Telegram Web Link
1
                         †                       

[      ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ !      ]

🕊

❝ ካይንሽ የፈሰሰው የዕንባ ጎርፍ : በፊትሽም የተንጠባጠበው በልጅሽ በወዳጅሽ ፊት ይቁም፡፡ የሠራሁትን  ኃጢአት ባስበው ልቡናዬ እጅግ ደነገጠብኝ ፥ አዕምሮ ሳለኝ አለል ዘለል እያልኩ በጽርዓት መኖሬን ባሰብሁት ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ:: የኃጢአቴን ብዛት በተቆጣጠርሁ ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ አንድ ሰዓት እንኩዋን ሃጢዓት ለመስራት አላቁዋረጥሁም፡፡

በሰውና በመላእክት ጉባኤ መሐከል ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ፡፡ በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስሁ ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ፡፡ ከዚህ እጅግ የሚያስፈራው ከሠራሁት ኃጢአት ፡ ፍዳ የተነሳ የሚዋሰኝ ባገኝ ብዬ::

ነገር ግን በማማለድ እኔን ለማዳን የምትችይውን አንቺን አማላጅ አገኘሁ:: ዘወትርም ከእኔ እንዳትርቂ አወቅሁ:: እንዲህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቼም አይደለም በሃይማኖት ያዝሁሽ በመዳሰስ አይደለም በዕደ ሕሊና ያዝሁሽ በዕደ ሥጋ አይደለም::

እኔ እለምናለሁ አንቺ ጸሎቴን ታሳርጊያለሽ ልጅሽም ኃጢአቴን ያስተሠርያል፡፡ የልቤን ግዳጅ ይሰጠኛል፡፡ እኔ ቁስለኛ ነኝ ፥ አንቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡ ❞

[  ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
2
2
                          †                          

[    🕊  ቤተ ክርስቲያን እናቴ 🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ ፣ ዘትጼንዊ መጽርየ ፣ ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ ፣ ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ ፤ ❞

[ እንደ ቀጋ የምትሸቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል ፤ ከእናቴ ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኁ ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኚ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል"

[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ]

🕊

❝ እንተ ተሐንጸት በስሙ ፣ ወተቀደሰት በደሙ ፣ ወተዐትበት በዕፀ መስቀሉ ጌሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ ፣ ❞

[ በስሙ ታነጸች በደሙም ከበረች በዕፀ መስቀሉም ተባረከች ወደ ርሷ [ ቤተ ክርስቲያን ] ኺዱ። የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ ነውና ]

[ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ]


[ 🕊 እንኳን አደረሳችሁ 🕊 ]


🕊                         💖                     🕊
2
2
#የወላዲተ_አምላክ_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የድንግልና ሕይወት ፤ እንደ ማንኛውም ሰው ድንግልና አይደለም። ይህን የመሰለ ድንግልና፣ ንፅሕናና ቅድስና ከእርስዋ በስተቀር በሌላ በማንም አልታየም። ሌሎች ከነቢብ ከገቢር ድንግል ቢባሉ(ቢሆኑ) ፥ ከሐልዮ ወይም ከማሰብ ድንግል አይደሉምና። በወንጌል "ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል" ተብሎ እንደ ተፃፈ። እርሷ ለነበረውም ለመጪውም ትውልድ የክብር አክሊል ናት። የዘወትር ድንግል(ወትረ ድንግል) የሆነች እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም፥ ምድራዊ ዘመኗን ሁሉ ፥ ቅድስናዋን ምንም ሳይልውጠው እንዴት መኖር ቻለች? አካላዊ ቃል በማህፀኗ ባደረ ጊዜ፣ ፈጣሪዋን ስትወልድ፣ በክንዷ ስታቅፈውና በዓይኖቿ ስታየውስ፥ ምን ተሰማት? ይህ ጥያቄ በሰው ልጅ ጥበብ የሚመልስ ወይም ሊገለጥ የሚቻል አይደልም።

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
8
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት  "    ]
             
             [     ክፍል አስር     ]

❝ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። ❞ [ ፪ጴጥ.፩፥፳ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                         👇
5
2
🕊

[ † እንኳን ለቅዱሱ አባታችን የዋህ ዻውሊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  †  ቅዱስ ዻውሎስ የዋህ  †  🕊

† በ፬ [ 4 ] ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ግብፅ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ቅዱሱ ስሙ ዻውሎስ ቢሆንም ብዙ ጊዜ የሚጠራው "የዋህ ዻውሊ" በሚል ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

የዋህ ዻውሊ ከሕጻንነቱ ጀምሮ መጻሕፍትን የተማረ: ግን ደግሞ ትዕቢት: ቁጣና ቂምን የማያውቅ ገራገር ሰው ነው:: እድሜው ለአካለ መጠን ሲደርስ ቤተሰቦቹ ሚስት አግባ አሉት:: እርሱ ባያስብበትም ወገኖቹን ላለማሳዘን አገባ:: እንዳለመታደል ሆኖ ግን ያገባት ሴት በጣም ቆንጆ በዚያም ላይ ክፉ ነበረች:: የዋህ ዻውሊ ክፋቷን ሁሉ ታግሶ ለበርካታ ዓመታት አብሮ ኖረ:: ልጆችንም አፈሩ::

አሁንም ግን እርሷ ከክፋቷ ልትታገስ አልቻለችም:: ይባስ ብሎ ዻውሊ በሌለበት ከሌሎች ወንዶች ጋር ትዘሙት ያዘች:: የዋሁ ሰው ይሕንኑ ያውቃል ግን የእግዚአብሔርን ሥራ ዝም ብሎ በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ለነገሩስ እሱ ያርሳል: ይቆፍራል: ነዳያንን ያበላል: እንግዳ ይቀበላል እንጂ ክፋትን ለማሰብ ጊዜ አልነበረውም::

አንድ ቀን ግን ለሥራ ወደ በርሃ ወጥቶ አንድ ግሩም ዜና ሰማ:: "አባ እንጦንስ ምንኩስና የሚባል ሕይወተ መላእክትን ጀምሯል: ደቀ መዛሙርትንም ይቀበላል" አሉት:: ግን ሚስትና ልጆች አሉትና ምን ያደርጋል?

የዋህ ዻውሊ ሙሉ ቀን ሢሠራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ግን የጠበቀው ሌላ ነው:: ሚስቱ በራሱ መኝታ ላይ ከአገልጋይ እረኛው ጋር ራቁታቸውን አገኛቸው:: ልብ በሉልኝ በትክሻው ሞፈርና ምሳር: መጥረቢያም ይዟል:: እርሱ ግን ክፉን አላሰበም:: ጥሩ ልብስ አንስቶ ሁለቱንም አለበሳቸው:: እንዲሕም አላቸው:- "ከዚሕ በሁዋላ እኔ አልመለስም:: ሀብት ንብረቴን ውረሱ: በደስታም ኑሩ:: የልጆቼን ነገር ግን አደራ" ብሏቸው ተነሳ::

በእጁ ምንም አልያዘም:: በትከሻው ያለችውን ብጣሽ ጨርቅ ይዞ ወደ በርሀ ተጉዋዘ:: አባ እንጦንስም ተቀብለው አስተምረው አመነኮሱት:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ራስን ዝቅ በማድረግ: በመታዘዝ አገለገለ:: ጾም: ጸሎትና ስግደቱንማ ማን ቆጥሮት::

እያለ እያለ ከብቅዐት ማዕርግ ደረሰ:: ምዕመናንም ሆነ መነኮሳት ሊጠይቁት ሲመጡ የእያንዳንዱ ኃጢአት በግንባራቸው ተጽፎ ይመለከት ነበርና ስለነሱ ሲያለቅስ ቅንድቡ ተላጠ:: ሰውነቱም አለቀ:: አንድ ቀን ጋኔን የያዘውን ሰው ፈውስ ብለው አመጡለት:: እርሱ ግን በአጋንንት ላይ ሥልጣን እያለው በትሕትና ተጠግቶ ጋኔኑን "አባ እንጦንስን ከምጠራብህ ቀስ ብለህ ውጣ" አለው:: ጋኔኑ ግን የፈራው መስሎት በትዕቢት "እንጦንስ ማነው?" አለው::

ያን ጊዜ የዋህ ዻውሊ እንደ እሳት ከጋለ ድንጋይ ላይ ቁሞ "ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው:: ይሕ ጋኔን ካልወጣ አልወርድም" አለ:: ወዲያው በዘንዶ አምሳል ከሴትዮዋ ወጥቶ እየጮኸ ወደ ቀይ ባሕር ገባ:: ቅዱስ ዻውሊ የዋሕም እንዲሕ በቅድስና ተመላልሶ በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::

" የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር: ደስታ: ሰላም: ትእግስት: ቸርነት: በጐነት: እምነት: የውሃት: ራስን መግዛት ነው:: እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም:: የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ::" [ገላ.፭፥፳፪] (5:22)

🕊

[ † ሰኔ ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አባ ዻውሊ የዋሕ
፪. ቅዱሳን ወክቡራን ቆዝሞስና ድምያኖስ [ ሰማዕታት ]
፫. ቅድስት ቴዎዳዳ ሰማዕት [ እናታቸው ]
፬. አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስ [ ሰማዕታት ]

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
፫. ቅዱስ ደቅስዮስ [ የእመቤታችን ወዳጅ ]
፬. አባ እንጦንዮስ [ አበ መነኮሳት ]

[ † አምላካችን ከቅዱስ ዻውሊ የውሃትን: ትእግስትን : በጐነትን : ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: አሜን:: † ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
👏2
3
፤ አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘላለም አልፈር።
፤ በጽድቅህ አስጥለኝ ታደገኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድነኝም።
፤ በጠንካራ ቦታ ታድነኝ ዘንድ አምላክና መሸሸጊያ ሁነኝ፤ ኃይሌ መጠጊያዬ አንተ ነህና።
፤ አምላኬ፥ ከኃጢአተኛ እጅ፥ ከዓመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ።
፤ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።
፤ ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው።
፤ ለብዙዎች መደነቂያ ሆንሁ፤ አንተ ግን ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
፤ አፌን ምስጋና ምላ ሁልጊዜ ክብርህንና ግርማህን እዘምር ዘንድ።
፤ በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፥ ጕልበቴም ባለቀ ጊዜ አትተወኝ።
፤ ጠላቶቹ በላዬ ተናግረዋልና፤ ነፍሴንም የሚሹአት በአንድነት ተማክረዋልና፥ እንዲህም አሉ።
፤ እግዚአብሔር ትቶታል፤ የሚያድነው የለምና ተከትላችሁ ያዙት።
፤ አምላክ ሆይ፥ ከእኔ አትራቅ፤ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 71 ቁ1-12

 
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
10🙏4
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት  "    ]
             
         [    ክፍል አስራ አንድ     ]

❝ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። ❞ [ ፪ጴጥ.፩፥፳ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                         👇
2
2
2025/07/11 18:53:59
Back to Top
HTML Embed Code: