድ ነገር መውሰድ ችግር አለው ይላል ስጋ ወደሙ ተቀበል ውዳሴ ማርያም ድገም ነው እሱማ ግን ይላል አሁን ይሄንን እኔ እንኳን ከጨነቀኝ እግዚአብሔር ግን እንዴት ይበሳጭ ይሆን በእውነቱ “ወሶበ ይበውእ ውስተ ልበ ንፁሐን አሜሃ ያነቅዎ ለተናግሮ” ስጋው ከሃጢያት ልቦናውን ከክፋት ከቂም ከልክሎ ስጋ ወደሙን የሚቀበል ሰው ይላል ያንጊዜ ሲቀበል አሜሃ ያነቅዎ ለተናግሮ የክርስቶስ ስጋና ደም በንስሃ የተዘጋጀ ሲገባ ያን ጊዜ ሚስጥር ለመናገር ያነቃቃዋል ይላል ጥበብሰ መድሃኒነ ውእቱ ቅዱስ ኤጲፋኒዮስ በቅዳሴው ሲናገር ጥበብ ይሏኋል ጥበብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብሎ ይናገራል ጥበብ ክርስቶስ ነው የክርስቶስ ጥበብነት ተዘነጋ ስለዚህ ከሰው ልጆች ከምድር ሃይማኖት ጠፍቷል እንዲህ አድርገህ ስሩን በጥሰህ 3 ቀን ደግመህ እንዲህ አድርገህ ይላል እንዲህ ያለ ስራይኛ በበዛበት በሐዲስ ኪዳን ስራይ በተበጠሰበት ሟርት ባለቀበት ጊዜ ስመ አጋንንትን የሚሰራና ከትቦ የሚቀመጥ በእውነቱ ይሄ ነው ቤተክርስቲያንን የሚታደጋት ማለት ነው ጉቦ እየበላን ጉቦኛ ዳኛ በደለን እንላለን ጉቦ የምንበላው እኛ ነን ታዲያ እንዲህ ያለ ሐይማኖት ከሰው ልጆች ጠፍቷልና አድነኝ ይላል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
እግዚአብሔር ያድነን አሜን!!!

🕊✞ ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም ፲ ✞🕊
🌻በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን🙏🏿
መስከረም 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፤
🕊✞ በዓለ ስዕለ አድኅኖ ✞🕊
✝️ይህች ቀን በቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሳት ስዕላት የሚነገርባት ክብርት ቀን ናት:: 'ስዕለ አድኅኖ' ማለት 'እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥበት: አንድም በቅዱሳኑ አማካኝነት ጸጋ የሚገኝበት: የሚያድን ስዕል' ማለት ነው::
🕊✞ ስለዚህ ነገር አንዳንዶቹ ሊነቅፉን ይፈልጋሉ:: እኛ ግን ከማን እንደ ተማርነው እናውቃለን:: ከመነሻው እኛ ስዕልን አናመልክም:: ይልቁኑ አምልኮን እንፈጽምበታለን እንጂ:: ስዕልን ለሰው ልጆች የሰጠ ራሱ ባለቤቱ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሠክራል::
🕊✞ እንዲያውም የመጀመሪያው ሰዐሊ ራሱ አምላካችን ነው:: አዳምን እንደ መልኩ: በምሳሌው ሲፈጥረው መላእክት የእግዚአብሔርን ምስል አዳም ላይ አይተዋልና:: (ዘፍ. 1:26) ለሙሴም ስዕለ ኪሩብን እንዲስል ያዘዘ ራሱ ነው:: (ዘጸ. 25:22) በዚያም ላይ ሆኖ ሙሴና አሮንን ሲነጋገራቸው ኑሯል::
🕊✞ በመቅደሰ ሰሎሞንም ተመሳሳይ ነገርን እናገኛለን:: (2ዜና. 7:12, 1ነገ. 9:1) በሐዲስ ኪዳንም ጌታ ስዕለ ኪሩብ ያለበትን መቅደስ ቤቴ (ማቴ. 21:13): የአባቴ ቤት(ዮሐ. 2:16) ሲለው: በቅዱስ ሰውነቱ ሲመስለውም (ዮሐ. 2:21) እንመለከታለን:: ቅዱስ ዻውሎስ ለገላትያ ሰዎች ስለ ስዕለ ስቅለት ሲያስታውሳቸው (ገላ. 3:1): ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በደም የተረጨች ልብስ ብሎ ያላትን መተርጉማን ያትታሉ:: (ራዕይ. 19:13)
🕊✞ በትውፊት ትምሕርት ደግሞ የመጀመሪያው ስዕል በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ የተሳለ ሲሆን ስዕሉም የእመቤታችን ነው:: "ሚካኤል በክነፊሁ ጾራ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ" እንዳለ ቅዱስ ያሬድ:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቃርዮስና ለቬሮኒካ (12 ዓመት ደም ይፈሳት ለነበረችው ሴት) መልክአ ገጹን ሠጥቷቸዋል::
('ቬሮኒካ' በላቲን 'ቬሮን-ኢኮን' 'እውነተኛ መልክ' እንደ ማለት ነው)
🕊✞ ቀጥሎም ዮሐንስ ወንጌላዊ ለጢባርዮስ ቄሣር ስዕለ ስቅለቱን ሲስልለት ቅዱስ ሉቃስ ደግም የእመቤታችን 'ምስለ ፍቁር ወልዳን' ስሏል:: ከዚያም ሲያያዝ ይሔው ከእኛ ደርሷል::
🕊✞ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በከተሞች አካባቢ ቅርጾች በዝተዋልና ይሔ አላስፈላጊ መዋስ (ያውም ከመናፍቃን) ቢቀር መልካም ነው ባይ ነኝ:: ኋላ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቁሞ ማውረድ ከባድ ነውና::
🕊✞ ጼዴንያ ✞🕊
🕊✞ በዚህች ቀን ቅዱስ ሉቃስ የሳላትና ሥጋን የለበሰችው: ከፊቷም ወዝ የሚወጣትና ድውያንን የምታድነው የድንግል ማርያም ስዕለ አድኅኖ ወደ ጼዴንያ ከወዳጇ ከብጽዕት ማርታ ዘንድ ገብታለች:: ቅድስት ማርታ ሃብት ንብረቷን በአብርሃማዊ ተግባር (በምጽዋትና እንግዳን በመቀበል) ላይ ያዋለች ክብርት ሴት ናት::
🕊✞ ለእመ ብርሃን ካላት ፍቅር የተነሳ እንቅልፍ አልነበራትም:: ተግታ ታገለግላትም ነበር:: ስዕሏን እንዲያመጣላት የላከችው ኢትዮዽያዊው መነኩሴ አባ ቴዎድሮስ የስዕሏን ተአምራት ባየ ጊዜ ለራሱ ለመውሰድ ሞክሮ ነበር:: (እርሱ ምን ያድርግ! እኔም ብሆን ይህንኑ ነበር የማደርገው)
🕊✞ ነገር ግን ከሁሉም በተሻለ የምትወዳት ቅድስት ማርታ ነበረችና በድንቅ ተአምር: በዚህች ቀን ወደ ጼዴንያ ገብታለች:: ቅድስት ማርታም ያለ ዕረፍት ስታገለግላት ኑራ ዐርፋለች:: ይህቺ ክብርት ስዕለ አድኅኖ የአሁን መገኛ 4 መረጃዎች አሉ:-
1.ያለችው ኢትዮዽያ ውስጥ (ደብረ ዘመዳ በሚባል ገዳም) ነው:: የመጣችውም ከግማደ መስቀሉ ጋር ነው::
2.ያለችው በቀደመ ቦታዋ ነው::
3.የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ወስደዋታል::
4.በፈጣሪ ጥበብ ተሰውራለች::
🕊✞ ልደታ ለማርያም ✞🕊
+በግብጽ ውስጥ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ: ማለትም በአስቄጥስ ደብረ አባ መቃርስ የእመቤታችንን ዜና ሕይወት የሚናገር 1 መጽሐፍ አለ:: መጽሐፉ እንደሚለው እመ ብርሃን ድንግል ማርያም የተጸነሰችው ታሕሳስ 17 ቀን ነው:: በዚህ ሒሳብ መሠረት ደግሞ እመ አምላክ የተወለደችው መስከረም 10 ቀን ነው:: ዓለማቀፍ ትውፊቱ ግን ነሐሴ 7 ተጸንሳ: ግንቦት 1 ቀን መወለዷን ያሳያል::
🕊✞ ተቀጸል ጽጌ / አጼ መስቀል ✞🕊
🕊✞ 'ተቀጸል ጽጌ' ማለት 'መስቀል ሆይ! በአበባ አጊጥ' እንደ ማለት ሲሆን 'አጼ መስቀል' ደግሞ አጼ ገብረ መስቀልን: አንድም አፄ ዳዊት ቀዳማዊን ይመለከታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
🕊✞ በሃገራችን ኢትዮዽያ የነገረ መስቀሉ ትምሕርት ከመጣ ጀምሮ መስቀል ይከበራል:: በአደበባባይ ግን እንዲከበር ያደረጉት የቅዱስ ካሌብ ልጅ አፄ ገብረ መስቀል ናቸው:: በወቅቱ ንጉሡ: ሠራዊቱ: ዻዻሱና ሕዝቡ በተገኙበት ቅዱስ ያሬድ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር-መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው: ከጠላትም ያድነናል" እያለ ይዘምር ነበር::
🕊✞ የአበባ ጉንጉንም ለመስቀሉና ለንጉሡ ይቀርብ ነበር:: ከ800 ዓመታት በሁዋላም አፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን ባስመጡ ጊዜ መስከረም ቀን ተተክሎ ታላቅ በዓልም ሆኖ ተከብሯል::
🕊✞ ንግሥተ ሳባ ✞🕊
+ይሕቺ ደግ ኢትዮዽያዊት ከ3 ሺ ዘመናት በፊት የነበረች ደግ እናት ናት:: በሥጋዊ ደረጃ ከታንዛንያ እስከ የመን ያስተዳደረች ስመ ጥር ንግሥት ስትሆን በመንፈሳዊው ደረጃ ደግሞ እግዚአብሔር የቀባውን ሰው ፍለጋ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛለች::
🕊✞ ከዚያውም አምልኮተ እግዚአብሔርን ከሥርዓተ ኦሪት ጋር አምጥታለች:: ድንግልናዋን ለታላቁ ንጉሥ ሰሎሞን ሰጥታ ምኒልክን ወልዳለች:: ይህቺ ንግሥት በጌታችን (በፈጣሪ) አንደበትም ተመስግናለች:: (ማቴ. 12:42) በስምም "ሳባ: አዜብና ማክዳ ተብላ ትታወቃለች:: ዛሬ ዕለተ ዕረፍቷ ነው::
🕊✞ እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን: ጸጋ በረከቷን: ከስዕሏም ረድኤት ትክፈለን:: የቅዱሳኑም ክብር አይለየን::
ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም
2.በዓለ ስዕለ አድኅኖ
3.ቅዱስ እፀ መስቀል (ተቀጸል ጽጌ)
4.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
5.ቅድስት ማርታ ዘጼዴንያ
6.ቅድስት ዮዲት ጥበበኛዋ
7.ንግስተ ሳባ / ማክዳ / አዜብ
8.ቅድስት መጥሮንያ ሰማዕት
9.አፄ ዳዊት ንጉሥ
10.ቅድስት አትናስያና 3 ልጆቿ
ወርኀዊ በዓላት
1 ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2 ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ
3 ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ
4 ቅድስት እሌኒ ንግስት
5 ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
🕊✞ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር:: ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? (ገላ. 3:1)🕊✞
✍️ዝክረ ቅዱሳን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር