Telegram Web Link
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷  "  ከእንባ የሚገኝ በረከት  " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[                       🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ አምላክ ሆይ ፥ ሕይወቴን ነገርሁህ ፤ እንባዬን እንደ ትእዛዝህ በፊተህ አኖርህ።

በጠራሁህ ጊዜ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፤ አንተ አምላኬ እንደ ሆንህ እነሆ ፥ አወቅሁ። በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ ፤ በእግዚአብሔር ቃሉን አከብራለሁ። ❞

[  መዝ . ፶፮ ፥ ፰ - ፲  ]



🕊                       💖                   🕊
🙏2👏1
🥰4
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

†   እንኳን አደረሳችሁ   †

[ †  ሰኔ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † ]


🕊 † ቅዱስ ሙሴ ጸሊም [ ጥቁሩ ሙሴ ] † 🕊

ግብጻውያን ስማቸውን ጠርተው ከማይጠግቧቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ ኢትዮዽያዊው አባ ሙሴ ጸሊም ነው:: በእኛ ኢትዮዽያውያን ግን ይቅርና በወርኀዊ በዓሉ [በ፳፬ [24] ] በዓመታዊ በዓሉ እንኩዋ ሲከበር ብዙም አይታይም::

ቅዱሱ ሰው በትውልዱ ኢትዮዽያዊ ሲሆን ያደገውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ እንደሆነ ይታመናል:: ገና በወጣትነቱ አገር የሚያሸብር ሽፍታ ነበር:: ሙሴ ጸሊም ወደ ግብጽ የሔደበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም መምለክያነ ጣዖት [ፀሐይን ከሚያመልኩ ሰዎች] ጋር ይኖር ስለ ነበር ምናልባት እነርሱ ወስደውት ሊሆን ይችላል::

ቅዱስ ሙሴ በምድረ ግብጽም በኃይለኝነቱ ምክንያት የሚደፍረው አልነበረም:: ፀሐይን ያመልካል: እንደ ፈለገ ቀምቶ ይበላል: ያሻውን ሰው ይደበድባል:: ነገር ግን በኅሊናው ስለ እውነተኛው አምላክ ይመራመር ነበርና አንድ ቀን ፀሐይን "አምላክ ከሆንሽ አናግሪኝ?" አላት:: እርሷ ፍጡር ናትና ዝም አለችው::

ቅዱስ ሙሴ ምንም አስቸጋሪ ሰው ቢሆንም ፈጣሪን መፈለጉን ግን ቀጥሏልና አንድ ቀን ተሳካለት:: መልካም ክርስቲያኖችን አግኝቶ . . . ወደ ገዳመ አስቄጥስ ቢሔድ በዛ ያሉ መነኮሳት ወደ እውነት እንደሚመሩት ነገሩት:: እርሱም ሰይፉን እንደታጠቀ ወደ ገዳም ገባ:: መነኮሳቱ ፈርተውት ሲሸሹ ታላቁ አባ ኤስድሮስ ግን ተቀብለው አሳረፉት::

"ምን ፈለግህ ልጄ?" አሉት:: "እውነተኛውን አምላክ ፊት ለፊት ማየት እፈልጋለሁ" የሙሴ ጸሊም መልስ ነበር:: አባ ኤስድሮስም "የማዝህን ሁሉ ካደረግህ ታየዋለህ" ብለው ወደ መነኮሳት አለቃ ቅዱስ መቃርስ ታላቁ ወሰዱት:: መቃሬም ክርስትናን አስተምረው አጠመቁትና ለአባ ኤስድሮስ መለሱላቸው::

ከዚህ ሰዓት በሁዋላ ነበር የአባ ሙሴ ጸሊም ሕይወት ፍጹም የተለወጠው:: በጻድቁ እጅ ምንኩስናን ተቀብሎ ይጋደል ጀመር:: በጠባቧ በር ይገባ ዘንድ ወዷልና ያ በሽፍትነት የሞላ አካሉን በገድል አረገፈው:: ከቁመቱ በቀር ከአካሉ አልተረፈለትም:: ወገቡን በአጭር ታጥቆ መነኮሳትን አገለገለ:: አጋንንት በቀደመ ሕይወቱ በሕልም: አንዳንዴም በአካል እየመጡ ይፈትኑት ነበር::

እንዳልቻሉት ሲረዱ ተሰብስበው መጥተው በእሳት አለንጋ ገርፈው አቆሳስለውት ሔዱ:: እርሱ ግን ታገሰ:: በበርሃ ለሚኖሩ አበው መነኮሳት ሁሉ ብርሃን በሆነ ሕይወቱ ሞገስ ሆነላቸው:: ለኃጥአን ደግሞ መጽናኛ ሆነ::

"በተራራ ላይ ያለች ሃገር ልትሠወር አይቻላትምና ስም አጠራሩ በመላው ዓለም ተሰማ:: ሁሉም "ሙሴ ጸሊም ይል ጀመር ፡፡"

በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን ራሱን "አንተ ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ: ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር:: ከቆይታ በኋላም በመነኮሳት ላይ እረኛ [አበ ምኔት] ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ:: የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ አጣፍጦ: ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ::

ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ፫፻፸፭ [375] ዓ/ም በርበረሮች [አሕዛብ] ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ፯ [7] ደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚሕች ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል::

ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው ያድለን::

🕊

[ †  ሰኔ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም [ ኢትዮዽያዊ ]
፪. "፯ቱ [ 7ቱ ] " ቅዱሳን መነኮሳት [ ደቀ መዛሙርቱ ]
፫. አባ ኤስድሮስ ታላቁ

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩ ፡ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
፪ ፡ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፫ ፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
፬ ፡ ቅዱስ አጋቢጦስ
፭ ፡ ቅዱስ አብላርዮስ
፮ ፡ አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን
፯ ፡ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ

" መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ "የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ" ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል::" [ሉቃ.፲፭፥፫-፯] (15:3-7)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3
#አባታችን__ተክለሃይማኖት

እልፍ አእላፍ ቢኖሩ ቃላት
ሥራው ብዙ ነው
#የተክለሃይማኖት
የምድር ስፋት ቢሆንም ሰሌዳ
ሁሌም አዲስ ነህ ሁሌም እንግዳ
ተክልዬ ተክልዬ ስንልህ
#ኢትዮጵያን
አስባት ዛሬም አትተዋት

#_ሰናይ_ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
12
🕯🕯🕯💖🕯🕯🕯

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ [ ጥቁሩ ሙሴ ]

ከሽፍትነት ህይወት ተጠርቶ በቅድስናና በንጽህና ህይወት ያሸበረቀ ገዳማዊ !

🕊

በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን ራሱን "አንተ ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ ፥ ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር::

ከቆይታ በኋላም በመነኮሳት ላይ እረኛ [አበ ምኔት] ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ:: የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ አጣፍጦ: ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ::

ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ፫፻፸፭ ዓ.ም [375 ዓ/ም] በርበረሮች [አሕዛብ] ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ፯ [7] ደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚሕች ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል::

ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው ያድለን::

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
1
4
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷   "  ብ ን ኖ ር ም ብ ን ሞ ት ም " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[                       🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና ፥ ለራሱም የሚሞት የለም ፤ በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና ፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።

ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና። ❞

[  ሮሜ . ፲፬ ፥ ፯  ]



🕊                       💖                   🕊
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🕊                      💖                      🕊


🕊  ተ ዋ ሕ ዶ   ሰ ማ ያ ዊ ት  🕊  ]


❝ የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ❞ [ ሮሜ.፲፬፥፲፯ ]


💖 O R T H O D O X Y  💖    ]


†                        †                         †
💖                     🕊                      💖
🙏4
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ †

[ †  እንኩዋን ከዘመነ ጸደይ ወደ ዘመነ ክረምት መሸጋገሪያ ለሆነችው ዕለትና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ   † ]

ስንዱ እመቤት ቤተ ክርስቲያን [ሃገራችን] ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት መጸው [ጽጌ] : ሐጋይ [በጋ]: ጸደይ [በልግ] ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::

በተለይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና "ሽሽታችሁ [ስደታችሁ] በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" ብሎናልና [ማቴ.፳፬፥፳] (24:20) ልንጸልይ ይገባናል:: በዘመነ ክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ የለበትምና ፍሬ ምግባር ሣናፈራ ሞት እንዳይመጣ: አንድም ክረምት የዝናብና የጭቃ ጊዜ በመሆኑ እንኩዋንስ ለስደት ለኑሮም አይመችምና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጸልይ:-

"በዝንቱ ክረምት በመዋዕሊነ:
እንበለ ፍሬ እንዘ በቆጽል ኀሎነ:
ናስተበቁዐከ እግዚኦ ኢይኩን ጉያነ::"
[ክረምት በተባለ በእኛ እድሜ:
ፍሬ ሳናፈራ በቅጠል /ያለ መልካም ሥራ/ ሳለን:
አቤቱ ጌታ ሆይ ስደትን አታምጣብን]

ቸሩ አምላካችን ከዘመነ መጸው በሰላም ያድርሰን:: ተረፈ ዘመኑንም የንስሃ: የፍሬና የበረከት ያድርግልን::

በዚሕች ዕለት እነዚህ ቅዱሳን ይከበራሉ:-

🕊 † ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ  †  🕊

በዘመነ ሐዋርያት ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ ማርያም ትባል ነበር:: እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ ቢሆንም ገና በልጅነቱ ድንግል ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች:: አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር:: ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል:: ቅዱስ ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል:: [ዮሐ.፲፬፥፳፪] (14:22)

ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ አሕጉራትን ዙሯል:: አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል:: አንዲት አጭር [ባለ አንድ ምዕራፍ] መልእክትም ጽፏል:: አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው:: ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ ደርቧል::

🕊 † ቅዱሳን ዺላጦስና አብሮቅላ †  🕊

ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን:: የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል:: የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል:: ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል:: በመጨረሻ ግን በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል::

ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ፴፮ [ 36 ] ቱ ቅዱሳት አንስት ነው:: ጌታችንን ተከትላ: ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ: ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ ዐርፏለች:: ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ::

ጌታችን ከሐዋርያው ይሁዳ: ከዺላጦስና አብሮቅላም ጸጋ በረከትን ያድለን::

🕊 

[ †  ሰኔ ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ [ከ፸፪ (72) ቱ አርድእት]
፪. ሰማዕቱ ዺላጦስ መስፍን
፫. ቅድስት አብሮቅላ [ሚስቱ]
፬. አባ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት
፭. የጸደይ መውጫ / የክረምትመግቢያ

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. አቡነ አቢብ /አባ ቡላ/
፮. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

" የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ : የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው : ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ: ምሕረትና ሰላም : ፍቅርም ይብዛላችሁ:: ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: " [ይሁዳ.፩፥፩] (1:1)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🙏2
2025/07/09 00:35:54
Back to Top
HTML Embed Code: