Telegram Web Link
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ

#መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡

በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

#አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦

ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

https://www.tg-me.com/dmtse_tewaedo
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
◦ሠሉስ(ማክሰኞ)

◦የሰሙነ ህማማት ሠሉስ(ማክሰኞ) "የጥያቄ ቀን" በመባል ይታወቃል ምክንያቱም ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ባደረገው አንጾሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበረ።

◦ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኃለው የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም?  ይለናል ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል እንደ መምህርም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸው ሁሉ በራሱ ስልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ

◦ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባን ነው በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል  ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምረን ነው።

እምበለ ደዌ ወሕማም፤
እምበለ ጻማ ወድካም አመ ከመ ዮመ ያብጸሐነ፤
ያብጸሐክሙ እግዚአብሔር በሰላም።

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት     
                             
❤️ስለ  ማይነገር ስጦታው   እግዚአብሔር ይመስገን ❤️


https://www.tg-me.com/dmtse_tewaedo
Forwarded from 📚👳‍♂ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት👳‍♂📚 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#የሰሙነ_ሕማማት_ረቡዕ

#ምክረ_አይሁድ_ይባላል
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቱዋ ማርያም) "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡

#የእንባ_ቀንም_ይባላል
ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8) ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

https://www.tg-me.com/orthoxy_ewet
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ጴጥሮስ አሸናፊ


ክህደተ ይሁዳ ወምክረ አይሁድ ፤ የመልካም መዓዛና የእንባ ዕለት
                        ሰሙነ ሕማማት ዘረቡዕ

❖ ምክረ አይሁድ

ወእምዝ ተጋብኡ ሊቃነ ካህናት ወሊቃናት ሕዝብ ውስተ ዐጸደ ሊቀ ካህናት ዘስሙ ቀያፋ።  ወተማከሩ ከመ ኢየሱስሃ በሕብል የአኀዝዎ ወይቅትልዎ። ወይቤሉ ባሕቱ አኮኬ በበዓል ከመ ሀከከ ኢይኩን ውስተ ሕዝብ።
በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው ሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥ ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ። የማቴዎስ ወንጌል 26:3-4

የአይሁድ ሊቃነ ካህናት እና ጸሐፍት ተሰብስበው ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን በመሆኑ ዕለቱ ምክረ አይሁድ ተብሏል፡፡
አይሁድ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡
"ወእምዝ ሖረ አሐዱ እምዐሠርቱ ወክልኤቱ አርዳኢሁ ዘስሙ ይሁዳ አሰቆሮታዊ ኀበ ሊቃነ ካህናት ወይቤሎሙ ሚመጠነ ትሁበኒ ወአነ ለክሙ አገብኦ። ወወሀብዎ ሠላሳ ብሩረ ። ወእምአሜሃ ይፈቅድ  ይርከብ ሣኅተ ከመ ያግብኦ ።"
በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸውበጌታ መያዝ ተስማምተዋል።
[ማቴ. ፳፮፥፩፡፲፬ ፣ ማር. ፲፬፥፩፡፪ ቁ ፲.፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፥ ፩፡፮]

❖ የመልካም መዓዛ ቀን

ወበጺሖ ኢየሱስ  ቢታንያ ቤተ ስምዖን ዘለምጽ መጽአት ኀቤሁ ብእሲት እንዘ ባቲ ብረሌ ዘምሉእ ዕፍረተ ውስቴቱ ዘብዙኅ ሤጡ ወሶጠት ዲበ ርእሱ ለኢየሱስ እንዘ ይረፍቅ ።
ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ (በለምጻሙ ሰምዖን) ቤት ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ዕለተ ረቡዕ የመዓዛ ቀን ተብሏል። ማቴ ፳፮፥፮-፯

❖ የእንባ ቀን

ይህም ይህቸው ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡
[ማቴ.፳፮፥፮፡፲፫ ፣ ማር.፲፬፥፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፥፩፡፰]
ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡
ማር ፲፬፥፱

እንበለ ደዌ ወሕማም ፤ እንበለ ጻማ ወድካም
   ዓመ ከመ ዮም ፤ ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ     
       እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ
           በፍስሓ ወበሰላም


https://www.tg-me.com/dmtse_tewaedo
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
የማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ኃላፊዎች ከመኖሪያ ቤታቸው በፀጥታ አካላት ታፍነው ተወሰዱ !

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን "ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ" ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸው ማህበረ ቅዱሳን ሚዲያ ገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት አልታወቀም።

https://www.tg-me.com/dmtse_tewaedo
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
ይህንን መንካት ያለባቸው ኦርቶዶክስ ብቻ ናቸው

የቱን መፅሀፍ ይፈልጋሉ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬📚 የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብይፈልጋሉ? የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካትመፅሐፉን ያግኙ። መልካም ንባብ 📖▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬📘📚 መፅሐፍ ቅዱስ 📘📚 የዋልድባ ገዳም ታሪክ📘📚 መጽሐፈ አክሲማሮስ 📘📚 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት   📘📚 መጽሐፈ አሚን ወሥርዓት📘📚 ሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን 📘📚 ሐይማኖተ አበው📘📚 ራዕየ ማርያም 📘📚 መልክዓ እግዚአብሔር 📘📚 ታቦተ ፅዮንን ፍለጋ📘📚 ፍካሬ ኢየሱስ ወትንቢተ ሳቤላ📘📚 መርበብተ ሰሎሞን 📘📚 የቶ መስቀል ትርጉም📘📚 ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ 📘📚 የ666 ሳይንሳዊ ምስጢር 📘📚 ህይወተ ቅዱሳን 📘📚 ውዳሴ ማርያም 📘📚 እመጓ📘📚 ዝጎራ 📘📚 መርበብት 📘📚 አንድሮሜዳ 1 & 2 📘📚የሳጥናኤል ጎል 1 - 4እና ሌሎችንም መፅሐፍት የሚያገኙበትመንፈሳዊ የቴሌግራም ቻናል ነው ።አሁኑኑ 𝐉𝐎𝐈𝐍 ብለው ይቀላቀሉን▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬       █    ✞   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒    ✞    █       █    ✞   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒    ✞    █       █    ✞   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒    ✞    █▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
2024/05/23 05:22:00
Back to Top
HTML Embed Code: