ዕርገተ እግዚእ
እንኳን ለጌታችን በዓለ ዕርገት ሐሙስ ግንቦት 21/2011ዓ.ም. አደረሳችሁ፥ አደረሰን፤ በዓሉን የሚመለከት ጽሑፍና ሥርዐተ ማኅሌቱን እንደተለመደው አቅርበንላችኋል፡፡ መልካም ንባብ፤ መልካም የምሥጋና ማኅሌት፡፡
‹‹አልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለመሕያው፤ ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡›› ዮሐ.3፥13
ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ይህ ኃይለ ቃል ክብር ምስጋና ይግባውና ስለጌታችን፣ አምላካችን፣ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት መውረድ ከድንግል ማርያም መወለድ እና የሰውነቱን ሥራ ጨርሶ በክብር ወደ ሰማይ ማረጉን የሚገልጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው አምላካችን ስለሁለት ዐቢይ ጉዳዮች ሰው ሆኗል፡፡
1. *ለቤዛነት /ዓለምን ለማዳን/
2. *ለአርአያነት /ምሳሌነት/
የሰውን ልጅ በመውደዱ ልዑል ባሕርዩን ዝቅ አድርጎ ከሰማይ ወረደ ሥጋ ለበሰ በምድር ላይ ተመላለሰ፤ ምድርን በኪደተ እግሩ ቀደሰ፤ ድውያንን ፈወሰ፤ ፍጹም ሰው እንደ መሆኑ ተራበ ፍጹም አምላክ መሆኑንም ያስረዳ ዘንድ አምስት ገበያ ሕዝብ በአምስት እንጀራ በሁለት ዓሣ አጠገበ ማቴ.14፥19 ለእኛ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ ዮሐ.13፥14 እኛም ፍለጋውን እንከተል ዘንድ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ለቢጽክሙ እናንተም ለባልንጀሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉ ብሎ አዘዘ፡፡ መምሕረ ትሕትና ነውና በዚህ ዓይነት መልኩ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በዚህ ዓለም ኖረ ለሐዋርያት ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን አስተማራቸው ትምህርት በሚገባ ከተረዳለት በኋላ ለድኅነተ ዓለም በማዕከለ ምድር በቀራንዮ ተሰቀለ፡፡
#ወገብረ_መድኀኒተ_በማዕከለ_ምድር_እንዲል_በምድር_መካከል_መድኀኒትን_አደረገ_መዝ.73፥12
‹‹እስመ ኢይደልዎ ለነቢይ መዊት በአፍአ ዘእንበለ በኢየሩሳሌም፤ ነቢይ በኢየሩሳሌም ነው እንጂ በውጭ ሊሞት አይገባውም፡፡›› ብሎ እንደተናገረ፡፡ ሉቃ.13፥33 በሞቱ ዓለምን አድኖ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጾ ተነሣ፡፡ ነቢያት እንደተናገሩ ‹‹እግዚአብሔር ይነሣል ጠላቶቹም ይበተናሉ››� መዝ.67፥1 ‹‹እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁ እግዚአብሔርም አስነሥቶኛልና ተነሣሁ፡፡›› መዝ.3፥5 ‹‹እግዚአብሔር አሁን እነሣለሁ ይላል መድኀኒትንም አደርጋለሁ በዕለቱም እገለጣለሁ››� መዝ.11፥5፡፡
‹‹ሥጋየ ደግሞ በተስፋ /በትንሣኤ/ ታድራለች ነፍሴን በሲዖል /በመቃብር/ አትተዋትምና/ እነሣለሁ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም፡፡›› መዝ.15፥9 ‹‹አቤቱ ንቃ ለምንስ ትተኛለህ ተነሥ ለዘወትርም አትጣለን›› መዝ.43፥23 ‹‹እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ›› መዝ.77፥65 ተብሎ የተተነበየውን ትንቢት ፈጽሞ ተነሣ፡፡ በሞቱ ሞታችንን ሻረልን፤ በመቀበሩም ሙስና መቃብርን አጠፋልን፡፡ ‹‹በሞቱ ሞትን አጠፋው›› እንዲል መጽሐፈ ኪዳን፡፡ ሕንፃ መነኮሳት ‹እርሱ በሁሉ ምሉዕ ሲሆን በመቃብር ለመቀበር ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘውት ታየ፡፡ ከመሬት ውስጥ በመቀበሩም ሙስና መቃብርን አጠፋ፤ ከሥሩም ነቀለው ከተነሣ በኋላ ትንሣኤውን መጀመሪያ ለማርያም መግደላዊት ገለጸ ማር.16፥9፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ትንሣኤው ሲመሰክር ‹‹ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረም፤ መጽሐፍ እንደሚል፤ በሦስተኛው ቀን ተነሣ፡፡ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፡፡ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ›› 1ቆሮ.15፥3-8 ብሎ ክርስቶስ ትንሣኤውን ለተከታዮቹ በሙሉ የገለጠ መሆኑን መስክሯል፡፡ የሚያምኑ ፈሪሳውያንም ‹‹ትንሣኤው ምትሐት ነው›› እንዳይሉ እየታየ እያስተማረ እስከ 40 ቀን ድረስ መቆየቱን ይገልጽልና፡፡ በዚህም የአርባ ቀን ከትንሣኤ በኋላ ቆይታው ሦስት ቀን ጉባኤ አድርጎ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛ ጊዜ ነበረ እንዲል ዮሐ.21፥14 ይህንም ሊቃውንት አባቶቻችን፡-
1. *የትንሣኤ
2. *የአግብኦተ ግብር /ዳግም ትንሣኤ/
3. *የጥብርያዶስ ነው ብለው አስቀምጠውታል በዚህ 40 ቀን ቆይታ መጽሐፈ ኪዳንን ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም ዕርገቱን ለመናገር ከሰማየ ሰማያት መውረዱን አስቀድሞ ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ማንም ወደ ሰማይ የወጣ የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው ብሎ ከዕርገቱ በኋላ በየማነ አብ፤ በዘባነ ኪሩብ በአምላክነት ሥልጣን ለመኖር ወደሰማይ የወጣ ከእርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ አስረግጦ ነገረን፡፡ ሲጀምር ከሰማይ መውረዱን ማስቀደሙ ወረደ ብሎ ዐረገ ለማለት ይመቻል፡፡ ተጸነሰ ተወለደ ለማለት ጥንቱ ከሰማያት ወረደ ማለት እንደሆነ ሁሉ፤ ‹‹ተሰቀለ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ ተነሣ'››ለማለት ‹‹ጥንቱ:- ተጸነሰ፤ ተወለደ፤ አደገ ተመላለሰ ሠላሳ ዓመት ኖረ›› የሚለው ነው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ዮሐንስ ጠርዝና ጠርዙን ይዞ ተናገረ፡፡ ‹‹ወረደ ዐረገ›› የሚሉት ሁለት ቃላት የዓለም ድኅነት መነሻና መድረሻ ናቸው፤ እነዚህን ሁለት ቃላት ስናይ በሁለቱ መካከል የተፈጸሙትን የአምላክ ሥራዎች ልብ ማለት ይገባል፡፡ ቤት በመሠረት ይጀመራል በጣሪያ ይፈጸማል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ይህን የቤዛነት ሥራ ሲያስረዳ በዮሐ.1፥14 ‹‹ቃል ሥጋ ኮነ፤� ቃል ሥጋ ሆነ›› ብሎ ጀምሯል ይህንም ቃል ‹‹ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም›› በማለት ሰው መሆኑን ብቻ ሳይሆን በአርያም የሚኖር መሆኑን አስተማረን፡፡ እንግዲህ ጌታችን ዕርገት እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አለመሆኑን ቀድሞ በነቢያት የተነገረ ኋላም በሐዋርያት የተመሰከረ መሆኑን ማወቅ ያስፈለጋል፡፡
#የክርስቶስ_ዕርገት_በትንቢተ_ነቢያት
‹‹ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም ጨለማ /ዲያብሎስ/ ከእግሩ በታች ነበር በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ በነፍሳትም ክንፍ በረረ››� መዝ.17፥9 ‹‹አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ መዝ.46፥5 ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ ፥ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ›› መዝ.67፥18፡፡
‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ፤ በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ›› መዝ.67፥33፡፡
#የክርስቶስ_ዕርገት_በትምህርተ_ሐዋርያት
ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ማር.16፥19 ‹‹እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡››� ሉቃ.24፥50 ‹‹ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው፤ እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ ለብሰው ሁለት ሰዎች /መላእክት/ በአጠገባቸው ቆሙ ደግሞም ‹‹የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት ዳግመኛ ይመጣል፡፡›› አሏቸው››� ሐዋ.1፥9-12 በማለት ሐዋርያት የክርስቶስን ዕርገት ከመላእክት ጋር ሆነው

እንደተመለከቱ ደስታውን እንደተካፈሉ ቅዱስ ሉቃስ ጽፎልናል፡፡ በትንሣኤው ነጭ ልብስ ለብሰው የታዩ መላእክት የደስታ ዘመን ነው ሲሉ በእርገቱም ነጭ ልብስ ለብሰው የዕርገቱን የምሥራች ለሐዋርያት አብስረዋል፡፡
/ምንጭ፤ የቃል ትምህርትና በመምህር ምሥጢረ ሥሳሴ ማናየ/
የአምላካችን ቸርነቱ ረድኤቱ አይለየን፡፡፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠
@EotcLibilery

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ አካሂዷል፡፡
የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና እድገት፣ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋትና ለመንፈሳዊ ልዕልና ልዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ መስጠት፣ ምትክ ለሌለው የሰው ልጅ ሕይወት ባለአደራ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላም ያለማቋረጥ መጸለይ፣ ጸሎተ ምሕላ ማወጅ፣ የሰላምና የአንድነት ጥሪ ማስተላለፉ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሰላምና ለአንድነት ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሁሉን አቀፍ ሥራ የሚሠሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ኮሚቴ” በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
ኮሚቴውም ዘላቂ ሰላምንና አንድነትን ለማስፈን፣ የዜጎችን ሕይወት እየነጠቀ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥረት እንዲያደርግ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ባካተተ መልኩ በየደረጃው የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና፣ ውይይቶችንና የጥናት መድረኮችን እንዲያዘጋጅ፤ አፈጻጸሙንም በየሦስት ወሩ ለቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት እንዲያደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
2. ለሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የትርጓሜ መጻሕፍትና የሴሚናሪ ደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት ዲግሪ እንዲሆን በተወሰነው መሠረት በመማር ላይ ያሉትና በቀድሞው ሥርዓተ ትምህርት ተምረው በመመረቅ ቤተ ክርስቲያናችንን በማገልገል ላይ የሚገኙት ምሩቃን ተጓዳኝ ትምህርቱን ተምረው ዲግሪያቸውን ማግኘት እንዲችሉ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ እንዲደረግ፣ በኮሌጁ የተጀመረው ሁለገብ ሕንፃም በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እንዲጠናቀቅ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3. በገዳማት አስተዳደር መምሪያ አስፈጻሚነት የተደረገው የአንድነት ገዳማት ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ በየዓመቱ እንዲካሄድና የአቋም መግለጫው ላይ የቀረቡት ሐሳቦች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በኩል እየታዩ በቅደም ተከተል እንዲፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስልፏል፡፡
4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችን እድገትና ሥልጣኔ ፈር ቀዳጅ በመሆን ያበረከተችው አስተዋጽኦ በታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ጉልህነት ያለው ሲሆን፣ አሁንም እየተሠራ ባለው የኮሪደር ልማት መርሐ ግብር ላይ ኃላፊነቷን እየተወጣች ትገኛለች፡፡
ይኽን ቋሚ ታሪክ ያልዘነጋው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ለግንባታ በሚያመች ሁኔታ አሰባስቦ በመስጠት ለፈረሱ ቤቶች ካሣ በመክፈል፣ በጽርሐ ምኒልክ ሕንጻ ምትክ በነባሩ ቦታ ላይ B+G+4+ቴራስ በመንግሥት በጀት መልሶ እንዲገነባ በማድረጋቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
በይዞታዎቻችንም ላይ ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ ለማካሄድ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተሰይሞ ገቢ የማሰባሰብ ሥራው በሕጋዊ መንገድ እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም በፈረሱት ቤቶች ምትክ የተረከብናቸውን ክፍት ቦታዎች በአጭር ጊዜ ማልማት ግዴታ ስለሆነ በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እንደ አባቶቻችሁ የታሪክ ባለቤቶች ትሆኑ ዘንድ ልማቱን በገንዘብና በእውቀት እንድታግዙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
5. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተፈጠረውን የአስተዳደር ችግር አስመልክቶ በብፁዓን አባቶች የሚመራው አጣሪ ልዑክ ባቀረበው ሪፖርት መሠረት ውይይት በማድረግና የሥራ ኃላፊዎቹን በማንሣት ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
ወደፊትም በየደረጃው ያለውን ችግር ማስተካከል ይቻል ዘንድ ችግሩን እያጠና የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ምልአተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
6. ዝክረ ኒቅያ በሚል መሪ ቃል ከመላው ሀገራችን በተወከሉ የምስክር ጉባኤ ቤቶች መምህራን በተካሄደው ጉባኤና የጥናት ውይይት የቀረበው ምክረ ሐሳብ እጅግ የሚጠቅም የሊቃውንት ድምጽ በመሆኑ በነገረ ማርያም፣ በነገረ ክርስቶስና በሌሎችም አስተምህሮዎች ዙሪያ የተሰጡት ሐሳቦች የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜን መሠረት በማድረግ ተብራርቶና ተስተካክሎ፣ የጎደለው ሞልቶ፣ የጠመመው ተቃንቶ በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በመጽሐፍ መልክ እንዲታተም፣ በሚዲያ ሊተላለፍ የሚገባው አስተምህሮ ደግሞ በሊቃውንት ጉባኤ ብቻ እንዲተላለፍ፣
የሊቃውንት ጉባኤውም በተሟላ የሰው ኃይልና በጀት ተጠናክሮ እንዲደራጅ፣ ሀገር አቀፍ ጉባኤው በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲደረግና የጉባኤው መዋቅር በየአህጉረ ስብከቱ እንዲጠናከር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
7. የመናገሻ አምባ ማርያምና የጋራው ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም ጥንታዊ የሆነ ሰፊ ታሪክ ያለው በመሆኑ ሁለቱ ገዳማት በአንድ አበምኔት በአንድነት ገዳም ሥርዓት በጋራ እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
8. በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት መነኰሳትን ከመላክ ጀምሮ፣በአስተዳደራዊና ቀኖናዊ አሠራር ክፍተት ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን በማረምና ሊቀ ጳጳሱን በማዛወር ማእከላዊ መዋቅር እንዲጠበቅ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን፣ ነባሩ መተዳደሪያ ደንብ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ሰይሟል፤
9. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ልቡና፣ በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል ያገኘቻቸው ዶግማዊ፣ ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሀብቶቿ የሕግ ጥበቃና ከለላ አግኝተው ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊና ሁለንተናዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ ተከብረውና ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
10. የ2018 ዓ.ም የመደበኛ እና የካፒታል ዓመታዊ በጀት ብር 5,407,415,607.25/አምስት ቢሊየን አራት መቶ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ዐሥራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር ከሃያ አምስት ሣንቲም/እንዲሆንና የበጀት አርዕስቱ ተጠብቆ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
11. በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ሕንጻ በተመለከተ የተፈጠረው የአሠራር ግድፈት እንዲታረም፣ ዩኒቨርስቲው ከባንክ ጋር የገባው የብድር ውል እንዲቋረጥና የተጀመረውን ሕንፃ በራሱ አቅም እንዲገነባ ሆኖ፤ የቤተ ክርስቲያናችንን አንጡራ ሀብት ማለትም ሕንጻዎችን፣ መሬቶችንና ሌሎች ቋሚ ንብረቶችን በማስያዝ የሚደረጉ ብድሮች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ የሚያደርግ መመሪያ ለሁሉም አህጉረ ስብከት እንዲተላለፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
12. የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅትን አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት መሠረት የሥራ ክፍተቱን በማረም በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች እንደየጥፋታቸው እንዲጠየቁና እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

13. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምርጫን አስመልክቶ በሥራ ላይ የነበሩት ብፁዓን አባቶች የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ በመሆኑ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚሠሩ ብፁዓን አባቶችን ለመምረጥ ዕጩዎችን የሚያቀርቡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመሰየም ምልዓተ ጉባኤው ተገቢውን ምርጫ አከናውኗል፡፡
በዚሁም መሠረት ፡-
*. ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ በደቡባዊ ዞን ማይጨው፣ የደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን መርጦ ሰይሟል
*. ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪጅነት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣የሸገር ከተማ እና የምስካዬ ኀዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስን መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀድያና ስልጤ አህጉረ ሰብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሜኖሶታና የኮሎራዶ አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መድቧል፡፡
14. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ሰብከት ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካልፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሚዲያ ያስተላለፏቸው ትምህርቶች ስሕተትና ነቀፋ ያለባቸው መሆናቸውን አምነው ቅዱስ ሲኖዶስንና መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታ በመጠየቅ ሊቃውንት ጉባኤ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቅስ ያቀረበውን አስተምህሮ የተማሩት የሚያምኑትና የሚያስተምሩት መሆኑን በመግለጻቸው ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስቱን አባቶች ይቅርታ ተቀብሎ ወደፊት እንዲህ ዐይነት የስሕተት ትምህርት ውስጥ እንዳይገኙና ነቀፋ ያለበትን ትምህርታቸውን በማረምና በማስተካከል ርቱዕ የሆነውን የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ሥርጭት ድርጅት በመቅረብ ትምህርት እንዲሰጡ በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
15. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ በግልና በቡድን ተደራጅተው ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመክፈት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር በወጣ መልኩ የቤተ ክርስቲያናችንን ልዕልና የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር የሚጋፋ ፣የአባቶችንና የአገልጋዮችን ተልእኮ የሚያደናቀፍ ያልተገባና መሠረት የሌለው መግለጫ የሚያሰራጩ አካላት እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዴየና ለመጨረሻ ጊዜ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
በመጨረሻም በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታየው ግጭትና መፈናቀል ተወግዶ፣የሰው ልጅ የመኖርና የመዘዋወር መብት ተከብሮ፣ ሰብዓዊ ክብሩ ተጠብቆ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በጋራ እንዲኖር፤ አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡
ግጭት፣ ጥላቻና ደም መፋሰስ፣ አካል ከማጉደልና ንብረት ከማጥፋት በቀር የሚያመጡት ክብርና ዘላቂ ሰላም ስለሌለ ልጆቻችን ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንድትፈቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ደጋግሞ ጥሪውን በማቅረብ በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላምና ዕርቅ እንዲሰፍን በመጸለይ ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ዓመታዊ ጉባኤውን በጸሎት አጠናቋል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

‘‘ትዳር‘‘ በርእሰ ሊቃውንት ቆሞስ አ...
EOTC Germany Archdiocese የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት
✝ትዳር✝
Size:-61.2MB
Length:-1:06:04
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
Size:-61.2MB
Length:-1:06:04
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
“ ካህኑን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ተገድለዋል። ሁለት ሰዎች ቆስለዋል ” - የሟች ቤተሰብና ነዋሪ
በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ልዩ ቦታው አንጎዶቼ ሁላ አርቦዬ ከተማ ባለወልድ ቤተክርስቲያን አካባቢ የደብሩን ኃላፊ ካህን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ፣ ሁለት መቁሰላቸውን የሟች ቤተሰብና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።
የሟች ካህን ቤተሰብ በሰጡን ቃል፣ “ትላንት 11ሰዓት ከአርቦዩ ገበያ ውለው ሲመለሱ እቤት ገባ ብሎ እንደወጣ ነው ከቤቱ አውጥተው ይዘውት ሂደው መኪና መንገድ ዳር የገደሉት” ብለዋል።
“ አንደኛውንም በሩ ላይ ነው የገደሉት። አንደኛውንም ከብቶች ሲነዱበት ‘ከብቶቹን ተውሉኝ’ ሲል እዛው ነው የገደሉት። ሦስቱንም እዛው ነው የገደሏቸው ” ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
“ ሟቹ ካህን ነው። ቀሲስ ተስፋ አለው ይባላል” ያሉ ሲሆን፣ የገዳዮቹን ማንነት በተመለከተ “ 'ሸኔ ናቸው' ነው የሚባለው ” ብለዋል።
ሟቾቹ ልጆች እንዳሏቸው፣ ካህኑም የአንጎዶቼ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን አገልጋይ፣ የሁለት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች አባት እንደነበሩ ተናግረዋል።
“ ከሟቾች ባሸገር አቶ ድንቁ ኃይሌ የሚባል የተመታ አለ፤ ሌሎች የት እንደደረሱ ያልታወቁ አሉ” ያሉት የሟች ቤተሰብ፣ “ከ15 ቀናት በፊት አንዲት ሴት ተገድላለች። አምስት ልጆች አግተው ወስደዋል” ሲሉም አስታውሰዋል።
አጋቾቹ አምስቱን ታጋቾች ገንዘብ እየተቀበሉ እንደመለሷቸው አስረድተው፣ “ገዳዮቹ ትላንትም ሦስቱን ሰዎች ከገደሏቸው በኋላ መከላከያዎች ገብተው ወዲያው ለቀው ወጡ፤ እነሱ ከወጡ በኋላ ሌሊት ስድስት ሰዓት ተመልሰው ከብትም፣ ገንዘብም ከሰው ላይ ወስደዋል ” ነው ያሉት።
አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው፣ “ ከአዳማ ወጣ ብሎ አርቦየ የምትባል ከተማ አለች፤ እዛ መሰመር ላይ ካህን አባትና ሌሎች ሰዎች ተገድለዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
“ ቀሲስ ተስፉ አለሙ፣ ጎረቤቶቻው አቶ በጋሻው ስዩም፣ አቶ ክፍሌ ገ/ክርስቶስ ተገለዋል። ሁለት ሰዎች ቆስለዋል። የቀብር ሥርዓታቸው ዛሬ 28/09/2017 ከቀኑ ሰባት ስዓት በደብሩ ተፈጽሟል። የተገደሉት ትላንት ማታ ነው ” ብለዋል።
“ መንግስት ዝቅ ብሎ ቢያየን፤ ቢመለከትን መፍትሄ ይመጣል ” ሲሉ ነዋሪዎቹ ያሳሰቡ ሲሆን፣ ከክልሉ ባለስልጣናት ምላሽ ለማግኘት ብንሞክርም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

የወርቅ መሰላል፥ ምሥጢር እና ትርጓሜ፥...
EOTC Germany Archdiocese የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት
✝የወርቅ መሠላል✝
Size:-132.4MB
Length:-2:23:00
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Size:-132.4MB
Length:-2:23:00
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
፲፬ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የቃለ ጉባኤ ማጠቃለያ እና የጋራ የውሳኔ ሐሳብ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፲፬ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ግንቦት 30 እና ሰኔ 1/ 2017 ዓ.ም ከየአህጉረ ስብከቱ የተወከሉ የሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ የዐዲስ አበባ ሀ/ስብከት አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተካሔዷል። በመሆኑም በጉባኤው ከቀረቡ ዓመታዊ ሪፖርቶች፣ ተዘጋጅተው ከቀረቡ ጥናታዊ ሰነዶች፣ ከየአህጉረ ስብከት ከቀረቡ አስተያየቶች እና ከጉባኤው ተሳታፊዎች ከተነሡ የውይይት ሐሳቦች ግብዓት በመነሣት ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
1.በጠቅላላ ጉባኤው የቀረበውን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትና የአህጉረ ስብከት አንድነቶች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የተሰጡ የሥራ አቅጣጫዎችን ጠቅላላ ጉባኤው ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን የሰንበት ት/ቤቶች የ5 ዓመት መሪ ዕቅድ አፈጻጸም በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ጉባኤው ወስኗል።
2.በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀው መሪ ዕቅድን በተመለከተ በትኩረት የምንከታተለውና የብዙ ምሁራን ጊዜ፣ ዕውቀትና ጉልበት የፈሰሰበት ሥራ ወደ ተፈለገው ውጤት እንዳይመጣ የሚደረገው የማሰናከል ሥራ በእጅጉ ያሳዘነን ከመሆኑም ባሻገር እናት ቤተ ክርስቲያናችን ዘመኑን የዋጀ ስልታዊ አካሔድ እንዳትከተል አሉታዊ ተጽዕኖ እና ከፍተኛ ሥጋት አሳድሯል። የመሪ ዕቅድ ትግበራውን በተያዘበት አግባብ ማፋጠን፣ የሊቃውንቱ፣ የካህናት የምእመናን የሰ/ት/ቤት አባላትና ባለድርሻ አካላትን ሚና በሕግ ማውጣት ሥራ ላይ ከፍ እንዲል በአጽንዖት እንጠይቃለን።
3.በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር በቃለ ዐዋዲ የተደነገገው የምእመናን፣ የካህናትና የሰንበት ት/ቤቶች ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ሊኖራቸው የሚገባ የሰበካ ጉባኤ ሱታፌ በጽኑዕ እንዲተገበር እንዲሁም የሰ/ት/ቤት አባላት በጊዜ በጉልበትና በዕውቀት ከሚሰጡት የጎላ አስተዋጽዖ አንጻር ውክልናችን በቁጥር ከፍ እንዲል አበክረን እንጠይቃለን።
4.ልዩ ልዩ የአስተዳደርና የቀኖና ጥሰት እየተፈጸመ የቅድስት ቤተክርስቲያን አንድነቷ እንዲሸረሸር የሚደረጉ ድርጊቶችን በጽኑዕ እንቃወማለን። የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና እንዲከበር፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲጸና፣ መለያየት እንዲወገድ ፣በዚህም የተፈጠሩ ልዩነቶች ተቀራርቦ በመነጋገርና የበደለ ክሶ፤ ያጠፋ በቀኖና ታርሞ እንዲስተካከሉ፣ በሀገር ሰላምና አንድነት ላይም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቀደመ ሚናዋን እንድትወጣ እንጠይቃለን።
5.በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው የሀብት ሥርጭት ፍትሐዊነት መጉደል ቤተ ክርስቲያን ከገጠር ወደ ከተማ እየተሰደደች መሆኗ በግልጽ የሚታይ በመሆኑ ለዚህ ችግር ትኩረት በመስጠት የአጥቢያ ዐቢይ ጉባኤን በማደራጀት ወደ ሥራ እንዲገባ እና በተደጋጋሚ እንደሚነሣው የፋይናንስ አስተዳደሩን የተማከለ የሚደረግበት ሥርዓት እንዲዘረጋ እንጠይቃለን።
6. አብዛኛው የቤተ ክርስቲያኗ ሀብት የሚመነጨው አጥቢያ ላይ በመሆኑ አስፈጻሚ አካላት ገንዘብ መልቀምና መጠበቅ ላይ በሀብት ምደባም ይሁን ለአስተዳደር ሥራ ብቻ ትኩረት በማድረጋቸው ሕፃናትን የማሠማራት፣ ወጣቶችንና ምእመናንን የመጠበቅ ሥራው በአብዛኛው ተዘንግቷል፣ ስለዚኽ ይኽ ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲስተካከል እንጠይቃለን።
7.የሰንበት ትምህርት ቤቶች መዋቅር የበጀት ዕጥረት ከፍተኛ በመኾኑ፣ ሥርዓተ ትምህርቱን ማስፈጸም፣ የመጽሐፍ ስርጭቱንና ሌሎችንም ዘርፈ ብዙ የሰንበት ትምህርት ቤት ሥራዎች ከፍተኛ እንቅፋት በመፍጠሩ መፍትሔ እንዲሰጠው እንጠይቃለን።
8.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የጠነከረ የኢኮኖሚ አቅምና ማኅበራዊ መስተጋብር ፈጥረው ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁና ለሀገርም ረብ ያለው ነገር ማበርከት እንዲችሉ የማድረግ ሚናዋን ዘንግታለች፣ ስለዚህም ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በቂ ሀብት በመመደብና ተገቢ አመራር በመስጠት በአባላት ሁለንተናዊ ሕይወት ዙሪያ አስፈላጊ ለውጥ ማምጣት እንዲቻል ጥረት ይደረግ ዘንድ በአጽንዖት እንጠይቃለን።
9.የሰንበት ት/ቤቶችም ኾነ ሌሎች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን የቅርብ ክትትል የሚፈልግ ኾኖ እያለ ሀገረ ስብከቶቻቸውን በዓመት ለውስን ጊዜያት አንዳንዴም አንዴ ብቻ በሚጎበኙ ሊቃነ ጳጳሳት የተነሣ አገልግሎቶች እየታወኩ ይገኛሉ፤ ስለዚህ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳቱ ሀገረ ስብከቶቻቸውን በተገቢው መልኩ እንዲከታተሉ የሚመለከተው አካል ተገቢ ቁጥጥር እንዲያደርግ በአጽንዖት እንጠይቃለን።
10.የሰንበት ት/ቤቶች ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነቶች ተወካዮች ተሰባስበው የሚመክሩበት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚወያዩበት ቀጣይ ሥራዎች የሚተልሙበት ጉባኤ ነው። ይኽ ጉባኤ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ከቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ከሌሎች የሥራ ሓላፊዎች ጋር የሚወያዩበትም ጭምር ነው። ይኹን እንጂ ይኽ ጉዳይ በትክክል ተፈጻሚ እየሆነ አይደለም። ስለዚኽ ይኽ ጉባኤ ከዚህ በኋላ የሚካሔዱ ጠቅላላ ጉባኤያት በቅዱስ ፓትርያርኩ ጸሎተ ቡራኬ ተከፍቶ፤ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቃለ ምዕዳን የሚዘጋ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም ተገኝተው የሚመሯቸው እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎች እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ተገኝተው የሰ/ት/ቤቶችን ጉዳይ በሓላፊነት የሚከታተሉባቸው እንዲኾኑ በአጽንዖት እንጠይቃለን።
11.. በዚኸ ጉባኤ ላይ በተለያዩ ምከንያቶች ያልተገኙ የአህጉረ ስብከት ተወካዮች እንዳሉ ቢታወቅም በተለይ ግን በትግራይ ከልል ከሚገኙ አህጉረ ስብከት ጋር በተፈጠረዉ እጅግ አሳዛኝ መለያየት የተነሣ የክልሉ አህጉረ ስብከት ተወካይ ወንድሞች እና እኅቶች ባለመገኘታቸዉ ጉባኤው ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶታል። ከዚህም በላይ ችግሩ ወደ ምእመናን እየሰፋ መሔዱ ጉባኤውን በእጅጉ አሳስቦታል፡፡ በ13ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አበክረን፣ ከወንበራችን በመነሣት በልመናና በልጅነት መንፈስ መፍትሔ እንዲያገኝ ብንጠይቅም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ባለማየታችንና ይኸ መለያየት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ሔዶ በአንዲቷ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ አደጋና የማይጠገን ስብራት እያደረሰ በመሆኑ ልዩነቶችን አስወግዶ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አግባብ የክልል ትግራይ አህጉረ ስብከት ወደ መዋቅራቸው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ይመለሱ ዘንድ፤ በእኛ በኩል የተቻለንን ኹሉ እንደምናደርግ ቃል በመግባት አሁንም ችግሩን ለመፍታትና እርቀ ሰላሙን ለማምጣት ከፍተኛዉን ድርሻ ሊወጡ የሚችሉት ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን እንደኾኑ እናምናለን፡፡ ይኽንኑ ለመፈጸም ቅዱስነትዎ ቃል ይገቡልን ዘንድ የቤተ ክርስቲያን ልደት ተብሎ በሚታወቀው በዛሬው በዓለ ጰራቅሊጦስ ስም ልክ እንደ አምናው ኹሉ ከመቀመጫችን በመነሣት በታላቅ አከብሮት እና ትሕትና እንጠይቃለን።
12.እነዚህ የ14ኛው ሀገር ዐቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የጋራ የውሳኔ ሐሳብ በቀጣይ የሲኖዶስ ስብሰባ አጀንዳዎች እንዲሆኑ አበክረን እንጠይቃለን።
ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

Audio
✝ያሉበትን ቤት ሁሉ ሞላው✝
በዓለ መንፈስ ቅዱስ
Size:-28MB
Length:-1:20:27
በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በዓለ መንፈስ ቅዱስ
Size:-28MB
Length:-1:20:27
በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሰባቱ መንጦላይት ወዴት ተጋረዱ
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት
በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት
አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ
ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ
ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው
መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ = = = = =
ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ
ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ
ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር
ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ = = = = =
እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ
ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ
ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት
ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ = = = = =
ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና
ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና
ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ
በመሰወሪያው ቀኝ ከልጅሽም ሊደርስ
ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል
መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል
በዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሀኑ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት
በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት
አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ
ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ
ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው
መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ = = = = =
ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ
ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ
ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር
ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ = = = = =
እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ
ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ
ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት
ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ = = = = =
ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና
ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና
ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ
በመሰወሪያው ቀኝ ከልጅሽም ሊደርስ
ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል
መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል
በዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሀኑ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from የመጻሕፍት ዓለም (𝕄𝕖ም𝕟𝕠𝕟 ✨)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዜና ሹመት
ብፀዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለተለያዩ የሥራ ኀላፊዎች ሹመቶችን ሰጡ።
( ሰኔ 09 2017 ዓ.ም)
በዛሬው ዕለት ብፀዕ አቡነ ሳዊሮስ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለመምሪያ ኀላፊዎች ዝውውር እና ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኀላፊዎች ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዚህም መሠረት፦
፩ኛ. መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ከጠቅላይ ቤተክህነት ቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ወደ ጠ/ቤ/ክህነት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ፤
፪ኛ. መ/ር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ ከጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር መምሪያ ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት EOTC TV ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
፫ኛ. ሊ/መ ሐረገወይን ጫኔ ከሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር መምሪያ፤
፬ ዶ/ር አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ ከጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ወደ ጠ/ቤ/ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ፤
፭ኛ. መ/ር ምትኩ ከንቲባ ከጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል መምሪያ ተዘዋዋሪ ሰባኪነት ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት የቅርሳቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ፤
፮ኛ. ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን ሥርጭት ድርጅት ወደ ቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ተዛውረው እንዲሠሩ ተመድበዋል።
በሌላ በኩል ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ጨምሮ የተወሰኑ አዳዲስ ዋና ክፍሎችን በመምረጥ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ፊርማ እንዲመደቡ አድርገዋል።
በዚህም መሠረት፦
፩ኛ. መ/ም አባ ገ/መድኅን ንጉሤ ከም/ሸዋ ሀገረ ስብከት ወደ ከዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተዛውረው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።
፪ኛ. መ/አእላፍ ማሙዬ ሸዋፈራው ከጠቅላይ ቤተክህነት ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ምክትል ኀላፊ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ፤
፫ኛ. መምህር አስናቀ ሸዋዬ ከጠቅላይ ቤተክህነት ቁጥጥር መምሪያ ተቆጣጣሪነት ወደ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከ ሂሳብ እና በጀት ዋና ኃላፊ፤
፬ኛ. ሊ/ኅሩያን ባዩ ተዘራ ከአዲስ ከተማ ቂርቆስ ልደታ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት የሰንበት ትምህር ቤቶች ክፍል ኀላፊ ወደ የሀ/ስብከቱ የሰው ኀይል አስተዳደር ዋና ክፍል ኀላፊ፤
፭ኛ. መ/ሰላም ጽጌ ከበረ ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የማኅበራት ማደራጃ ዋና ክፍል ኀላፊ፤
፮ኛ. ሊቀ ሥልጣናት አባ ጥዑመ ልሳን ኪዳነ ማርያም ከመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት ዋና ክፍል ኀላፊ፤
፯ኛ. መ/ስብሐት ዐቢይ ዘለቀ ከቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተዛውረው የሀገረ ስብከቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ጸሐፊ ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።
መረጃው፡-የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኘነት መምሪያ ነው፡፡

#ሰኔ_፲፪ በዓለ ተዝካሩ #ለቅዱስ_ሚካኤል ሊቀ መላእክት #ወቅዱስ_ላሊበላ
#ቅዱስ_ሚካኤል_አፎምያንና_ባሕራንን_ያዳነበት_እለእስክንድሮስ_ቅዳሴ_ቤቱን_ያከበረበትና_የቅዱስ_ላሊበላ_ዕረፍቱ_ነው፡፡
#ሰኔ_፲፪ #መከበሩ_ስለምንድን_ነው_ቢሉ_፤
ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር፤ ንሥረ አርያም የሚባል፥ ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፥ ንዑድ ክቡር የሆነ ፥ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው እንዲሁም የሌሎችም ቅዱሳን መታሰቢያ ቀናቸው (ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት) ፡፡ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው እነርሱም፤
#share
፠፩. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል፤
፠፪. ባሕራንን ያዳነበት፤
፠፫. የአስተራኒቆስ ሚስት ቅድስት አፎምያን ያዳነበት፤ በዓለ እረፍቷም በዚሁ እለት ነው፤
፠፬. በግብፅ ሃገር ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረበት፤
፠፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት፤
፠ ሐናፄ መቅደስና በሰማያት ያለ ምሥጢርን የተመለከተ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዓለ ዕረፍቱ ነው፤
፠67ኛ ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት ዘእስክንድርያ እረፍቱ ነው፤
፠የእስክንድርያ 6ኛ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ (ወንጌላዊና ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የክርስትና ጥምቀትን ያጠመቀው፥ ዲቁናና ቅስናን የሾመው) እረፍቱ ነው፡፡
ማብራሪያ፤
#፩. ቅዱስ ሚካኤል በፈቃደ እግዚአብሔር ከዲያብሎስ ጋር ተዋግቶ ያሸነፈበት፤ አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት እለት በመሆኑ ነው፡፡ ቀድሞ ከ100 ነገደ መላእክት ኃይላት የሚባሉ የ10 ነገደ መላእክት አለቃ ነበር፤ በዚህች ቀን ግን የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ አጋእዝት የተባሉትንና ሳጥናኤል(ሰማልያል) ይመራቸው ለነበሩት 10 ነገዶች በተጨማሪ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በአጠቃላይ ለሌሎችም 100 (99ኝ) ነገደ መላአክት አለቃ ሁኗል፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡
#፪. ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት፤ ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312 - 326/ በግብፅ ሃገር ንግሥት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ያሠራችውንና ጣዖት ይመለክበት የነበረውን ቤተ ጣዖትን አፍርሶ በቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በታላቅ ክብር ያከበረበት እለት ነው፡፡
#፫. ባሕራንን ያዳነበት
ሊቀ ጳጳሳት እለ እስክንድሮስ የተሠራውን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ከሚያከብሩ ምእመናንን አንዱ የባሕራን አባት ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር፤ በዚህ ሰው ላይ ላይ ጥላቻ ያደረበትና ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጸጋ ጐረቤት ነበረው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር፡፡
ይህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውም በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ። ሚስቱንም ጠርቶ ‹‹በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመመጽወት ቸል አትበይ! የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ፤ ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው›› አላት፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር። ይህም ደገኛ ሰው በሰላም ዐረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ። ሚስቱም የመውለጃዋ ሰዓት በደረሰ ጊዜ ታላቅ ጭንቅ ላይ ኾነች እርሷም መልአኩን ቅዱስ ሚካኤል እንዲደርስላት ተማጸነችው በሰላምም ተገላገለች፡፡ መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና ‹‹ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል›› አለ። ያን ጊዜ ያ ባለጸጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ሐዘን ተነካ፤ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።
ብላቴናውም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት፡፡ ባለጸጋው እኔ ጋር ተንከባክቤ ላሳድገው ብሎ ከእናቱ ከተቀበለ በኋላ፤ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው፤ እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።
በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያንን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣውና ወደ ቤቱ ወስዶ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው። ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን "ባሕራን" ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ፡፡
ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዐሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ጸጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ፡፡ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ። በግ ጠባቂውንም ‹‹ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው፣ ኪራዩንም እከፍልሃለው›› ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው። ባለጸጋውም ገብቶ ጥቂት ካረፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ ‹‹ልጅህ ነውን?›› ብሎ ጠየቀው። በግ ጠባቂውም ‹‹አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው›› አለው። ባለጸጋውም በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም ስላወቀ ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ፤ ይገድለውም ዘንድ ፈለገ፡፡ በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሐሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን ‹‹ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ›› አለው።
ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ ‹‹ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ›› ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ‹‹እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ›› አለው። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ‹‹ይህችን የመልእክት ደብዳቤ ይዞ ወደ አንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው፤ ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ›› የሚል ጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ፤ በአገልጋዩ (በሹሙ)ና በእርሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው፡፡ ለመንገዱም የሚሆነው ስንቅ ሰጥቶ ላከው።

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ 12 ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡
#፬. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን፤ ወደፊት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽ ጌታችን የነገረውና የሕንጻዎቹን አሠራር ዝርዝር የነገረው በዚሁ እለት ነው፡፡
ባሕራንም መልእክቱን ለማድረስ ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው፡፡ ባሕራንም ‹‹ከአንድ ባለጸጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እርሱን ለማድረስ ዕገሊት ወደምትባል አገር እሄዳለሁ›› አለው። ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም "እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ?" አለው፡፡ ባሕራንም ‹‹ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹እሺ ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ›› አለው፡፡ ባሕራንም አሳየው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በሞቱ ደብዳቤ ላይ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትዕዛዝ ጽፎበታል፡፡ በደብዳቤው ላይ የተጻፈውን የሞት መልእክት ደምስሶ ‹‹ከእኔ ከባለጸጋ ዕገሌ የተጻፈ›› ይልና ‹‹ይህን መልእክት ይዞ ለመጣሰው ዕገሊት የምትባለዋን ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን ፥ በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና፤ በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በእኔና በአንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ›› የሚል ጽሑፍ ጻፈበት "እንግዲህ ወደ ባለጸጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ አለው፤ ባሕራንም ‹‹እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ›› ብሎ ጉዞውን ቀጠለና የዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።
ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለጸጋውን ልጅ አጋባው፣ የሠርጉንም በዓል እስከ ፵ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ። ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለጸጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ "ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው?" ሲል ጠየቀ፡፡
ሰዎቹም ‹‹ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታ፤ እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ፵ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል›› አሉት። ያም ባለጸጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት። ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር። በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ። ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቈጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን፡፡
#፭. አፎምያን ያዳነበት
ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡
ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጕል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፤ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም ፥ በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኵሴ መስሎ አጋንንትን መነኰሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡
እርሷም ‹‹ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ›› አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም ‹‹እኛማ በነግህ ጸልየናል?›› አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን ‹‹...እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ፥ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ፥ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ›› አላት፡፡ ቅድስት አፎምያም ‹‹አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ፥ አትጸልዩ ያልከኝ፤ ጌታ ምጽዋትን መጽውቱ ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? ርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም፤ ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?›› ብላ ሞገተችው፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡
ከላይ እንዳየነው በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡
በሰኔ 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?›› በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