Telegram Web Link
1⃣9⃣
👉እባብን በተለያየ ቦታ የሚጠቀሙት መጀመርያ ሰይጣን አዳምና ሄዋንን ያሳሳተው በእባብ ስለሆነ ነው። ኦሪት ዘፍጥረት 3:14 ላይ እባብ የሰይጣን መጠቀሚያ ስለሆነ ተረግሞ እናያለን። ከዛን ጊዜ ቡሃላም እባብ የሰይጣን መገለጫ ሆናለች፤ ብዙም ሳይቆይ ፍየልንም በጥጋብና ማን አለኝ ባይ ጸባይዋ በኮከብ ቆጠራቸው የሳጥናኤልን ትርጉም እንድትይዝ አድርገዋል በዛም ሲያመልኩ ቆይተዋል።

👉እባብ በግብጽ ጸሃይን ከቦ ይዞ፣ ዞሮ የራሱን ጭራ ሲበላ (አላለማዊ ህይወትን ለመግለጽ Oroborus)፣ በማይ፣ ሜክሲኮ፣ ሮም ለጣኦታቸው ስያሜ ሰተውታል።

በእምነታቸው በምስሉ ላይ እንደምናየው እባብ ከመረገሙ በፊት ክንፍ ነበረው ብለው ያምናሉ ስሙንም Can (ካን፣ እባብ) ይሉታል።

ለምሳሌ
-በማያ የእሳት አምላክ Vul ብለው ሲጠሩት በሮም ሁለት ቃላትን አንድ ላይ የማስተሳሰር ባህል ስላለ Can በመጨመር ጣኦቱን Vulcan ይሉታል አሁን ላይ Volcano የሚለው ስያሜም የተቀዳው ከዚህ ነው።
-በሮም Vatic ማለት ነብይ (Prophet) ማለት ሲሆን Can (እባብ) በመጨመር Vatican (መለኮታዊ እባብ) የሚለውን ይጠቀማሉ
-KulKul በማያ ቋንቋ ቆንጆ ወፍ ማለት ሲሆን Can (እባብ) በመጨመር ሉሲፈር መጋለቢያ የሚሉትን Kulkulcan ይሉታል፤ ተመሳሳይ አገላለጽ በሜክሲኮ Quetzalcoatl (ክንፍ ያለው እባብ) ይሉታል። ይሄ እንስሳ ማለትም የሉሲፈር መጋለቢያ የሚባለው ክንፍ ያለው እባብ አሁን ላይ Phoenix የሚለውን ስያሜ አለው።
2⃣0⃣
👉Phoenix ማለት በምስሉ ላይ እንዳስቀመጥኩላችኩ በተለያየ መልኩ ስትገለጽ የአፈ ታሪክ ወፍ ናት፤ ተቃጥላ ከአመዷ እንደገና የምትወለድ ወፍ ማለት ነው። በጥንት ግሪክና ሮም Fenex (Phenex) ስትባል ከላይ እንደገለጽኩት የሉሲፈር መጋለቢያ ፈረስን [The one who ferries Osiris(Lucifer)] ትወክላለች። በግሪክ አቆጣጠርም (Numerical) Fenex የሚለው ድምር 666 ይሰጠናል። እንደ ሉሲፈርም ብርሃን ሰጪ ብለው ያመልኳታል፤ ምክንያቱም የሉሲፈር መንፈስ በውስጧ ስላለ ነው።

የነገ ሰው ይበለንና ትምህርቱን ካቋረጥንበት ነገ እንቀጥላለን በሰላም ያሳድረን።

ያወቃችሁትን ሼር ማድረግን አትርሱ
ለአስተያየታችሁ @Comment_DidYouKnowbot
2⃣1⃣
👉Phoenix/Fenex የተባለውን የአፈታሪክ ወፍ ለመግለጽ በህይወት ያለን ወፍ እንደ ባህላቸው በማመላከት ጣኦትን ያመላካሉ፣ ይሰግዳሉ
-ግብጽ ... Heron (የውሃ ወፍ)
-ሰሜን አሜሪካ ... Eagle (ንስር አሞራ)
-መካከለኛና ደቡብ አሜሪካ ... Quetzal
-ባቢሎን፣ አሳይረን፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ጃፓን፣ ሮም፣ ግሪክ ... Peacock

ከሁሉም Peacoke የተባለችውን ወፍ በአምልኮት በስፋት ስለሚጠቀሙባት ስለሷ እንመልከት።

👉በባቢሎን፣ ግሪክ፣ ሮም፣ ህንድ ... ገነት በአይኖች የተሞላች ናት፤ አይኖች ኮከቦችን ይገልጻል። ኮከብ ደግሞ የነሱ አምላክ የሚሉአቸው እና የሞቱ ሰዎች መቀመጫ ብለው ያምናሉ። በPeacock ላባ ላይ ያለው የአይን ምልክት እነዛን ይወክሉባቸዋል።

👉Peacock/Fenex ከኮከብ ቆጠራ (Zodiac) ጋር በጥልቅ ትገናኛለች።

👉በህንዱይዝም ራማያና በተባለው የአምልኮ መጽሃፋቸው ጣኦት ኢንድራ (god Indra) የተባለው ራሱን ወደ እንስሳ ሲቀይር ወደ Peacock ነበር።

👉ትላንት በጠቀስኩት በግልጽ ሉሲፈርን (ዲያቢሎስን) የሚያመልኩት Yezidis የተባሉት ማህበረሰቦች 7 በPeacock ቅርጽ የተሰራ የድንጋይ ሃውልት አላቸው፤ ይሄም 7 ፈለክ (Planet) ይወክላል። Seitan ብለው ያመልኩታል ይሄም በአረብኛ Teitan/satan ማለት ነው፤ አማርኛ ሰይጣን።
2⃣2⃣
👉በህንድ ደልሂ የሚገኘው በ1620 የተገነባው የንጉስ መቀመጫ (Throne) የPeacock ቅርጽ ይዞ ተሰርቷል። ይሄም ንጉሱ በህዝቡ ላይ ሃይል እንዲሰጣቸው እና ገነት ላይ ያሉትን አምላክ የሚሏቸው ከነሱ ጋር እንዲሆኑና ህዝቡን እነዲገዙ የሰይጣን አምልኮት የንጉሳዊ መቀመጫ ነው።

👉በፈረንሳይ ቅዱስ ሜሪስ (St.Maurice) በተባለው በክርስትና ስም የታሙዝን መወለድን የሚያመልኩበት ቤተ መቅደስ ውስጥ ተስሎ ይገኛል።

👉በሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ መስታወቱ ላይ የPeacock ስእል ሲገኝ በሀውልት ደግሞ ሰሚራሚስ (የታሙዝ እናት) በአንድ እጇ መሬትን በሌላ እጇ የpeacock ምስል የያዘ በጀርባዋ 12 ኮከቦች ይሄም የZodiac (ኮከብ ቆጠራ) ጥንቁልና አምላካት የተባሉትን ለመግለጽ ነው።

👉በግሪክና ሮም መንግስቱ በህዝቡ ላይ ጠለቅ ያለ ሃይል እንዲኖረው ይሄንን የሰይጣን አምልኮት ምስላቸውን በሳንቲማቸው ላይ አሳትመውታል።
2025/07/08 23:13:09
Back to Top
HTML Embed Code: