18 ሰዓታት በፈጀ  የቀዶ ህክምና 20 ሳ.ሜ ከፍታ ያለው የጭንቅላት እጢ በተሳካ ሁኔታ ተወገደ

18 ሰዓታት በፈጀ የጭንቅላት እጢ በቀዶ ህክምና ማስተካከል መቻሉን የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።በሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አለምሰገድ ጫኔ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በቀዶ ህክምናው ዋና ዋና ተግባራት በጭንቅላቱ ላይ የነበረውን 20 ሳንቲሜትር ከፍታ የለው እብጠት በቀዶ ህክምና እንዲወጣ ተደርጓል ።

አያይዘውም እብጠቱ የወጣበትን ቦታ በሌላ የሰውነት ክፍል የመተካት ተግባር ተከናውኗል።በሶስተኛ ደረጃ ከታካሚው ከተለያዮ የሰውነት ክፍሎች ማለትም ከእጆቹ ላይ ደም ቅዳና ደም መልስ ተመሳሳይ ደም ስሮችን ወደጭንቅላቱ እንዲደርስ ተደርጓል  በማለት ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በአራተኛ ደረጃ ደግሞ በቀዶ ህክምና  ወቅት በሰውነት ክፍሉ የደም መፍሰስ ችግር እንዳይኖር አስቀድሞ በቂ ደም የመያዝና  የደም ስሮችን የመቋጠር ተግባር  መከናወኑ ተገልጿል።በመጨረሻም ታካሚው ከ18 ሰአታት በኋላ በፅኑ ህሙማን ክፍል እንደቆየ ተደርጓል ያሉት አቶ አለምሰገድ በአሁኑ ሰአት  በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

በዚህም የተሳካ ቀዶ ህክምና የተሳተፉ የተለያዩ  ስፔሻሊስቶች ፣  ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች፣ አኒስቴትክስ፣ ነርሶች ፣ፖርተሮች እና ፅዳቶች  ሲያከናውኑ የነበሩ የቡድን አባላቶች ስራ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ  ተጠቅሷል።ዶ/ር አብዱራዛቅ  የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ስፔሻሊስት ባለሙያና የማክሮ ሰርጀሪ ሰብ ስፔሻሊስት በዚህ ህክምና ላይ ለተሳተፉ አጠቃላይ ሰራተኞች  ምስጋናቸውን  አቅርበዋል።

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
በአውስትራሊያ በቀጥታ ስርጭት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ጳጳስን ጨምሮ አራት ሰዎች በስለት ተወጉ፡፡

በጩቤ ከተወጉት መካከል የአሶራውያን ኦርቶዶክስ ጳጳስ ብጹዕ ቢሾፕ ማር ማሪ ይገኙበታል፡፡

በዋክሌይ በሚገኘው የክርስቶስ በጎ እረኛ ቤተክርስቲያን ድንገተኛ ሁከት ከተከሰተ በኋላ ውጥረት ነግሷል ተብሏል፡፡

ክስተቱ የተፈጸመው በምዕራብ ሲድኒ ዋክሌይ በሚገኘው የክርስቶስ መልካም እረኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ሲል Anadolu Agency ዘግቧል።

የጥቃቱ ዝርዝር ሁኔታ እስካሁን አልተረጋገጠም ያለው ፖሊስ ነገር ግን ብቻውን እንደፈፀመ የሚታመንበት ወንጀለኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል ሲል አስታውቋል። (ቪዲዮው ከላይ ተያይዟል)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
በስለት የተወጉት የኦርቶዶክስ ጳጳስ ጥቃት አድራሹን “ይቅርታ ብያለሁ” አሉ

ባለፈው ሰኞ በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በቀጥታ በሚተላለፍ ሰብከት ላይ ሳሉ በስለት ጥቃት የደረሰባቸው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በፍጥነት እያገገሙ እንደሆነ ገልጸው ጥቃቱን እንዳደረሰ ለተጠረጠረው ግለሰብም ይቅርታ እንዳደረጉ ተናግረዋል።

ጳጳሱ በተቀረጸ ድምጽ ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰቡ እንዲረጋጋም ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ሳምንት በተፈጸመው ጥቃት አራት ሰዎች ተጎድተዋል። ፖሊስ ጥቃቱ ሃይማኖታዊ መነሻ ያለው የሽብር ድርጊት ነው ብሏል።

ከክስተቱ በኋላ ጳጳሱ በሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ሁከት ተፈጥሯል። ጥቃቱን እንዳደረሰ የተጠረጠረ እና ራሱም የተጎዳው የ 16 ዓመት ታዳጊ በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም እስካሁን ክስ አልተመሰረተበትም። ባለስልጣናት የታዳጊውን እምነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ታዳጊው በአረብኛ ሲጮህ እና “ነብዩ” የሚልበትን ቪዲዮ የሀገሪቱ የስለላ ቢሮ እየመረመረው እንደሆነ የተቋሙ ኃላፊ ተናግረዋል። አራት ደቂቃ ርዝማኔ ባለው እና በቤተክርስትያኑ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው ድምጽ ላይ ጳጳሱ “ማንም ይሁን ማን” ይህንን ላደረገው ግለሰብ ይቅርታ አድርጌያለሁ ሲሉ ይደመጣሉ።

“እናም ለአንተ ሁልጊዜ እጸልያለሁ። ይህንን እንድታደርግ የላኩህ ማንም ይሁኑ ማን በኃያሉ ኢየሱስ ስም ይቅርታ አድርጌላቸዋለሁ” ብለዋል። “የክርስቶስን ተግባር እንድትፈጽሙ እፈልጋለሁ። ጌታችን ክርስቶስ እንድንጣላ በፍጹም አላስተማረንም። መጥፎ ስራ እንድንሰራ አላስተማረንም” ብለዋል።

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ስለ ጊዜ.....

ኒዉዬርክ ከካሊፎርኒያ በ 3 ሰዓት ትቀድማለች ነገር ግን ይህ ካሊፎርኒያን ቀርፋፋ አያደርጋትም ምክንያቱም የራሷ ጊዜ አላትና ፡፡

አንዳንድ ሰዉ በ22 አመቱ ይመረቃል ነገር ግን ጥሩ ስራ ለመያዝ 5 አመት ይፈጅበታል፡፡

አንዳንዱ በ25 አመቱ የድርጅት ሃላፊ ሆኖ በ5ዐ አመቱ ሲሞት ሌላዉ በ50 ዓመቱ ሃላፊ ሆኖ እስከ 9ዐ ዓመት ይኖራል፡፡

ኦባማ በ55 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጨረሰ ነገር ግን ትራምፕ በ7ዐ ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጀመረ! ይሄ ትራምፕን ኀላ ቀር አያደርገዉም፡፡

ጊዜ በሕይወታችን ወሳኝ ነገር ነዉ ፡፡ ፈጣሪ በጊዜዉ ሁሉን ነገር ዉብ ያደርጋል

ስለዚህ.... ከሁሉ በኋላ የቀረን ወይም ወደፊት የቀደምን አይምሰለን ሁሉም ሰዉ የራሱ የሆነ የኑሮ ሩጫና የተፈጠረበት አላማ አለዉ! ሁላችንም የራሳችን የሆነ የጊዜ ክልል አለን!

Dr. Mihret Debebe

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
በአዲሶ አበባ በዛሬዉ ዕለት በጣለዉ ከባድ ዝናብ የ 4 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር አስታዉቋል ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
እግር ኳስ በኢትዮጵያ ተዓምራቱ እንደቀጠለ ነው።

ይህ ክስተት ጎል አግብተው ደስታቸውን እየገለፁ ይመስላል ግን አይደለም ዳኛውን ከበው እያናገሩት ነው። አንዱ ተጨዋች ለማናገር ሜዳው ሁላ አልበቃውም ተጨዋች ላይ ወጥቶ ነው የሚያናግረው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
⚡️በካንሰር የሚሰቃየው አንድ የላኦሺያ ስደተኛ በአሜሪካ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ፓወር ቦል ሎተሪ አሸንፏል።

ገንዘቡን ካንሰሩን ለሚያከመው ለአንድ ጥሩ ሐኪም እንደሚያውለው እና ቤተሰቡንም እንደሚረዳ ተናግሯል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
"አንዱ ሰለ ሁሉ ሞተ" (2ኛ ቆሮ ም 5:14)

ለመለው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ መታሰቢ ዕለት በሰላም አደረሳቹ🙏

መልካም በዓልን

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
በምሥራቅ ወለጋ ዞን ሁለት ጭንቅላት ያለው ህጻን ተወለደ።

በኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ ትላንት ከረፋዱ 10 ሰዓት ላይ አንዲት እናት በተደረገላት የቀዶ ህክምና ከአንገት በላይ ሁለት ጭንቅላት (Dicephalic parapagus) ያለው ወንድ ልጅ፤ ክብደቱ 4.2 ኪ.ግ የሚመዝን በሰላም ተገላግላለች።

ልጁ የተወለደው በሲሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን በሆስፒታሉ የህጻናት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ቶኩማ ባይሳ የልጁን ቀጣይ ህይወት ለመወሰን ወደ ከፍተኛ ሆስፒታል ሪፈር እንዲደረግ መወሰኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ቶኩማ አክለውም፥ እናትየው የመጀመሪያ ልጇ እንደሆነ ጠቅሰው አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳለች ገልጸዋል።

ዘገባው የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ዲቪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ ሆኗል።

የአሜሪካ ዲቪ (Diversity Visa) ሎተሪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ መደረጉን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አሳውቋል።

መ/ቤቱ፥ አመልካቾች መመረጥ አለመመረጣቸውን / ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማየት የሚችሉት በ dvprogram.state.gov/ESC/ ላይ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት #ብቻ መሆኑን አሳስቧል።

ከዚህ ውጭ የዲቪ ውጤት የሚታይበት ምንም አይነት መንገድ የለም።

N.B. ዲቪ የሚደርሳቸው ሰዎች የሚስጥር ቁጥሩን እስከ ቀጣይ አመት መስከረም መጨረሻ ቀናት መያዝ አለባቸው።

ምናልባትም  " ዲቪ ደርሷችኃል ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው የምንደውለው፣ ኢሜል / ቴክስት መልዕክት የሚንልከው " የሚሉ አጭበርባሪ ስለሚኖሩ ጥንቃቄ አድርጉ ተብሏል።

እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ፥ የዲቪ ተመራጭ መሆን ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሆንም።

የዲቪ ሎተሪ ተመራጭ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ሲሆን በቀጥታ ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሰጥም።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
በ55,000 ብር ከገዛናው በሬ በ100,000 ብር የሚገመት ወርቅ ተገኘ።

በወላይታ ዞን በዳሞት ፑላሳ ወረዳ ሻንቶ ከተማ ለትንሳኤ በዓል ለእርድ በ55,000 ብር ከተገዛው በሬ የተገኘው ወርቅ በ100,000 ብር ተሽጧል።

ከዚህ በፊት በወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ ለገና ከታረዱት በሬዎች በ235,000 ብር የሚገመት ወርቅ መገኘቱን መዘገባችን የሚታወስ ነው።

መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ።

Via:- Bonga Ethiopia

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ይህ ወጣት ቲክቶከር በቁጥጥር ስር መዋሉን ታውቋል።

አቶ አለሙ ቢጫ ለተባሉ ግለሰብ ህክምና በቲክቶክ የተሰበሰበ 350 ሽህ ብር "ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ"በማለት በአደባባይ የተናገረው ወጣት ዛሬ ሚያዚያ 28/2016 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

የጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የቅን ልቦች ከተባለ ድርጅት አቤቱታ ቀርቦለት ወጣቱን ሲፈልግ መቆየቱ ተሰምቷል።

ወጣቱ ሰሞኑን አጠፋሁት ያለውን 350 ሽህ ብር ለታካሚው አለሙ ቢጫ መመለሱ ታውቋል።ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ በዋስትና እንደሚለቀ ይጠበቃል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ብዙ ዜጎቻቸውን በስቅላት የሚቀጡ ሀገራት እነማን ናቸው🤔

እንደ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከሆነ የሞት ፍርድ ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን ፍርዳቸው በስቅላት ወይም አንገታቸው ተቀልቶ የሚገደሉ እንዳሉም ተገልጿል፡፡

በ2022 ዓመት ብቻ 2 ሀገራት ዜጎቻቸውን በስቅላት ቀጥተዋል የተባለ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ መከሰት በሞት የሚቀጡ ዜጎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓልም ተብሏል፡፡

ቻይና ብዙ ዜጎቿን በስቅላትበመቅጣት ከዓለማችን ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን በዓመት በአማካኝ 1 ሺህ ዜጎችን በስቅላት ቀጥታለች፡፡

ሌላኛዋ ሀገር ኢራን ስትሆን ከ570 በላይ ዜጎችን በስቅላት ስትቀጣ አፍሪካዊቷ ግብጽም ዜጎቿን በስቅላት ከሚቀጡ ሀገራት መካከል ተጠቅሳለች፡፡
ሳውዲ አረቢያ፣ አሜሪካ እና ሲንጋፖር በተጨማሪነት የተጠቀሱ ሀገራት ሲሆኑ ሀገራቱ ዜጎቻቸውን በሞት እየቀጡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ዛሬ የአህዮች ቀን ነው ስለ አህያ አስገራሚ ተፈጥሮ እንንገራችሁ

1. አንድ አህያ ከርሱ ተመሳሳይ መጠን ካለው ፈረስ በጉልበት ይበልጣል።

2. አህዮች አራቱንም እግሮቻቸውን በአንድ ጊዜ ማየት ይችላሉ።

3: የአህያ ወተት የምድራችን ውድ ወተት ነው።

4. የአህያ ጩኸት በበረሃ ውስጥ እስከ 60 ማይል ድረስ ይጓዛል

5. አህዮች 95% የሚሆነውን በመጠቀም በሚያስደንቅ ሁኔታ ቀልጣፋ የምግብ መፍጫ ሥርዓት አላቸው።

6. ጤናማ አህዮች ከ50 አመት በላይ ሊኖሩ ይችላሉ

9. ዓይነ ስውር አህያ ብዙ ጊዜ ከሚያይ አህያ ጋር ይተሳሰራል። የሚያየው አህያም በደንብ ይመራዋል

10. አህዮች በሌሎች እንስሳት ላይ የተረጋጉና ጥቃት ማያደርሱ ናቸው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ለስድስት ዓመታት ባለቤቱን ቤት ውስጥ ቀብሮ ቤተሰቦቿን አረብ ሀገር ሄዳለች ብሎ ያታለለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ ፡፡

በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ ውስጥ አቶ ደበበ ተሰማ እና ወ/ሮ ዝናሽ ባይሳ የተባሉ ጥንዶች ከ2004 ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ አንድ ልጅ አፍርተው በትዳር አብረው ይኖሩ እንደነበር የሸገር ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ  ከ2004 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ሚስት ወ/ሮ ዥናሽ ወደ አረብ ሀገር ሄዳ ነበር፡፡ ከአረብ ሀገር ስትመለስ አንድ ልጅ ወልደው በመኖር ላይ ሳሉ ከቆይታ በኃላ ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ነው ምሽት ላይ  ሚስት በድጋሚ ኮንትራት ስላላት ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ ሀሳብ ታቀርባለች ባል ግን በዚህ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡

ከሀገር መውጣት  እንደማትችል እና እዚው አብረን መኖር አለብን በማለት በሀሳቧ እንደማይስማማ ያሳውቃታል፤ በሁኔታው ወደ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ውስጥ ይገባሉ  ጭቅጭቁ እና አለመግባባቱም ከሮ ባል አካፋ አንስቶ የሚስቱን ጭንቅላቷን ከመታት በሓላ በህይወት ትኑር አትኑር የሚለውን ሳያረጋግጥ ቤት ውስጥ ጭቃ ለመመረግ የተቆፈረ የአፈር ጉድጓድ ውስጥ ይቀብራታል፡፡

ባል ከሶስት ቀን በሓላም ወደ ቤተሰቦቿ በመሄድ ልጃቸው  ወደ አረብ ሀገር እንደሄደች ይነግራቸዋል፤ ቤተሰቦቿም እንዴት ሳትነግራቸው እንደሄደች ላቀረቡለት ጥያቄ እንዳትሄድ እናንተ ስለከለከላቿት ነው ብሎ ያሳምናቸዋል እነሱም ይቅናት በማለት ጉዳዩን እንደተውት  ተገልፆአል፡፡

በዚህ ሁኔታ ግን ለ6 ዓመት ያህል ቤተሰቦቿ ስለሷ ምንም አይነት መረጃ ባለማግኘታቸው ተጠራጥረው ባልን ይጠይቁታል ባልም እሱ ጋር እንደምትደውል እና የቤት እና የመኪና መግዣ እስኪሞላላት ወደ ሀገር አልመለስ እንዳለችው ለቤተሰብ ይናገራል፡፡

ቤተሰቦቿም በሁኔታው በድጋሚ ጥርጣሬ ውስጥ ስለገቡ ለፖሊስ ያመለክታሉ። ፖሊስም ጉዳዩን ለማጣራት  ኢምግሬሽን እና ዜግነት ምዝገባ አገልግሎት ያመለከትታል በዚህም ወ/ሮ ዝናሽ ወደ ሀገር ውስጥ መመለሷን እንጂ ከሀገር መውጣቷን የሚያመላክት መረጃ እንደሌለ ለፖሊስ መረጃው ይደርሰዋል፡፡

ፖሊስ በቀጥታ ባለቤቷን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማጥራት ሲጀምር አቶ ደበበ ሚስቱን ለስድስት ዓመታት  ቆፍሮ መቅበሩን እና ቤተሰቧን ሲያታልል እንደነበር  ቃል ይሰጣል በዚህ መሰረትም የግለሰቧ አስክሬንም ተቆፍሮ እንዲወጣ የኦሮሚያ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ክትትል በማድረግ ለጳውሎስ ሆስፒታል ፓቶሎጂስቶች አስክሬኑን እንዲመረምሩ በመደረጉ የአስክሬም ምርመራው ለፖሊስ ይደርሰዋል፡፡

የሸገር ከተማ ፖሊስ እና የገላን ከተማ ፖሊስ ባደረጉት ምርመራ ባል ጥፋተኛ መሆኑ በመረጃ በመረጋገጡ የምርመራ መዝገቡን ለሸገር ከተማ ዓቃቢ ህግ ተልኳል፡፡ ዓቃቢ ህግም በአቶ ደበበ ላይ  ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ መስርቶበት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ተከሳሽ ደበበ ተሰማ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የሸገር ከተማ አስተዳዳር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሸገር ከተማ አስተዳደር የህፃናት እና ሴቶች ጉዳይ ፅ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ረቢሱ ደቻሳ ጨምረው መናገራቸውን ብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥንን ጠቅሶ ዳጉ ጆርናል አስነብቧል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
2024/05/15 17:39:28
Back to Top
HTML Embed Code: