Telegram Web Link
2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷     "  እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር አ ለ !  " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[           🕊   ስብከት    🕊              ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬


❝ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ ፤ ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ፥ ያሳያል።

እርሱ ብቻ የማይሞት ነው ፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል ፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም ፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን ፤ አሜን። ❞

[  ፩ጢሞ . ፮ ፥ ፲፬ - ፲፮  ]



🕊                       💖                   🕊
6🙏1
3
🕊

[ †  እንኩዋን ለስደተኛው ሊቀ ዻዻሳት "አባ ቴዎዶስዮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † ]

🕊   †  አባ ቴዎዶስዮስ   †   🕊

ጻድቁ ሊቀ ዻዻሳት ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ከልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ በመንኖ ጥሪት የሚኖር ደግ ሰው ነበር:: ያ ዘመን መለካውያንና ልዮናውያን [ክርስቶስን ፪ [2] ባሕርይ የሚሉ] የሰለጠኑበት ዘመን ነበር:: በአንጻሩ ደግሞ ተዋሕዶን የሚያምኑ ሊቃውንትና ምዕመናን ቁጥራቸው የተመናመነ ነበር::

ችግሩ ግን ይህ ብቻ አልነበረም:: በጊዜው ተዋሕዶን አምኖ መገኘት እስከ ሞት የሚደርስ ዋጋንም ያስከፍል ነበር:: ለዚሕም ነው ሮማውያን ሃይማኖትን በግድ ለማስለወጥ ከነገሥታቱ ጋር የተቆራኙት:: ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ደሴት ውስጥ ከተገደለ በሁዋላ በግብፅ የተሾሙ ሊቃነ ዻዻሳት አብዛኞቹ መከራና ስደትን ቀምሰዋል:: ትልቁን ቦታ ግን አባ ቴዎዶስዮስ ይወስዳል::

አባ ቴዎዶስዮስ ለእስክንድርያ [ግብፅ] ፴፫ [33] ኛ ፓትርያርክ ነው:: እረኝነት [ዽዽስና] እንዳሁኑ ዘመን ሠርግና ምላሽ አይደለምና ገና እንደ ተሾመ የቀረበለት ጥያቄ አንድ ነበር:: "ተዋሕዶን ትተህ መለካዊ ትሆናለህ ወይስ የሚከተልብህን ፍርድ ትቀበላለህ?" አሉት:: ይህንን ያሉት ከንጉሡ ዮስጢያኖስ የመጡ መልእክተኞች ነበሩ:: መልሱ ፈጣን ሆነባቸው:: "እኔንም ሆነ ሕዝቤን ከቀናችው እምነታችን በምንም ልትለዩን አትችሉም" አላቸው::

በዚህ ምክንያት በቀጥታ ግዞት [ስደት] ተፈረደበት:: ወደ በርሃ ሲያግዙት ካህናት : መምሕራንንና ምዕመናንን አደራ ብሏቸው ነው የሔደው:: መናፍቃኑ እሱን ካሰደዱ በሁዋላ ሕዝቡን ለመቀየር ብዙ ደክመዋል:: ግን ሊሳካላቸው አልቻለም:: ምክንያቱም አደርነትን የማይረሱ ደጋግ መምሕራን ነበሩና ነው::

በዚያ ላይ አባ ቴዎዶስዮስ ጦማር [መልእክት] በየጊዜው ይጽፍላቸው ነበር:: እጅግ ብዙ ከሆኑት መልእክቶቹ የተወሰኑት ዛሬም ድረስ ሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ::

በዚሕ አስቸጋሪ ዘመን መልካም ነገሮችም ነበሩ:: ቀዳሚው ማሕቶተ ተዋሕዶ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ ሲሆን ፪ [2] ኛው ደግሞ የንጉሡ ሚስት የተባረከችው ታኦድራ ናት::

አባ ቴዎዶስዮስ በግዞትና በስደት ሳለ ንግሥቲቱ ትራዳው : ምዕመናንንም ትንከባከብ ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ከሊቀ ዻዻሱ ዘንድ ክህነትን ተቀብሎ ከሶርያ እስከ ምድረ ግብጽ ስለ ተዋሕዶ ሕልውና ተጋድሏል:: ምናልባትም ከሐዋርያው ቅዱስ ዻውሎስ በሁዋላ በፈሊጥ ክርስትናን በማስፋፋት ቀዳሚ አባት ነው:: [በነገራችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብ ማሰርን ያስተማረ አባትም ነው]

፪ [2] ቱ [አባ ቴዎዶስዮስና ቅዱስ ያዕቆብ] ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ ስለ ደከሙ የዘመኑ ምዕመናን በስማቸው "ያዕቆባውያን እና ቴዎዶስዮሳውያን" ተብለው ተጠርተዋል:: አባ ቴዎዶስዮስ ግን ሲታሠር ሲፈታ : ሲሰደድ ሲመለስ ብዙ ተሰቃየ::

ሕዝቡን ግን በመልካም እረኝነት ጠብቆ : ከተኩላ አፍ ታደገ:: በዚህች ቀንም ዐርፎ ተቀብሯል:: በፓትርያርክነት ያገለገለባቸው ዘመናት ፴፪ [32] ዓመታት ሲሆኑ ከእነዚህ ዓመታት ፳፰ [28] ቱ ያለቁት በስደትና በመከራ ነው::

እግዚአብሔር የአባቶቻችን ስደት አስቦ ከነፍስ ስደት ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

🕊

[ † ሰኔ ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ዻዻሳት
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ
፫. ቅዱስ ባስልዮስ
፬. ቅዱስ ባሊዲስ

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]

" ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና:: " [ማቴ.፭፥፲] (5:10)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
5🙏1
3
ድል አለ በስምህ ድል አለ በቃልህ ተራራው ይናዳል #አማኑኤል ስልህ ባህር ይከፈላል መድሀኒአለም ስልህ የመኖራችን ትርጉም የቀራኒዮ ንጉስ የድንግል ማርያም ልጅ ቸሩ #አማኑኤል ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ #ሲከፍችሁ ክንዱን ዘርግቶ አለሁ ይበላችሁ 🙏 በያለንበት ሁላችንንም ይጠብቀን

                  
#ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
8🙏2
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ:: አሜን::

🕊   †  ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ [ እል-በረዳይ ] [ St. Jacob baradaeus ]  †   🕊


[ በተለይ በሃገራችን የተዘነጋ የሚመስለው የምሥራቅ ኮከብ - ኮከበ ጽባሕ ]

🕊

"ያዕቆብ" ለሚል ስም ትርጉምን የሰጡ አበው በ2 መንገድ ያትቱታል::

፩. አኃዜ ሰኮና:: ነገሩ ከወልደ ይስሐቅ ወርብቃው ርዕሰ አበው ያዕቆብ ጋር የተያያዘ ቢሆንም አበው ግን ለትህትና ይተረጉሙታል::
፪. አእቃጺ / አሰናካይ:: ነገሩ ስድብ [ አሉታዊ ] ይምሰል እንጂ በዚህ ስም የተጠሩ አበው ሁሉ ለአጋንንትና ለመናፍቃን ትልቅ መሰናክል ሆነውባቸው ኑረዋልና አባባሉ ምስጋና እንጂ ነቀፋን አይወክልም::

የ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን ምሥራቃዊ ኮከብ ቅዱስ ያዕቆብም ለመለካዊ መናፍቃንና ለተዋሕዶ ተገዳዳሪዎች ትልቅ መሰናክል ሆኖባቸዋል:: የቀናችውን ቀርነ ሃይማኖትንም አጽንቷል::

ብዙ ጊዜ "ዘ" - እልበረዲ መባሉን ይዘው በ"ዘ" ምክንያት እልበረዲን እንደ ሃገር የቆጠሯት አልጠፉም:: በረከታቸው ይድረሰንና ትጉሑ ዻዻስ አቡነ ጐርጐርዮስ ካልዕ ግን ለዚሁ መላምት "የለም!" ባይ ናቸው::
'የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ' በተሰኝ ተወዳጅ መጽሐፋቸው "እል-በረዲ" ማለትን በዓረብኛ ከሠጋር በቅሎ : ከሥሙር ሠረገላ ጋር አነጻጽረው አስቀምጠውታል:: ለምን ቢባል

- እንደ ሠረገላ በተፋጠነ አገልግሎቱ ወዳጅንም ጠላትንም አስደምሟልና::
+ቅዱስ ያዕቆብ የተወለደው በ፮ኛው መቶ ክ ዘመን መጀመሪያ [ በ፭፻ አካባቢ ] ሲሆን ያረፈው ደግሞ በ፭፻፸፰ ዓ/ም እንደሆነ ይታመናል:: ነገሩን ልብ ስንለው ቅዱስ ማኅሌታይ ያሬድን - ወዲህ በዘመን : ወዲያ ደግሞ በአገልግሎት ይመስለዋል::

እርግጥ ነው ለውለታው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት" ስትባል የእኛዋስ ምናለ "ያሬዳዊት" ብትባል የሚል ቁጭትን ያመጣል::
+ ጊዜው [ ፭ኛውና ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን] ወዲህ ወርቃማ : ወዲያ ደግሞ ጨለማ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ዘመን ነበር::
¤ በብርሃንነቱ በተለይ በምሥራቁ ዓለም ያበሩ አበው እነ ያዕቆብ ዘስሩግ : ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ : ያዕቆብ ዘእልበረዲን የመሰሉ አበው ተገኝተውበታል:: ሲያልፍ ደግሞ ዘይኑንና አንስጣስዮስን የመሰሉ ደጋግ ነገሥታት በዘመኑ መነሳታቸውን እናስባለን::

+ በተቃራኒው ግን ዘመኑ ቤተ ክርስቲያን ለ፪ የተከፈለችበት : መለካውያን የነገሥታቱ ደጀን አላቸውና ተዋሕዶ ሃይማኖትን ከሥሯ ነቅሎ ለማጥፋት ብዙ የሞከሩበት ዘመን ነውና ጨለማነቱ ይጐላብናል::
+ በእርግጥም ከመርቅያን እስከ ዮስጢኖስ ዳግማዊ ዘመን ድረስ ለ፻ ዓመታት መለካውያኑ የልዮን ልጆች ፪ ባሕርይ ማለትን ሊያሰፉ : ተዋሕዶንም ሊያጠፉ የከፈቱት ዘመቻ ሊሳካ ጫፍ የደረሰ ይመስል ነበር::

+ ግን አማናዊት ቤቱን የማይተው አማናዊው ጌታ መድኃኔ ዓለም አርመኖቹን ስቦ በ፬፻፺ዎቹ ወደ መንጋው ቀላቀለ:: በግብጽ አባ ቴዎዶስዮስን : በሶርያ ደግሞ ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስን አስነስቷል:: ከቤተ መንግስትም ስም አጠራሯ ያማረ ንግሥት ታኦድራን ማርኯል:: በእነዚህ ቅዱሳን ትጋት የለመለመችው ተዋሕዶ እንደ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ያለ አርበኛን ግን ያገኘችው በጭንቅ ቀን ነበር::

+ ሰው መሆን ሰው በጠፋባቸው ቀናት ነውና : በግብጽና በቁስጥንጥንያ በትምህርትና ምናኔ ላይ የነበረው ቅዱሱ ታጥቆ ለአገልግሎት የተሰለፈው በ፭፻፴ዎቹ አካባቢ ነበር::
+ ጊዜው ወዲህ አንበሳው ቅዱስ ሳዊሮስ ከሶርያ ወደ ግብጽ እንደተሰደደ ያረፈበት ነበር:: ወዲያ ደግሞ ሊቁ አባ ቴዎዶስዮስ የግብጹ ለግዞት የተዳረገበት ነበርና የተዋሕዶ ምዕመናን ያለ እረኛ ተቅበዘበዙ:: የቤተ መንግስቱ ተጽዕኖ ደግሞ ፪ ባሕርይ በማይሉት ላይ እሥራትና ግድያን ወደ ማወጅ ተሸጋግሯልና የምእመናን ቁጥር እጅጉን መመንመኑ ቀጠለ::
+ ይህ ዕረፍት የነሳው ቅዱስ ያዕቆብ በበኩሉ ነገሩን በዝምታ ሊያልፈው አልወደደምና አገልግሎቱን አሰፋ:: ሌሊቱን በጸሎት ያድራል:: ቀን በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ማስተማር ባይችል በየቦታው እየዞረ ያስተምር ነበር::
+ ከትምህርቱ ጣዕምና ከመልእክቱ ሥምረት የተነሳም ምእመናን እንደገና ተነቃቁ:: እርሱም ከግብጽ እስከ ሶርያ : አልፎም እስከ ቁስጥንጥንያ ድረስ ያለ ዕረፍት ሲሰብክ ፵ ዘመናትን አሳለፈ:: በተለይ አዲስ አማኞችን ያጠምቅ ዘንድ በእሥረኛው ቅዱስ ቴዎዳስዮስ ኤዺስ ቆዾስነትን ተቀብሏል::

+ የሶርያ [ አንጾኪያ ] የፕትርክና መንበሩ ክፍት ሆኖ እርሱን ቢጠብቀውም እርሱ ግን የዚህ [ የስልጣን ] ፈላጊ አልነበረምና ሌሎች እንዲሾሙበት አድርጉዋል::
+ ቅዱስ ያዕቆብ በስብከት አገልግሎት ምሥራቁን ዓለም ሲያበራ የተባበሩት ደቀ መዛሙርት ቢኖሩም ያሳለፈው ድካምና መከራ ግን ተወዳዳሪ አልነበረውም:: በተለይ የወቅቱ የአንጾኪያ ኃያላን መኩዋንንትና ሹመኛ መናፍቃን ብዙ አሳደውታል::
+ እርሱ ግን በጥበብና በፈሊጥ እዚያው ደጃቸው ላይ የነበሩ ምዕመናንን በእረኝነት ጠብቁአል:: ለዚህ ሲባልም ራሱን እየቀያየረ የመሣፍንቱን አጥሮችና ቅጥሮች አልፏል:: ለቤተ ክርስቲያን ክብርም እንደ እብድ : እንደ ሴትም መስሎ የወንጌልን ዘር ዘርቷል::

¤ ከብዙ ፈተናና አገልግሎት በሁዋላም በተወለደ በ፸፰ ዓመቱ [ በ፭፻፸፰ ዓ/ም ] ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::

¤ ትልቁ መታሰቢያው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት" : ምዕመኑ "ያዕቆባውያን" መባላቸው ሲሆን እኛ ደግሞ በአንገታችን ላይ እንድናስራት ባስተማረን ማዕተብ [ ማኅተም ] ዘወትር እናስበዋለን:: ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብን በአንገት ላይ ስለ ማሰር ያስተማረ እርሱ ነውና::

¤ የምሥራቁን ኮከብ እል-በረዲ ያዕቆብን በየዓመቱ ሰኔ ፳፰ ቀን በነገረ ቅዱሳን መደበኛ ጉባኤ [ ጐንደር ] እናከብራለን:: ሶርያውያን ደግሞ July 31 [ ሐምሌ ፳፬ ቀን ] ያከብሩታል::

" እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: " [ ማቴ. ፭ ፥ ፲፫ - ፲፮ ]

አምላከ ቅዱስ ያዕቆብ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን:: ከቅዱሱ በረከትም አይለየን::

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
1🙏1
5
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት  "    ]
             
         [    የመጨረሻ ክፍል     ]

❝ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። ❞ [ ፪ጴጥ.፩፥፳ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                         👇
🙏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🕊                      💖                      🕊



የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለእመቤታችን ያለው ረብ [ ጥቅም ] !



[   💖 O R T H O D O X Y  💖    ]



†                        †                         †
💖                     🕊                      💖
🙏1
🕊

[ †  እንኩዋን ለቅዱሳን ነገሥታት "ማርቆስ እና ቴዎድሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † ]

ማንኛውም ሰው

¤ ቢጾም ቢጸልይ
¤ መልካም ቢሠራ
¤ ለእግዚአብሔር ቢገዛ
¤ አልፎም ቢመንን ይደነቃል:: ይሕንን ሥራ ንጉሥ ሆነው ስለ ሠሩትስ ምን እንላለን? ማድነቅ የሚለው ቃል የሚገልጸው አይመስለኝም::

¤ ወርቅና ብር በእግር እየተረገጠ
¤ የሚበላውና የሚጠጣው ተትረፍርፎ ሳለ
¤ አገር ምድሩ እየሰገደላቸው
¤ ሁሉ በእጃቸው
¤ ሁሉም በደጃቸው ሳለ...
ይህንን ሁሉ ስለ ክርስቶስ ፍቅር የተውትን ጻድቃን ነገሥታት የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከእነዚህ መካከል ዛሬ የሚከበሩትን ፪ [2] ቱን እናዘክር::

🕊  †  ቅዱስ ማርቆስ ንጉሠ ሮም  †   🕊

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቅዱስ ጻድቅ: የዋህ: ንጹሕና ገዳማዊ ብላ ትጠራዋለች:: ሮም እንደ ዛሬ ጠባብ ከተማ ሳትሆን ዓለምን በክንዷ ሥር ቀጥቅጣ የምትገዛ ኃያል ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ማርቆስ የልዑላኑ ቤተሰብ ነውና በሮም ተወልዶ በእመቤታችን ቤተ መቅደስ ውስጥ አድጉዋል::

የየዕለት ሙያው ጾምና ጸሎት: መጻሕፍትንም መመልከት ነበር:: ነባሩ ንጉሥ ሲሞት መሣፍንቱ ቅዱስ ማርቆስን በድንግልናው ገና ወጣት ሳለ በዚያች ታላቅ ሃገር ላይ አነገሡት:: ንጉሥ ቢሆንም ሙሉውን ሌሊት በእመቤታችን ፊት ሲጸልይና ሲያለቅስ ያነጋ ነበር::

ስለ ፍቅርም ድንግል ማርያም ተገልጻ "ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?" አለችው:: ቅዱስ ማርቆስም "ለሕዝቡ ፍቅር አንድነትን ሰላምን ስጪልኝ:: እኔ በማስተዳድርበት ቦታ ሁሉ ጠብ ክርክር ይጥፋልኝ:: ፍቅር ይንገስልኝ" ሲል መለሰላት:: ድንግል እመቤታችንም "እንደ ቃልህ ይሁን" ብላ አጋንንት ወደ ሃገሩ እንዳይገቡ ከለከለችለት:: በዚህም ቅዱስ ማርቆስ ከነገሠ ጀምሮ ለ5 ዓመታት ጠብ ክርክር: ክፋትና ችግር አልነበረም:: ሁሉም ተፋቅሮን ያጸና ነበር እንጂ::

ከ ፭ [5] ዓመታት በሁዋላ ግን ሕዝቡና ሹማምንቱ ተሠብስበው አንድ ነገርን መከሩ:: ቅዱስ ማርቆስን አጋብተው ለብዙ ጊዜ እንዲመራቸው ማለት ነው:: ምክንያቱም አኗኗሩ እንደ መነኮሳት ነውና ጠፍቶ እንዳይሔድ በመስጋታቸው ነው:: ከዚያም የሕዝቡ አለቆች ተመርጠው ሃሳባቸውን አቀረቡለት:: እርሱ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጭራሹኑ እንዲህ ዓይነት ሃሳብ መጥቶበት አያውቅም::

"እስኪ በጸሎት ላስብበት" ብሎ መለሳቸው:: እነርሱ ግን ወደውታልና ድጋሚ ተሰብስበው ሌላ ነገርን መከሩ:: እርሱ ሳያውቅ መልካም ሴት መርጠው: ሥርዓተ ተክሊል አዘጋጅተው: ድግሱንም አዘጋጅተው በግድም ቢሆን ሊያጋቡት ቆረጡ:: ቅዱስ ማርቆስ የተደረገውን ሁሉ ፈጣሪ ገልጦለት በጣም ደነገጠ::

ፈጥኖ ወደ እመ ብርሃን ስዕል ቀርቦ አለቀሰ:: "እመቤቴ! እኔ ካንቺ ጋር እንጂ ከዚህ ዓለም ጋር መኖር አልችልም" አላት:: እመ ብርሃን ከሰማይ ወደ እርሱ ወርዳ "የምነግርህን ስማኝ:: በሌሊት ተነስተህ ወደ ማሳይህ በርሃ ሒድ" ብላው ተሠወረች:: ቅዱስ ማርቆስ ደስ እያለው የንግሥና ልብሱን ጥሎ: ቆሻሻ ጨርቅ ለብሶ በሌሊት ከቤተ መንግስቱ ወጣ::

ወደ ሁዋላ አልተመለከተም:: እመቤታችን እየመራችው ደብረ ቶርማቅ የሚባል በርሃ ውስጥ ባሕር ተከፍሎለት ገባ:: ሕዝቡ መልካም እረኛ መሪን አጥቷልና በሮም ከተማ ታላቅ ለቅሶና ሐዘን ተደረገ:: ቅዱስ ማርቆስ ግን በደብረ ቶርማቅ በጾም: በጸሎትና በተጋድሎ ማንንም ሳያይ ለ፷ [60] ዓመታት ኖረ::

በዚህች ቀንም ዐርፎ ወደ ወደደው ክርስቶስ ሒዷል:: ሥጋውን የሚቀብር አልነበረምና ከሰማይ ፲፪ [12] ቱ ሊቃነ መላእክትና ፲፪ [12] ቱ ሐዋርያት ወረዱ:: በዝማሬ ሲገንዙትም በድኑ ከመሬት ፭ [5] ክንድ ከፍ ብሎ ተንሳፈፈ:: መላእክቱና ሐዋርያቱም በማሕሌት እዚያው ደብረ ቶርማቅ ውስጥ ቀብረውታል::

🕊 † ቅዱስ ቴዎድሮስ ንጉሠ ኢትዮዽያ  † 🕊

በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል:: በርግጥ በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን ፲፰፻፵፭-፲፰፷ [1845-1860] ነው:: በበጎ ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ የምናስበው ቀዳማዊው ነው::

ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ-ዳዊት [ግማደ-መስቀሉን ያመጡት] እና የተባረከችው ሚስታቸው ፅዮን ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ  ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም ነው::

በኢትዮዽያ ለ፫ [3] ዓመታት ከ፲፫፻፺፮-፲፫፻፺፱ [ከ1396-1399] ብቻ ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን
¤ ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል: ፍርድ እንዳይጉዋደል ይታትር የነበር:
¤ ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር:
¤ ወገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ:
¤ ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር::

ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር:: በነገሠ በ፫ [3] ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል:: ከመቃብሩም ላይ ጸበል ፈልቁዋል::

ቸር አምላክ መልካም መሪ ለሃገራችን: በጐ እረኛንም ለነፍሳችን ያድለን:: ከቅዱሳን ነገሥታቱም ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

[ †  ሰኔ ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ማርቆስ ንጉሠ ሮም [ጻድቅ: ንጹሕና ገዳማዊ]
፪. ቅዱስ ቴዎድሮስ ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፫. ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ኢትዮዽያዊ [ፍልሠቱ]
፬. ፯ቱ "7ቱ" ቅዱሳን መስተጋድላን [አባ አብሲዳ: አባ ኮቶሎስ: አባ አርድማ: አባ ኒኮላስ: አባ ሙሴ: አባ እሴይ: አባ ብሶይ]
፭. ቅዱሳን አባ ሖር: አባ ብሶይ: አባ ሖርሳና እናታቸው ቅድስት ይድራ [ሰማዕታት]

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅድስት አርሴማ ድንግል
፫. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፭. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፮. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]

" አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል:: የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው:: የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም:: በበጐ በረከት ደርሰህለታልና:: ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ:: ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም:: ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ:: በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው:: [መዝ.፳፥፩-፭] (20:1-5)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
4🙏1
2
#ወዳጆቼ

#ፍቅር_ካለ_እግዚአብሔር_አለ እግዚአብሔር ካለ ደግሞ ሁሉ ነገር አለ ፤ ፍቅር ማለት ፍጹም ሰው ፈልጎ ማግኘትና መውደድ ሳይሆን ፣ ጎደሎውን ሰው ፍጹም አድርጎ መቀበል ነው። ሰማህ ወዳጄ እግዚአብሔር አምላክ ከኛ ለመሸሽ በቂ የሆነ ምክንያት እያለው ፣ የታገሰን ፣ በደላችን ደስ አሰኝቶት ሳይሆን ስለሚወደን ነው ። ማንም ሰው ፀሐይን ያለችበት ድረስ ሄዶ ለመንካት ቢሞክር መቅለጡ ግድ ነው ነገር ግን ያለንበት ድረስ መጥታ ታሞቀናለች ። #እግዚአብሔር አምላክንም ማንም በመለኮቱና በአምላክነቱ ሊያየውና በግርማውም ፊቱ ሊቆም አይችልም ። ነገር ግን ላይ መሄድ ለማንችለው ታች ድረስ ሊፈልገን መጥቶ በፍቅሩ ፀሐይ አሞቀን። መግደል የሚችለው ሞተ ኃይልም ፍቅርም ያለው አምላክ ከኃይል ይልቅ በፍቅር ተደሰተ ማንም የራሱን በደል ተሸክሞ ተጠያቂ መሆን በማይፈልግበት ዓለም ላይ ስለ የሁላችንን በደል ተሸክሞ ተጠያቂ ሆነልን      

#መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🙏
                           
የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
15🙏4
                         †                         

🕊  ይህች ዕለት የተቀደች ናት 🕊 ]

❝ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ ለውሉደ  ሰብእ  መድኀኒት ... ❞

🕊

❝ ይህች ዕለት የተቀደች ናት ። ለሰው ልጆችም  መድሃኒት ናት።በየጊዜውና በየሰአቱ መሪ ትሁነን። እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ።

ሁልጊዜ መሀሪ ሰውን ወዳጅ ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው ሰንበትን በእውነት አክብሩ። መዋደድን ገንዘብ አድርጉ። ሰንበትን አክብሩ ጽድቅንም ስሩ። ነቀዝ የማይበላውን የማያረጀውን የማይጠፋውን ሰማያዊ መዝገብ [ ሃብት ] አከማቹ። ❞

🕊

[   ቅዱስ ያሬድ    ]


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
1🙏1
2025/07/09 16:33:17
Back to Top
HTML Embed Code: