Telegram Web Link
➋ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በባህር ሲጓዙ የተጨነቁትን የተራዳበት ዕለት ነው።
በአንድ ዘመን ብዙ ሰዎች ከግብፅ አውራጃ መጥተው ወደ ባሕር ማዶ ሄዱ፡፡ ከባሕሩም በደረሱ ጊዜ በመርከብ ላይ ተሳፍረው ከየብሱ ጥቂት በራቁና ወደ ባሕሩ መካከል በደረሱ ጊዜ ጽኑ ነፋስ ተነሳባቸው ለመስጠም እስኪ ደርሱ ድረስ፡፡

የማዕበሉ ሞገድ እየጨመረ እየጸና ከፍ አለ፡፡ ታላቅም ማዕበል መጥቶ ሊገለብጣቸው ደረሰ፡፡ ፍጹም ጥፋትና ክፉ ሞት እንደ መጣባቸው ባዩ ጊዜ ጽኑ ሐዘን ያዛቸው፡፡ የሚያድናቸው የሚያጽናናቸው አጥተው ተስፋ ቆረጡ፡፡ ያን ጊዜ እንዲህ ብለው ጮኹ፡፡

‹‹የመላእክት አለቃቸው ግሩም ገናና የምትሆን ሚካኤል ሆይ የተአምራትና የይቅርታ መልአክ ነህና፡፡ ልዑል ቸርነቱን የሚገልጥብህ መልአክ ሆይ! እግዚአብሔር ፍቅሩን የሚያስታውቅብህ መልአክ ሆይ ወደኛ ተመልከት እርዳን፡፡ የተጨነቅን እኛን አድነን፡፡ ከመጣብን ሞትና ጥፋት እንድን ዘንድ ስለኛ ወደ ፈጣሪህ ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር ለምንልን፡፡ አሁን የሞት መጋረጃ ዓይናችንን ሸፍኖታልና፡፡ ፍጹም የጥፋት ጥላንም አይተናታልና›› ብለው በፍጹም ልቦናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡

በመርከብ ውስጥ ያሉት ሁሉ ጽኑ ለቅሶ እያለቀሱ መራራ እንባ እያፈሰሱ ጮኹ፡፡ ከባሕር ጽኑ ማዕበል ከሞት ያድናቸው ዘንድ ያን ጊዜ በዚያች ሰዓት እግዚአብሔር የልቦናቸውን ሐዘንና ልመናቸውን ሰማቸው፡፡ ያን ጊዜም ይረዳቸው ዘንድ ቸር መልአኩን ሚካኤልን ላከላቸው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወረደ መርከቡን በእጁ ይዞ ሳበው፡፡

በመርከቡ ውስጥ ያሉትንም ወደ የብስ አወጣቸው፡፡ በደኅናቸው ተሻገሩ፤ ክፉ ነገር ጥቂትስ እንኳ ፈጽሞ አላገኛቸውም፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ገናና የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ልመናውና አማላጅነቱ ፈጽሞ ይጠብቀን፡፡ ከጽኑ ጠላት እጅ በክንፎቹ ጋርዶ ይሰውረን፡፡

➌ በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል
በዚህ እለት መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመበት እለት ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል
ኢያሱ ወልደ ነዌ ሕዝቡን እየመራ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዐይኑን አንሥቶ ቢመለከት እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ።
ወደ እርሱም ቀርቦ «ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን?» አለው። እርሱም «እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወደ አንተ መጥቻለሁ» ብሎታል። ኢያ ፭፥፲፫-፲፭። ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ይሁዳ «የመላእክት አለቃ ሚካኤል» በማለት መስክሮለታል ይሁዳ ፩፥፱።

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በደሴተ ፍጥሞ በግዞት ሳለ በተመለከተው ራእይ ሃላፊያትና መጻእያት ተገልጠውለት ስለነበረ «በሰማይም ሰልፍ (ጦርነት) ሆነ፤» ካለ በኋላ «ሚካኤልና መላእክቱም ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም ከነሠራዊቱ ተዋጋቸው። አልቻላቸውምም ከዚያም በኋላ በሰማይ ቦታ አልተገኘላቸውም። ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ ወደ ምድርም ተጣለ መላእክቱም (የዘንዶው ሠራዊት) ከእርሱ ጋር ተጣሉ፤» ብሏል። ራእ ፲፪፥፯-፱።ዳን ፲ ፡፲፫ " ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ" የመላእክት አለቃ መሆኑን መስክሯል፡፡
በሌላ በኩል ቅዱስ ዳንኤል ፲፪፥፩ እንዲህ ይላል፦ «በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው (በአማላጅነት በተራዳኢነት የሚቆመው) ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል ሕዝብም በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤» ብሏል።
ዩሐንስ በራእዩ ፩ ፡ ፲፰ ያየው "ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መላእክ ሲወርድ አየሁ ከክብሩም የተንሳ ምድር በራች" ብሎ የመላእኩን ክብረ ተናግሯል የመላእክት አለቃ መሆኑን መስክሯል፡፡

➍ እስራኤልን ከግብፅ እየመራ ወደ ሀገራቸው ያስገባበት ዕለት የሚታሰብበት እለት ነው፡፡
ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጡትን ሕዝብ እግዚአብሔር ቀኑን በደመና ዓምድ ሌሊቱን ደግሞ በብርሃን ዓምድ መርቷቸዋል እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው መና ከሰማይ ያወረደላቸው ተአምራትን ያደረገላቸው ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው በደመና መጋረጃ የጋረዳቸውበክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው። መላእኩ በዚሁ እለት የሰራውን ድንቅ ስራ እንመሰክራለን፡፡

ኅዳር አሥራ ሁለት ቀን በየዓመቱ በማኅሌት እና በቅዳሴ የምናከብረው በዓለ ሹመቱን በማሰብ ቴዎብስታ ዱራታዎስ ያደረገው ታምረ እና በባህር የተጨነቁትን ያዳነበት በማሰብ ነው። ሌላው እና ዋንኛው የምናከብረው ይህ ለእስራኤል ዘሥጋ የተደረገውን የበለጠው ደግሞ እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ክርስቲያኖች ይደረግልናል።

☞ሰለማይንገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ምልጃና ጠብቆቱ ፍቅርና ርህራሄው በእኛ በልጆቹ ላይ አድሮ ለዘላለም ይኑር አሜን፡፡

🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏
🙏54👍1
✞✞✞ #ጾመ_ነቢያት_የገና_ጾም ✞✞✞
🌾✞ ኅዳር 15 ይጀምራል ✞🌾

ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡
ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡
ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡
ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡
በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡
#ምንጭ፦ ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፤ ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
🙏7👍4🥰21
🌾#መልክዐ_ኪዳነ_ምሕረት🌾

🌾ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤
አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡

🌾ሰላም ለአእዛንኪ እለ ተበሥራ ኪዳነ፤
እም አፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ፤
አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእይኒ ደይነ ፤
እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ ፤
ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ፡፡

🌾ሰላም ለእራኅኪ ተመጣዌ ኅብስት ወማይ፤
ሶበ ያመጽኡ ለኪ መላእክተ ሰማይ ፤
እንዘ ሀሎኪ ማርያም በመቅደሰ ኦሪት ዐባይ፤
ይትወከፍ ሊተ ኪዳንኪ ከመ መሥዋዕተ ሠርክ ኅሩይ፤
ለእመ ኅፍነ ማይ አስተይኩ ለጽሙዕ ነዳይ።

አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤ አመ ይሰደድ እምገነት፡፡🙏
🥰5🙏32👏1
🌾#ሐይማኖትኪ_አድኀነተኪ🌾

✝️"ከፈሪሳውያንም አንድ ከእርሱ ጋር ይበላ ዘንድ ለመነው፤ በፈሪሳዊው ቤትም ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። እነሆም በዚያች ከተማ ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ሴት፤ በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደ ተቀመጠ ባወቀች ጊዜ፥ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ አመጣች። በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች።

✝️የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ። ኢየሱስም መልሶ፦ ስምዖን ሆይ፥ የምነግርህ ነገር አለኝ፡ አለው። እርሱም፦ መምህር ሆይ፥ ተናገር፡ አለ። ለአንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት በሁለተኛውም አምሳ። የሚከፍሉትም ቢያጡ ለሁለቱም ተወላቸው።

✝️እንግዲህ ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው ማንኛው ነው ስምዖንም መልሶ፦ ብዙ የተወለቱ ይመስለኛል፡ አለ። እርሱም፦ በእውነት ፈረድህ፡ አለው። ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች። አንተ አልሳምኸኝም፤ እርስዋ ግን ከገባሁ ጀምራ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም። አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች።

✝️ስለዚህ እልሃለሁ፥ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል። እርስዋንም፦ ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል፡ አላት። ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው፦ ኃጢአትን እንኳ የሚያስተሰርይ ይህ ማን ነው? ይሉ ጀመር። ሴቲቱንም፦ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፡ አላት።"
✍️ሉቃስ ፯፥፴፮-፶

🙏አቤት አምላክ ሆይ! የፈሪሳዊቷን ዓይነት ንፁህ ዕምነት አድለን። አሜን🙏
🙏84👍3🥰1
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
Photo
🌾✝️ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ሐጺር ✝️🌾

የቤተክርስቲያን አበው ሊቃውንት እንደሚሉት ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም። እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር። በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስን ያህል አጭር አልነበረም። በዚህም ምክንያት "ዮሐንስ ሐጺር" (አጭሩ ዮሐንስ) በመባል የሚታወቀው።

ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: (ቁመቱ እጅግ ያጠረ፤ ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን)" እንደ ማለት ነው።
ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ነው። ወላጆቹ ምንም እንኳ በሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም እጅግ መልካም ክርስቲያን ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል። ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትምኽርምትን ተምሯል።

ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር በትሕትናው፤ በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ስለገበር፤ አባ ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው ነበር። እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ "አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር።

ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው፤ እርሱም እርሱው ተደብድቦ፤ እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ። አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ ፯ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል።

አባ ባይሞይ ይኽንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ ሆኖ አይደለም። አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምህርት ስለነበረው እንጂ።

አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው። (የአካባቢው ጅብ መናጢ ክፋ ነበርና) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው። ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ፤ ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል።

ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው። "ምን ላድርገው አባ?" አለው፤ "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው፤ ከዚያ አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት። ይህ ነገር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ ወስዶ ተከለው።

ከዚያም ለኹለት ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው። ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ አስር ኪሎ ሜትር ያኽል ከገዳሙ ይርቅ ነበር። ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ።

በሦስተኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ፤ ደግሞም አፈራ። ካፈራው በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምህሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ ሰጠው። አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም፤ እጅግም አደነቀ፤ አለቀሰም።

ለሁላችንም እንደ ዮሐንስ ያለ ትህትናን ያድለን
የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ረድኤት በረከት ይድረሰን። 🙏
🙏42👍2🥰2
🌾#የቅዱስ_መርቆሬዎስ_ሰማዕትነት🌾

ኅዳር 25
❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ መካነ ልደቱ ቀጶዶቅያ ሲኾን ወላጆቹ በተወለደ ጊዜ ስሙን ፒሉፓዴር ብለውታል ትርጓሜውም “የአብ ወዳጅ” ማለት ሲኾን በመንፈሳዊ ትምህርት አጠንክረው አሳድገውታል፤ “ወተውህቦ ኀይል ዐቢይ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ወተሰምዐ ዜናሁ በኲሉ ወተለዐለ እምሰብአ ቤተ መንግሥት” ይላል
❖ ታላቅ የድል አድራጊነት ኀይል እንደ ዳዊት፣እንደ ሶምሶን ተሰጥቶት ዜናው በኹሉ ቦታ ሲሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችን ይልቅ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በዚኽ ምክንያት ከ249-251 ዓ.ም. በጊዜው በነበረው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘንድ በ17 ዓመቱ ጀምሮ ባለሟልነት አግኝቷል፡፡
❖ ከዚያም በሮም ላይ የበርበር ሰዎች ተነሥተው የዳኬዎስን መንግሥት ሊወጉት መጡ፤ እጅግ ብዙዎችም ነበሩና ንጉሡ እጅግ ፈራ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን እንደ ሶምሶን ኃይለ እግዚአብሔር ዐድሮበት “እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ አለውና አትፍራ” አለው፡፡
❖ “ወእምዝ ርእዮ ቅዱስ መርቆሬዎስ ለመልአከ እግዚአብሔር በውስተ ቀትል ወሰይፍ በሊኅ ውስተ እዴሁ” ይላል፤ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በውጊያው ውስጥ የተሳለ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገልጦለት ሰይፉን በመስጠት “ጠላቶችኽን ድል ባደረግኽ ጊዜ ፈጣሪኽ እግዚአብሔርን ዐስበው” ብሎ ሰጥቶታል፤ አንዱ ራሱ ለውጊያ የያዘው ሰይፍ ኹለተኛም ከመልአኩ የተቀበለው ብሩህ ሰይፍ ነበርና በዚኽ ምክንያት “አበ አስይፍት” (የሰይፎች አባት) ተብሏል፤ ይኽም ሊታወቅ ኹለት ሰይፎች ይዞ ይሣላል፡፡
❖ ከዚኽ በኋላ በ249 ዓ.ም ንጉሡ ዳኬዎስ ፈጣሪው ክርስቶስን ክዶ ለአርጤምስ ጣዖታት ዕጣን ሊያቀርብና በዓልን ሊያደርግ ወደዶ በዓልን ባደረገ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን ከርሱ ጋር አልወጣም፤ ቅዱስ ሚካኤልም ለቅዱስ መርቆሬዎስ ተገልጾ በአምላኩ በክርስቶስ ስም መከራን በትዕግሥት እንዲቀበል ነግሮታል።
❖ ንጉሡ ዳኬዎስም አስጠርቶት “ድልን ለሰጡን ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልወጣኽ የእኔንስ ፍቅር ለምን ተውኽ” ብሎ ጠየቀው፤ በዚኽ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሡ ፊት ትጥቁንና ልብሱን ወርውሮ “ንጉሥ ሆይ ድልን የተቀዳጀነው በሰው እጅ በተሠሩ በነዚህ ደናቁርት ጣዖታት አይደለም፤ መልአኩን ልኮ ሰይፍን በሰጠኝ በጌታዬ በመድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት እንጂ፤ አኹንም እኔ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም” በማለት መለሰለት፡፡
❖ ንጉሡም እጅግ ተቈጥቶ ርጥብ በኾኑ የሽመል በትሮችና እንዲደበደብና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገረፍ አዘዘ፤ ሥጋውንም በቢላዋ እየቆራረጡ ከበታቹ እሳት ሲያነዱ ከሰውነቱ ከወጣው ከብዙ ደም የተነሣ እሳቱ ጠፍቷል፡፡
❖ ከዚያም ወደ እስር ቤት በጣሉት ጊዜ ጌታችን በዚያች ሌሊት ተገልጾለት ከሕመሙ ከስቃዩ ኹሉ ፈውሶታል። ከሓዲው ዳኬዎስም ቅዱስ መርቆሬዎስ ካለው ተወዳጅነት የተነሣ ሰዎች እንዳይነሡበት በመፍራት የቀጶዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ኾነች ወደ ቂሳርያ በብረት ማሠሪያ ታሥሮ እንዲላክና አንገቱ እንዲቆረጥ አዘዘ።
❖ ከዚያም ቅዱስ መርቆሬዎስ እጆቹን ዘርግቶ አምላኩ ክርስቶስ በገነት እንዲቀበለው ለመነ፤ ያን ጊዜ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ በታላቅ ግርማ ተገለጸለት፤ "የተመረጥክ ልጄ መርቆሬዎስ ሆይ ከቅዱሳን ጋር ወደ ዘላለማዊ ማረፊያኽ ና፤ ጸሎትኽ መልካም መዐዛ እንዳለው ዕጣን ወደ እኔ ዐረገ፤ የአንተ ስም በሚጠራበት ቤተ ክርስቲያን ኹሉ ተአምር ይደረጋል፤ በአንተ ምልጃ የሚማፀኑኝን አድናቸዋለው፤ የገድልኽን መጽሐፍ የሚጽፉ የሚያነቡ ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባለትና መርቆሬዎስን ባረከው።
❖ ቅዱስ መርቆሬዎስም በእጅጉ ተደስቶ በንጉሡ ትዕዛዝ አንገቱን ሊቆርጡ የተዘጋጁትን ፈጥነው እንዲፈጽሙ ለመናቸው፤ ከዚያም በጉልበቱ ተንበርክኮ
"ጌታዬ ሆይ ኃጢአታቸውን አትቁጠርባቸው" ብሎ ልመናን ካቀረበ በኋላ ኅዳር 25 በ250 ዓ.ም. ከሓድያኑ ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት በክርስቶስ ስም የሰማዕትነትን አክሊል በ25 ዓመቱ ተቀዳጀ።
❖ ያን ጊዜ ከበድኑ መዓዛው እንደ ሽቱና ዕጣን እጅግ ደስ የሚል ሽታ ይወጣ ነበር፤ ከበድኑና ከተቀበረበት ቦታ ብዙ ተአምራት ተደረጉ፤ በርካቶች ሕሙማን ተፈወሱ፤ የሰማዕታት ዘመን ካለፈም በኋላ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውለታልና፡፡ እመቤታችን በግብጽ በደብረ ምጥማቅ ጉልላት ላይ ከግንቦት 21-25 ድረስ በተገለጠች ጊዜ ዐብረዋት ከሚመጡ ሰማዕታት ውስጥ ቅዱስ መርቆሬዎስ ነበረበት።
❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈጣን ተራዳኢነቱ የሚታወቅ ሲኾን ከሓዲው ዑልያኖስ ብዙ ክርስቲያኖችን በሚገድልበት ጊዜ ታላላቆች ሊቃውንት የነበሩትን ቅዱስ ባስልዮስና ቅዱስ ጎርጎርዮስ በአምላክ እናት ሥዕልና አጠገቧ በተሣለው በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ቆመው ቢማፀኑ፤ እመቤታችን ሰማዕቱን አዝዛው ፈጥኖ ደርሶ ክርስቶስን የካደው ክርስቲያኖችን የሚፈጀው ዑልያኖስን ቀሥፎታል፤ ይኽም በመላው ዓለም በሚሣለው በሥዕሉ ላይ ይታያል ።
❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም የቅዱስ መርቆሬዎስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”
(በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው) እያለ መስክሮለታል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል
ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡
(የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሶታል፨
[ተወዳጆች ሆይ ከበረከቱ ትሳተፉ ዘንድ በበዓሉ ዕለት የተራቡትን በመመገብ፤ የተጠሙትን በማጠጣት፤ የታመሙትን በመጠየቅ፤ ያዘኑትን በማጽናናት፤ በዓሉን በማክበር ታስቡት ዘንድ እመክራችኋለሁ የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን🙏
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
🙏5👍2
መርቆሬዎስ @EOTC2921 .mp3
1.3 MB
🌾#መርቆሬዎስ🌾

መርቆርዮስ /፬/
የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ
እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ //፪//

ባስልዮስ ጎርጎሪዮስ ሰምሯል ልመናቸው
ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ
እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆርዮስ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
ዑልያኖስ ተገድሏል ሐይማኖት ይስፋፋል
ብሎ መሰከረ መርቆሬዎስ ሃያል
ገፀ ከላባቱ ባህርይ ቀየሩ
እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ
መርቆሬዎስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ
በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ
መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዎስ ወደደ
ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ
በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ
ስሙ ተሰየመ ከሰማዕታት ጋ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር
መፍቅሬ አብ ካለ ያኘሎፓዴር
ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ
ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ
#አዝ---✞✞✞----___---✞✞✞--
🥰2👍1
🌾#ሰላም_ለከ🌾

ሰላም ለከ ኦ መርቆሬዎስ ዘሮሜ (፪)
ሰማዕት ተጋድሎ (፫) ኮንከ ፈፃሜ (፪)

#ትርጉም
የሮሜው ቅዱስ መርቆሬዎስ ሆይ ሰላም እልሃለሁ
የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈፃሚ ሆንክ
🥰2
🌾#መርቆሬዎስ🌾

መርቆሬዎስ ትሩፈ ምግባር/2/
ትሩፈ ምግባር /4/ መርቆሬዎስ ትሩፈ ምግባር
🥰2
🌾#ቅዱስ_መርቆሬዎስ🌾

ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማእታዊው የእኛ አባት (2)
ተዋህዶ ምሰሶ ሆንካት(2)
ከእናትህ ማህፀን ቸሩ አምላክ ሲያስብህ(2)
ለኢትዮጵያ ብርሃን አረግህ(2)
2👍2
🌾#የምእመናን_አባት🌾

የምእመናን አባት አገልጋይ የአምላክ ባለሟል መርቆሬዎስ/፪/
ተቀበለ ዛሬ/፬/ አክሊለ ሰማዕታት/፪/ ኧኸ
2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🌾🌻🙏#መድኃኔዓለም🙏🌻🌾

መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው

➥ለተጨማሪ...
youtube.com/EOTC2921
facebook.com/eotc2921
tiktok.com/@eotc2921
www.tg-me.com/EOTC2921
instagram.com/eotc2921
🥰2👍1
መድኃኔዓለም_አዳነን_በማይሻር_ቃሉ___Medhania.3gp
1.3 MB
#መድኃኔዓለም_አዳነን

መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/
ደስ ይበለን /2/ እልል በሉ /2/
አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/
🌾#ጸሎትና_ምክረ_አበው🌾

🌾‹‹ጸሎት የማያፈቅር ሰው ብታይ ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለህ፣ወደ እግዚአብሔር የማይጸልይ ከሆነ በመንፈሳዊነቱ ሞቷል….ህይወትም የለውም›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌾‹‹ጸሎት ችላ የሚል ሰው እንዲሁም ለንስሐ የሚያበቃ  ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሏል›› የሶሪያው ማር ይስሐቅ
🌾‹‹ጸሎት አእምሮን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ነው ›› የሶሪያው ማር ይስሐቅ
🌾‹‹ጸሎት ጸጋን ይጠብቃል፣ቁጣንም ያሸንፋል…ትዕቢትንም የመከላከል ዝንባሌ ያሳድርብናል›› የሶሪያው ማር ኤፍሬም
🌾‹‹የመንፈስ ፍሬዎችን ያለ ፀሎት ገንዘባችን ልናደርጋቸው አንችልም›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌾‹‹ጸሎት የማያረጅ ትዕግስትን ገንዘብ የምናደርግበት ታላቅ የጦር መሣሪያ ነው››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌾‹‹በጸሎት ግዜ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገርክ አይደለምን??እንዴት ያለ መብት ነው!!!›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌾‹‹ጸሎትን ለማድረግ አታቅማማ፣ሥጋ ከመብል(ከምግብ) በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች›› አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ
🌾‹‹ያለ ጸሎት የምናደርገው ወይም የምንናገረው ነገር መጨረሻው ውደቀት ነው፡፡ፍጻሜው ኃጢአት ወይም ጉዳት ነው፡፡በማናውቀው ምስጢራዊ በሆነ መልኩ ሲጎዳን እንመለከተዋለን›› አባ አጋቶን
🌾‹‹ሰው እራሱን ኃጢአተኛ እንደሆነ እያሰበ ወደ እግዚአብሔር ካልጸለየ ጸሎቱ ተቀባይነት አይኖረውም›› አባ አጋቶን
🙏9🥰64👍1👏1
🌿🌾#በዓታ_ለማርያም🌾🌿

እመቤታችን አባትና እናቷ ኢያቄምና ሐና በስዕለት (ለቤተ መቅደስ ሊሰጡ ብፅዓት ገብተው) ያገኟት ናት፡፡ በአባት በእናቷ ቤትም ፫ ዓመት ተቀመጠች፤ ከእንግዲህ ወዲያማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባኤ አድርጎ ቆያቸው።
ከዚያውም ደርሰው እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ ፯ እጅ አብርታ፥ ከመብረቅ ፯ እጅ አስፈርታ፥ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታየቻቸው፤ እነርሱም እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምን እንጋርድላታለን? ብለው ሲጨነቁ በዚህም መካከል እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኀብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች።
ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው፡፡ ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር ላንተ ነው የሚኾነውና ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፤ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ ሲጠጋ ወደ ሰማይ ራቀው፥ መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደ ሰማይ ራቃቸው፥መጠቃቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡
ሁለተኛም ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ነገር የሚያውቅ የለም፤ ሕፃኒቱን ከዚያው ትተሽ አንቺ ወዲህ ነዪ አላት፤ እሽ ብላ ሕፃኒቱን እዚያው ትታ ወደነሱ ሄደች፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወርዶ ፩ ክንፉን ጋርዶ ፩ ክንፉን አጎናፅፎ ኅብስቱን አብልቷት፥ ወይኑን አጠጥቷት፤ እመቤቴ ሆይ መንገድ ባስመታሁሽ ማሪኝ ብሎ የብርሃን መሶብ፥ የብርሃን ጽዋ ይዞ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
ሕዝቡም የምግቧማ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋራ ምን ያጋፋታል፤ ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን እንጂ ብለው ዙፋኑን ዘርግተው፥ ምንጣፏን አንጥፈው፥ መጋረጃውን ግራና ቀኝ ጋርደው ከቤተ መቅደስ አኖሯት፡፡
ይኸውም የተደረገው ታኅሣሥ ፫ ዕለት ነው፤ በኣታ የሚለው ስያሜም የተሰጠው በዚሁ ነው፡፡ ‹‹አመ ፫ ለታኅሣሥ በኣታ›› እንዳለ መቅድመ ተአምር፡፡ በዚህም፤
መቅደሲቱ ወደ መቅደስ ገባች፤
ቅድስቲቱ ወደ ቅድስት ገባች፤
ክብርቲቱ ወደ ክብርት ቤቷ ገባች፤
ልዩ የሆነችው ወደ ልዩ ሥፍራ ገባች፤
ቅድስተ ቅዱሳኗ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገባች፤
ንጽሕተ ንጹሐኗ ወደ ንጽሕ አዳራሽ ገባች፤
ቤተ መቅደሷ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች፡፡
ሊቃውንትም ‹‹መቅደስ ዘኢትትነሠት /የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ››/ እያሉ አመሠገኗት፡፡
እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች፤ ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላእክት ጋራ እየተጫወተች 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች፡፡
‹‹ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ፤ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ፲ተ ወ፪ተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ወስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ። ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ››። እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ
ምግቧ ከየት የተገኘ ነው ቢሉ በገበሬ እጅ ያልተዘራ በቤተ ሰብእ እጅ ያልተሠራ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ ያማረ የተመረጠ ነው እንጂ ፡፡ ‹‹ኦ ድንግል አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይኪ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እም ሰማየ ሰማያት ዘበሰለ፡፡ ኦ ድንግል አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይኪ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድ›› (ድንንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን እንጂ፡፡ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጥን ነው እንጂ፡፡) /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/።
✞ ስታድግም በንጽሕናና በቅድስና ነው፡፡ ‹‹ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና ኖርሽ እንጂ።›› /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/
✞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ብዙ የክፋት ምክር ይመክሩ ነበር። ከዚህም ውስጥ አንዱ መጥቁል ወደሚባል ጠንቋይ ሄደው ‹‹ፍታሕ ማዕከሌነ ኢያቄም ወሐና›› ብለው እመቤታችንን እንዲያጠፋ እጅ መንሻን ሰጡት፤ መጥቁልም በመካከል አይሁድ በኋላ ሁነው ነጋሪት እየጎሰሙ፥ እምቢልታ እየነፉ እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ለመግደል ለቤተ መቅደስ ፪ ምንዳፈ ሐፅ ሲቀራቸው፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ እዚያ ድረስ ያልተደረገና ያልተነገረ መብረቅ ነጎድጓድ ወርዶ አጋንንትንም፥ መጥቁልንም፥ አይሁድንም ቀጥቅጦ አጠፋቸው። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በማግሥቱ ወጥታ አይታ መጥቁል ሆይ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንህ ካንተ መከራ መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ከዚህ በኋላ በድኑ ለዝክረ ነገር የ፫ ቀን መንገድ እየሄደ ይሸት ጀመር።
✞እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊሮስ፣ ሰራሰቅሰሬል›› ብላ የአምላክ ኅቡዕ ስምን ብትደግም መሬት ተከፍቶ ዋጣቸው ከነሥጋቸውም ሲኦል ወረዱ፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እጅግ ታፈረች የሚናገራት ጠፋ ‹‹ኦ ግርምት ድንግል›› /እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም/።

🙏የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጣዕጧ፡ ፍቅሯ፡ በረከቷና ረድኤቷ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኒታችን ከፈጣሪያችንና ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለዘላለሙ ይኑር፡፡ አሜን🙏

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
👍1🙏1
2025/10/20 10:15:51
Back to Top
HTML Embed Code: