Telegram Web Link
2
#ወዳጆቼ

#ፍቅር_ካለ_እግዚአብሔር_አለ እግዚአብሔር ካለ ደግሞ ሁሉ ነገር አለ ፤ ፍቅር ማለት ፍጹም ሰው ፈልጎ ማግኘትና መውደድ ሳይሆን ፣ ጎደሎውን ሰው ፍጹም አድርጎ መቀበል ነው። ሰማህ ወዳጄ እግዚአብሔር አምላክ ከኛ ለመሸሽ በቂ የሆነ ምክንያት እያለው ፣ የታገሰን ፣ በደላችን ደስ አሰኝቶት ሳይሆን ስለሚወደን ነው ። ማንም ሰው ፀሐይን ያለችበት ድረስ ሄዶ ለመንካት ቢሞክር መቅለጡ ግድ ነው ነገር ግን ያለንበት ድረስ መጥታ ታሞቀናለች ። #እግዚአብሔር አምላክንም ማንም በመለኮቱና በአምላክነቱ ሊያየውና በግርማውም ፊቱ ሊቆም አይችልም ። ነገር ግን ላይ መሄድ ለማንችለው ታች ድረስ ሊፈልገን መጥቶ በፍቅሩ ፀሐይ አሞቀን። መግደል የሚችለው ሞተ ኃይልም ፍቅርም ያለው አምላክ ከኃይል ይልቅ በፍቅር ተደሰተ ማንም የራሱን በደል ተሸክሞ ተጠያቂ መሆን በማይፈልግበት ዓለም ላይ ስለ የሁላችንን በደል ተሸክሞ ተጠያቂ ሆነልን      

#መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🙏
                           
የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
15🙏4
                         †                         

🕊  ይህች ዕለት የተቀደች ናት 🕊 ]

❝ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ ለውሉደ  ሰብእ  መድኀኒት ... ❞

🕊

❝ ይህች ዕለት የተቀደች ናት ። ለሰው ልጆችም  መድሃኒት ናት።በየጊዜውና በየሰአቱ መሪ ትሁነን። እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ።

ሁልጊዜ መሀሪ ሰውን ወዳጅ ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው ሰንበትን በእውነት አክብሩ። መዋደድን ገንዘብ አድርጉ። ሰንበትን አክብሩ ጽድቅንም ስሩ። ነቀዝ የማይበላውን የማያረጀውን የማይጠፋውን ሰማያዊ መዝገብ [ ሃብት ] አከማቹ። ❞

🕊

[   ቅዱስ ያሬድ    ]


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
1🙏1
🥰124
🕊                        💖                       🕊

      [         የደብተራ ልጅ ነኝ  !          ]

🕊                        💖                       🕊

ደብተራ ማለት ፦

፩ ኛ. [  ደብተራ ብርሃን ማለት ነው ]

እግዚአብሔር በብርሃን ድንኳን ሊቀ ነቢያት ሙሴን በአምሳለ ንጉሥ ተገልጾ በብርሃን ድንኳን በሰባት የእሳት መጋረጃ ፳፪ [22] ቱን ሥነ ፍጥረት በልቡናው ሥሎ ቃል በቃል ፭፻፸ [570] ጊዜ አነጋግሮታል። የደብተራ ልጅ ማለት የብርሃን ልጅ ማለት ነው። ወይም ሰማያዊ ወልደ ሰማያዊ ማለት ነው።


፪ ኛ. [   ደብተራ ኦሪት ናት   ]

ባስልኤል ፥ ኤልያብን ያህል ጠበብት ፣ ሙሴን ያህል ነቢይ ፣ አሮንን ያህል ካህን ፣ አስነሥቶ ያሳነጻት ናት። ታቦተ ሕጉ ያለባት ፣ አምልኮቱ የሚመሠከርባት ፣ ሕጉ የሚነገርባት ድንኳን ደብተራ ኦሪት ትባላለች። የደብተራ ልጅ ማለት የሕግ ልጅ የመቅደስ አገልጋይ ማለት ነው።ሕገ ኦሪትን ያወቀ እንደሙሴ እንደ አሮን  ያለ ማለት ነው።

፫ ኛ. [  ደብተራ ድንግል ማርያም ናት  ]

በአምሳላዊት ድንኳን በረድኤት ይገለጽ የነበረው እግዚአብሔር በንጽሕና በቅድስና በታነጸች በአማናዊት ደብተራ በእመቤታችን ማህጸን በኲነት ተገልጿልና ደብተራ ትባላለች።  የደብተራ ልጅ ማለትም የድንግል ማርያም የቃል ኪዳን ልጅ ማለት ነው። እንደ ጴጥሮስ እንደ ጳውሎስ መሆን ነዋ!

፬ኛ. ደብተራ መስቀል መድኅነ ዓለም ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል መሠዊያ ነውና ደብተራ ተብሏል ሕያው ደመ መለኮት የነጠበበት ቅዱስ መስቀል የከበረ ደብተራ ነው። የደብተራ ልጅ ማለትም የመስቀል ልጅ ማለት ነው። ወይም መስቀለኛ መስቀላዊ ማለት ነው።

፭ኛ. ደብተራ ርዕሱ ድንኳን ይባላል። በዘር በሩካቤ ያይደለ እንበለ ዘር እንበለ ሩካቤ የተወለደ የመድኅን አካሉ ደብተራ ተብሏል። ሠዋዒ፣ ተሠዋዒ፣ ተወካፌ መሥዋዕት፣ ነውና እንደ ብሉይ ሊቀ ካህናት ከአፍአ ወደ ውስጥ ደመ በግዕን ይዞ ለሥርኤት ወደ ደብተራ ኦሪት አልገባም። ራሱን በደብተራ ርዕሱ አቀረበ እንጂ። የደብተራ ልጅ ማለትም የክርስቶስ ልጅ ማለት ነው። በክርስቶስ የሚያምን የክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።

፮ ኛ. [  ደብተራ ቤተ ክርስቲያን   ]

ክርስቲያኖች የሚሰበሰቡባት መቅደሰ ወንጌል ደብተራ ተብላለች አገልጋዮቿም ካህናተ ደብተራ ይባላሉ። የደብተራ ልጅ ማለትም የመቅደስ አገልጋይ ቅዳሴውን የሚቀድስ፣ ቅኔውን የሚቀኝ፣ ድጓውን የሚያዜም፣ ዝማሜውን የሚዘም  ብራናውን የራመመ ቀለሙን የቀመመ ማለት ነው። የረቀቀ የተራቀቀ ምጡቅ መርጌታ ማለትኮ ነው !

ከደብተራ ሙያ አንዱን ሳያውቁ መንቀፍ ወፍ ነዳሽ፣ ጉም አፋሽ መሆን ነው። ለደብተራነት ማዕር መድረስ ጭንቅ ነው እንጂ ልጅ መሆንስ ቢሹትም አይገኝ።

ደብተራ እያሉ መተንኮስ በይፋ ክርስትናን እና ክርስቲያኖችን በመጥላት የሚደረግ ስሑት ድንቁርና ነው። ጠንቋይን ለተከበረው ደብተራ መስጠት አይቻልም ጨለማ ከብርሃን ጋር ኅብረት የለውምና። ሀገር በቀል የዕውቀት ሐሳቦችን የደብተራ ዕውቀት ነው አንቀበልም አንሰማም ማለት ግን ኦርጂናል የጣሊያን አእምሮ ነው።

ደብተራ ዶክተሮች ሳይኖሩ ዶክተር ነበር። በተውሶ ጭፍን ግልበጣ የተሠራ አእምሮ እውነትን ካልጠላት የተማረ አይመስለውም ማለት ነው? ከውሸተኛ ተንኮለኛ ቁም ነገር አገኛለሁ ከማለት ዑቅያኖስ ሜዳ ሁኖ እህል ይዘራበታል ማለት ይቀላል። ወይም ሰሜን ተራራ ደልዳላ ሜዳ ይሆናል ማለት ይሻላል።

© ተጻፈ ከደብተራ ልጅ ገብረ መድኅን እንየው


[ ደብተራ በሚለው ስም ሰይጣናዊ የሆነ ሥራን የሚሠሩ ግለሰቦች የቤተክርስትያንና የምዕመናን ጠላቶች እንጂ ቤተክርስቲያንን መወከል የሚችሉ አይደሉም። ]



🕊                        💖                       🕊
4🔥1
                        †                          

እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

🕊  †  መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ  †  🕊

🕊                        💖                     🕊

" በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። "

[ ሉቃ.፩፥፲፬ ]


† የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ :-

- በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ
- በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
- በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
- እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
- የጌታችንን መንገድ የጠረገ
- ጌታውን ያጠመቀና
- ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን :-

ነቢይ :
ሐዋርያ :
ሰማዕት :
ጻድቅ :
ገዳማዊ :
መጥምቀ መለኮት :
ጸያሔ ፍኖት :
ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች::


"ሰባኬ ወንጌል በጥዑም ልሣኑ ፣
ርስነ መለኰት ገሠሠት የማኑ ፣
ጸጉረ ገመል ተከድነ ዘባኑ ፣
ለዮሐንስ ሂሩቶ ንዜኑ ንዜኑ" ድጓ ዘዮሐንስ።

ትርጉም ፦

{ በጣፋጭ አንደበቱ ወንጌልን የሚሰብክ ፣
ቀኙ የሚያቃጥል መለኮትን የዳሰሰች ፣
ጀርባው በግመል ጸጉር የተሸፈነ ፣
የዮሐንስን ደግነት ፈጽመን እንናገራለን }


" እውነት እላችኋለሁ ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፡፡" [ ማቴ.፲፩፥፲፩ ]


እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ስለወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።


🕊                        💖                     🕊
2🙏2
🙏5
🕊                    💖                   🕊

[  ግፉዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ  !  ]

                        🕊                       

❝ ሰላም ለዮሐንስ ግፉዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ  ወስቡሕ ላእከ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ ❞

[ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ ፤ መንገድ ጠራጊ ፤ ካህን ድንግል ሰማዕት ፣ ነቢይና አገልጋይ ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ]

[ አቤቱ ስላጠመቀኽ ስለ ዮሐንስ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ ከታናሽነቴ ዠምሮ እስከ ዛሬ አንተን የበደልኹኽን ኅጢአቴን ስለ ርሱ ብለኽ እኔን አገልጋይኽን አንጻኝ አሜን። ]

[ ተአምኆ ቅዱሳን ]

🕊

❝ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። ❞

[ ሉቃ.፩፥፲፬ ]


[ 🕊 እንኳን አደረሳችሁ 🕊 ]


🕊                        💖                       🕊
🙏31
1
2025/07/08 22:01:54
Back to Top
HTML Embed Code: