፤ አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘላለም አልፈር።
፤ በጽድቅህ አስጥለኝ ታደገኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድነኝም።
፤ በጠንካራ ቦታ ታድነኝ ዘንድ አምላክና መሸሸጊያ ሁነኝ፤ ኃይሌ መጠጊያዬ አንተ ነህና።
፤ አምላኬ፥ ከኃጢአተኛ እጅ፥ ከዓመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ።
፤ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።
፤ ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው።
፤ ለብዙዎች መደነቂያ ሆንሁ፤ አንተ ግን ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
፤ አፌን ምስጋና ምላ ሁልጊዜ ክብርህንና ግርማህን እዘምር ዘንድ።
፤ በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፥ ጕልበቴም ባለቀ ጊዜ አትተወኝ።
፤ ጠላቶቹ በላዬ ተናግረዋልና፤ ነፍሴንም የሚሹአት በአንድነት ተማክረዋልና፥ እንዲህም አሉ።
፤ እግዚአብሔር ትቶታል፤ የሚያድነው የለምና ተከትላችሁ ያዙት።
፤ አምላክ ሆይ፥ ከእኔ አትራቅ፤ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 71 ቁ1-12
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

❤10🙏4
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " ቅ ዱ ሳ ት መ ጻ ሕ ፍ ት " ]
[ ክፍል አስራ አንድ ]
❝ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። ❞ [ ፪ጴጥ.፩፥፳ ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇

❤2
🕊
✞ የሰኔ ፳፫ [ 23 ] ✞
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
❖ ሰኔ ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
🕊 † ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል † 🕊
መፍቀሬ ጥበብ :
¤ ጠቢበ ጠቢባን:
¤ ንጉሠ እሥራኤል:
¤ ነቢየ ጽድቅ:
¤ መስተሣልም [ ሰላማዊ ] . . . እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ሰሎሞን የታላቁ ነቢይና ንጉሥ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትና የቅድስት ቤርሳቤህ [ቤትስባ] ልጅ ነው:: ከ ፫ [3] ሺ ዓመታት በፊት የተወለደው ቅዱስ ሰሎሞን እስከ ፲፪ [12] ዓመቱ ድረስ በቤተ መንግሥት ከአባቱ ጋር አድጉዋል::
ቅዱስ ዳዊት ፸ [70] ዘመን በሞላው ጊዜ የአካሉን መድከም አይቶ አዶንያስ በጉልበት እነግሣለሁ ቢልም አልተሳካለትም:: እግዚአብሔር ሰሎሞንን መርጧልና ገና በ፲፪ [12] ዓመቱ ነገሠ:: ልበ አምላክ አባቱ ዳዊት ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት መከረው::
"ልጄ ሆይ ! ልብህን ስጠኝ:: ፈጣሪህንም አምልክ" አለው::
ቅዱስ ሰሎሞን እንደ ነገሠ በገባዖን ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረበ:: ጌታም ተገልጾ "ምን ትፈልጋለህ?" አለው:: ሰሎሞንም ልክ እንደ አባቱ ማስተዋልን: ልቡናን ለመነ:: በዚህም ጌታ ደስ ስለተሰኘ "አልቦ እምቅድሜከ: ወአልቦ እምድኅሬከ - ከአንተም በፊት: ከአንተም በኋላ እንዳንተ ያለ ጠቢብና ባለጠጋ ሰው የለም: አይኖርም" ብሎት ተሠወረ:: ቅዱስ ሰሎሞን ለ፵ [40] ዓመታት በእሥራኤል ላይ ነገሠ::
ግሩም በሆነ ፍትሑ: በልዩ ጥበቡ ዓለም ተገዛለት:: እግዚአብሔር የመረጣት የእኛዋ ንግስተ ሳባ /አዜብ/ማክዳም ትፈትነው ዘንድ ሒዳ ምኒልክን [እብነ መለክን] ጸነሰች:: በኋላም ታቦተ ጽዮንና ሥርዓተ ኦሪት መጣልን:: ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን ድንግል ማርያም ከእነሱ ዘር እንደምትወለድ ነግሮት ነበርና ያበጀሁ መስሎት ሴቶችን አብዝቶ ነበር::
ነገር ግን :-
¤ አንደኛ ሰው [ሥጋ ለባሽ] ነውና:
¤ ሁለተኛ ደግሞ ከብዙ ሴቶች መካከል ከአንዷ እመ ብርሃን ትገኛለች መስሎት ነበር:: ነገሩ መንገድ ስቶበት ከአሕዛብ
[ከፈርዖን ልጅ] ጋር በመወዳጀቱ ለጣዖት አሰገደችው:: እግዚአብሔር እጅግ አዘነ::
በራዕይ ተገልጦ "ስለ ወዳጄ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ላይ ክፉን አላደርግም" አለው:: ታላቁ ነቢይ ሰሎሞን ይህንን ሲሰማ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ማቅ ለብሶ: አመድ ነስንሶ በፍጹም ልቡ አለቀሰ:: ንስሃ ገባ:: መፍቀሬ ንስሃ ጌታችንም ንስሃውን ተቀበለው::
የይቅርታው መገለጫም ተወዳዳሪ የሌላቸውን ፭ [5] መጻሕፍት ገለጠለት:: ተናገራቸው:: ጻፋቸው:: እሊሕም :-
፩. መጽሐፈ ጥበብ
፪. መጽሐፈ ተግሣጽ
፫. መጽሐፈ መክብብ
፬. መጽሐፈ ምሳሌ
፭. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ናቸው::
ቅዱስ ሰሎሞን ልዩ የሆነውን ቤተ መቅደስ በመስራቱም ይደነቃል:: ደጉ ንጉሥ: ጠቢብና ነቢይ ሰሎሞን በዚህች ዕለት በ፶፪ [52] ዓመቱ ዐርፎ ወደ ፈጣሪው ሔዷል::
🕊 † አባ ኖብ † 🕊
ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ሰማዕት አባ ኖብ አርፏል:: በዚሕ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን ቢኖሩም ዋናው ይኼው ቅዱስ ነው::
አባ ኖብ እንደ ገዳማውያን በበርሃ የተጋደለ: እንደ ሊቃውንት መጻሕፍትን ያመሰጠረ: በተለይ ደግሞ በዘመነ ሰማዕታት ጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን የተቀበለ አባት ነው:: ስለ ገድሉ ብዛት "ኃያል ሰማዕት": አንገቱን ስላልተቆረጠም "ሰማዕት ዘእንበለ ደም" ይባላል:: ዘመነ ሰማዕታትን ካለፉ ፸፪ [72] ቱ ከዋክብትም አንዱ ነው::
ከመፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን: ከኃያሉ ሰማዕት አባ ኖብ በረከትን አምላካችን ይክፈለን::
🕊
[ † ሰኔ ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን [ንጉሠ እሥራኤል]
፪. ቅዱስ አባ ኖብ [ሰማዕት ወጻድቅ]
፫. ቅዱሳን መርቆሬዎስ: ፊልዾስና ቶማስ [ሰማዕታት]
[ † ወርኃዊ በዓላት ]
፩ ፡ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
፪ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፫ ፡ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፬ ፡ አባ ሳሙኤል
፭ ፡ አባ ስምዖን
፮ ፡ አባ ገብርኤል
፯ ፡ ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
" የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ:: ሰባኪው :- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል::" [መክ.፲፪፥፩-፱] (12:1-9)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

#እኔ__ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ #እሰግዳለሁ።
፤ አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ፤ መንገዴን በፊትህ አቅና።
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፤ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
፤ አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፤ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና።
፤ በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ #ለዘላለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለህ፤ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ #ይመካሉ።
፤ አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 5፣7-11
#___ሰናይ____ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
፤ አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ፤ መንገዴን በፊትህ አቅና።
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፤ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
፤ አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፤ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና።
፤ በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ #ለዘላለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለህ፤ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ #ይመካሉ።
፤ አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 5፣7-11
#___ሰናይ____ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
❤13🙏1
🕊 † 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ በእኛም ባሕርይ ተገለጠ ! ]
🕊 💖 🕊
❝ ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ከአብ ባሕርይ የተገኘ አንድ ወልድ ቃል እንደሆነ ተናገሩ ፤ ከባሕርይ አምላክ [ ከዘለዓለም ] የተገኘ የባሕርይ አምላክ ፤ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ፤ ሁሉ የተፈጠረበት እርሱ ነፍስን ሥጋን ነሥቶ ሰው ሆነ።
ከድንግልም በሥጋ ይወለድ ዘንድ ወደደ። በእኛም ባሕርይ ተገለጠ ፤ ሰው የሆነበት ባሕርይ ይህ ነው። አብ አንድ ነው ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድ ነው ፤ ይኸውም ከአብ የተገኘ አንድ ቃል ነው ፤ ሰው ሆነ። ገንዘቡ ከሚሆን ከልዑል ጌትነቱም አልተለየም ሰውም ቢሆን በአምላክነቱ ጸንቶ ይኖራል። ገዢ እርሱ በተገዢ ባሕርይ ተገለጠ ፤ ንዴት በሚስማማው በእኛ ባሕርይ ሳለ ፍጹም መለኮት ገንዘቡ ነው።
በድካመ ሥጋ ተገልጦ ሳለ የኀያላን መላእክት ጌታ ነው ፤ በሰው መጠን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ሳለ ከፍጥረት ሁሉ በላይ ነው ፤ ከኃጢአት ብቻ በቀር በሰውነቱ የሰውነት ሥራ ሁሉ ገንዘቡ ነው። አንድ የእግዚአብሔር ልጅ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ፤ ሕይወት ፣ ኀይል የሚሆን እርሱ እግዚአብሔር ባሕርዩ ያልነበረ ሥጋን ተዋሐደ ፤ ሰው ስለሆነም በሥጋ ተገለጠ ፤ በማይመረመር ረቂቅ ተዋሕዶ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ ሥጋን ስለተዋሐደ የሰውነትን ሥራ ሁሉ ገንዘብ አደረገ ፤ ሥጋም ገንዘቡ ነው የሌላ አይደለም። ❞
[ 🕊 ቅዱስ ቄርሎስ 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
[ ክፍል አርባ ሁለት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ ገዳም ምድራዊ ገነት ነው፡፡ ስለዚህ ልባችንን ጌታን እንደሚያገለግሉ መላእክት ይመስል ዘንድ እናዘጋጀው፡፡ አንዳንዴ በዚህ ገነት ውስጥ የሚኖሩ የድንጋይ ልቦች አሏቸው፡፡ ዳግመኛም አንዳንዴ በጸጸት አማካኝነት መጽናናትን አግኝተው እንዲህ ባለው መንገድ ትዕቢትን አሊያም አጉል ድፍረትን በማስወገድ ፣ ድካማቸውንም በእንባዎቻቸው
ያቀላሉ፡፡
ጥቂት እሳት ብዙውን ስም ያለዝበዋል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ጥቂት ትሕትና [ ተዋርዶ ] ዘወትር ቍጠኝነትን ፣ ቸልተኝነትን ፣ የልባችንንም ድንዳኔ ሁሉ ድንገት አለዝቦ ፣ አጣፍጦ ፣ በማስወገድ ይደመስሰዋል፡፡
አንድ ጊዜ ሁለት ሰዎች በድብቅ ተቀምጠው [ ቁጭ ብለው ] የመናንያንን ጻማዎች ሲመለከቱና ልቅሶአቸውን ሲሰሙ ተመለከትሁ፡፡ ሆኖም ግን አንደኛው ይህን ያደርግ የነበረው እነርሱን ለመምሰል ሲሆን ፣ ሌላኛው ግን ዕድሉን ሲያገኝ በግልጽ ለማፌዝና ስለ እግዚአብሔር ብሎ የሚደክመውን ሰው ከመልካም ሥራው ይገታው ዘንድ ነበር፡፡
ሌሎችን የሚያስቆጡትንና የሚያስመርሩትን ያለ አግባብ ዝም አትበላቸው፡፡ እንድትፋጠንም ስትታዘዝ በሁኔታህና በድርጊትህ አትዘግይ፡፡ አሊያ ግን ከክፉዎችና ከአመፀኞች የባስክ ትሆናለህ፡፡ ብዙውን ጊዜ ኢዮብ እንደ ተናገረው ያሉ ነገሮችን እመለከታለሁ ፣ ያም ነፍስ በሀኬት ጠባይና አንዳንዴም በበዛ ብልሃት መታወኳ ነው፡፡ [ ኢዮ.፲፫፥፩ ] እኔም ከክፋት ዓይነቶች ብዛት የተነሣ ተገረምሁ፡፡
የድምፆቹ ማደናገር ዘማሪውን ውሉ ለማይታወቅ ድምፅ የሚዳርገው ነውና ከሌሎች ጋር እንጂ ለብቻው ያልሆነ ሰው ከጸሎት እንደሚያገኘው ጥቅም ያለ ከሌሊት ዝማሬ [ ከዝማሬ ] አያገኝም፡፡ ❞
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡
† እንኳን አደረሳችሁ †
[ † ሰኔ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † ]
🕊 † ቅዱስ ሙሴ ጸሊም [ ጥቁሩ ሙሴ ] † 🕊
ግብጻውያን ስማቸውን ጠርተው ከማይጠግቧቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ ኢትዮዽያዊው አባ ሙሴ ጸሊም ነው:: በእኛ ኢትዮዽያውያን ግን ይቅርና በወርኀዊ በዓሉ [በ፳፬ [24] ] በዓመታዊ በዓሉ እንኩዋ ሲከበር ብዙም አይታይም::
ቅዱሱ ሰው በትውልዱ ኢትዮዽያዊ ሲሆን ያደገውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ እንደሆነ ይታመናል:: ገና በወጣትነቱ አገር የሚያሸብር ሽፍታ ነበር:: ሙሴ ጸሊም ወደ ግብጽ የሔደበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም መምለክያነ ጣዖት [ፀሐይን ከሚያመልኩ ሰዎች] ጋር ይኖር ስለ ነበር ምናልባት እነርሱ ወስደውት ሊሆን ይችላል::
ቅዱስ ሙሴ በምድረ ግብጽም በኃይለኝነቱ ምክንያት የሚደፍረው አልነበረም:: ፀሐይን ያመልካል: እንደ ፈለገ ቀምቶ ይበላል: ያሻውን ሰው ይደበድባል:: ነገር ግን በኅሊናው ስለ እውነተኛው አምላክ ይመራመር ነበርና አንድ ቀን ፀሐይን "አምላክ ከሆንሽ አናግሪኝ?" አላት:: እርሷ ፍጡር ናትና ዝም አለችው::
ቅዱስ ሙሴ ምንም አስቸጋሪ ሰው ቢሆንም ፈጣሪን መፈለጉን ግን ቀጥሏልና አንድ ቀን ተሳካለት:: መልካም ክርስቲያኖችን አግኝቶ . . . ወደ ገዳመ አስቄጥስ ቢሔድ በዛ ያሉ መነኮሳት ወደ እውነት እንደሚመሩት ነገሩት:: እርሱም ሰይፉን እንደታጠቀ ወደ ገዳም ገባ:: መነኮሳቱ ፈርተውት ሲሸሹ ታላቁ አባ ኤስድሮስ ግን ተቀብለው አሳረፉት::
"ምን ፈለግህ ልጄ?" አሉት:: "እውነተኛውን አምላክ ፊት ለፊት ማየት እፈልጋለሁ" የሙሴ ጸሊም መልስ ነበር:: አባ ኤስድሮስም "የማዝህን ሁሉ ካደረግህ ታየዋለህ" ብለው ወደ መነኮሳት አለቃ ቅዱስ መቃርስ ታላቁ ወሰዱት:: መቃሬም ክርስትናን አስተምረው አጠመቁትና ለአባ ኤስድሮስ መለሱላቸው::
ከዚህ ሰዓት በሁዋላ ነበር የአባ ሙሴ ጸሊም ሕይወት ፍጹም የተለወጠው:: በጻድቁ እጅ ምንኩስናን ተቀብሎ ይጋደል ጀመር:: በጠባቧ በር ይገባ ዘንድ ወዷልና ያ በሽፍትነት የሞላ አካሉን በገድል አረገፈው:: ከቁመቱ በቀር ከአካሉ አልተረፈለትም:: ወገቡን በአጭር ታጥቆ መነኮሳትን አገለገለ:: አጋንንት በቀደመ ሕይወቱ በሕልም: አንዳንዴም በአካል እየመጡ ይፈትኑት ነበር::
እንዳልቻሉት ሲረዱ ተሰብስበው መጥተው በእሳት አለንጋ ገርፈው አቆሳስለውት ሔዱ:: እርሱ ግን ታገሰ:: በበርሃ ለሚኖሩ አበው መነኮሳት ሁሉ ብርሃን በሆነ ሕይወቱ ሞገስ ሆነላቸው:: ለኃጥአን ደግሞ መጽናኛ ሆነ::
"በተራራ ላይ ያለች ሃገር ልትሠወር አይቻላትምና ስም አጠራሩ በመላው ዓለም ተሰማ:: ሁሉም "ሙሴ ጸሊም ይል ጀመር ፡፡"
በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን ራሱን "አንተ ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ: ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር:: ከቆይታ በኋላም በመነኮሳት ላይ እረኛ [አበ ምኔት] ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ:: የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ አጣፍጦ: ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ::
ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ፫፻፸፭ [375] ዓ/ም በርበረሮች [አሕዛብ] ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ፯ [7] ደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚሕች ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል::
ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው ያድለን::
🕊
[ † ሰኔ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም [ ኢትዮዽያዊ ]
፪. "፯ቱ [ 7ቱ ] " ቅዱሳን መነኮሳት [ ደቀ መዛሙርቱ ]
፫. አባ ኤስድሮስ ታላቁ
[ † ወርኃዊ በዓላት ]
፩ ፡ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
፪ ፡ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፫ ፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
፬ ፡ ቅዱስ አጋቢጦስ
፭ ፡ ቅዱስ አብላርዮስ
፮ ፡ አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን
፯ ፡ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ
" መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ "የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ" ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል::" [ሉቃ.፲፭፥፫-፯] (15:3-7)

❤3