Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
፲፬ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የቃለ ጉባኤ ማጠቃለያ እና የጋራ የውሳኔ ሐሳብ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፲፬ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ግንቦት 30 እና ሰኔ 1/ 2017 ዓ.ም ከየአህጉረ ስብከቱ የተወከሉ የሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ የዐዲስ አበባ ሀ/ስብከት አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተካሔዷል። በመሆኑም በጉባኤው ከቀረቡ ዓመታዊ ሪፖርቶች፣ ተዘጋጅተው ከቀረቡ ጥናታዊ ሰነዶች፣ ከየአህጉረ ስብከት ከቀረቡ አስተያየቶች እና ከጉባኤው ተሳታፊዎች ከተነሡ የውይይት ሐሳቦች ግብዓት በመነሣት ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡

1.በጠቅላላ ጉባኤው የቀረበውን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትና የአህጉረ ስብከት አንድነቶች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የተሰጡ የሥራ አቅጣጫዎችን ጠቅላላ ጉባኤው ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን የሰንበት ት/ቤቶች የ5 ዓመት መሪ ዕቅድ አፈጻጸም በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ጉባኤው ወስኗል።

2.በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀው መሪ ዕቅድን በተመለከተ በትኩረት የምንከታተለውና የብዙ ምሁራን ጊዜ፣ ዕውቀትና ጉልበት የፈሰሰበት ሥራ ወደ ተፈለገው ውጤት እንዳይመጣ የሚደረገው የማሰናከል ሥራ በእጅጉ ያሳዘነን ከመሆኑም ባሻገር  እናት ቤተ ክርስቲያናችን ዘመኑን የዋጀ ስልታዊ አካሔድ እንዳትከተል አሉታዊ ተጽዕኖ እና ከፍተኛ  ሥጋት አሳድሯል። የመሪ ዕቅድ ትግበራውን በተያዘበት አግባብ ማፋጠን፣ የሊቃውንቱ፣ የካህናት የምእመናን የሰ/ት/ቤት አባላትና ባለድርሻ አካላትን ሚና በሕግ ማውጣት ሥራ ላይ ከፍ እንዲል በአጽንዖት እንጠይቃለን።

3.በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር በቃለ ዐዋዲ የተደነገገው የምእመናን፣ የካህናትና የሰንበት ት/ቤቶች ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ሊኖራቸው የሚገባ የሰበካ ጉባኤ ሱታፌ በጽኑዕ እንዲተገበር እንዲሁም የሰ/ት/ቤት አባላት በጊዜ በጉልበትና በዕውቀት ከሚሰጡት የጎላ አስተዋጽዖ አንጻር ውክልናችን በቁጥር ከፍ እንዲል አበክረን እንጠይቃለን።

4.ልዩ ልዩ የአስተዳደርና የቀኖና ጥሰት እየተፈጸመ የቅድስት ቤተክርስቲያን አንድነቷ እንዲሸረሸር የሚደረጉ ድርጊቶችን በጽኑዕ እንቃወማለን። የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና እንዲከበር፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲጸና፣ መለያየት እንዲወገድ ፣በዚህም የተፈጠሩ ልዩነቶች ተቀራርቦ በመነጋገርና የበደለ ክሶ፤ ያጠፋ በቀኖና ታርሞ እንዲስተካከሉ፣ በሀገር ሰላምና አንድነት ላይም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቀደመ ሚናዋን እንድትወጣ እንጠይቃለን።

5.በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው የሀብት ሥርጭት ፍትሐዊነት መጉደል ቤተ ክርስቲያን ከገጠር ወደ ከተማ እየተሰደደች መሆኗ በግልጽ የሚታይ በመሆኑ ለዚህ ችግር ትኩረት በመስጠት የአጥቢያ ዐቢይ ጉባኤን በማደራጀት ወደ ሥራ እንዲገባ እና በተደጋጋሚ እንደሚነሣው የፋይናንስ አስተዳደሩን የተማከለ የሚደረግበት ሥርዓት እንዲዘረጋ እንጠይቃለን።

6. አብዛኛው የቤተ ክርስቲያኗ ሀብት የሚመነጨው አጥቢያ ላይ በመሆኑ አስፈጻሚ አካላት ገንዘብ መልቀምና መጠበቅ ላይ በሀብት ምደባም ይሁን ለአስተዳደር ሥራ ብቻ ትኩረት በማድረጋቸው ሕፃናትን የማሠማራት፣ ወጣቶችንና ምእመናንን የመጠበቅ ሥራው በአብዛኛው ተዘንግቷል፣ ስለዚኽ ይኽ ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲስተካከል እንጠይቃለን።

7.የሰንበት ትምህርት ቤቶች መዋቅር የበጀት ዕጥረት ከፍተኛ በመኾኑ፣ ሥርዓተ ትምህርቱን ማስፈጸም፣ የመጽሐፍ ስርጭቱንና ሌሎችንም ዘርፈ ብዙ የሰንበት ትምህርት ቤት ሥራዎች ከፍተኛ እንቅፋት በመፍጠሩ መፍትሔ እንዲሰጠው እንጠይቃለን።

8.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የጠነከረ የኢኮኖሚ አቅምና ማኅበራዊ መስተጋብር ፈጥረው ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁና ለሀገርም ረብ ያለው ነገር ማበርከት እንዲችሉ የማድረግ ሚናዋን ዘንግታለች፣ ስለዚህም ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በቂ ሀብት በመመደብና ተገቢ አመራር በመስጠት በአባላት ሁለንተናዊ ሕይወት ዙሪያ አስፈላጊ ለውጥ ማምጣት እንዲቻል ጥረት ይደረግ ዘንድ በአጽንዖት እንጠይቃለን።

9.የሰንበት ት/ቤቶችም ኾነ ሌሎች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የብፁዓን  አበው ሊቃነ ጳጳሳትን የቅርብ ክትትል የሚፈልግ ኾኖ እያለ ሀገረ ስብከቶቻቸውን በዓመት ለውስን ጊዜያት አንዳንዴም አንዴ ብቻ በሚጎበኙ  ሊቃነ ጳጳሳት የተነሣ አገልግሎቶች እየታወኩ ይገኛሉ፤ ስለዚህ ብፁዓን  አበው ሊቃነ ጳጳሳቱ ሀገረ ስብከቶቻቸውን በተገቢው መልኩ እንዲከታተሉ የሚመለከተው አካል ተገቢ ቁጥጥር እንዲያደርግ በአጽንዖት እንጠይቃለን።

10.የሰንበት ት/ቤቶች ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነቶች ተወካዮች ተሰባስበው የሚመክሩበት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚወያዩበት ቀጣይ ሥራዎች የሚተልሙበት ጉባኤ ነው። ይኽ ጉባኤ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ከቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ከብፁዓን  አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ከሌሎች የሥራ ሓላፊዎች ጋር የሚወያዩበትም ጭምር ነው። ይኹን እንጂ ይኽ ጉዳይ በትክክል ተፈጻሚ እየሆነ አይደለም። ስለዚኽ ይኽ ጉባኤ ከዚህ በኋላ የሚካሔዱ ጠቅላላ ጉባኤያት በቅዱስ ፓትርያርኩ ጸሎተ ቡራኬ ተከፍቶ፤ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቃለ ምዕዳን የሚዘጋ፤ ብፁዓን  አበው ሊቃነ ጳጳሳትም ተገኝተው የሚመሯቸው እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎች እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ተገኝተው የሰ/ት/ቤቶችን ጉዳይ በሓላፊነት የሚከታተሉባቸው እንዲኾኑ በአጽንዖት እንጠይቃለን።

11.. በዚኸ ጉባኤ ላይ በተለያዩ ምከንያቶች ያልተገኙ የአህጉረ ስብከት ተወካዮች እንዳሉ ቢታወቅም በተለይ ግን በትግራይ ከልል ከሚገኙ አህጉረ ስብከት ጋር በተፈጠረዉ እጅግ አሳዛኝ መለያየት የተነሣ የክልሉ አህጉረ ስብከት ተወካይ ወንድሞች እና እኅቶች ባለመገኘታቸዉ ጉባኤው ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶታል። ከዚህም በላይ ችግሩ ወደ ምእመናን እየሰፋ መሔዱ ጉባኤውን በእጅጉ አሳስቦታል፡፡ በ13ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አበክረን፣ ከወንበራችን በመነሣት በልመናና በልጅነት መንፈስ መፍትሔ እንዲያገኝ ብንጠይቅም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ባለማየታችንና ይኸ መለያየት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ሔዶ በአንዲቷ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ አደጋና የማይጠገን ስብራት እያደረሰ በመሆኑ ልዩነቶችን አስወግዶ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አግባብ የክልል ትግራይ አህጉረ ስብከት ወደ መዋቅራቸው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ይመለሱ ዘንድ፤ በእኛ በኩል የተቻለንን ኹሉ እንደምናደርግ ቃል በመግባት አሁንም ችግሩን ለመፍታትና እርቀ ሰላሙን ለማምጣት ከፍተኛዉን ድርሻ ሊወጡ የሚችሉት ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን እንደኾኑ እናምናለን፡፡ ይኽንኑ ለመፈጸም ቅዱስነትዎ ቃል ይገቡልን ዘንድ የቤተ ክርስቲያን ልደት ተብሎ በሚታወቀው በዛሬው በዓለ ጰራቅሊጦስ ስም ልክ እንደ አምናው ኹሉ ከመቀመጫችን በመነሣት በታላቅ አከብሮት እና ትሕትና እንጠይቃለን።

12.እነዚህ የ14ኛው ሀገር ዐቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የጋራ የውሳኔ ሐሳብ በቀጣይ የሲኖዶስ ስብሰባ አጀንዳዎች እንዲሆኑ አበክረን እንጠይቃለን።

ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በጣም እናመሰግናለን 50,000k ጉዞ ወደ 100,000k meniber
Audio
ያሉበትን ቤት ሁሉ ሞላው
         በዓለ መንፈስ ቅዱስ
Size:-28MB
Length:-1:20:27

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሰባቱ መንጦላይት ወዴት ተጋረዱ
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት
በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት

አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ
ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ
ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው
መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው
      ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
      ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል

አዝ = = = = =

ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ
ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ
ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር
ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር
       ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
       ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል

አዝ = = = = =

እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ
ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ
ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት
ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት
       ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
       ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል

አዝ = = = = =

ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና
ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና
ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ
በመሰወሪያው ቀኝ ከልጅሽም ሊደርስ
ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል
መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል

በዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሀኑ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from የመጻሕፍት ዓለም (𝕄𝕖ም𝕟𝕠𝕟 )
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዜና ሹመት

ብፀዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለተለያዩ የሥራ ኀላፊዎች ሹመቶችን ሰጡ።

( ሰኔ 09 2017 ዓ.ም)

በዛሬው ዕለት ብፀዕ አቡነ ሳዊሮስ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለመምሪያ ኀላፊዎች ዝውውር እና ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኀላፊዎች ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በዚህም መሠረት፦

፩ኛ. መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ከጠቅላይ ቤተክህነት ቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ወደ ጠ/ቤ/ክህነት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ፤

፪ኛ. መ/ር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ ከጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር መምሪያ ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት EOTC TV ዋና ሥራ አስኪያጅ፤

፫ኛ. ሊ/መ ሐረገወይን ጫኔ ከሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር መምሪያ፤

፬ ዶ/ር አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ ከጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ወደ ጠ/ቤ/ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ፤

፭ኛ. መ/ር ምትኩ ከንቲባ ከጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል መምሪያ ተዘዋዋሪ ሰባኪነት ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት የቅርሳቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ፤

፮ኛ. ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን ሥርጭት ድርጅት ወደ ቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ  ተዛውረው እንዲሠሩ ተመድበዋል።

በሌላ በኩል ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ጨምሮ የተወሰኑ አዳዲስ ዋና ክፍሎችን በመምረጥ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ፊርማ እንዲመደቡ አድርገዋል።

በዚህም መሠረት፦

፩ኛ. መ/ም አባ ገ/መድኅን ንጉሤ ከም/ሸዋ ሀገረ ስብከት ወደ ከዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተዛውረው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።

፪ኛ. መ/አእላፍ  ማሙዬ ሸዋፈራው ከጠቅላይ ቤተክህነት ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ምክትል ኀላፊ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ፤

፫ኛ. መምህር  አስናቀ ሸዋዬ ከጠቅላይ ቤተክህነት ቁጥጥር መምሪያ ተቆጣጣሪነት ወደ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከ ሂሳብ እና በጀት ዋና ኃላፊ፤

፬ኛ. ሊ/ኅሩያን ባዩ ተዘራ ከአዲስ ከተማ ቂርቆስ ልደታ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት የሰንበት ትምህር ቤቶች ክፍል ኀላፊ ወደ የሀ/ስብከቱ የሰው ኀይል አስተዳደር ዋና ክፍል ኀላፊ፤

፭ኛ. መ/ሰላም ጽጌ ከበረ ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የማኅበራት ማደራጃ ዋና ክፍል ኀላፊ፤

፮ኛ. ሊቀ ሥልጣናት አባ ጥዑመ ልሳን ኪዳነ ማርያም ከመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት ዋና ክፍል  ኀላፊ፤

፯ኛ. መ/ስብሐት ዐቢይ ዘለቀ ከቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተዛውረው የሀገረ ስብከቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ጸሐፊ ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።

መረጃው፡-የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኘነት መምሪያ ነው፡፡
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
#ሰኔ_፲፪   በዓለ ተዝካሩ #ለቅዱስ_ሚካኤል ሊቀ መላእክት #ወቅዱስ_ላሊበላ 
#ቅዱስ_ሚካኤል_አፎምያንና_ባሕራንን_ያዳነበት_እለእስክንድሮስ_ቅዳሴ_ቤቱን_ያከበረበትና_የቅዱስ_ላሊበላ_ዕረፍቱ_ነው፡፡

   #ሰኔ_፲፪ #መከበሩ_ስለምንድን_ነው_ቢሉ_
ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር፤ ንሥረ አርያም የሚባል፥ ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፥ ንዑድ ክቡር የሆነ ፥ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው  እንዲሁም  የሌሎችም ቅዱሳን መታሰቢያ ቀናቸው  (ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት) ፡፡ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው  እነርሱም፤
   #share
፠፩. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል፤
፠፪. ባሕራንን ያዳነበት፤
፠፫. የአስተራኒቆስ ሚስት ቅድስት አፎምያን ያዳነበት፤ በዓለ እረፍቷም በዚሁ እለት ነው፤
፠፬. በግብፅ ሃገር ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረበት፤
፠፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት፤
፠ ሐናፄ መቅደስና በሰማያት ያለ ምሥጢርን የተመለከተ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዓለ ዕረፍቱ ነው፤
፠67ኛ ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት ዘእስክንድርያ እረፍቱ ነው፤
፠የእስክንድርያ 6ኛ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ (ወንጌላዊና ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የክርስትና ጥምቀትን ያጠመቀው፥ ዲቁናና ቅስናን የሾመው) እረፍቱ ነው፡፡

ማብራሪያ፤
#፩. ቅዱስ ሚካኤል በፈቃደ እግዚአብሔር ከዲያብሎስ ጋር ተዋግቶ ያሸነፈበት፤ አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት እለት በመሆኑ ነው፡፡ ቀድሞ ከ100 ነገደ መላእክት ኃይላት የሚባሉ የ10 ነገደ መላእክት አለቃ ነበር፤ በዚህች ቀን ግን የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ አጋእዝት የተባሉትንና ሳጥናኤል(ሰማልያል) ይመራቸው ለነበሩት 10 ነገዶች በተጨማሪ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በአጠቃላይ ለሌሎችም 100 (99ኝ) ነገደ መላአክት አለቃ ሁኗል፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡

#፪. ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት፤ ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312 - 326/ በግብፅ ሃገር ንግሥት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ያሠራችውንና ጣዖት ይመለክበት የነበረውን ቤተ ጣዖትን አፍርሶ በቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በታላቅ ክብር ያከበረበት እለት ነው፡፡

#፫. ባሕራንን ያዳነበት
ሊቀ ጳጳሳት እለ እስክንድሮስ የተሠራውን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ከሚያከብሩ ምእመናንን አንዱ የባሕራን አባት ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር፤ በዚህ ሰው ላይ ላይ ጥላቻ ያደረበትና ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጸጋ ጐረቤት ነበረው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር፡፡

    ይህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውም በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ። ሚስቱንም ጠርቶ ‹‹በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመመጽወት ቸል አትበይ! የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ፤ ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት  ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው›› አላት፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር። ይህም ደገኛ ሰው በሰላም ዐረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ። ሚስቱም የመውለጃዋ ሰዓት በደረሰ ጊዜ ታላቅ ጭንቅ ላይ ኾነች እርሷም መልአኩን ቅዱስ ሚካኤል እንዲደርስላት ተማጸነችው በሰላምም ተገላገለች፡፡ መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና ‹‹ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል›› አለ። ያን ጊዜ ያ ባለጸጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ሐዘን ተነካ፤ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።

ብላቴናውም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት፡፡ ባለጸጋው እኔ ጋር ተንከባክቤ ላሳድገው ብሎ ከእናቱ ከተቀበለ በኋላ፤ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው፤ እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።

በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያንን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣውና ወደ ቤቱ ወስዶ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው።  ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን "ባሕራን" ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ፡፡

ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዐሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ጸጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ፡፡ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ። በግ ጠባቂውንም ‹‹ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው፣ ኪራዩንም እከፍልሃለው›› ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው። ባለጸጋውም ገብቶ ጥቂት ካረፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ ‹‹ልጅህ ነውን?›› ብሎ ጠየቀው። በግ ጠባቂውም ‹‹አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው›› አለው። ባለጸጋውም በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም ስላወቀ ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ፤ ይገድለውም ዘንድ ፈለገ፡፡ በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሐሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን ‹‹ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ›› አለው።

ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ ‹‹ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ›› ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ‹‹እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ›› አለው። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ‹‹ይህችን የመልእክት ደብዳቤ ይዞ ወደ አንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው፤ ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ›› የሚል ጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ፤ በአገልጋዩ (በሹሙ)ና በእርሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው፡፡ ለመንገዱም የሚሆነው ስንቅ ሰጥቶ ላከው።
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ 12 ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

#፬. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን፤ ወደፊት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽ ጌታችን የነገረውና የሕንጻዎቹን አሠራር ዝርዝር የነገረው በዚሁ እለት ነው፡፡


ባሕራንም መልእክቱን ለማድረስ ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው፡፡ ባሕራንም ‹‹ከአንድ ባለጸጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እርሱን ለማድረስ ዕገሊት ወደምትባል አገር እሄዳለሁ›› አለው። ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም "እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ?" አለው፡፡ ባሕራንም ‹‹ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹እሺ ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ›› አለው፡፡ ባሕራንም አሳየው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በሞቱ ደብዳቤ ላይ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትዕዛዝ ጽፎበታል፡፡ በደብዳቤው ላይ የተጻፈውን የሞት መልእክት ደምስሶ ‹‹ከእኔ ከባለጸጋ ዕገሌ የተጻፈ›› ይልና ‹‹ይህን መልእክት ይዞ ለመጣሰው ዕገሊት የምትባለዋን ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን ፥ በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና፤ በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በእኔና በአንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ›› የሚል ጽሑፍ ጻፈበት "እንግዲህ ወደ ባለጸጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ አለው፤ ባሕራንም ‹‹እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ›› ብሎ ጉዞውን ቀጠለና የዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።
ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለጸጋውን ልጅ አጋባው፣ የሠርጉንም በዓል እስከ ፵ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ። ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለጸጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ "ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው?" ሲል ጠየቀ፡፡
ሰዎቹም ‹‹ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታ፤ እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ፵ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል›› አሉት። ያም ባለጸጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት። ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር። በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ። ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቈጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን፡፡

#፭. አፎምያን ያዳነበት
ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡
ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጕል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፤ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም ፥ በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኵሴ መስሎ አጋንንትን መነኰሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡

እርሷም ‹‹ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ›› አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም ‹‹እኛማ በነግህ ጸልየናል?›› አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን ‹‹...እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ፥ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ፥ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ›› አላት፡፡ ቅድስት አፎምያም ‹‹አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ፥ አትጸልዩ ያልከኝ፤ ጌታ ምጽዋትን መጽውቱ ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? ርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም፤ ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?›› ብላ ሞገተችው፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡

ከላይ እንዳየነው በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡  ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሰኔ 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?›› በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ
ጠየቀችው፡፡ ለጊዜው ‹‹በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም›› ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ። ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእርሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡  በመቀጠልም ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ሰይጣናዊ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን "ድረስልኝ" እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል (በአ.አ፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ ባሉ) ከሚከበርባቸው በርካታ ገዳማትና አድባራት 208ቱን እንጠቁምዎ፡፡ (ምንጭ ፤ ዋሊ ገጽ)

ሰኔ ፲፪ የቅዱስ ሚካኤል እና የቅዱስ ላሊበላን በዓል በየት ሊያከብሩ ዐስበዋል?
#ቅዱስ_ሚካኤል_አፎምያንና_ባሕራንን_ያዳነበት_እለእስክንድሮስ_ቅዳሴ_ቤቱን_ያከበረበትና_የቅዱስ_ላሊበላ_ዕረፍቱ_ነው፡፡
#በመላው_ዓለም_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፪፻፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ገዳማት ካሉ አሳውቁን)

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በአዲስ_አበባ_የሚከብርባቸው_ #፵፮ #ገዳማትና_አድባራት፡፡፡
፩. የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (በኦሪት ዘመን መሥዋዕተ ኦሪት ይሰዋበት የነበረ፥ ዋሻ ቤተ ክርስቲያኑ በ4ኛው ክ/ዘመን በአብሃ ወአጽብሃ ዘመን የተመሠረተ) (የቅዱስ ላሊበላም በዓለ ዕረፍት በማኅሌት በወረብ ጨምር ሳይቀር የሚከበርበት ነው)
አድራሻው፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ሾላ መገናኛ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(4 ኪሎ) → ሾላ መገናኛ፤

