Telegram Web Link
👉በአለም ለቢዝነስ የሚጠቅሙንን 4 ዋና ዋና ቋንቋዎችን አብረን ቀስ በቀስ እንማማራለን። ከሁሉም በላይ ግዕዝ ብንማማር እወድ ነበር ነገር ግን ያገኘውት PDF በስርአት የተሰራ ስላልሆነ ለማንበብም አስቸጋሪ ነው ነገር ግን መጽሐፉን በElite መጽሃፍ ቻናላችን @EliteBooks እልክላችኋለሁ ለማንበብ ሞክሩ፤ ከሱ የተሻለ የግዕዝ መማርያ መጽሃፍ ያለው ሰው ካለ በውስጥ መስመር ላኩልኝ
@Comment_DidYouKnowbot

ከታች ያሉትን ተራ በተራ ቀስ እያልን አስፈላጊ ነገሮችን እንማራለን

1. Mandarin Chinese - The business language of the future

2. German - The European business language

3. Arabic - The gateway to the Middle East

4. Spanish - The language of the fastest growing American market segment

5. Russian - The language of diplomacy and trade

6. French - The former English

7. Japanese - The language of robotics

8. Korean - The language of trust and technology

@EliteLanguage
ቋንቋ 1 - ቻይንኛ

ቁጥሮች/ Numbers

0 = Líng (ሊንግ)
1 = Yī (ዪ)
2 = Èr (ኧር)
3 = Sān (ሰን)
4 = Sì (ስ)
5 = Wŭ (ዉኡ)
6 = Liù (ሊዮ)
7 = Qī (ቺ)
8 = Bā (ባ)
9 = Jiŭ (ጂዮኦ)
10 = Shí (ሽ)
11 = Shí Yī (ሽ ዪ)
12 = Shí Èr (ሽ ኧር)
.
.
20 = Èr Shí (ኧር ሽ)
21 = Èr Shí Yī (ኧር ሽ ዪ)
.
.
100 = Yī Băi (ዪ ባይ)

@EliteLanguage
ለእርስዎ ምን አይነት ቋንቋ በደንብ ማወቅ ይፈልጋሉ?
Anonymous Poll
39%
ግዕዝ
15%
ቻይንኛ
19%
አረብኛ
1%
ጃፓንኛ
18%
ስፓኒሽ
5%
ኮሪያኛ
3%
ሩስያን
👉የቻይንኛ ቀናት እና ወራትን ማታ ላይ ስለምንጀምር ቁጥሮቹን በደንብ መለማመዳችሁን ቀጥሉ፤ የራሳችሁን ጥያቄ እያወጣችሁ ራሳችሁን መፈተንና በቃላችሁ ቁጥሮቹን መለማመዳችሁን ቀጥሉ።
| Elite series Channels🇪🇹 |
ቋንቋ 1 - ቻይንኛ

ቀናት እና ወራት

👉በቻይና ቀን እና ወር አቆጣጠራቸው በጣም ቀላል ነው።
ቀናትን ሲቆጥሩ ቀን1 ፣ ቀን2 ... እያሉ ሲሆን ወራትን ደግሞ 1ወር ፣ 2ወር እያሉ ነው የሚቆጥሩት ቁጥሮችን ደግሞ ትላንት በዚህ @EliteLanguage ቻናላችን በደንብ ስለተማርን ቀናቱን ለመቁጠር ይቀለናል፤ ልዩነቱ ቀናት ላይ የእሁድ ሲለይ በወራት ደግሞ ከጥር መጀመራቸው ነው። እንደሚከተለው በግልጽ አስቀምጬላችኋለው።

፨ ቀን = XīngQí (ሲንግቺ) ፨

ሰኞ - ቀን1 = XīngQí Yī (ሲንግቺ ዪ)
ማክሰኞ - ቀን2= XīngQí Èr (ሲንግቺ ኧር)
.
.
.
.
እሁድ - XīngQí Tiān (ሲንግቺ ቲኣን)

፨ ወር = Yuè (ዩኧ)፨

ጥር - 1ወር = Yī Yuè (ዪ ዩኧ)
የካቲት - 2ወር = Èr Yuè (ኧር ዩኧ)
.
.
.
.
ነሀሴ - 8ወር = Bā Yuè (ባ ዩኧ)
መስከረም - 9ወር = Jiŭ Yuè (ጂዩኦ ዩኧ)
ጥቅምት - 10ወር = Shí Yuè (ሽ ዩኧ)
ህዳር - 11ወር = Shí Yī Yuè (ሽ ዪ ዩኧ)
ታህሳስ - 12ወር = Shí Èr Yuè (ሽ ኧር ዩኧ)
| Elite series Channels🇪🇹 |
👌እናንተን ላለማሰልቸት እና የጠራ አቀራረብ እንዲኖረው በማሰብ ተሳታፊ ለማብዛት የሚላኩትን ማስታወቂያዎችን አቁሚያለው። እኔ የማካፍለውን ደግሞ ብዙ ሰው ጋር ሲደርስ ይበልጥ እንድሰራ ስለሚገፋፋኝ ይሄንን በመረዳት ተሳታፊዎች እንዳይቀንሱ እናንተ በቻላችሁት መጠን ሼር በማድረግ በመተባበር አሪፍ ቻነል እናድርገው፤ አመሰግናለው።

Elite series Channels

Facts- @EliteFacts

Books- @EliteBooks

Language Learn- @EliteLanguage

Sport- @EliteSportss

👉Comment: @Comment_DidYouKnowbot
ቋንቋ 1 - ቻይንኛ🇨🇳

ሰአታት
ለእናንተ ቀለል እንዲል በሶስት ክፍሎች ከፍዬዋለው ቀስ እያላችሁ ተለማመዱት። በElite ቋንቋ መማርያ ቻነላችን @EliteLanguage እኔ እየተለማመድኩ ያለሁትን ቋንቋ አብረን ለመለማመድ እና ይሄን ጊዜ ለራሳችን ጥቅም እንድናውለው በማሰብ ስለሆነ ረጋ ብላችሁ ከዚ በፊት ጊዜ ያጠፋችሁትን በዚህ ጊዜ ለማካካስ ሞክሩ።

ክፍል 1
Miăo = ሰኮንድ (ሚያኦ)
Fēn Zhōng = ደቂቃ (ፈን ጆንግ)
Xiăo Shi = ሰአት (ሲያኦ ሽ)
Tiān = ቀናት (ቲየን)
Xīng Qí = ሳምንት (ሲንግ ቺ)
Yuè = ወር (ዩኧ)
Niān = አመት (ኒየን)

ክፍል 2
👉ቲየን (Tiān) ማለት ቀን እንደሆነ ከላይኛው አይተናል
Jīn Tiān = ዛሬ (ጂን ቲየን)
Zuō Tiān = ትላንት (ዞኦ ቲየን)
Míng Tiān = ነገ (ሚንግ ቲየን)
Guò Qù = ያለፈ (ጉኦ ቺዩ)
Xiàn Zài = አሁን (ሲየን ዛይ)
Jiān Glāí = ወደፊት (ጂ ግላይ)

ክፍል 3
Zăo Shang = ጥዋት (ዛዎ ሻንግ)
Zhōng Wŭ = ቀትር (ጀንግ ዉ)
Xià Wŭ = ከሰአት በኋላ (ሲያ ዉኡ)
Wăn Shàng = ምሽት (ዋን ሻንግ)
Yè Wăn = ለሊት (ዩየ ዋን)
Wŭ Yè = እኩለ ለሊት (ዉኡ የ)

በምትለማመዱበት ጊዜ ተመሳሳይ ነገሮቻቸውን በመለየት እና ከአማርኛ ጋር በማያያዝ መለማመዳችሁን ቀጥሉ።

🙏አመሰግናለው (Xià Xià)
👌መልካም እድል (Zhù nĭ hăo yùn)
| Elite series Channels🇪🇹 |
2025/07/01 07:05:11
Back to Top
HTML Embed Code: