🕊✞ #ኅዳር_ሚካኤል ✞🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ኅዳር 12
እንኳን ለታላቁ መልአክ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሰን፦
✉ለምንድን ነው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ወር በገባ በ12 የሚከበረው የሚታሰበው?
✉ህዳር 12 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምን ምን ያደረገበት እንየሆነ እንመለከታለን።
#ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡
✔ስለዚህ ስለ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፤ ጠባቂነትና አማላጅነት ከአባቶቻቸው የተማሩትን በኑሮአቸው ያዩትን አባቶቻችን ጽፈዋል፡፡ ስለ ቅዱስ ሚካኤል ከጻፉት አባቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል፡-
+ ዮሐንስ አፈወርቅ
+ ኤዎስጣቴዎስ ዘአንፆኪያ
+ ቅዱስ መቃርዮስ
+ ቅዱስ ያሬድ
+ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
+ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባዲማቴዎስ ናቸው፡፡
✔እኛም የአባቶቻችንን አንደበት አንደበታችን አድርገን በኅዳር 12 ክቡር ገናና የሆነ ቅዱስ ሚካኤል ካደረጋቸውና ከሠራቸው ብዙ ተአምራት ውስጥ የተወሰኑትን በመልአኩ ተረዳኢነት እንዲህ ብለን እንናገራለን አንጽፋለን፡፡
❖የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ለምን ወር በ12 ይከበራል?
✔በእስክንድርያ ሀገር ውስጥ ‹‹ሳተርን›› (ዙሐል) የተባለ ቤተ ጣዖት ነበራቸው። ይህን የንግስት ክሌዎፓትራ በእስክንድርያ (በግብፅ ) ‹‹ሳተርን›› (ዙሐል) ለሚባለው ጣዖት ቤተ ጣዖት ያሰራችለት እርሷ እንደሆነቸ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ ፡፡
✔ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እስክንድርያው ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312- 326/ ዘመን ድረስ ነበር፡፡ እለ እስክንድሮስ ሊያጠፋው ሲነሣ ሕዝቡ ከልቡ ገና የአምልኮ ጣዖት ስላልጣፋ 18 ፓትርያርኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት፡፡ እለ እስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት በነበረው በ12 ነው። እስክንድሮስም ስአስተምሮ የሳተርን አጠፋው።
ሕዝብ በ12 በገባ ሳተርን›› (ዙሐል) እናከብር ነበር አንተ እርሱን አጠፋህብን ሰለዚህ የለመድነው እንዳይቀር አንድ ነገር አድርግልን አሉት እስክንድሮስም በ12 የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እንዲያከብሩ አውጆ ቤተ ጣዖቱንም በቅዱስ ሚካኤል ስም ሰይሞ ቤተክርስቲያን አደረገው፡፡ ከዚህ በኋላ በቅዱስ ሚካኤልም ስም አብያተ ክርስቲያናት መታነጽ ጀመሩ በዓሉ በዚህ ቀን እንዲከበር ተወስኗል፡፡
✔ይህ ወደ እኛ የመጣው እስክንድሮስ ካረፈ በኋላ ቅዱስ አትናቴዎስ በተሾመ ጊዜ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ከኢትዮጵያ ሀገር ተልከው በእስክንድርያ ሀገር ጵጵስና ይዘው ሲመጡ ቅዱስ አትናቴዎስ ወር በገባ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል እንዲያከብሩ አስተምሯቸው አንድ ሕዝብ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን በአል ሲያከብሩ እግዚአብሔር ሲያመሰግኑ ተመልክተው ይህ ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው መተዋል አባቶቻችንም ወር በገባ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል እንዲ ዘከር እንዲከበር እንዲቀደስ በፍትሐ ነገስ ሥርዓት ሰርተውልናል።
❖ህዳር 12 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምን ምን ያደረገበት ነው?
✔ህዳር 12 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምን ምን ያደረገበት እንየሆነ እንመለከታለን፡፡
➊ቅዱስ ዱራታዎስ ቴዋብለት (ቴውብስታ) ቤት የተገለጠበት ቤታቸውን የባረከበት ዕለት ነው።
እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዋብለት ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያረጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን አጡ፡፡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስን ወደ በጎች እንዲሔድና በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ አዘዘው፤ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሔዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ አዘዘው፡፡
መልአኩም ወደ ቤት ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አስጠነቀቀው፡፡ ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ፡፡
✔ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ፤ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ፡፡ የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ዱራታዎስንም የዓሳውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፤ በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሳው ሆድ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዋብስታን እንዲህ አላቸው፡፡ ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሳውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ፤ እግዚአብሔር አስባችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁን ምጽዋዕታችሁን በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፡፡
በኋላኛውም መንግስት ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል፡፡›› ብሎ ባርኳቸው ከእንርሱ ተሰወረ።
•••••• #ይቀጥላል•••••

➋ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በባህር ሲጓዙ የተጨነቁትን የተራዳበት ዕለት ነው።
በአንድ ዘመን ብዙ ሰዎች ከግብፅ አውራጃ መጥተው ወደ ባሕር ማዶ ሄዱ፡፡ ከባሕሩም በደረሱ ጊዜ በመርከብ ላይ ተሳፍረው ከየብሱ ጥቂት በራቁና ወደ ባሕሩ መካከል በደረሱ ጊዜ ጽኑ ነፋስ ተነሳባቸው ለመስጠም እስኪ ደርሱ ድረስ፡፡
የማዕበሉ ሞገድ እየጨመረ እየጸና ከፍ አለ፡፡ ታላቅም ማዕበል መጥቶ ሊገለብጣቸው ደረሰ፡፡ ፍጹም ጥፋትና ክፉ ሞት እንደ መጣባቸው ባዩ ጊዜ ጽኑ ሐዘን ያዛቸው፡፡ የሚያድናቸው የሚያጽናናቸው አጥተው ተስፋ ቆረጡ፡፡ ያን ጊዜ እንዲህ ብለው ጮኹ፡፡
‹‹የመላእክት አለቃቸው ግሩም ገናና የምትሆን ሚካኤል ሆይ የተአምራትና የይቅርታ መልአክ ነህና፡፡ ልዑል ቸርነቱን የሚገልጥብህ መልአክ ሆይ! እግዚአብሔር ፍቅሩን የሚያስታውቅብህ መልአክ ሆይ ወደኛ ተመልከት እርዳን፡፡ የተጨነቅን እኛን አድነን፡፡ ከመጣብን ሞትና ጥፋት እንድን ዘንድ ስለኛ ወደ ፈጣሪህ ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር ለምንልን፡፡ አሁን የሞት መጋረጃ ዓይናችንን ሸፍኖታልና፡፡ ፍጹም የጥፋት ጥላንም አይተናታልና›› ብለው በፍጹም ልቦናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡
✔በመርከብ ውስጥ ያሉት ሁሉ ጽኑ ለቅሶ እያለቀሱ መራራ እንባ እያፈሰሱ ጮኹ፡፡ ከባሕር ጽኑ ማዕበል ከሞት ያድናቸው ዘንድ ያን ጊዜ በዚያች ሰዓት እግዚአብሔር የልቦናቸውን ሐዘንና ልመናቸውን ሰማቸው፡፡ ያን ጊዜም ይረዳቸው ዘንድ ቸር መልአኩን ሚካኤልን ላከላቸው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወረደ መርከቡን በእጁ ይዞ ሳበው፡፡
✔በመርከቡ ውስጥ ያሉትንም ወደ የብስ አወጣቸው፡፡ በደኅናቸው ተሻገሩ፤ ክፉ ነገር ጥቂትስ እንኳ ፈጽሞ አላገኛቸውም፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ገናና የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ልመናውና አማላጅነቱ ፈጽሞ ይጠብቀን፡፡ ከጽኑ ጠላት እጅ በክንፎቹ ጋርዶ ይሰውረን፡፡
➌ በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል
በዚህ እለት መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመበት እለት ነው፡፡
✔መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል
ኢያሱ ወልደ ነዌ ሕዝቡን እየመራ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዐይኑን አንሥቶ ቢመለከት እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ።
ወደ እርሱም ቀርቦ «ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን?» አለው። እርሱም «እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወደ አንተ መጥቻለሁ» ብሎታል። ኢያ ፭፥፲፫-፲፭። ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ይሁዳ «የመላእክት አለቃ ሚካኤል» በማለት መስክሮለታል ይሁዳ ፩፥፱።
✔ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በደሴተ ፍጥሞ በግዞት ሳለ በተመለከተው ራእይ ሃላፊያትና መጻእያት ተገልጠውለት ስለነበረ «በሰማይም ሰልፍ (ጦርነት) ሆነ፤» ካለ በኋላ «ሚካኤልና መላእክቱም ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም ከነሠራዊቱ ተዋጋቸው። አልቻላቸውምም ከዚያም በኋላ በሰማይ ቦታ አልተገኘላቸውም። ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ ወደ ምድርም ተጣለ መላእክቱም (የዘንዶው ሠራዊት) ከእርሱ ጋር ተጣሉ፤» ብሏል። ራእ ፲፪፥፯-፱።ዳን ፲ ፡፲፫ " ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ" የመላእክት አለቃ መሆኑን መስክሯል፡፡
በሌላ በኩል ቅዱስ ዳንኤል ፲፪፥፩ እንዲህ ይላል፦ «በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው (በአማላጅነት በተራዳኢነት የሚቆመው) ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል ሕዝብም በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤» ብሏል።
ዩሐንስ በራእዩ ፩ ፡ ፲፰ ያየው "ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መላእክ ሲወርድ አየሁ ከክብሩም የተንሳ ምድር በራች" ብሎ የመላእኩን ክብረ ተናግሯል የመላእክት አለቃ መሆኑን መስክሯል፡፡
➍ እስራኤልን ከግብፅ እየመራ ወደ ሀገራቸው ያስገባበት ዕለት የሚታሰብበት እለት ነው፡፡
ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጡትን ሕዝብ እግዚአብሔር ቀኑን በደመና ዓምድ ሌሊቱን ደግሞ በብርሃን ዓምድ መርቷቸዋል እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው መና ከሰማይ ያወረደላቸው ተአምራትን ያደረገላቸው ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው በደመና መጋረጃ የጋረዳቸውበክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው። መላእኩ በዚሁ እለት የሰራውን ድንቅ ስራ እንመሰክራለን፡፡
✔ኅዳር አሥራ ሁለት ቀን በየዓመቱ በማኅሌት እና በቅዳሴ የምናከብረው በዓለ ሹመቱን በማሰብ ቴዎብስታ ዱራታዎስ ያደረገው ታምረ እና በባህር የተጨነቁትን ያዳነበት በማሰብ ነው። ሌላው እና ዋንኛው የምናከብረው ይህ ለእስራኤል ዘሥጋ የተደረገውን የበለጠው ደግሞ እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ክርስቲያኖች ይደረግልናል።
☞ሰለማይንገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ምልጃና ጠብቆቱ ፍቅርና ርህራሄው በእኛ በልጆቹ ላይ አድሮ ለዘላለም ይኑር አሜን፡፡
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏

✞✞✞ #ጾመ_ነቢያት_የገና_ጾም ✞✞✞
🌾✞ ኅዳር 15 ይጀምራል ✞🌾
✔ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡
✔ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡
✔ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡
✔ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡
✔ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡
ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡
✔በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡
✔በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡
#ምንጭ፦ ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፤ ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

Telegram
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

🌾✞ #መልክዐ_ኪዳነ_ምሕረት ✞🌾
🌾ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤
አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡
🌾ሰላም ለአእዛንኪ እለ ተበሥራ ኪዳነ፤
እም አፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ፤
አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእይኒ ደይነ ፤
እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ ፤
ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ፡፡
🌾ሰላም ለእራኅኪ ተመጣዌ ኅብስት ወማይ፤
ሶበ ያመጽኡ ለኪ መላእክተ ሰማይ ፤
እንዘ ሀሎኪ ማርያም በመቅደሰ ኦሪት ዐባይ፤
ይትወከፍ ሊተ ኪዳንኪ ከመ መሥዋዕተ ሠርክ ኅሩይ፤
ለእመ ኅፍነ ማይ አስተይኩ ለጽሙዕ ነዳይ።
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤ አመ ይሰደድ እምገነት፡፡🙏
🌾ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤
አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡
🌾ሰላም ለአእዛንኪ እለ ተበሥራ ኪዳነ፤
እም አፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ፤
አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእይኒ ደይነ ፤
እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ ፤
ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ፡፡
🌾ሰላም ለእራኅኪ ተመጣዌ ኅብስት ወማይ፤
ሶበ ያመጽኡ ለኪ መላእክተ ሰማይ ፤
እንዘ ሀሎኪ ማርያም በመቅደሰ ኦሪት ዐባይ፤
ይትወከፍ ሊተ ኪዳንኪ ከመ መሥዋዕተ ሠርክ ኅሩይ፤
ለእመ ኅፍነ ማይ አስተይኩ ለጽሙዕ ነዳይ።
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤ አመ ይሰደድ እምገነት፡፡🙏
🌾✞ #ሐይማኖትኪ_አድኀነተኪ ✞🌾
✝️"ከፈሪሳውያንም አንድ ከእርሱ ጋር ይበላ ዘንድ ለመነው፤ በፈሪሳዊው ቤትም ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። እነሆም በዚያች ከተማ ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ሴት፤ በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደ ተቀመጠ ባወቀች ጊዜ፥ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ አመጣች። በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች።
✝️የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ። ኢየሱስም መልሶ፦ ስምዖን ሆይ፥ የምነግርህ ነገር አለኝ፡ አለው። እርሱም፦ መምህር ሆይ፥ ተናገር፡ አለ። ለአንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት በሁለተኛውም አምሳ። የሚከፍሉትም ቢያጡ ለሁለቱም ተወላቸው።
✝️እንግዲህ ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው ማንኛው ነው ስምዖንም መልሶ፦ ብዙ የተወለቱ ይመስለኛል፡ አለ። እርሱም፦ በእውነት ፈረድህ፡ አለው። ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች። አንተ አልሳምኸኝም፤ እርስዋ ግን ከገባሁ ጀምራ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም። አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች።
✝️ስለዚህ እልሃለሁ፥ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል። እርስዋንም፦ ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል፡ አላት። ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው፦ ኃጢአትን እንኳ የሚያስተሰርይ ይህ ማን ነው? ይሉ ጀመር። ሴቲቱንም፦ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፡ አላት።"
✍️ሉቃስ ፯፥፴፮-፶
🙏አቤት አምላክ ሆይ! የፈሪሳዊቷን ዓይነት ንፁህ ዕምነት አድለን። አሜን🙏

Photo
🌾✝️ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ሐጺር ✝️🌾
የቤተክርስቲያን አበው ሊቃውንት እንደሚሉት ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም። እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር። በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስን ያህል አጭር አልነበረም። በዚህም ምክንያት "ዮሐንስ ሐጺር" (አጭሩ ዮሐንስ) በመባል የሚታወቀው።
ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: (ቁመቱ እጅግ ያጠረ፤ ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን)" እንደ ማለት ነው።
ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ነው። ወላጆቹ ምንም እንኳ በሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም እጅግ መልካም ክርስቲያን ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል። ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትምኽርምትን ተምሯል።
ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር በትሕትናው፤ በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ስለገበር፤ አባ ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው ነበር። እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ "አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር።
ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው፤ እርሱም እርሱው ተደብድቦ፤ እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ። አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ ፯ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል።
አባ ባይሞይ ይኽንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ ሆኖ አይደለም። አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምህርት ስለነበረው እንጂ።
አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው። (የአካባቢው ጅብ መናጢ ክፋ ነበርና) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው። ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ፤ ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል።
ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው። "ምን ላድርገው አባ?" አለው፤ "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው፤ ከዚያ አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት። ይህ ነገር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ ወስዶ ተከለው።
ከዚያም ለኹለት ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው። ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ አስር ኪሎ ሜትር ያኽል ከገዳሙ ይርቅ ነበር። ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ።
በሦስተኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ፤ ደግሞም አፈራ። ካፈራው በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምህሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ ሰጠው። አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም፤ እጅግም አደነቀ፤ አለቀሰም።
ለሁላችንም እንደ ዮሐንስ ያለ ትህትናን ያድለን
የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ረድኤት በረከት ይድረሰን። 🙏

🌾✞ #የቅዱስ_መርቆሬዎስ_ሰማዕትነት ✞🌾
ኅዳር 25
❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ መካነ ልደቱ ቀጶዶቅያ ሲኾን ወላጆቹ በተወለደ ጊዜ ስሙን ፒሉፓዴር ብለውታል ትርጓሜውም “የአብ ወዳጅ” ማለት ሲኾን በመንፈሳዊ ትምህርት አጠንክረው አሳድገውታል፤ “ወተውህቦ ኀይል ዐቢይ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ወተሰምዐ ዜናሁ በኲሉ ወተለዐለ እምሰብአ ቤተ መንግሥት” ይላል
❖ ታላቅ የድል አድራጊነት ኀይል እንደ ዳዊት፣እንደ ሶምሶን ተሰጥቶት ዜናው በኹሉ ቦታ ሲሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችን ይልቅ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በዚኽ ምክንያት ከ249-251 ዓ.ም. በጊዜው በነበረው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘንድ በ17 ዓመቱ ጀምሮ ባለሟልነት አግኝቷል፡፡
❖ ከዚያም በሮም ላይ የበርበር ሰዎች ተነሥተው የዳኬዎስን መንግሥት ሊወጉት መጡ፤ እጅግ ብዙዎችም ነበሩና ንጉሡ እጅግ ፈራ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን እንደ ሶምሶን ኃይለ እግዚአብሔር ዐድሮበት “እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ አለውና አትፍራ” አለው፡፡
❖ “ወእምዝ ርእዮ ቅዱስ መርቆሬዎስ ለመልአከ እግዚአብሔር በውስተ ቀትል ወሰይፍ በሊኅ ውስተ እዴሁ” ይላል፤ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በውጊያው ውስጥ የተሳለ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገልጦለት ሰይፉን በመስጠት “ጠላቶችኽን ድል ባደረግኽ ጊዜ ፈጣሪኽ እግዚአብሔርን ዐስበው” ብሎ ሰጥቶታል፤ አንዱ ራሱ ለውጊያ የያዘው ሰይፍ ኹለተኛም ከመልአኩ የተቀበለው ብሩህ ሰይፍ ነበርና በዚኽ ምክንያት “አበ አስይፍት” (የሰይፎች አባት) ተብሏል፤ ይኽም ሊታወቅ ኹለት ሰይፎች ይዞ ይሣላል፡፡
❖ ከዚኽ በኋላ በ249 ዓ.ም ንጉሡ ዳኬዎስ ፈጣሪው ክርስቶስን ክዶ ለአርጤምስ ጣዖታት ዕጣን ሊያቀርብና በዓልን ሊያደርግ ወደዶ በዓልን ባደረገ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን ከርሱ ጋር አልወጣም፤ ቅዱስ ሚካኤልም ለቅዱስ መርቆሬዎስ ተገልጾ በአምላኩ በክርስቶስ ስም መከራን በትዕግሥት እንዲቀበል ነግሮታል።
❖ ንጉሡ ዳኬዎስም አስጠርቶት “ድልን ለሰጡን ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልወጣኽ የእኔንስ ፍቅር ለምን ተውኽ” ብሎ ጠየቀው፤ በዚኽ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሡ ፊት ትጥቁንና ልብሱን ወርውሮ “ንጉሥ ሆይ ድልን የተቀዳጀነው በሰው እጅ በተሠሩ በነዚህ ደናቁርት ጣዖታት አይደለም፤ መልአኩን ልኮ ሰይፍን በሰጠኝ በጌታዬ በመድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት እንጂ፤ አኹንም እኔ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም” በማለት መለሰለት፡፡
❖ ንጉሡም እጅግ ተቈጥቶ ርጥብ በኾኑ የሽመል በትሮችና እንዲደበደብና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገረፍ አዘዘ፤ ሥጋውንም በቢላዋ እየቆራረጡ ከበታቹ እሳት ሲያነዱ ከሰውነቱ ከወጣው ከብዙ ደም የተነሣ እሳቱ ጠፍቷል፡፡
❖ ከዚያም ወደ እስር ቤት በጣሉት ጊዜ ጌታችን በዚያች ሌሊት ተገልጾለት ከሕመሙ ከስቃዩ ኹሉ ፈውሶታል። ከሓዲው ዳኬዎስም ቅዱስ መርቆሬዎስ ካለው ተወዳጅነት የተነሣ ሰዎች እንዳይነሡበት በመፍራት የቀጶዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ኾነች ወደ ቂሳርያ በብረት ማሠሪያ ታሥሮ እንዲላክና አንገቱ እንዲቆረጥ አዘዘ።
❖ ከዚያም ቅዱስ መርቆሬዎስ እጆቹን ዘርግቶ አምላኩ ክርስቶስ በገነት እንዲቀበለው ለመነ፤ ያን ጊዜ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ በታላቅ ግርማ ተገለጸለት፤ "የተመረጥክ ልጄ መርቆሬዎስ ሆይ ከቅዱሳን ጋር ወደ ዘላለማዊ ማረፊያኽ ና፤ ጸሎትኽ መልካም መዐዛ እንዳለው ዕጣን ወደ እኔ ዐረገ፤ የአንተ ስም በሚጠራበት ቤተ ክርስቲያን ኹሉ ተአምር ይደረጋል፤ በአንተ ምልጃ የሚማፀኑኝን አድናቸዋለው፤ የገድልኽን መጽሐፍ የሚጽፉ የሚያነቡ ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባለትና መርቆሬዎስን ባረከው።
❖ ቅዱስ መርቆሬዎስም በእጅጉ ተደስቶ በንጉሡ ትዕዛዝ አንገቱን ሊቆርጡ የተዘጋጁትን ፈጥነው እንዲፈጽሙ ለመናቸው፤ ከዚያም በጉልበቱ ተንበርክኮ
"ጌታዬ ሆይ ኃጢአታቸውን አትቁጠርባቸው" ብሎ ልመናን ካቀረበ በኋላ ኅዳር 25 በ250 ዓ.ም. ከሓድያኑ ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት በክርስቶስ ስም የሰማዕትነትን አክሊል በ25 ዓመቱ ተቀዳጀ።
❖ ያን ጊዜ ከበድኑ መዓዛው እንደ ሽቱና ዕጣን እጅግ ደስ የሚል ሽታ ይወጣ ነበር፤ ከበድኑና ከተቀበረበት ቦታ ብዙ ተአምራት ተደረጉ፤ በርካቶች ሕሙማን ተፈወሱ፤ የሰማዕታት ዘመን ካለፈም በኋላ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውለታልና፡፡ እመቤታችን በግብጽ በደብረ ምጥማቅ ጉልላት ላይ ከግንቦት 21-25 ድረስ በተገለጠች ጊዜ ዐብረዋት ከሚመጡ ሰማዕታት ውስጥ ቅዱስ መርቆሬዎስ ነበረበት።
❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈጣን ተራዳኢነቱ የሚታወቅ ሲኾን ከሓዲው ዑልያኖስ ብዙ ክርስቲያኖችን በሚገድልበት ጊዜ ታላላቆች ሊቃውንት የነበሩትን ቅዱስ ባስልዮስና ቅዱስ ጎርጎርዮስ በአምላክ እናት ሥዕልና አጠገቧ በተሣለው በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ቆመው ቢማፀኑ፤ እመቤታችን ሰማዕቱን አዝዛው ፈጥኖ ደርሶ ክርስቶስን የካደው ክርስቲያኖችን የሚፈጀው ዑልያኖስን ቀሥፎታል፤ ይኽም በመላው ዓለም በሚሣለው በሥዕሉ ላይ ይታያል ።
❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም የቅዱስ መርቆሬዎስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”
(በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው) እያለ መስክሮለታል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል
ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡
(የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሶታል፨
[ተወዳጆች ሆይ ከበረከቱ ትሳተፉ ዘንድ በበዓሉ ዕለት የተራቡትን በመመገብ፤ የተጠሙትን በማጠጣት፤ የታመሙትን በመጠየቅ፤ ያዘኑትን በማጽናናት፤ በዓሉን በማክበር ታስቡት ዘንድ እመክራችኋለሁ የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን🙏
✍በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
ኅዳር 25
❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ መካነ ልደቱ ቀጶዶቅያ ሲኾን ወላጆቹ በተወለደ ጊዜ ስሙን ፒሉፓዴር ብለውታል ትርጓሜውም “የአብ ወዳጅ” ማለት ሲኾን በመንፈሳዊ ትምህርት አጠንክረው አሳድገውታል፤ “ወተውህቦ ኀይል ዐቢይ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ወተሰምዐ ዜናሁ በኲሉ ወተለዐለ እምሰብአ ቤተ መንግሥት” ይላል
❖ ታላቅ የድል አድራጊነት ኀይል እንደ ዳዊት፣እንደ ሶምሶን ተሰጥቶት ዜናው በኹሉ ቦታ ሲሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችን ይልቅ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በዚኽ ምክንያት ከ249-251 ዓ.ም. በጊዜው በነበረው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘንድ በ17 ዓመቱ ጀምሮ ባለሟልነት አግኝቷል፡፡
❖ ከዚያም በሮም ላይ የበርበር ሰዎች ተነሥተው የዳኬዎስን መንግሥት ሊወጉት መጡ፤ እጅግ ብዙዎችም ነበሩና ንጉሡ እጅግ ፈራ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን እንደ ሶምሶን ኃይለ እግዚአብሔር ዐድሮበት “እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ አለውና አትፍራ” አለው፡፡
❖ “ወእምዝ ርእዮ ቅዱስ መርቆሬዎስ ለመልአከ እግዚአብሔር በውስተ ቀትል ወሰይፍ በሊኅ ውስተ እዴሁ” ይላል፤ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በውጊያው ውስጥ የተሳለ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገልጦለት ሰይፉን በመስጠት “ጠላቶችኽን ድል ባደረግኽ ጊዜ ፈጣሪኽ እግዚአብሔርን ዐስበው” ብሎ ሰጥቶታል፤ አንዱ ራሱ ለውጊያ የያዘው ሰይፍ ኹለተኛም ከመልአኩ የተቀበለው ብሩህ ሰይፍ ነበርና በዚኽ ምክንያት “አበ አስይፍት” (የሰይፎች አባት) ተብሏል፤ ይኽም ሊታወቅ ኹለት ሰይፎች ይዞ ይሣላል፡፡
❖ ከዚኽ በኋላ በ249 ዓ.ም ንጉሡ ዳኬዎስ ፈጣሪው ክርስቶስን ክዶ ለአርጤምስ ጣዖታት ዕጣን ሊያቀርብና በዓልን ሊያደርግ ወደዶ በዓልን ባደረገ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን ከርሱ ጋር አልወጣም፤ ቅዱስ ሚካኤልም ለቅዱስ መርቆሬዎስ ተገልጾ በአምላኩ በክርስቶስ ስም መከራን በትዕግሥት እንዲቀበል ነግሮታል።
❖ ንጉሡ ዳኬዎስም አስጠርቶት “ድልን ለሰጡን ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልወጣኽ የእኔንስ ፍቅር ለምን ተውኽ” ብሎ ጠየቀው፤ በዚኽ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሡ ፊት ትጥቁንና ልብሱን ወርውሮ “ንጉሥ ሆይ ድልን የተቀዳጀነው በሰው እጅ በተሠሩ በነዚህ ደናቁርት ጣዖታት አይደለም፤ መልአኩን ልኮ ሰይፍን በሰጠኝ በጌታዬ በመድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት እንጂ፤ አኹንም እኔ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም” በማለት መለሰለት፡፡
❖ ንጉሡም እጅግ ተቈጥቶ ርጥብ በኾኑ የሽመል በትሮችና እንዲደበደብና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገረፍ አዘዘ፤ ሥጋውንም በቢላዋ እየቆራረጡ ከበታቹ እሳት ሲያነዱ ከሰውነቱ ከወጣው ከብዙ ደም የተነሣ እሳቱ ጠፍቷል፡፡
❖ ከዚያም ወደ እስር ቤት በጣሉት ጊዜ ጌታችን በዚያች ሌሊት ተገልጾለት ከሕመሙ ከስቃዩ ኹሉ ፈውሶታል። ከሓዲው ዳኬዎስም ቅዱስ መርቆሬዎስ ካለው ተወዳጅነት የተነሣ ሰዎች እንዳይነሡበት በመፍራት የቀጶዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ኾነች ወደ ቂሳርያ በብረት ማሠሪያ ታሥሮ እንዲላክና አንገቱ እንዲቆረጥ አዘዘ።
❖ ከዚያም ቅዱስ መርቆሬዎስ እጆቹን ዘርግቶ አምላኩ ክርስቶስ በገነት እንዲቀበለው ለመነ፤ ያን ጊዜ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ በታላቅ ግርማ ተገለጸለት፤ "የተመረጥክ ልጄ መርቆሬዎስ ሆይ ከቅዱሳን ጋር ወደ ዘላለማዊ ማረፊያኽ ና፤ ጸሎትኽ መልካም መዐዛ እንዳለው ዕጣን ወደ እኔ ዐረገ፤ የአንተ ስም በሚጠራበት ቤተ ክርስቲያን ኹሉ ተአምር ይደረጋል፤ በአንተ ምልጃ የሚማፀኑኝን አድናቸዋለው፤ የገድልኽን መጽሐፍ የሚጽፉ የሚያነቡ ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባለትና መርቆሬዎስን ባረከው።
❖ ቅዱስ መርቆሬዎስም በእጅጉ ተደስቶ በንጉሡ ትዕዛዝ አንገቱን ሊቆርጡ የተዘጋጁትን ፈጥነው እንዲፈጽሙ ለመናቸው፤ ከዚያም በጉልበቱ ተንበርክኮ
"ጌታዬ ሆይ ኃጢአታቸውን አትቁጠርባቸው" ብሎ ልመናን ካቀረበ በኋላ ኅዳር 25 በ250 ዓ.ም. ከሓድያኑ ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት በክርስቶስ ስም የሰማዕትነትን አክሊል በ25 ዓመቱ ተቀዳጀ።
❖ ያን ጊዜ ከበድኑ መዓዛው እንደ ሽቱና ዕጣን እጅግ ደስ የሚል ሽታ ይወጣ ነበር፤ ከበድኑና ከተቀበረበት ቦታ ብዙ ተአምራት ተደረጉ፤ በርካቶች ሕሙማን ተፈወሱ፤ የሰማዕታት ዘመን ካለፈም በኋላ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውለታልና፡፡ እመቤታችን በግብጽ በደብረ ምጥማቅ ጉልላት ላይ ከግንቦት 21-25 ድረስ በተገለጠች ጊዜ ዐብረዋት ከሚመጡ ሰማዕታት ውስጥ ቅዱስ መርቆሬዎስ ነበረበት።
❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈጣን ተራዳኢነቱ የሚታወቅ ሲኾን ከሓዲው ዑልያኖስ ብዙ ክርስቲያኖችን በሚገድልበት ጊዜ ታላላቆች ሊቃውንት የነበሩትን ቅዱስ ባስልዮስና ቅዱስ ጎርጎርዮስ በአምላክ እናት ሥዕልና አጠገቧ በተሣለው በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ቆመው ቢማፀኑ፤ እመቤታችን ሰማዕቱን አዝዛው ፈጥኖ ደርሶ ክርስቶስን የካደው ክርስቲያኖችን የሚፈጀው ዑልያኖስን ቀሥፎታል፤ ይኽም በመላው ዓለም በሚሣለው በሥዕሉ ላይ ይታያል ።
❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም የቅዱስ መርቆሬዎስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”
(በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው) እያለ መስክሮለታል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል
ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡
(የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሶታል፨
[ተወዳጆች ሆይ ከበረከቱ ትሳተፉ ዘንድ በበዓሉ ዕለት የተራቡትን በመመገብ፤ የተጠሙትን በማጠጣት፤ የታመሙትን በመጠየቅ፤ ያዘኑትን በማጽናናት፤ በዓሉን በማክበር ታስቡት ዘንድ እመክራችኋለሁ የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን🙏
✍በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
Telegram
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
መርቆሬዎስ @EOTC2921 .mp3
1.3 MB
🌾✞ #መርቆሬዎስ ✞🌾
መርቆርዮስ /፬/
የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ
እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ //፪//
ባስልዮስ ጎርጎሪዮስ ሰምሯል ልመናቸው
ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ
እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆርዮስ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
ዑልያኖስ ተገድሏል ሐይማኖት ይስፋፋል
ብሎ መሰከረ መርቆሬዎስ ሃያል
ገፀ ከላባቱ ባህርይ ቀየሩ
እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ
መርቆሬዎስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ
በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ
መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዎስ ወደደ
ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ
በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ
ስሙ ተሰየመ ከሰማዕታት ጋ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር
መፍቅሬ አብ ካለ ያኘሎፓዴር
ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ
ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
መርቆርዮስ /፬/
የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ
እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ //፪//
ባስልዮስ ጎርጎሪዮስ ሰምሯል ልመናቸው
ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ
እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆርዮስ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
ዑልያኖስ ተገድሏል ሐይማኖት ይስፋፋል
ብሎ መሰከረ መርቆሬዎስ ሃያል
ገፀ ከላባቱ ባህርይ ቀየሩ
እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ
መርቆሬዎስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ
በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ
መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዎስ ወደደ
ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ
በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ
ስሙ ተሰየመ ከሰማዕታት ጋ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር
መፍቅሬ አብ ካለ ያኘሎፓዴር
ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ
ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
🌾✞ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ✞🌾
ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማእታዊው የእኛ አባት (2)
ተዋህዶ ምሰሶ ሆንካት(2)
ከእናትህ ማህፀን ቸሩ አምላክ ሲያስብህ(2)
ለኢትዮጵያ ብርሃን አረግህ(2)
ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማእታዊው የእኛ አባት (2)
ተዋህዶ ምሰሶ ሆንካት(2)
ከእናትህ ማህፀን ቸሩ አምላክ ሲያስብህ(2)
ለኢትዮጵያ ብርሃን አረግህ(2)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🌾🌻🙏✞ #መድኃኔዓለም ✞🙏🌻🌾
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
➥ለተጨማሪ...
youtube.com/EOTC2921
facebook.com/eotc2921
tiktok.com/@eotc2921
www.tg-me.com/EOTC2921
instagram.com/eotc2921
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
➥ለተጨማሪ...
youtube.com/EOTC2921
facebook.com/eotc2921
tiktok.com/@eotc2921
www.tg-me.com/EOTC2921
instagram.com/eotc2921