፪. አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (ራስ ካሳ ሚካኤል) (ጭቁኑ) /የቅዱስ ላሊበላ ታቦትም አብሮ ይከብራል/፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ራስ ካሳ
ታክሲ፤ ከ4ኪሎ(ከ6 ኪሎ) → ፈረንሳይ፡፡

፫. ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (አዲሱ ሚካኤል)
አድራሻ፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፥ መርካቶ አውቶቡስ ተራ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(4ኪሎ) → መርካቶ አውቶቡስ ተራ፡፡

፬. አፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (ወህኒ ቤት) (ከርቸሌ)
አድራሻ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፥ ቡልጋርያ (ከርቸሌ) (አፍሪካ ኅብረት)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ቄራ፡፡

፭. ኮተቤ (ሲኤምሲ) (አልታድ) ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ /ሳጠራው/ (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲኤምሲ)
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ካራ አሎ ፥ አባዶ አጠገብ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ሲኤምሲ፡፡

፮. መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ መካኒሳ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → መካኒሳ፡፡

፯. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ላፍቶ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡

፰. ቤተል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ቤተል፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኃሎች → አየር ጤና፡፡
ወይም፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት → አለም ባንክ/ኤር ጤና/፡፡

፱. ኤረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤልና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ጎሮ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ (ፒያሳ) → ጎሮ፡፡

፲. መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅድስት አርሴማ ገዳም፤ (የራስ መኰንን ደን /ጋራው /ጫካው/ /ጽድ/ ሚካኤል/)
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ቀጨኔ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከመርካቶ)(ከአዲሱ ገበያ) → ቀጨኔ፡፡

፲፩. አያት ጨፌ ኢያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ (በ1980ዓ.ም ጽላቱ ከነ ድርሳናቱ ተቀብሮ የተገኘበት)
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 9፥ ጎሮ ሰፈር፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ጎሮ፡፡

፲፪. ካራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤል፥ 24ቱ ካህናተ ሰማይና ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አባዶ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → አባዶ

፲፫. ቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ቦሌ ሚካኤል፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቦሌ ሚካኤል፡፡

፲፬. የካ አባዶ ገ/አ/ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አባዶ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → አባዶ

፲፭. ምሥራቀ ፀሐይ ዳንሴ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 10 ከጉራራ ከፍ ብሎ፤
ታክሲ፤ ከጊዮርጊስ (4 ኪሎ) (6 ኪሎ) → ፈረንሳይ → ጉራራ፡፡

፲፮. ወረገኑ ቅዱስ ሚካኤልና አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ሩዋንዳ አጠገብ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ (ቦሌ) → ወረገኑ፡፡

፲፯. ቃሊቲ ሰፈረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቃሊቲ → ሰፈረ ገነት፡፡

፲፰. ንቡ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ሃራብሳ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ቱሉ ዲምቱ → ንቡ ሚካኤል፡፡

፲፱. ጀሞ (መካኒሳ) ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጀሞ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (ሜክሲኮ) → ጀሞ፡፡

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#እንዲሁም_በአዲስ_አበባ_በአንድነት_ተሠሩ_በሚከተሉት_አብያተ_ክርስቲያናት_ይከበራል
፳. ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ጎላ (ኢምግሬሽን ጀርባ)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል (ኢምግሬሽን)፡፡

፳፩. ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ዮሴፍ፥ ደጃዝማች መርዕድ መንገድ፥ ቀለበት መንገድ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ከላጋር (ከፒያሣ) (ከ4 ኪሎ) (ከቦሌ)(ከመገናኛ) → ቃሊቲ መናኸሪያ /በቀለበት መንገድ/
ወይም፤ ከሳሪስ አቦ → ቦሌ /በቀለበት መንገድ/

፳፪. ጀሞ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጀሞ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (ሜክሲኮ) → ጀሞ፡፡

፳፫. ቃሊቲ ደብረ ቊስቋም ማርያምና ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቃሊቲ → ሰፈረ ገነት፡፡

፳፬. ኮተቤ ማኅደረ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ሎቄ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ሎቄ፡፡

፳፭. ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ለቡ፥ ፉሪ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ለቡ፡፡

፳፮. ቂሊንጦ መካነ ፍስሐ ቅዱስ ሚካኤልና በዓታ ለማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ቂሊንጦ ኮዬ ዐደባባይ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ቱሉዲምቱ፡፡
ወይም፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ → ቂሊንጦ፡፡

፳፯. ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ አቃቂ ኬላ አጠገብ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ቱሉዲምቱ፡፡
ወይም፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ → ቱሉዲምቱ፡፡

/ ©#ገዳማትና_አድባራት #Monasteries_and_Churches /
#እንዲሁም_በድርብነት_በሚከተሉት_አብያተ_ክርስቲያናት_ይከበራል
፳፰. መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ወቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ 6 ኪሎ ዐደባባይ፤
ታክሲ፤ ከጊዮርጊስ → 6 ኪሎ (ማርቆስ)፡፡

፳፱. ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ገርጂ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቦሌ በሚል ታክሲ → መስቀል ዐደባባይ፡፡

፴. ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ልደታ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጦር ኃይሎች በሚለው ታክሲ → ልደታ፡፡
፴፩. ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አረዳ ክፍለ ከተማ፥ ሰባራ ባቡር፥ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አጠገብ (አርበኞች መንገድ)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → በዊንጌት አስኮ /ሩፋኤል ፊንሐስ/ ታክሲ →  ዮሐንስ፡፡

፴፪. ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት፥ ጠሮ፥ አራት መንታ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → ዊንጌት → ጠሮ፡፡

፴፫. ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ልኳንዳ፥ ፈጥኖ ደራሽ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → መርካቶ → ኮልፌ አጣና ተራ → ልኳንዳ → (በስተግራ ባለው አስፓልት በእግር 5 ደቂቃ ፈጥኖ ደራሽ ማሰልጠኛ)፡፡

፴፬. ቃሌ ተራራ ደብረ መድኀኒት አቡነ ሀብተ ማርያም ወቅድስት ልደታ ወቅድስት አርሴማ ገዳም፤
አድራሻው፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አስኮ፥ ካኦ ጄጄ ዱቄት ፋብሪካ፥ ቃሌ ተራራ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → አስኮ፤

፴፭. ማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ የሺ ደበሌ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → መርካቶ → የሺ ደበሌ፡፡

፴፮. ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ገርጂ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ገርጂ፡፡

፴፯. ኮተቤ ደብረ ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና አቡነ ሀብተ ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ኮተቤ፥ ካራ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ኮተቤ (ካራ)

፴፰. ረጲ መካነ ጎልጎታ መድኃኔ ዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ካራ ቆሬ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → አለም ባንክ → ካራቆሬ (ረጲ)፡፡

፴፱. ፉሪ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጋራ ኦዳ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጋራ ኦዳ፡፡

፵. ሐመረ ወርቅ ማርያምና አርሴማ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ወርቁ ሰፈር፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → ወርቁ ሰፈር፡፡

፵፩. ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → ሰፈረ ገነት፡፡

፵፪. ቦሌ ቡልቡላ ምስካበ ቅዱሳን አባ ሳሙኤል ዘዋልድባና ቅዱስ አማኑኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ቡልቡላ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ሳሪስ አቦ → ቡልቡላ መድኀኔ ዓለም (ኮንዶሚኒየም)→ ወደ ላይ በአስፓልቱ የ5 ደቂቃ የእግር መንግድ፡፡
ወይም፤ ከቦሌ መድኃኔ ዓለም → ቡልቡላ (በአዲሱ መንገድ)

፵፫. ደብረ ዐባይ ቅድስት አርሴማ ወቅዱስ ሚካኤል ወመርቆሬዎስ ወአቡነ ሀብተ ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አለም ባንክ፥ ግራር፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ጦር ኄሎች → አለም ባንክ → ግራር፡፡

፵፬. አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ አቃቂ፥ ጋራው መድኃኔዓለም፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → አቃቂ፡፡

፵፭. ሣሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሣሎ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → ሣሎ፡፡

፵፮. ቤተል) ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ቤተል፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት (ጦር ኀይሎች) → ቤቴል፡

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ጥንታውያን #፳ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #እየላ_ቅዱስ_ሚካኤል፤ (#የ3 #ሺህ_ዓመታት_ባለታሪክ፤ ከታቦተ ጽዮን ጋራ በ980 ከክ.ል.በ. ታቦቱ የመጣ፤ መሥዋዕተ ኦሪት ይቀርብበት የነበረ፤ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መጥቶ የባረከው)
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → ግዳን (እየላ)፡፡

፪. ሰሜን ትግራይ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል፤ (መሥዋዕተ ኦሪት ይቀርብበት የነበረ)
አድራሻው፤ ሰሜን ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ሰሜን ትግራይ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎሃ ጽዮን ወይም ደብረ ማርቆስ በሚለው መኪና ዐባይ በረሃ ላይ መውረድ፤

፫. ዘጌ ወንጀጣ ቅድስ ሚካኤል፤(መሥዋዕተ ኦሪት ይቀርብበት የነበረ)
አድራሻው፤ ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት፥ ዘጌ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕርዳር → ዘጌ (20 ኪ.ሜ)

፬. ጎሐ ጽዮን ቅዱስ ሚካኤል፤ (በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን የተሠራ)
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ፍቼ ሀገረ ስብከት፥ ጎሐ ጽዮን፥ ዐባይ በረሃ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎሃ ጽዮን ወይም ደብረ ማርቆስ በሚለው መኪና ዐባይ በረሃ ላይ መውረድ፤

፭. ሸኖ ጎልባ ደብረ ሣሕል ቅዱስ ሚካኤል ደብር፤ (በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን የተመሠረተ)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ሰኖ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ሸኖ፡፡

፮. መላሃይዘንጊ ቅዱስ ሚካኤል፤ (በ8ኛው ክፍለ ዘመን የታነጸ)
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ፍቼ ሀገረ ስብከት፥ ጎሐ ጽዮን፥ ዐባይ በረሃ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎሃ ጽዮን ወይም ደብረ ማርቆስ በሚለው መኪና ዐባይ በረሃ ላይ መውረድ፤

፯. ላስታ ላሊበላ ቤተ ሚካኤል፤ (በ11ኛው ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ የታነፀ፥ ከ11ዱ የላስታ ላሊበላ ፍልፍል ሕንጻዎች አንዱ)
አድራሻው፤ ላስታ ሀገረ ስብከት፥ ላሊበላ ከተማ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ፡፡

፰. ገርዓልታ ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል፤
አድራሻው፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ገርዓልታ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → ገርዓልታ፡፡

፱. ሚካኤል ዓምባ፤ (በ11ኛው ክፍለ ዘመን የታነጸ)
አድራሻው፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ውቅሮ፥ (በመቀለና በአዲግራት መሃል)፥ አጽቢ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ውቅሮ → አጽቢ፤

፲. ባሕር ዳር ሽንብጥ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ (በ13ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተ)
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፥ ቀበሌ 13
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር ከተማ → ሆስፒታል በሚል ታክሲ (ዲፖ ጋር)፡፡

፲፩. እስቴ አበርጉት ቅዱስ ሚካኤል ፤ (በአፄ ዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት በልጃቸው በአቡነ ፊልሞና የተሠራ ታሪካዊ ጠበል ያለበት)
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ እስቴ ወረዳ፥ ደስኳ አጋማች ቀበሌ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → እስቴ፡፡

፲፪. በሮ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል፤ በ16ኛው መ/ክ/ዘመን መጨረሻ የተመሠረተ
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ሳይንት ወረዳ
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → አማራ ሳይንት፡፡
ወይም፤ ከጎጃም በመርጠሉ ማርያም → አማራ ሳይንት

፲፫. ጎንደር ፊት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ በአፄ ፋሲለደስ ዘመነ መንግሥት ተመሠረተ፤
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡

፲፬. ጎንደር አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡
፲፭. ተንታ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ (ንጉሥ ሚካኤል በሚያስደንቅ ሁኔታ ያሠሩት)
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ አምባሰል፥ ተንታ ወረዳ፥ ጠዓት ቀበሌ፥ እሜገኝ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጻድቃኔ፡፡

፲፮. አጃና ቅዱስ ሚካኤል፤ (በቀስተ ደመና ጠበል አጥማቂው)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ተጉለት፥ አጃና፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጻድቃኔ → አጃና፡፡

፲፯. ቦንብ አርግፍ ቅዱስ ሚካኤል (ሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት፤ የጁ ወልዲያ)
፲፰. ቦረዳ ቅዱስ ሚካኤል
፲፱. ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል (ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ ኢቲሳ)
፳. አንኮበር ቅዱስ ሚካኤል (ሰሜን ሸዋ ሀ/ስብከት)

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፻፱ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
1.. ግሸን ደብረ ከርቤ ቅዱስ ሚካኤል
ጎሚስታው ሚካኤል (ትግራይ)
እንዳ ቅዱስ ሚካኤል (ትግራይ)
መቀለ ቅዱስ ሚካኤል
5. ጾረና ቅዱስ ሚካኤል (ኤርትራ)
አለም ገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል (አለም ገና፤ ሰበታ መስመር)
ደብረ ዘይት /ቢሾፍቱ/ ደብረ አሚን ቅዱስ ሚካኤል
ዱከም ቅዱስ ሚካኤል
ናዝሬት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
10. ድሬዳዋ ቅዱስ ሚካኤል
ጭሮ አሰበ ተፈሪ ቅዱስ ሚካኤል (ድሬዳዋ፥ አሰበ ተፈሪ)
ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል (ክርስቲያኖች ስለ ሃማኖቶቻው በ2015 ዓ.ም. ሰማዕታት የሆኑበት)
አርባ ምንጭ ላከ ኢየሱስና ሚካኤል
ዲላ ቅዱስ ሚካኤል
15. አሰላ ደብረ ሰላም ቅድስ ሚካኤል
ጂጂጋ ቅዱስ ሚካኤል
ሚዛን ቴፒ ደብረ ኀይል ቅዱስ ሚካኤል
ቦንጋ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል
ኢሉባቦር ሌንቃ ቅዱስ ሚካኤል
20. እነሞርና ኤነር ወረዳ ቅዱስ ሚካኤል (ጉራጌ ሀ/ስብከት)
አሰቦት ደብረ ወገግ ቅዱስ ሚካኤል (ምሥ. ሀረርጌ ሀ/ስብከት)
ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል
ኩክ የለሽ ዛሪያ ቅዱስ ሚካኤል
ጅሩ ሞቶሎኒ ቅዱስ ሚካኤል (ጅሩ አርሴማ ውስጥ)
25. መንዝ ይገም ቅዱስ ሚካኤል
መሐል ሜዳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
የሲጠር ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል (መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ)
ወንጪት ቅዱስ ሚካኤል (በነብር የሚጠበቅ)
ሸዋሮቢት ጫሬ ቅዱስ ሚካኤል
30. ወልዲያ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
ኮምቦልቻ ቅዱስ ሚካኤል
ደሴ ጢጣ ደብረ ሲና ቅዱስ ሚካኤል
ራያ ቆቦ ቅዱስ ሚካኤል
ደብረ ማርቆስ ዋሻው ቅዱስ ሚካኤል
35. ደብረ ማርቆስ አጠገብ ብዕርና ቅዱስ ሚካኤል
ደምበጫ ቅዱስ ሚካኤል
መርዓዊ ደብረ ኀይል ቅዱስ ሚካኤል
ባሕር ዳር ድባንቄ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
አዘዞ አይራ ቅዱስ ሚካኤል
40. ዛራ ቅዱስ ሚካኤል (ባሕር ዳር አጠገብ ሐሙሲት)
ጉመር ደብረ ኅሩያን ቅዱስ ሚካኤል
ካምባ ቅዱስ ሚካኤል
ሳንቃ ወይራ ቅዱስ ሚካኤል
ዳስ ዓምባ ቅዱስ ሚካኤል
ላሐ ቅዱስ ሚካኤል
ጊራራ ቅዱስ ሚካኤል
መለኮዛ ቅዱስ ሚካኤል
ዋይሎ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
ጣፎ ጪኤሚሰ ሚካኤል (ለገጣፎ)
50. ለኩ ከታ ደብረሳህል ቅዱስሚካኤል ካቴድራል
አጣራ ሚካኤል
ሐረር ሚካኤል
ገፈርሳ ሚካኤል
ጂማ ደብረ ሣህል ሚካኤል
55. የዶፋ ሚካኤል ሽንኮራ የሚገኘው
አዋሮ ሚካኤል (አምቦ ከተማ)
ሐርቡ ሰንጣ ቅዱስ ሚካኤል (ወለጋ፥ ሆሮ ጉዱሩ፥  አበ ደንጎሮ ወረዳ፤ #ቀዳሽም_አስቀዳሽም_የለሌው ቀብር ስኖር ብቻ የሚከፈት)
ደብረ ገሊላ ሚካኤል (ዱከም)
60. ደደሩ ሚካኤል
ቶጫ ሚካኤል (በዳውሮ)
ገንዶ ሚካኤል (በዳውሮ)
ባሌ ሚካኤል (በዳውሮ)
ተፒ ሚካኤል(ተፒ)
65. አረካ ሚካኤል (ወላይታ)
ዘንዘልማ ቅዱስ ሚካኤል (ባሕር ዳር አጠገብ)
ቦዲቲ መካነ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል
እኩቲ ሚካኤል (ካፋ ዞን፥ ዴቻ ወረዳ)
ወልቂጤ ቅዱስሚካኤል
70. ሁልባራቅ ቅዱስ ሚካኤል (ስልጤ ዞን)
ጋራው ሚካኤል (ባሌ ጎባ)
ወልመራ ደብረ መዊዕ ሚካኤል
ቦንጋ ሚካኤል
ኩጢ ሚካኤል
75. ኩቲ ሚካኤል (ከቦንጋ ከተማ አጠገብ)
የካ ሚካኤል
ሸኮ ሚካኤል (ቤንች፥ ሸኮ ዞን፥ ሸኮ ወረዳ)
ጭሪይ ሚካኤል (ክፍል)
ፀጉር ሚካአኤል (የዲቲዉ)
80. ኬላ ሚካኤል (ደቡብ ሶዶ ፥ ክስታኔ)
ደሉ /ሻመን /ሚካኤል
ዬህታ ሚካኤል
ሸሬብ ሚካኤል
ጉስ ሚካኤል
85. ዝፍት ሚካኤል (አሪ ዞን፥ ሴሜን አሪ ወረዳ)
ጣጤሳ ሚካኤል
ጡጤ ሚካኤል
ጡሪ ሚካኤል
ወቀራ ሚካኤል
90. ዛዳ ሚካኤል
ኮዶ ሚካኤል
ኤዞ ሚካኤል
ቦሮዳ ሚካኤል
ሊሻና ሚካኤል
95. ዶቃማ አ/ም ሚካኤል (ጋሞ ሀገረ ስብከት)
ሻለኛ ሚካኤል (ሰሜን ሸዋ፥ ዥማ ዳር)
ቃንቆ ሚካኤል።
ባሺ ቅዱስ ሚካኤል (ካፋ /ቦንጋ፥ ጨታ ወረዳ)
ጆሌ ሚካኤል
100. አባዜቦ ሚካኤል (መቄት)
ደምበኣታ ሚካኤል
ጨሞ ሚካኤል
የጫ ሚካኤል
አገዮ ሚካኤል
105. የባርዛው ሚካኤል
የሳዝጋው ሚካኤል
የላሃው ሚካኤል
ድባና ሚካኤል
አበርጉት ሚካኤል
110. ንፋሦ ሚካኤል
ጠሎ ዋሻ ሚካኤል
ዳዩ ሚካኤል
የቦርገላው ሚካኤል
አዋሽ አርባ ቅዱስ ሚካኤል (አፋር)
115. ጋራ ጎዶ ደብረ ምሕረት ሚካኤል
ሞጆ ሚካኤል
አዳማ (ናዝሬት) ሚካኤል
መቂ ሚካኤል
ቦኩ ሚካኤል
120. ቆቃ ሚካኤል
ኩርፋ ሚካኤል
ተጉለ ሚካኤል
ዓይንማይ ሚካኤል
አርባምንጭ ሚካኤል
125. ኦለንጭቲ ደ/መ ሚካኤል
ሲጋዲ ሚካኤል (ቻግኒ)
ፓዌ መንደር አራት ሚካኤል
ፓዌ መንደር ሁለት ሚካኤል
ለምለም ሚካኤል (#ኩተሬ_አንድ_የኦርቶዶክስ_እምነት_ተከታይ_ያለበት)
130. ቱርሚ ሚካኤል
ቡርካመሩ ሚካኤል
ላሃ ሚካኤል
ሳላይሽ ሚካኤል
ስሲማ ሚካኤል
135. ኮይሻ ሚካኤል
ቦርገላ ሚካኤል
በርዛ ሚካኤል
ሳዝጋ ሚካኤል
139. ዶፋ ሚካኤል (ምንጃር)

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከብርባቸው_ #፪ #ጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ላስ ቬጋስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ወቅዱስ ዑራኤል ወቅድስት ማርያም ቤ/ን፤
አድራሻ፤ ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት፥ አሜሪካ፥ ላስቬጋስ (USA, 2575 Westwind Rd. Las Vegas, NV 89146)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር ማረፊያ → አሜሪካ ላስ ቬጋስ፡፡

፪. ላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል እና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ፤
(USA, 2575 Westwind Rd. Las Vegas, NV 89146)
አድራሻ፤ ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት፥ አሜሪካ፥ ላስቬጋስ (USA, 5985 S Lindell Rd, Las Vegas, NV 89118)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር ማረፊያ → አሜሪካ ላስ ቬጋስ፡፡

፫. ጀርመን ዳርምሽታት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ጀርመን ሀገረ ስብከት፥ ዳርምሽታት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር ማረፊያ → ጀርመን፡፡

(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ገዳማት ካሉ አሳውቁን)
ምንጭ #ዋልድባዋሊ ገጽ
🔴 እግዚአብሔር በሚያደርገው በጎ ነገር...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
እግዚአብሔር በሚያደርገው በጎ ነገር ሚካኤል ይታዘዛል
                         
Size 51.2MB
Length 55:18

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
2025/06/27 05:53:53
Back to Top
HTML Embed Code: