Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ለሊት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ሳይደርስበት እንደቀረ ተገለፀ‼️
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6, ለሊት የሞባይል ባንኪንግ ሲስተም ችግር ያጋጠመው ሲሆን የችግሩ መንስኤ በሞባይል አፕሊኬሽኑ update ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።

የሞባይል ባንኪንጉ ተጠቃሚዎች ገንዘብ በሚያዘዋውሩበት ጊዜ ከአካውንታቸው ተቀናሽ ባለማድረጉ ምክንያት ባንኩን ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ሊጥል ችሏል።

በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አጋጣሚውን በመጠቀም በነፃ ወደ ሌሎች ባንኮች ገንዘብ ሲያዘዋውሩ አድረዋል።

ይህ ዜና እስከተሰራበት ጊዜ ድረስ የዚህ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ ሲስተም አገልግሎት መስጠት ያቆመ ሲሆን ባንኩ የደረሰውን ችግር ወደነበረበት ለመመለስ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
Forwarded from Arifpay Ethiopia
Announcing the Grand Prize Winner of the ArifDeveloper Challenge🎉✈️

We are delighted to congratulate Kibru Demeke on emerging as the brilliant mind who secured victory in the prestigious ArifDevelopers Challenge. As the esteemed champion, Kibru Demeke has been awarded a trip to Tokyo for 5 days.

Once again, congratulations Kibru Demeke, and we sincerely hope you enjoy your well-earned trip to Tokyo!

#Arifpay #ArifDeveloperCompetition #ArifpayDevelopersEvent  #GrandPrizeWinner #Tokyotrip #Innovation #InnovationInMotion  #Empowerment #POS #Seamless #DigitalPayment #ArifpayInnovation #Ethiopia #ExclusiveOffer #ATMCard #Seamless #Ease #Convenience #Convenient #POS #Discount #Wallets #LimitedTime #Savings #FintechInnovation #DigitalPayments #POSSales #Merchant #ArifpayExclusive #MSME98SolutionForEthiopia #call9395
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በአንድ አካል ሁለት ጭንቅላት ያላቸው ልጆች ተወለዱ

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንድ አካል ጭንቅላታቸው የተያያዙ መንታ ልጆች አንዲት እናት መገላገሏን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው እለት ከምሽቱ 3፡30 ገደማ የወለደችው እናት እድሜዋ 40 ዓመት ሲሆን የአምስት ልጆች እናት መሆኗ ተገልፆል፡፡

ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱት ህፃናቶቹ እና እናትየው በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል

በሆስፒታሉ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ እንደሆነ እና ወደ አዲስ አበባ ሪፈር እንደሚደረጉ ነገር ግን ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ መሆኑን  በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቨ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ሁለት እና ሦስት መንትያ ልጆች ተወልደው ቢታወቅም ይህ ክስተት  የመጀመሪያ ነው ሲሉ ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በደምቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ሁለት ጭንቅላት ያለላቸው ልጆች መወለዳቸው ይታወሳል፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ይፋ አደረገ! 😁

በባን
ኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያለአግባብ ከባንካችን የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10,857 የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መመለሳቸውን ባንኩ ገልጿል፡፡

ባንኩ "የተሰጠውን ተደጋጋሚ እድል ተጠቅመው ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦች አሉ ያለ ሲሆን ባንካችን ገንዘቡን ለማስመለስ በተከታታይ ስለሚወስዳቸው እርምጃዎች በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ በባንካችን ድረ-ገጽ እና የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለማውጣት ተገደናል ብሏል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ባንካችን የተለያዩ ምክንያቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የገንዘብ መመለሻ ጊዜውን ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ያራዘመ በመሆኑ፣ ይህን የመጭረሻ እድል ተጠቅማችሁ ገንዘቡን እድትመልሱ እያሳሰብን፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ የምናቀርብ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን ብሏል፡፡

ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ይፋ አድርጓል።
https://combanketh.et/list-of-customers

😁😁

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ንግድ ባንክ በ4ኪሎ 😁

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ መልኩ ገንዘብ አልመለሱም ያላቸውን ደንበኞቹ ምስል በየቅርንጫፍ መለጠፍ ጀምሯል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ይህ ፓስታ ሳይሆን ሐዋሳ ከተማ ከ8 ዓት ህፃን ጉሮሮ በቀዶ ህክምና የወጣ ትል/ፓራሳይት/ ነው።

ትሉ የልጁን ጉሮሮ በመዝጋት ከተበከለ በኋላ በቀዶ ጥገና ተወግዷል።

እነዚህ ትሎች/ፓራሳይቶች/ ወደ አንጀታችን የሚገቡት የእጃችንን ንፅህና ባለመጠበቅ ነው። በተጨማሪም ንፁህ ያልሆኑ/የተበከሉ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን በመመገብ ወደ እኛ ይተላለፋል።

ስለዚህ የምግብ ንፅህናን በመጠበቅ እራሳችንን እና ሌሎችን ከበሽታው እንጠብቅ!
(ዶክተር ናፊያ),Photo credit hakim

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ሶፎኒያስ የገደሉት ተይዘዋል

ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ውስጥ ከዘረፉት ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ወንጀሉን የፈፀሙ አካላትን ለመቆጣጠር  የምርመራና የክትትል ቡድኑ ሌት ከቀን በመስራት ውጤት ማምጣቱ ገልፆል፡፡                        
     
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አሽከርካዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተ-ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ወጣት ሶፎኒያስ አስራት ተገድሎ ይገኛል፡፡
የወጣቱ መገደል ሪፖርት የደረሰው አዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ እና የክትትል ቡድኖችን በማዋቀር የገዳዩቹን   ማንነት ለማወቅ ወንጀለኞቹን ህግ ፊት ለማቅረብ ወደ ስራ ይገባል፡፡

ሟች ወጣት ሶፎኒያስ  መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ናሆም ሆቴል አካባቢ ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ ሦስት ግለሰቦችን በግል በተደረገ ስምምነተ‍ ያለአፕልኬሽን ምዝገባ በኮድ 2 ቪትዝ አሳፍሮ

ወደ ቦሌ ሚካኤል ለማድርስ መሄዱን ጉዳዩን ለመመርመር የተቋቋመው የምርመራና የክትትል ቡድን  አባላት ባሰባሰቡት ማስረጃ ያረጋግጣሉ፡፡ 
ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀል ለመፈፀም አቅደው እና ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ መስለው ሹፌሩን በመቅረብ ካሳፈራቸው በኋላ አንገቱን በገመድ አንቀው በመግደል አስክሬኑን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5

አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ በመጣል  አይነቷ ቪትዝ የሴሌዳ ቁጥር ኮድ 2A 93488 ተሽከርካሪ ጨምሮ ሁለት ሞባይል ስልኮችን ዘርፈው ይሰወራሉ፡፡

ፖሊስ ወንጀሉ ከተፈፀመበት ጊዜ አንስቶ ቀን ከሌት  ባደረገው ብርቱ ክትትል ልዩ ልዩ ፖሊሳዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰረቁትን ተሽከርካሪ ፣ ሦስቱን ዋና ወንጀል ፈፃሚዎች እና የሰረቁትን መኪና እንዲሁም ሶስት አባሪዎቻቸውን ጨምሮ በብርቱ ክትትል መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ከወንጀል ፈፃሚዎቹ እጅ ላይ ባለቤታቸው  የማን እንደሆኑ የማይታወቁ 7 የስልክ ሲም ካርዶችን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን ጨምሮ ገልፆል፡፡ ምንም እንኩዋን ወንጀሉ በስውር የተፈፀመና  ማንነታቸው የማይታወቁ ቢሆን በተደረገ ብርቱ ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ  በመለየት ሦስት ዋና ወንጀል ፈፃሚዎችንና ሦስት ግብራበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም ለዚህ ስራ ስኬታማነት ቀና ትብብር ላደረጉ አካላት አዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቦ የምርመራ ሥራው እንዳበቃ የፍርድ ሂደት ውጤቱን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገለፅ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡ የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ህጉን ጠብቀው አገልግሎት ሲሰጡ በአፕልኬሽኑ ተመዝግበው እንዲሆን ፖሊስ እንደሁልግዜውም አሁንም ያሳስባል።

Via AAP

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
#ትዝብት_ከ_ቲክቶከር👇😂😂😂🙄

ለ2 አራት ምግብ በልተው ሂሳብ ሲባሉ የለንም ሰሃን እንጠብ አሉ። አይቻልም ደውላችሁም ቢሆን አስመጡ ተባሉ ። ቲክቶከሮች ነን በልቶ ያለመክፈል ቪዲዮ እየሰራን ነው ብለው የቆዩ ቪዲዮዎቻቸውን አሳዩ። ለሬስቶራንቱም ማስታወቂያ ነው ብለው ሰከሱ ። ባለቤቱና ጥበቃዎች ጓዳ አስገብተው መከሯቸው። ሰሃኑንም አጠቡ። ለማስታዎሻ ይህንን ፎቶ አነሷቸው ። ችግሮችን በመመካከር መፍታት ይቻላል።

#huleadismedia

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENST
በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በዛሬው እለት ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ ፖሊሶች ቆሰሉ

👉🏼 ተጨማሪ ሌላ አንድ መንገደኛ ግለሰብም ተገድሏል


በዛሬዉ እለት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ካደረጉ ሰዎች ዉስጥ ሁለቱ ሲገደሉ ሌላኛዉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የአዲስአበባ ፖሊስ ፤ ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት ሰዎች በአዲስአበባ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለ ሲሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን ተኩስ ከፍተዋል ብሏል።

ግለሰቦቹ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም  ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ገልጿል። በተጨማሪም ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል ብሏል ፖሊስ፡፡

ሌላዉ አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው መጥቀሱን ዳጉ ተመልክቷል፡፡ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ መቁሰላቸዉንም ፖሊስ አረጋግጧል።

ሌላዉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ታጣቂዎቹ  በመኪናቸው እንዲጭኗቸው  ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በታጣቂዎቹ ተገድለዋል ሲል ፖሊስ ወንጅሏል፡፡  አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ  ጨምሮ ገልጿል ፡፡

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
2024/06/11 11:49:30
Back to Top
HTML Embed Code: