#ወላዲተ__አምላክ
#ድንግል_ማርያም ወላዲተ አምላክ እነደሆነች ማመን #የኦርቶዶክሳዊነት መሠረት መለኪያ መስፈሪያ ጣምም ነው። ማንም ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን #ድንግል_ማርያም ወላዲተ አምላክ እንደሆነች የማያምን ቢኖር #ከልዑል_እግዚአብሔር እቅፍ የወጣ ነው ሃይማኖትም የለውም"
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ነባቤ_መለኮት
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam

❤8🙏4
🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን። ✞
[ ✞ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]
🕊 † ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ † 🕊
ቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተከተሉበት ሰዓት እድሜአቸው በ፫ ደረጃ የተከፈለ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያሳያል::
¤ እንደ ዮሐንስ ወንጌላዊ ያሉት በ፳ ዎቹ ውስጥ:
¤ ቅዱስ ታዴዎስን የመሰሉት ደግሞ በ፴ ዎቹናና በ፵ ዎቹ ውስጥ የነበሩ ሲሆን
¤ እነ ቅዱስ ዼጥሮስ ደግሞ በ፶ ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ነበሩ:: ደቀ መዛሙርቱ ከወጣቶችም: ከጐልማሶችም ከአረጋውያንም የተዋቀሩ ነበሩ ማለት ነው::
ቅዱስ ታዴዎስ በቀደመ ስሙ ልብድዮስ ይባል የነበረ ሲሆን በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ [በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች] ስምዖን እና ይሁዳ እየተባለም ተጠርቷል::
ቅዱሱ ጌታችን ተከትሎ : -
¤ ከ፲፪ቱ አንዱ ሆኖ በፈጣሪው ተመርጦ:
¤ 3 ዓመት ከ፫ ወር ከጌታ እግር ተምሮ:
¤ በዕርገቱ ተባርኮ:
¤ በበዓለ ሃምሳም ፸፪ ልሳናትን ተቀብሎ:
¤ ሐዋርያት ዕጣ ሲጣጣሉ የበኩሉን አሕጉረ ስብከት ተካፍሎ ዓለምን ዙሯል::
ቅዱስ ታዴዎስ አንድ ቀን ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር ወደ አንዲት ሃገር ይገባሉ:: ታዲያ ለቀናት ያለ ምግብ ወንጌልን ሲሰብኩ ቆይተው ነበርና ደጐቹ ሐዋርያት ራባቸው:: ወደ ከተማዋ ሳይገቡ አንድ ሽማግሌ ሲያርስ አይተው ሰላምታን ሰጡትና "እባክህ እርቦናልና አብላን" አሉት:: እርሱም ምንም ወገኑ ከአሕዛብ ቢሆነ አሳዝነውት በሬዎቹን ሳይፈታ እየሮጠ ሄደ::
ያን ጊዜ ቅዱስ ታዴዎስ ሊቀ ሐዋርያትን "እርሱ እስኪመጣ ለምን አናርስም" አለው:: ፪ቱ ተነስተው ታዴዎስ ሞፈር: ዼጥሮስ ደግሞ ስንዴውን ያዘ:: ቅዱሳኑ እየዘሩ ያረሱት ሰውየው ምግብ ይዞ እስኪመጣ አድጐ: አፍርቶ: እሸት ሆኖ ቆየው::
ገበሬው የተደረገውን ተአምራት ባየ ጊዜ ደነገጠ:: ሊያመልካቸውም ወደደ:: እነርሱ ግን "እኛ የልዑል ባሮች ነን" ብለው በክርስቶስ ማመንን አስተማሩት:: "ልከተላችሁ" ቢላቸው "የለም! ከእሸቱ ይዘህ ወደ ከተማ ግባና ራት አዘጋጅልን:: እኛ እንመጣለን" አሉት::
እርሱ ወደ ቤቱ ሲመለስ አሕዛብ ነገሩን ተረዱ:: ተሠብሥበውም "እነዚህ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እሳትም ሰይፍም አይበግራቸውም" ብለው ወደ ከተማ እንዳይገቡ ከበሩ ላይ ራቁቷን የሆነች ዘማ አቆሙ::
ቅዱስ ታዴዎስ ገና ከርቀት ስላያት ቀና ብሎ ቅዱስ ሚካኤልን "እርዳን" አለው:: ሊቀ መላእክትም ድንገት ወርዶ ዘማዋን ሴት በጸጉሯ በዓየር ላይ ሰቀላት:: በከተማዋ ያሉ አሕዛብም ይህንና ሌሎች ተአምራትን አይተው ሁሉም በጌታችን አምነው ተጠመቁ:: ለሐዋርያቱም ሰገዱላቸው::
አንድ ቀን ግን አንድ ጐረምሳ ባለ ጠጋ ቅዱስ ታዴዎስ "ሀብት ንብረታችሁን መጽውቱ" ሲል ሰምቶት ዘሎ የሐዋርያውን ጉሮሮ አንቆ ከሞት አድርሶት ነበር:: ያን ጊዜ "ጌታየ! ለካ ሀብታም ከሚጸድቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ያልክ ለዚህ ነው!" ብሏል:: ባለ ጠጋው "እንዴት ይሆናል?" ቢለው መርፌ አሠርቶ ግመሉን ከነ ባለቤቱ በሰው ሁሉ ፊት ፫ ጊዜ አሳልፎታል::
ያም ማለት ጌታችን እንዳለው "በሰው ዘንድ የማይቻለው በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል::" [ማር.፲፥፳፫] በዚህ ምክንያትም ያ ክፉ ባለ ጸጋ ወደ ልቡናው ተመልሶ ከቅዱስ ታዴዎስ እግር ሥር ወደቀ:: ሐዋርያውም አለው "ሀብትህን ለነዳያን ስጥ:: ይህንንም በትር እንካና እየዞርክ ወንጌለ መንግስትን ስበክ::" ባለ ጸጋውም የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ በክብር ዐርፏል::
ቅዱሳኑ ታዴዎስና ዼጥሮስ ግን በሃገሪቱ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው: ካህናትን ሹመው: ያቺን በዓየር ላይ የሰቀሏትን ዘማም የተባረከች መበለት አድርገው: በሌሎች አሕጉራት ወንጌልን ለማዳረስ ወጥተዋል::
ቅዱስ ታዴዎስም እስከ እርጅናው ድረስ ለወንጌል ሲተጋ ኑሯል:: ጌታችንም በየጊዜው በአካል እየተገለጸ አጽናንቶታል:: ከብዙ የድካምና የመከራ ዘመናት በሁዋላም በዚህች ቀን ዐርፏል::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ ሐዋርያ በረከት ይክፈለን::
[ † ሐምሌ ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ [ከ፲፪ቱ ሐዋርያት]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፫. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፬. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፭. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፮. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
" ጌታ ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን "ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል!" አላቸው:: ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ:: ጌታ ኢየሱስም ደግሞ መልሶ "ልጆች ሆይ! በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው! ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" አላቸው:: " [ማር.፲፥፳፫-፳፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

❤3🙏2
#የምንሰጠው_ሌላው_ስለሚያስፈልገው_ነው!
አንድ ሰው እንዲህ አለ "መስጠትን ተምሬያለው ተርፎኝ ሳይሆን #ማጣትን_ስለማውቀው ነው!" በእርግጠኝነት በአንድም በሌላም አጋጣሚ መራብን የማያውቅ ሰው የለም! የተራበን ሰው የሆነ ምግብ ስትሰጠው ምን ሊሰማው ይችላል? ብርዱ ያሰቃየውን ሰው ልብስ ስትደርብለት እንዴት አድርጎ ይደሰት! ታድያ የዚህ #ደስታ_ምንጭ ከመሆን በላይ በዚህ ምድር ምን ትልቅ ነገር ይገኛል! የተረፈህ ስለሆንክ ስለሞላህ አይደለም ግን #ስለሚያስፈልጋቸው ጥቂቷን ስጥ እና #ብዙ_ተደሰት ወንድሜ እህቴ አንቺም ካለችሽ አጉርሺ ስለሚመልሱልሽ ሳይሆን #ስለሚያስፈልጋቸው ነው!
#_ሰናይ__ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

❤10🙏1
†
🕊 💖 ቅዱስ ታዴዎስ 💖 🕊
🕊
❝ ስማቸው ጴጥሮስና እንድርያስ ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ፣ ፊልጶስና በርተሎሜዎስ ፣ ቶማስና ማቴዎስ ፣ ታዴዎስና ናትናኤል ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ማትያን በመባል ለሚጠሩ ለ ፲፪ ቱ የመድኅን ሐዋርያት ሰላምታ ይገባል። ❞
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
❝ አቤቱ በስምኽ የሰበኩ ፤ በታላቅ መከራ በረኀብና በጥም ፤ በብርድና በመራቆት ፤ በመውዛትና በመድከም ፤ ከነገሥታትና ከመኳንንት ዘንድ ተፈርዶባቸው መከራን በመቀበል በምድር ኹሉ ውስጥ የቃልኽን መዝገብ ስለዘሩ ስለነዚኽ ደቀ መዛሙርትኽ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ በእሳት በመከራ የተቀበለ አለ ፤ በጦርም የተወጋ አለ ፤ በሰይፍም የተቆረጠ አለ ፤ በመንኰራኲርም የተፈጨ አለ ፤ በደንጊያም የተወገረ ፤ በበትርም የተቀጠቀጠ አለ ፤ ስለነርሱ ብለኽ ማረኝ አስበኝም ፤ ስለሥቃያቸው ስለመቸገራቸውና ስለደማቸው ብለኽ የእኔን የአገልጋይኽን የዕዳ መጽሐፌን ቅደድ ፤ አሜን። ❞
[ ተአምኆ ቅዱሳን ]
[ 🕊 እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🕊 ]
🕊 💖 🕊

🙏1
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ም ክ ረ ቅ ዱ ሳ ን 🕊
▷ "ድል መንሳትና የአሸናፊነት ሕይወት!"
[ " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ " ]
[ 🕊 ]
-----------------------------------------------
❝ ነገር ግን ሞት ቢሆን ፥ ሕይወትም ቢሆን ፥ መላእክትም ቢሆኑ ፥ አለቆችም ቢሆኑ ፥ ያለውም ቢሆን ፥ የሚመጣውም ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንደማይችል አምናለሁ።
ኃይልም ቢሆን ፥ ከፍታም ቢሆን ፥ ዝቅታም ቢሆን ፥ ሌላ ፍጥረትም ቢሆን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል የለም። ❞
[ ሮሜ . ፰ ፥ ፴፰ ]
🕊 💖 🕊
👇

❤3
#መልካም_አድርግና_እርሳው...
ስላደርግኸው ስለዚህ ነገር ማንኛውንም ዓይነት #ውዳሴም ሆነ ሙገሳ አትሻ። መልካም ያደረግህለት ሰው አንተ እንዳደረግህለት ለአንተ መልካም የሆነውን አጸፋ እንዲመልስልህ ወይም አንተ አንደተንከባከብከው እርሱም #እንዲንከባከብህ አትጠብቅ።
#መልካም ስታደርግ በምላሹ #መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን! መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን። መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን። መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገር ይሁን።
እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል። መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ።
#መልካም__ቀን🙏

❤11
🕊
[ † እንኳን ለዓምደ ሃይማኖት ቅዱስ ቄርሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
🕊 † ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ † 🕊
† ቅዱስ ቄርሎስን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን " ዓምደ ሃይማኖት የሃይማኖት ምሰሶ" ይሉታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ሊቁ የተወለደው በእስክንድርያ [ግብጽ] በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እናቱ የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስ እህቱ ነበረችና አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ወስዶ አሳድጐታል:: ገና በልጅነቱ ወደ አባ ሰራብዮን ገዳም ገብቶ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በጾም: በጸሎትና በትሕትና የታሸ ነውና ሲማር አንድ ጊዜ ካነበበው በሕሊናው ተስሎ ይቀር ነበር::
ቅዱስ ቴዎፍሎስ "ምዕመናንን አስተምርልኝ" ብሎ ወደ ከተማ አመጣው:: መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ሲያስተምር ወይ ደግሞ መጻሕፍትን ሲያነብ ከምዕመናን ወገን ስንኩዋን የሚያወራና የሚንቀሳቀስ ቀርቶ የሚቀመጥም አልነበረም:: ጣዕመ ስብከቱም ብዙዎችን ለወጠ::
ከዚያም በ፬፻፲፪ [412] ዓ/ም አጎቱ የነበረው ፓትርያርክ አባ ቴዎፍሎስ ሲያርፍ ዻዻሳትና ሊቃውንት በአንድነት ቅዱስ ቄርሎስን መረጡ:: የእስክንድርያም ፳፬ [24] ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን አበራች:: በቅድስናው: በሊቅነቱ: በስብከቱ: በድርሰቶቹና በትጋቱ በፍጹም አገለገላት::
በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን "2 አካል: ባሕርይ ነው" [ሎቱ ስብሐት!] የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ ፪ የከፈለው እመቤታችንን የአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: [ላቲ ስብሐት!]
ነገሩን ቅዱስ ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ [የቁስጥንጥንያ ንጉሥ] ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ:: ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ፬፻፴፩ [431] ዓ/ም በኤፌሶን ከተማ የመናፍቃኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና ፪፻ [200] ቅዱሳን ሊቃውንት ተገኙ::
የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በሁዋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ ማሕበር ማር [ቅዱስ] ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: ድንግል ማርያምም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::
የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት ፲፪ [12] አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::
† ከእነዚህም አንዱ ድንግል ማርያም "ታኦዶኮስ [የእግዚአብሔር እናቱ] ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን :-
¤ የአምላክ እናት:
¤ ዘላለማዊት ድንግል:
¤ ፍጽምት:
¤ ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::
ጉባዔው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::
እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሒዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች:: ቅዱስ ቄርሎስ ግን ለ፴፪ [32] ዘመናት በመንበሩ ላይ አገልግሎ: ፍሬ ትሩፋት አፍርቶ: ብዙ ድርሰቶችንም ደርሶ በ፬፻፵፬ [444] ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: ከድርሰቶቹም ቅዳሴው: ድርሳነ ቄርሎስና ተረፈ ቄርሎስ ይጠቀሳሉ::
† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቶቻችን ጸሎት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን:: ከሊቁም በረከቱን ይክፈለን::
🕊
[ † ሐምሌ ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ [ዓምደ ሃይማኖት]
፪. ቅዱስ ክልስቲያኖስ ዘሮሜ [ታላቅ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት]
፫. አባ ሉቅያስ ኤዺስ ቆዾስ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
† " የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ:: የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው:: ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ: እስከ ዘለዓለምም ያው ነው:: ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምሕርት አትወሰዱ:: ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም:: በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና:: " † [ዕብ.፲፫፥፯]