Telegram Web Link
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ሰኔ ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

🕊  † ቅዱስ አቡናፍር ገዳማዊ  †  🕊

ጻድቁ ተወልዶ ያደገው በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ነው:: ወቅቱ ሥርዓተ መነኮሳት የሚጠበቅበት:አበው ባሕታውያን እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝተው የደመቁበት ነበር:: ታላቁ አቡናፍርም ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: በሥርዓት አድጎ: መጻሕፍትንም ተምሮ ገና በወጣትነቱ መንኗል::

ሥርዓተ መነኮሳትን ከአባ ኤስድሮስ ታላቁ አጥንቶ ገዳሙንና መምሕሩን እየረዳ ለብዙ ዓመታት በጾምና በጸሎት ኑሯል:: መነኮሳቱ ስለ ትሕትናውና ስለ ታዛዥነቱ ፈጽመው ያከብሩት ነበር::

ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋውያን መነኮሳት ጭው ባለ በርሃ ስለሚኖሩ ባሕታውያን ሲጨዋወቱ: ሲያደንቁዋቸውም ሰማ:: እርሱ በዛ ወቅት ባሕታውያን በበርሃ መኖራቸውን አያውቅም ነበርና ሒዶ መምሕሩን አባ ኤስድሮስን ጠየቃቸው:: እርሳቸውም "አዎ ልጄ! ከዚሕ በጣም ርቅው: ንጽሕናቸውን ጠብቀው: ከሰውና ከኃጢአት ተይለው የሚኖሩ ገዳማውያን አሉ" አሉት::

ቅዱስ አቡናፍር "በዚሕ ካሉት መነኮሳትና በበርሃ ካሉት ማን ይበልጣል?" ቢላቸው "እነርሱ በጣም ይበልጣሉ:: ዓለም እንኩዋ ከነ ክብሯ የእግራቸውን ሰኮና አታህልም" አሉት:: ይሕንን የሰማው ቅዱስ አባ አቡናፍር ጊዜ አላጠፋም::

ከመምሕሩ ቡራኬ ተቀብሎ ወደ በርሃ ሔደ:: ለብዙ ቀናት ከተጉዋዘ በኋላ አንድ ባሕታዊ አግኝቶ አብሯቸው ተቀመጠ:: ከእርሳቸው ዘንድም ሥርዓተ ባሕታውያንን ተምሮ እንደገና ወደ ዋናው በርሃ ጉዞውን ቀጠለ::

ከብዙ ቀናት መንገድ በኋላም አንድ ሠፊ ሜዳ ላይ ደረሰ:: አካባቢው የውሃ ጠብታ የማይገኝበት: ይቅርና መጠለያ ዛፍ የሣር ዘር እንኩዋ የሌለበት ወይም በልሳነ አበው "ዋዕየ ፀሐይ የጸናበት: ልምላሜ ሣዕር የሌለበት: ነቅዐ ማይ የማይገኝበት" ቦታ ነበር:: በዚህ ቦታ ይቅርና የሰው ልጅ አራዊትም አይኖሩበትም::

ለአባ አቡናፍር ግን ተመራጭ ቦታ ነበር:: ቅዱሳኑን ይሕ አያሳስባቸውም:: ምክንያቱም ለእነርሱ ምግባቸውም: ልብሳቸውም ፍቅረ ክርስቶስ ነውና:: አባ አቡናፍር ወደ ፈጣሪ ጸለዩ:: በእግዚአብሔር ቸርነት ከጎናቸው አንዲት ዘንባባ [በቀልት] በቀለች:: ከእግራቸው ሥርም ጽሩይ ማይ [ንጹሕ ምንጭ] ፈለቀች::

ጻድቁ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: ዓመታት አለፉ:: ልብሳቸውን ፀሐይና ብርድ ጨርሶት ቅጠል ለበሱ:: በዚያ ቦታም የሰው ዘርን ሳያዩ ለ፷ [60] ዓመታት በተጋድሎ ኖሩ:: የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስ እግዚአብሔር አባ በፍኑትዮስን [የባሕታውያንን ዜና የጻፈ አባት ነው] ላከላቸው::

ቃለ እግዚአብሔርን እየተጨዋወቱ ሳለ የአባ አቡናፍር አካሉ ተለወጠ:: እንደ እሳትም ነደደ:: አባ በፍኑትዮስም ደነገጠ:: ታላቁ ገዳማዊ ግን እጆቻቸውን ዘርግተው ጸለዩ: ሰገዱና አማተቡ:: ነፍሳቸውም ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ቅዱሳን መላዕክትም በዝማሬና በማኅሌት አሳረጉዋት:: የሚገርመው ደግሞ አባ በፍኑትዮስ ይሕን ሲያይ ቆይቶ ዘወር ቢል ዛፏ ወድቃለች: ቅርንጯም ደርቃለች::

ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱሳን አበው ባሕታውያን መታሠቢያ ናት::

ከሰው [ ከዓለም ] ርቀው: ንጽሕ ጠብቀው: ዕጸበ ገዳሙን: ግርማ አራዊቱን: ጸብዐ አጋንንትን ታግሠው የኖሩ: ስማቸውን የምናውቀውንም ሆነ የማናውቃቸውን እንድናከብራቸው ቤተ-ክርስቲያን ሥርዓትና በዓል ሠርታለች::

አምላካችን ከአበው ባሕታውያን ጸጋ በረከት ይክፈለን::

🕊

[ † ሰኔ ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ አቡናፍር ገዳማዊ [ስም አጠራሩ የከበረ:
ሽምግልናው ያማረ አባት]
፪. አበው ቅዱሳን ባሕታውያን [ ዛሬ የሁሉም ቅዱሳን ባሕታውያን [በተለይም የስውራኑ] ዓመታዊ በዓል ነው::

- ከሰው: ከዓለምና ከኃጢአት ርቀው
- ንጽሕ ጠብቀው
- ዕጸበ ገዳሙን
- ድምጸ አራዊቱን
- ግርማ ሌሊቱን
- የሌሊቱን ቁር
- የመዓልቱን ሐሩር
- ረሐቡን: ጽሙን: መራቆቱን . . . ሁሉ
ስለ ፍቅረ-ክርስቶስ ሲሉ ታግሠውታልና::

"ዛሬም በየበርሃው የወደቁ: ስለ ዓለም ምሕረትን
የሚማጸኑ አሉ::"

አምላካቸው በረከታቸውን ያድለን።

፫. የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ከግብጽ እንዲመለስ የነገረበት [ተዝካረ ሚጠታ ለእግዝእትነ ማርያም]
፬. አፄ ይኩኖ አምላክ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩፡ ኪዳነ ምሕረት ማርያም
፪፡ ቅድስት ኤልሳቤጥ
፫፡ አባ ዳንኤል ገዳማዊ
፬፡ ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሠ ሮሜ
፭፡ አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
፮፡ ቅዱስ ሐርቤ ንጉሠ ኢትዮጵያ

" . . . ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ: ከዚሕም በላይ በእሥራትና በወኅኒ ተፈተኑ . . . ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: ዕብ.፲፩፥፴፮] (11:36) "

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2
5
#ኪዳነምህረት_እናቴ 16 🙏🙏

#የብርሃን_እናቱ_ሆይ ካንቺ በነሳው ስጋ እኛነታችንን አከበረ፡ መዐዛሽ ስቦት አንችን በወደደ ጊዜ ድህነታችን ተሰራ #ድንግል_ሆይ እውነተኛው የህይወት እንጀራ : ጣፋጩን የነፍስ መጠጥ አማናዊው የፅድቅ ብርሀን የፈነጠቀብሽ ነሽና ከትውልድ መሀል #ብፅዕናሽን እንናገራለን ጥማችንን የቆረጠ ጥዑም ወይን ረሀባችንን ያጠፋ እውነተኛው መብል ካንቺ ወጥቶልናልና #እንወድሻለን ምስራቃዊት በራችን ሆይ ከሴቶች አንችን የሚመስል የለም፡ ባንቺ ላይ ስለተደረገልን ታላቅ ነገር ዛሬም ለዘላለምም ስምሽን እናገናለን፡፡

#ዝምተኛይቱ_ድንግል_ሆይ አንቺ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የአይሁድ ሴቶች አይደለሽም በትሕትና ተልመሽ በንፅሕና አጊጠሽ የባህርያችንን መመኪያ ያስገኘሽልን የፅድቅ በራችን ነሽ።

#አንችን_ማመስገን የነፍስ ምግብ የህሊና እርካታ ነው #ስናመሰግንሽ እናርፋለን ስናርፍ #እናመሰግንሻለን። ክብርሽ ከሰማይ ምስጋናሽም ከአርያም ነውና አንችን ለማመስገን ልቦናችን ይብራ አሜን🙏

           #_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
10🙏2
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[   በቦታው ሁሉ ምሉ ነውና !  ]

🕊                    💖                       🕊


❝ ነፍሱን በሲኦል አልተወም ፥ ሥጋውም ሙስና መቃብርን አላየም። መለኮት ከሁለቱ [ ከነፍስ ከሥጋ ] አልተለየም ፤ ሁለንተናው ከነፍስ ጋር በሲኦል ነበረ። በሲኦልም ለጻድቃን የምሥራችን አበሠረ። ሁለንተናውም ከሥጋ ጋር በመቃብር ነበረ እንጂ። በቦታው ሁሉ ምሉ ነውና መለኮት በሕማም ድል አይነሣም ለሕማም አይገኝም። [ መዝ.፲፮ [፲፭]፥፲ ፤ ፹፰ [፹፯]፥፫-፮ ። ግብ ሐዋ.፪፥፳፯ ። ፩ጴጥ.፫፥፲፱ ና ፳ ]

ሌሎችም ባለማወቃቸው ቃል ሰው ስለመሆኑ ሲናገሩ 'ነፍስን ሥጋን አልነሣም እግዚአብሔር ቃል እንደ ዕሩቅ ብእሲ መርጦ አደረበት እንጂ' ይላሉ። ዳግመኛም ቃል በባሕርዩ እንደ ታመመ እንደ ሞተ  አብም እንደ አስነሣው ይናገራሉ ፥ ይህንን የሚናገሩ ሦስቱ ሞቱ እንዲያሰኝባቸው አያውቁም።

እግዚአብሔር ቃል በባሕርዩ ከሞተስ እነሆ አብም ዳግመኛ ሞተ እርሱ ራሱ [ ወልድ ] እኔ በአብ ህልው ነኝ አብም በእኔ ህልው ነው እኛ አንድ ነን ብሏልና።

ዳግመኛ እኔን ያየ አባቴን አየ ብሏልና ፤ ይህም እኔ የነገርኳችሁ ቃል እኔ ከራሴ አንቅቼ የነገርኳችሁ አይደለም ፤ በእኔ ህልውና ያለ አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል እንጂ ብሏልና።

እኛ ግን ፦

ከእኛ ባሕርይ በነሣው ሥጋ እንደ ታመመ እንደ ሞተ እናምናለን
። እርሱ እግዚአብሔር ቃልም የተዋሐደውን ሥጋ ከሙታን ለይቶ እንዳስነሣው ፤ ያስነሣውም ሌላ እንዳይደለ እናምናለን ፤ ቅዱሳን አባቶቻችን ያስተማሩትን ትምህርት ትተው ክርስቶስ ፈጽሞ እንዳልታመመ እንዳልሞተ እንዳልተነሣ የሚናገሩ አሉ ፤ ይህንንም በመናገራቸው መለኮት ያጻፋቸውን መጻሕፍት ሁሉ ይለውጣሉ ፤ ሐሰትም ያደርጓቸዋል። [ ፪ጴጥ.፪፥፫-፲፮ ]

ለእኛ ግን ፦

እግዚአብሔር ያጻፋቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርታችን ናቸው። መንፈስ ቅዱስም ክርስቶስ የማይታመም ፍጹም አምላክ ፤ የሚታመም ፍጹም ሰው ያለመለየትም አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው ብሎ በሐዋርያት አድሮ ተናገረ ፤ በሊቃውንት አድሮ አስተማረ ፤ ካልታመመ ካልሞተ ፤ ካልተነሣ ሌሎችን እንደምን ያስነሣል ?
[ ፩ቆሮ.፲፪፥፫ ፤ ፩ጴጥ.፩፥፲፩ ]

አልሞተም አልተነሣም የሚሉ ግን መለኮት ያጻፋቸው መጻሕፍትን ሐሰተኞች ያደርጓቸዋል ፤ ባለማወቃቸውም አምላክ የለም ፤ ትንሣኤም ቢሆን ፤ መንግሥተ ሰማያትም ቢሆን ወቀሳም ቢሆን ፍርድም ሲሆን የለም ይላሉ እርሱ ግን እንደ ከሀሊነቱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል። ❞

[    🕊   ቅዱስ ቄርሎስ   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                     🕊                      💖
4
1
                         †                         


እግዚአብሔር ያጽናናሽ ቅድስት ቤተክርስቲያን !

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም ፥ ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደስ መካከል እስከ ጠፋው እስከ [ ካህኑ ] ዘካርያስ ደም ድረስ ፥ ከዚህ ትውልድ እንዲፈለግ አዎን እላችኋለሁ ፥ ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል። ❞

[ ሉቃ.፲፩፥፶ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
😢7
😢13
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷  " ሦስቱ የቅዱሳን ማዕረጋት ! "

[   " በሶርያ ቅዱሳን አባቶች ... ! "   ]

[                        🕊                        ]
-----------------------------------------------

-▷ የእግዚአብሔር ፍቅር ብልጭታ
-▷ ነፍስን መቀደስ
-▷ ተመሥጦና ፍጹም ደስታ


❝ እንግዲህ ፥ ወዳጆች ሆይ ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን ፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ። ❞ [ ፪ቆሮ . ፯ ፥ ፩ ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇
4
ሰው ከእግዚአብሔር ሲለይ ፦ 
ዓይኑ ያልተፈቀደውን ሁሉ ያያል።
ምላሱ ሰውን አራጅና አዋራጅ ትሆናለች።
ጀሮው የሰውን ኃጢአትና ገመና ሰሚ ይሆናል።
እጆቹ የሰውን ንብረትና አካል ዘራፊ ይሆናሉ።
እግሮቹ ነፍስንና ስጋን ወደሚያበላሹ ቦታዎች ይሮጣሉ።
ስጋው የዝሙት ፈረስ ይሆናል።
ልቡ የፍርሀትና የጭንከት ከበሮ ይመታል።
አእምሮው የአጋንንትና የሰይጣናት መስሪያ ቤት  ይሆናሉ።

          
#_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
🙏75😢1
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

[ 🕊 ✞ አባ ገሪማ [ ይስሐቅ ] መደራ ✞ 🕊 ]

አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ፡፡

እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ፯ [7] ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ: መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል::

አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው አባ ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር::

ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው::

እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ [ገሪማ] ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር::

አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ፰ መቶ ሜትር [800 ሜትር] ተጠራርጎ ሸሸ::

ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ  [ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ] አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ፡፡

አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል::

ጻድቁ ወንጌልን: ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል :-

፩. ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር "በጽባሕ
ይዘርዕ: ወበሠርክ የአርር" እንዲል::
፪. ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::
፫. አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ::
፬. ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች::
፭. አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን
አቁመዋታል::

ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ: መታሰቢያህን ያደረገ: እስከ ፲፪ [12] ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ ሕያዋን አድርሰዋቸዋል፡፡

[ 🕊 ✞ አባ ለትጹን የዋህ ✞ 🕊 ]

ስመ ጥሩ ጻድቅ አባ ለትጹን በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ የተወለዱ:

- በፍጹም ተግሣጽ ያደጉ:
- ከልጅነታቸው ጀምሮ ራሳቸውን በሕገ ወንጌል የመሩ:
- አንድ ቀን በሰሟት የወንጌል ቃል የመነኑ:
- ገዳም ገብተው በትሕትና ለዘመናት ያገለገሉ:
- በመጨረሻም ወደ ትልቅ ተራራ ወጥተው ተጋድሏቸውን
የፈጸሙ ታላቅ አባት ናቸው::

ከየዋሕነታቸው የተነሳ ኃጢአተኛ ሰው ሲያገኙ ራሳቸው ንስሃ ይገቡ ነበር:: አንዴ ግን እናቱን ፲ [10] ጊዜ በዝሙት ያረከሰ: ስትጸንስም መርዝ አጠጥቶ ጽንሱን በማሕጸኗ የገደለና በሥጋ ወደሙ ላይ የተዘባበተ ሰው ሊሞት ሲል ደረሱ::

አጋንንት ሲዖል ታች ሲጥሉትም ተመለከቱ:: ኃጢአቱ ጭንቅ ቢሆንም የእርሱን ንስሃ ሊቀበሉ ጀመሩ: ከንስሃቸው ጽናት የተነሳ ሞቱ:: ጌታችን ከሞት አስነስቶ "አትለምነኝ: አልምረውም" አላቸው::

ጻድቁ ተስፋ አልቆረጡምና ቀጠሉ:: ለ፪ [2] ኛ ጊዜ ሞቱ:: አሁንም ቀጠሉ: ፫ [3] ኛ: ፬ [4] ኛ: ፭ [5] ኛ ጊዜም ሞቱ:: በ፮ [6] ኛው ግን መፍትሔ መጣ:: ጌታችን አእላፍ መላእክትን አስከትሎ: ያችንም ኃጥእ ነፍስ ይዞ መጣ:: "ፍርዴ አይታጠፍምና ወደ ገነት አላስገባትም:: ስለ አንተ ጽድቅና የዋሕነት ደግሞ ሲዖል አልጥላትም:: ስለዚሕም እንዳልተፈጠረች ትሁን" ብሎ እፍ አለባት:: ፈጥና ወደ ትቢያነት ተቀየረች::

ጻድቁም የፈጣሪያቸውን ቸርነት አድንቀው ሰገዱ:: ከብዙ ዘመናት ተጋድሎ በኋላም በዚህች ቀን ዐረፉ::

[ 🕊 ✞ አባ ዸላሞን ፈላሲ ✞ 🕊 ]

ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ታላላቅ ገዳማውያን አንዱ አባ ዸላሞን የአባ ለትጹን ወዳጅ ነበር:: ይሕ ቅዱስ ከአጋንንት ጋር በገጠመው ጦርነት ምክንያት ለየት ይላል:: ከ፷ [60] ዓመታት በላይ እንኳን ሳቅና ደስታ ቀና ብሎም ሰው አላየም::

በነዚሁ ዘመናት ሁሉ ቅንድቡ እስኪላጥ አልቅሷል:: በዓለም ያሉ አጋንንት ሁሉ ተሰብስበው አሰቃይተውታል:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ቸርነት: በወዳጁ በአባ ለትጹን ጸሎትና በትጋት አሸንፏቸው ዛሬ ዐርፏል::

ቸሩ አምላካችን ከታላላቁ ቅዱሳን ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::

🕊

[ †  ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ብጹዕ አባ ገሪማ [ይስሐቅ] ዘመደራ
፪. አባ ለትጹን ዐቢይ ወየዋሕ
፫. አባ ዸላሞን ፈላሲ
፬. ቅድስት አርሴማ ጻድቅት
፭. ሰማዕታት እለ አኮራን
፮. ፯፼ ፹፻ ሰማዕታት ማኅበረ ቅዱስ ተክለሃ ይማኖት

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩ ፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት
፪ ፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ
፫ ፡ ቅዱሳን መክሲሞስ ወደማቴዎስ
፬ ፡ ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ

" እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: " [መዝ. ፴፮፥፳፰-፴፩] (36:28-31)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
5
4
                         †                         

የእሥር ዜናዎች !

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

በናዳ ማርያም ገዳም ለበርካታ ዓመታት ጉባኤ ዘርግተው በማስተማር ላይ የሚገኙት ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ የኔታ ይባቤ መታሰራቸው ተገለጸ !

ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም [ተሚማ/ አዲስ አበባ]

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሰሜን ሜጫ ወረዳ ቤተ ክህነት ድል በትግል ቀበሌ የምትገኘው የፈለገ ብርሃን ናዳ ቅድስት ማርያም እና ክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም አበምኔት የሆኑት ታላቁ ሊቅ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ በትናንትናው ዕለት  መታሠራቸውን ለማወቅ ችለናል።

የመረጃ ምንጬቻችን ጨምረው እንደገለፁልን ለጊዜው ምክንያቱን በግልጽ ለማወቅ ባይቻልም ለጥያቄ ይፈለጋሉ ተብለው መወሰዳቸውን ገልጸውልናል።

ከ1979 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ወንበር ዘርግተው ጉባኤ ተክለው ለ38 ዓመታት ቅኔና የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜን ያስተማሩት እኚህ አባት አሁንም በማስተማር  በርካታ ደቀመዛሙርትን ያስመረቁ የክብረ ደናግል ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም መሥራችና አበምኔት /አስተዳዳሪ ናቸው።

ጉዳዩን ተከታትለን ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርስ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

[ ዘገባው የተ.ሚ.ማ ነው ]

እንዲሁም ሊቀ ትጉኃን ደረጀ ነጋሽ [ ዘወይንዬ ] ለጥያቄ ተፈልገዋል በሚል መወሰዳቸው ተገልጿል።

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
2025/07/10 15:27:09
Back to Top
HTML Embed Code: