Telegram Web Link
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ጥር 06/2012 (15 January 2020)
Educational Strategy Center
6 - ቦታዎች በ0አመት
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ጥር 07/2012 (16 January 2020)
Yuncheng Cylinder Manufacturing PLC
6 - ቦታዎች በ0አመት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

#.ልዩ የማይቀርበት የዕቅበተ እምነት ጉባኤ#

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች አስቀድመን በልዑል እግዚአብሔር ስም የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን የፊታችን ዓርብ ከመጋቢት 11 ጀምሮ እስከ13/07/2012 ዓ/ም ድረስ 💠 በ ካራ ቆሬ ረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ-ክርስቲያን 💠 ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በጋራ በመሆን ልዩ የዕቅበተ እምነት ጉባኤ የተዘጋጀ ሲሆን እርሶም የመርሐ-ግብሩ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ በአክብሮት ጋብዘንዎታል።
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
#መርሐ_ግብሩ_ከያዛቸው_መካከል

፩ ትምህርተ ወንጌል
፪ የበገና መዝሙር
፫ ምክረ አበው
፬ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጥናታዊ ገለፃ በፕሮጀክተር የተጋዘ

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

ምክረ አበውን በተመለከተ ከምዕመናን የተነሱ ጥያቄዎች መልስ ይስጥበታል።

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

"ኑ እና ስለቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታ እንወቅ እንረዳ"

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

የማህበሩ አባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑና Join ይበሉት።

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
@Rebi_Medhanealem_Church
@Rebi_Medhanealem_Church
@Rebi_Medhanealem_Church
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
# ህልመ ሌሊት (በህልም መርጨት)
በአፍላ የጉልምስና ወቅት አባለ ዘርዕ ወደ ሙሉ የዕድገት ደረጃ መድረስ ብቻ ሳይሆን መሥራትም ይጀምራል፡፡
በዚህ ወቅት ከኃፍረተ አካል ዘርዓ ብእሲ የተባለ ፈሳሽ ነገር ይወጣል፡፡ የወንድ ወጣቶች ሰውነት ይነስም ይብዛ በየጊዜው "ዘርዓ ብእሲ" ወይም "የወንድ ዘር" ተብሎ የተጠቀሰውን ፈሳሽ ንጥረ ነገር ያስወጣል፡፡ ለዘር የበቁ ወጣቶች ዘር የሚከፍሉት ወይም የሚወጣቸው በልዩ ልዩ መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም በሚያልሙበት ወቅት ነው፡፡ የዚህ አይነቱን ሕልም መጽሐፈ መነኮሳት በአንድ ስፍራ "ሕልመ ጽምረት" በሌላ ቦታ ደግሞ "መስቆርርት ሕልም" ሲለው ይገኛል፡፡ ሕልሙን ያየው ሰው ደግሞ "ዝንየት መታኝ" ወይም "ሕልመ ሌሊት አገኘኝ" ይላል፡፡
"ሕልመ ሌሊት" ኃጢአት ነውን?
በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ የሚከሠት ሕልመ ሌሊትን እንደ ኃጢአት እንዲቆጠርና እንዳይቆጠር የሚያደርጉ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ስለዚህ ህልመ ሌሊትን በጥቅሉ ኃጢአት ነው ወይም አይደለም ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን እንደ ኃጢአት እንዲቆጠር የሚያደርጉ ሁኔታዎችን በመጠኑ መዘርዘር ይቻላል....[Read more](https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEW4c6a4s66UQCzegg)
እቺን ነገር ሁላችንም ፌስቡክ ላይ ከዘመዴ ፎቶ ጋር ፖስት እናድርጋት

Facebook # free ZEMDKUN BEKELE Free speech Right # Speech Right # Speech Right
Facebook # free ZEMDKUN BEKELE Free speech Right # Speech Right # Speech Right
Facebook # free ZEMDKUN BEKELE Free speech Right # Speech Right # Speech Right
Forwarded from ምጥን ቅመም (Mitin Kimem) (Yishak Kelemework)
ክፍል ስምንት

በጸሎት ሰዓት ውጋት እና እራስ ምታት

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ

ተወዳጆች ሆይ በክፍል ሰባት የአየር አጋንንት በጸሎት ጊዜ በሆድ ቁርጠት፣ ሆድ በመንፋት፣ በግሳት እና በፈስ እንዴት እንደሚፈትነን ተመልክተናል፡፡ እነሆ በዚህ ክፍል ደግሞ የአየር አጋንንት በጸሎት ጊዜ በእራስ ምታት እና በውጋት እንዴት እንደሚፈትነንና እንቅፋት እንደሚሆንብን እናያለን፡፡ ቅዱሳን አምላክ ምስጢሩን ይግለጽልን፡፡

ወዳጆቼ የአየር አጋንንት እና ሌሎችም ርኩሳን መናፍስት ጸሎታችንን ለማደናቀፍ፣ ሐሳባችንን ለመበታተን የሚጠቀሙበት ስልት አንዱ ውጋት፣ ክፍተኛ እና ድንገተኛ እራስ ምታት ነው፡፡ ወጋቱም ድገተኛና ከፍተኛ ውጋት ነው፡፡ ይህን መሰል ፈተና ቅዱስ ጳውሎስ እጅጉን ተፈትኖበታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የሥጋዬ መውጊያ›› በማለት የጠቀሰው በውጋት፣ በከፍተኛ እራስ ምታት ይፈተን ስለ ነበር ነው፡፡ /2 ቆሮ 12÷7/ የአየር አጋንንት ጭንቅላታችንን ግራ እና ቀኝ፣ ደረታችንን፣ ጀርባችንን፣ ሆዳችንን በውጋት ቅስፍ አስርጎ ይይዘናል፡፡ ይህ ስልቱ አንደኛ የጸሎታችንን ተመስጦ ለማሳጣት ሲሆን ሁለተኛ ‹‹አሞኛል፣ መጸለይ አልቻልኩም›› ብለን እንዳንጸልይ ለማድረግ ነው፡፡ አንዳንዶች በከፍተኛ ውጋት እየተሰቃዩ ሐኪም ቤት ሄደው መፍትሔ ያጣሉ፡፡ ሌሎች ዘላቂ ሳይሆን ጊዜያዊ መፍትሔ ያገኛሉ፡፡ ግን ችግሩ አይለቃቸውም፡፡ አጋንንት በደዊ እየተመሰለ ስለሚዋጋን ነው ወጋት፣ ቁርጥማት የሚያሰቃየን፡፡ ስለዚህ በጸሎታችን ጊዜ የአየር አጋንንትና ሌሎቹም መናፍስት በውጋት ስለሚዋጉን ቻል አድርጎ ፈተና መሆኑን አውቀን ልንጸልይ ይገባል፡፡

ወዳጆቼ በአሁን ሰዓት እራስ ምታት የብዙ ሰዎች ችግር እየሆነ ነው፡፡ ለእራስ ምታት ሕመም በሳይንሱ ብዙ ምክንያት እና መላ ምት ቢቀመጥለትም በመንፈሳዊው ግን እራሳችን ወይም አእምሮአችን የሰውነታችን ሞተር ስለሆነ አጋንንት እኛን ለመዋጋት ይጠቀምበታል፡፡ እራሳችን በሕመም ከተያዘ ሙሉ ሰውነታችን ሥራውን አቀላጥፎ ለመሥራት አይችልም፡፡ ቢችልም በሚፈለገው ደረጃ አይደለም፡፡ አጋንንት እራሳችንን/አእምሮአችንን በፍልጠት፣ በውጋት በመምታት ጸሎት እንዳንጸልይ ብንጸልይም ድንዝዝ ብለን እንድንጸለይ ያደረገናል፡፡ በእራስ ምታት ተይዘን የምንጸልየው ጸሎት ተመስጦና የሐሳብ መሰብሰብ ስለማይኖረው ‹‹እንደዚህ እያመመኝ ከምጸልይ ቢቀርስ፣ እግዚአብሔር ሕመሜን ያውቀዋል›› ብለን በቀላሉ ጸሎታችንን እንድንተው ያደረገናል፡፡

የአንዳንዶቻችንማ ልክ ጸሎት እንደጀመርን ከየት መጣ እስክንል ድረስ እራስ ምታት ይነሳብናል፡፡ እራስ ምታቱም አንጎላችንን ግራና ቀኝ፣ ዓይናችንንና ቅንድባችን ሥር የሕመም ስሜት ይሰማናል፡፡ ይህ የሕመም ስሜት የጸሎታችንን ሞራል ስለሚቀንሰው የመጸለይ ፍላጎታችን ሙትት ይላል፡፡ ወዳጆቼ ስንጸልይ ውስጣችን ያለው አጋንንት፣ ዓይነ ጥላው፣ ዛሩ፣ መተት ድግምቱ ስለሚጨንቀው እኛን በውጋት በእራስ ምታት ያስጨንቀናል፡፡ ከመናፍስቱ ጎራ በሕክምና መፍትሔ በማይገኝላቸው ሕመም እየተመሰለ ሰዎችን ከሚያሰቃዩት ከአየር አጋንንት በተጨማሪ የዛር መናፍስት አንዱ ናቸው፡፡

ሌሎቻችንን ደግሞ እራሳችንን ለሁለት ከፍሎ ግማሽ ፊታን የእኛ ፊት እስከማይመስለን ድረስ ያመናል፡፡ ሰው ሲናገረን በተለይ ጮክ ካሉ ጆሮአችን ውስጥ ገብተው የጮሁ እስኪመስለን ያመናል፡፡ ሐኪሙም ‹‹ማይግሪን›› ብሎ ስም ያወጣለታል አጋንንቱም የማይድን እራስ ምታት ሆኖ ይቀመጥብናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ስለዚህ በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፣ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ›› በማለት አጋንንት የሥጋው መውጊያ ሆኖ ይፈትነው እንደነበር ጽፎልናል፡፡ /2ኛ ቆሮ 12÷7/ ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስን የፈተነው አጋንንት እኛንም በእራስ ምታት በውጋት፣በቁርጥማት ሊፈትነን ስለሚችል በእነዚህ አጋንንታዊ ችግር ምክንያት ጸሎታችንን ልንተው አይገባም፡፡

ከፍተኛ የእራስ ምታት ያለባችሁ ሰዎች ጻድቃኔ ማርያምን ተሳልማችሁ ከዛ አጃና ቅዱስ ሚካኤል ሔዳችሁ እዛ ለራስ ምታት ፍቱን የሆነ ጸበል አለ እሱን ብትጠመቁ ይለቃቹኃል፡፡

‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6

‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8

ክፍል ዘጠኝ

በጸሎት ሰዓት የዝሙት ሐሳቦች

ይቀጥላል ….

ግንቦት 14-9-12 ዓ.ም
አዲስ አበባ
@Mitinkimem
@Mitinkimem
@Mitinkimem
Forwarded from ምጥን ቅመም (Mitin Kimem) (Yishak Kelemework)
Ethio Jobs
#ክፍል_ስድስት

#በጸሎት_ሰዓት_ማዛጋት

/ማዛጋት የአየር አጋንንት ብቻ ሳይሆን የጠቋርም ምልክት ነው/

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ

ተወዳጆች ሆይ በክፍል አምስት በጸሎት ሰዓት በእንቅልፍ እና በመደበት እንዴት እንደሚፈትነን አይተናል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ ስለ ማሳጋት ስናነሳ ማዛጋት ከመሰልቸት እና ከድካም እንደሚመጣ እና በተለይም የማይግሪን ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክት እንደሆነ የሥጋ ጠቢባቡ ይናገራሉ፡፡ እኛ ግን ሲደክመን በነገሮች ስንሰላች የምናሳየው ማዛጋት ሳይሆን በጸሎት ሰዓት በልዩ ሁኔታ ስለምናዛጋው ነው፡፡

ወዳጆቼ ማዛጋት በጸሎት እና በቅዳሴ ሰዓት ላይ ጎልቶ ይታይብናል፡፡ በተለይ በጸሎት ሰዓት ደግሞ ይብስብናል፡፡ አንዳንዶች በግል፣ በቤተሰብ እና በማሕበር ጸሎት መካከል ያዛጋቸወዋል፡፡ ሌሎት በቅዳሴ መሐል ያዛጋቸዋል፡፡ በጸሎት ሰዓት የምናዛጋው ወይም የምናፋሽገው ውስጣችን ያለው አጋንንት ጸሎቱ ሲከብደው፣ በስውር ሲጨንቀው፣ አለሁ ሲለን የሚያሳየው ባሕርይ ነው፡፡ አንዳንዶች ማዛጋትን የርኩስ መንፈስ ውስጣችን የመኖሩ ምልክት አድርገው ላይቀበሉት ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንዳየነው ማዛጋት ከድካም፣ ከመሰልቸትና እንዲሁም ከለመድነው ሱስ መቋረጥ ጋር ስለሚገናኙት ነው፡፡

ለምሳሌ ቡና መጠጣት ያስለመድንበት ሰዓት ሲያልፍ ልናዛጋ ወይም ልናፋሽግ እንችላለን፡፡ ግን በጸሎት መሃል የምናዛጋው በፍጹም ከልማድና ከሱስ ጋር ይገናኝም፡፡ በነገራችን ላይ የቡና፣የጫት እና የሌሎችም ነገሮች ሱሰኞች ሆንን የሱስ ሰዓታችን ሲያልፍ የምናዛገው አምሮን ሳይሆን ያስለመደን አጋንንት ‹‹ሰዓቴ አልፏል ምሴን አምጣ›› እያለ እያዛጋ እየጠየቀን ነው፡፡ አንድም ሰዓቴ አልፏል እያለ እያስታወሰን ነው፡፡ እስኪ ልብ በሉ አንድ የጫት ሱሰኛ ለአንድ ሳምንት ጫት መቃሙን ቢተው በየሰዓቱ ነው የሚያዛገው፡፡ ግን አንድ ሰው ለአንድ ሳንምት እንጀራ ትቶ ሌላ ነገር ቢበላ እንጀራ ባለመብላቱ አያዛጋውም፡፡ ምናልባት ሊያምረው ይችላል፡፡ ማዛጋት ቢኖርብን ከጊዜ በኋላ የለመድነው ጫት ሳይሆን ከሕፃንነት ጀምሮ ስንበላ ያደግነውን እንጀራ ስንተው ነበር፡፡ ስለዚህ በሱስ ማጣት ማዛጋት እና በጸሎት ሰዓት ማዛጋት ቅሉ ቢለያይም የአጋንንት ነው፡፡

አንዳንዴ ከማዛጋታችን ወይም ከማፋሸጋችን የተነሳ እራሳችንን መቆጣጠር አንችልም፡፡ ማዛጋቱ ወይ ማፋሸጉ እየባሰ ሲሄድ ሳናለቅስ እንባችን ከዓይናችን ላይ ይንጠባጠባል፡፡ ከማዛጋታችን የተነሳ አገጫችን የሚላቀቅ፣ አፋችን የሚሰነጠቅ እስኪመስለን ልንደርስ እንችላለን፡፡ አንዳንዶች ጸሎታቸውን በማዛጋት ጀምረው በማዛጋት የሚጨርሱ አሉ፡፡ ግን ይህ በሚሆንበት ሰዓት በፍጹም አትሳቀቁ ይልቁንም በጸሎት በርቱ፡፡ የሚፈትናችሁን መናጢ በጸሎታችሁ ኃይል አይታችኃልና፡፡ በጸሎት ሰዓት ማዛጋት አጋንንት እንደሚፈትነን ምልክት ነው፡፡ በተለይ ዓይነ ጥላ፣ ዛር በተለይም ጠቋር፣ መተት፣ እጀ ሰብዕ፣ የዛር ብዳ ወዘተ ካለብን መንፈሱ በውስጣችን ሲጨናነቅ እናዛጋለን፡፡

ወዳጆቼ ጠቋር የተሰኘ ከእናት አባት ከአያት ቅድመ አያት ሲዋረሰን፣ ሲያድርብን መንፈሱ በውስጣችን ይደበቃል፡፡ ከዛ ብርቱ ጸሎት ስንጀምር መንፈሱ እራሱን ከማጋለጡ በፊት በማዛጋት ይገለጣል፡፡ በሚገርም ሁኔታ ማቆም እና መቆጣጠር እና ሰውን እስክናፍር ድረስ ያዛጋናል፡፡ በማዛጋት መካከል ሰውነታችን ይወጣጠራል፣ ከትከሻችን ወደ ኃላ እየሳበ ያንጠራራናል፣ ድምጽ ማውጣት እንጂ የሚቀረን ከመጮህ ባልተናነሰ መልኩ ሃሃሃሃ… እያልን በከፍተኛ ሁኔታ እናፋሽጋለን፡፡ ይህ ከአየር አጋንንት ለሌላ የዛር መንፈስ የሆነው የጠቋር ምልክት ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ እስኪ ወደ ኃላ ሂዱና በእናት በአባታችሁ እና በአያቶቻችሁ በልኩል የነበረውን በየዋህነት ከባዕድ አምልኮ ጋር የተገናኘ ነገር ጠይቋቸው፡፡ በእርግጠኝነት ‹‹አዎ በፊት ነበረ አሁን ትተውታል፤አያታችሁ ታመልክ ነበር ግን ትታ ንስሐ ገብታ ሞታለች፣ በፊት ሲወራ እሰማለሁ ግን እኔ አልደረስኩበትም ወዘተ ….›› እያሉ ይነግሯችኃል፡፡

እኛም ትተው ንስሐ ገብተው መቁረባቸውን፣መሞታቸውን ስናስብ መንፈሱ እኛ ጋር ያለ አይመስለንም፡፡ ወዳጆቼ የሚያመልኩት ቤተሰቦቻችን ንስሐ ገቡ እንጂ አጋንንትቱ ንስሐ አልገባም፡፡ በተሰቦቻችን ቆርበው ሞቱ እንጂ ያመልኩት የነበረው አጋንንት አይሞትም፡፡ የዘር ሐረጋችንን እየተከተለ፣ ዕድላቸውን እየከለለ፣ በቁማቸው እየገደለ ባዶ ያደርገናል፡፡

የማዛጋት ምልክት ስናይ በጸሎት ከበረታን በማዛጋቱ መንፈሱ ወደ መጋለጡ ይሄዳል፡፡ አጋንንቱ ሊለፈልፍ ይችላል፡፡ ስለዚህ በጸሎታችን ሰዓት እንዳንዴ ቤተሰቦቻችንና የሚያውቁን ሰዎች ፊት ልናዛጋ እንችላለን፡፡ ይሄ ሊያስጨንቀን አይገባም፡፡ ወዳጆቼ መቼም አጋንንት እንደ ነፋስ አይደል? በጸሎት ሰዓት በማዛጋት የሚፈትነን አጋንንት በጸሎት እየበረታን ከሄድን እንደ ጢስ እየተነነ፣ እንደ ጉም እየበነነ በመሄድ ከላያችን፣ ከዙርያችን ይርቃል፡፡ ያኔ ማዛጋት እና መወጣጠር፣ መንጠራራቱ ከእኛ ይወገዳል፡፡ ስለዚህ ማዛጋት በውስጣችን አንዳች የማናውቀው ክፉ መንፈስ የመኖሩ ምልክት ነው፡፡

‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6

‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8

ክፍል ሰባት
በጸሎት ሰዓት የሆድ ቁርጠት

/ሆድ መነፋት፣ ግሳት እና ፈስ/

ይቀጥላል ….

ግንቦት 13-9-12 ዓ.ም
አዲስ አበባ
👉👉👉@Mitinkimem👈👈👈
👉👉👉@Mitinkimem👈👈👈
👉👉👉@Mitinkimem👈👈👈
~ ከእኛዎቹ አፈጣድቆች
የወሀቢና የጴንጤ ኅብረት ይገርማል
*~★★~*

• በኢንቦክስ መጥቶ ምነው ጠፋህ ዘመዴ ከሚል ጉደኛ ይሰውራችሁ። ለማንኛውም htpp.www.tg-me.com/ZemedkunBekeleZ የሚለውን ቴሌግራም ቻናሌንም ተቀላቀሉ። ወጥር ዘመዴ !!

#ETHIOPIA | ~ ጎበዝ ኧረ ቢያንስ ፌስቡክህ ላይ ሼር አድርገው። አትፍራ አትንቦቅቦቅ። የትም ሁን የትም ሞት እንደሁ አይቀርም። ደግሞም ብሰደብ፣ ብወቀስ እኔው ነኝና አትፍራ።

•••
መስሎህ ነው እንጂ እግዚአብሔር ከእኔ የበለጠ ለስሙ ቀናኢ የሆነ ሊቅ ያስነሳል። እናም ብዙ አትደሰት። አትደሰት። እንደ ወሀቢ እስላም አንተም ኦርቶዶክሱ የተዋሕዶ ልጅ ነኝ ባዩ እኔን እንደ ጠላት አይተህ አትደሰት። ሆኖም ግን አንድ ቀን ዘመዴ እኮ ቢኖር የምትልበት ጊዜም ይመጣል። እኔ ዘመዴ ለአንተ ጠላትህ አይደለሁም። እንደ ቤትህ ውሻ ጮሄ ባስደነብርህ፣ እንቅልፍ ብነሳህ፣ ሌባ፣ ዘራፊ መጣ ብዬ ከሞቀ እንቅልፍህ ባናጥብህ እንጂ እንደ አራጅ ወሃቢ አንገትህን በካራ፣ እንደ ሲዳማ ጴንጤ ቤተክርስቲያንህን በቤኒዝን የማቃጥል ክፉ አይደለሁም። እናም ከአራጅ እኩል በእኔ መጥፋት አትደሰት። ግድየለም ከወሀቢው፣ ከሀገር አፍራሹ፣ ከመናፍቁ፣ ከሙሰኛው፣ ከነፍሰ ገዳዩ እኩል ጮቤ አትርገጥ። ደግሞም የፈለገ ቢሆን እኔው ዘመዴ የሀረሩ ቆቱ እኔው እሻልህሃለሁ። ከምር እንደ ወሀቢይ እስላሙና እንደ መናፍቁ መተባበር ባትችል እንኳ ከእነሱ ጋር እኩል አትውቀጠኝ። ግድየለህም። ጡር ነው።

•••
እኔ ለገንዘብ ብዬ የምሠራው አንዳች ነገር የለም። ለዚህ ነው በጀርመን ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር ጎዳና ላይ ከነ ልጆቼ ወድቄ እንኳ ችግሬን ውጬ በጎዳና ዋይፋይ ቀን ተሌት እንደ እብድ ለሀገሬና ለቤተ ክርስትያኔ ስጮህ የነበረው። አምስት ሳንቲም አላስቸገርኩህም፣ ወደፊትም አላስቸግርህም። ምን ሆነህ ነው ግን የፈለገ ብትጠላኝ እንዴት ከወሀቢይ እኩል ትጠላኛለህ? እሺ እነሱስ ይስደቡኝ፣ አንተ ግን ምንነክቶህ ነው? ምን በድዬህ ነው? ከምር ደስስ አይልም። ባይከፋኝም አዝንብሃለሁ። እኔ ባለማዕተብ ነኝ። እኔ ቢያንስ የድንግል እመቤቴ ልጅ ነኝ። እኔንማ ባትወደኝ እንኳ ከወሀቢይ እኩል አትውቀጠኝ። ባይሆን ለብቻችን ስንሆን ምንአባክንስና ነው ብለህ ሾጥ አድርገኝ። ግረፈኝ። ከወሀቢይ ጋር ግን እኩል በሰይፍ በሜንጫ አትጨፍጭፈኝ። ተው እንጂ በማርያም ምን አደረግኩህ። ይሄን ያህል ደስ አይልም።

•••
እኔ ዘመዴ ድሮም አሁንም፣ ነገም ከነገወድያም የአንተን እርዳታ፣ የአንቺንም እርዳታ አልፈልግም። እመቤቴን እውነቴን ነው የማናችሁንም እርዳታ አልፈልግም። የሞተ ሰውና ከሀገር የራቀ ሰው ጉዳቱና ጥቅሙ የሚታወቀው እየቆየ ሲመጣ ነው። አዎ ያን ጊዜ ነው ጉዳት ጥቅሙ የሚገባችሁ። የእኔና የእኔን መሰል ጥቂት ጓዶቼ ጥቅምና ጉዳትም እንደዙያው። አሁን ላለው የጨዋታ አሰላለፍ ቢያንስ ጎል ባናስገባ ውጤት አስጠብቀን ለመውጣት አናንስም። እናም ቢያንስ ቢያንስ እንደ እነሱ መተባበር ቢያቅታችሁ፣ እንደ እነሱ ተባብራችሁ ፌስቡኬን ማስከፈት ቢያቅቷችሁ፣ እንደነሱ ላይክና ሼር ለማድረግ ባትችሉ፣ ባትፈቅዱ እንዲየው ከወሀቢማ ጋር ሆናችሁ አትሙኝ፣ አትውቀጡኝ። ኧረ ይደብራል። ይታዘቡአችኋልም። የጊዜው ጊዜ የኋላ ኋላ ምቹ ጊዜ ሲገኝ መልሰው እንደ ጅጅጋው፣ እንደ ከሚሴው እንደ በሻሻው እናንተኑ አጋድመው ማረዳቸው ላይቀር ብዙ ባታሽቃብጡላቸው ደስስ ይለኝ ነበር። ከምር እውነቴን ነው።

•••
በግሌ እኮ እኔን ያስቀየመኝ እስላምም ሆነ ጴንጤ የለም። ሚስቴን የቀማኝ ጴንጤ የለም። ገንዘቤን የዘረፈኝ የስልጤ የወሀቢይ እስላም የለም። እኔን በግሌ የነካኝ አካል የለም። እኔን የበሰጨኝ፣ እንደ እብድም ቱግ አድርጎ ከእነሱ ጋር የሚያላትመኝ የማንም ጎጋ የወሀቢይ እስላም ተነሥቶ አምላኬን በክፍት አፉ ስለሰደበ፣ መጽሐፍ ቅዱሴ በወሀቢይ ስለተብጠለጠለ፣ የእመቤታችን ክብሯን ዝቅ ስላደረጉብኝ፣ ታቦታችንን፣ ቅዱሳት ሥዕላትንና ቅዱሳን አባቶቼን ስለሰደቡብኝ ነው በራሴ ተነሳሽነት ልካቸውን ነግሬ ጥጋቸውን ያስያዝኩት። እናም ማዕተብ አስረህ ከእነሱ እኩልማ አትዝመትብኝ።

•••
ትግሬ ሆነህ የምትጠላኝ ህወሓትን ስለነቀፍኩብህ ነው። ኦሮሞ ሆነህ የምትጠላኝ አራጅ ኦነግን ስለነቀፍኩብህ ነው። የእነ በጋበሻው ፍቅር፣ የትዝታው፣ የአሰግድ፣ የዘረፌ ፍቅር ስለበረታብህ ነው። የዐብይ ንግግር ስለማረከህ፣ መልኩን ወደህ እኔን ለምን ትተቸዋለህ ብለህ እንጂ ሌላ በምን ትጠላኛለህ። ውደደኝ አልልህም። ግን በቃ አለ አይደል ቢለዋ ከያዘ አራጅ ጋር ጧፍ ይዘህ አታስፈራራኝ። ከምር እውነቴን ነው።

•••
እንዳልኩህ ትንሽ የሚያመው ነገር በእኔ ከፌስቡክ መታገድ ከመናፍቃኑና ከአራጅ ወሀቢዩ እኩል የእኛው ጉዶችን ጮቤ መርገጥ ነው። እሱ ነገሩ ያማል። እነሱ እሳትና ጭድ ሆነው ሳለ በአንዱ በእኔ ላይ በዐዋጅ ኅብረት ፈጥረው ፌስቡክን ሲያጨናንቁት ሳይ እደመምባቸዋለሁ። የዘመድኩንን ፔጅ ለቃችሁ ውጡ ብለው መንጋቸውን አዘው ቤቴን ከክርፋት ሲያጸዱልኝ ሳይ ቀናሁባቸው። አንተ ግን ተደብቀህ ታነባለህ። ሼርና ላይክ እነሱን እንደሚያበሳጫቸው እያወቅክ ግግም ትላለህ። የእኔን ጦማር ሼር ወይ ደግሞ ላይክ ካደረግክ ክብርህ ይቀንሳል፣ እኔም በላይክና በሼር ቁጥር ዝናና፣ ሀብትና ሥልጣን የማገኝ ስለሚመስልህ በቅናት እጅህን አጣምረህ በጓዳ ተደብቀህ ታነበኛለህ። በል ሲልህ ደግሞ ከወሀቢ በላይ ወሃቢይ መስለህ ልትሰድበኝ፣ ልታማኝ ከች ትላለህ። ከምር ነውር ነው።

•••
ጴንጤና ወሀቢይ እንኳ ኅብረት ፈጥረው አላህ ወአክበር፣ ኢየሱስ ጌታ ነው እየተባባሉ ውኃና ዘይት የሆኑ ፍጥረቶች በጋራ ሲያድሙብኝ የእኔዎቹ ሰቀቀናም ቀናተኛ በቀቀኖች አብሮ ከጠላት ጋር ማዘጥዘጥ ነው የሚያመው። እነሱ እሳትና ጭድ ሆነው ሳለ በአንዱ በእኔ ላይ በዐዋጅ ኅብረት ፈጥረው ፌስቡክን ሲያጨናንቁት ሳይ ግን እደመምባቸዋለሁ። ከምር ይገርሙኛል። ተመልከቱ ቤንጤውም ወሀቢውም ምንም እንኳ በእምነት ባይመሳሰሉም የኦርቶዶክስ የሆነን ለማጥፋት ግን ውኃ ጠብሰን ካልበላን፣ በአንድ ፖፖ ካልተጸዳዳን ሲሉ ስታይ ትደነቅባቸዋለህ። በዚህ በኩል እኛ ገና ነን። በእኔ ከፌስቡክ መታገድ ከመናፍቃኑና ከአራጅ ወሀቢዩ እኩል አንዳንድ የእኛው ጉዶች ያለመጠን ማቃጠርና የሌለ ጮቤ መርገጥ ነው። እሱ ነገሩ ትንሽ ይገርማልም ያማልም። እንጂ ምንም የሚመጣ አዲስ ነገር የለም። በሆነው፣ በተደረገው ነገር የእኔን አሸናፊነት የሚያረጋግጥልኝ እንጂ ቅንጣት ታክል አንገት የሚያስደፋኝ አይደለም። አሸናፊ ነኝ።

•••
ዘመዴ ጣና ደረቀ፣ ላሊበላ ተሰነጠቀ፣ አክሱም ሊወድቅ ነው ወዘተ ለማለት በውስጥ መስመር የሚወተውተኝን ሰውዬና ሴትዮ እሺ ምን እናድርግ ስለው ስላት ጻፈው አንተ ብዙ አንባቢ አለህ ይሉኛል። ሲጻፍ ግን አንዲቷንም ጦማር ላይክም ሼርም አያደርጓትም። ተደብቆ መተኮስ ብቻ። የሼር ጥቅም ያልገባቸው፣ የላይክ ጥቅም ያልገባቸው ስንትና ስንት መቶ ኪሎ ምቀኛ፣ ፈሪ፣ አስተኳሽ ብቻ መሆን የሚፈልግ አለ መሰላችሁ። ሌላው ሞቶሎት እሱ ነፃ መውጣት የሚፈልግ። በዚህ በዚህ እነሱ ይበልጡናል።
ም።

•••
ለነገሩ እኔ ብቻዬን አይደለሁም። ዘወትር ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ የምላት የአምላክ እናት አማላጄ እመቤታችን እናቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ከእኔ ጋር ናት። ብቻዬን ሚልዮን ሆኜ እንድታይ ያደረገኝ እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ነው ስሙ የተመሰገነ ይሁን። ብቻዬንማ አይደለሁም። ቢሆንም ግን አያሸንፉንም እንጂ በመረዳዳት አሳምረው ይበልጡ
ቻዬን ሚልዮን ሆኜ እንድታይ ያደረገኝ እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ነው ስሙ የተመሰገነ ይሁን። ብቻዬንማ አይደለሁም። ቢሆንም ግን አያሸንፉንም እንጂ በመረዳዳት አሳምረው ይበልጡናል።

•••
እስከምችለው ድረስ እንደ ዜጋ ለሃገሬ እንደ አማኝ ለጥንታዊቷ ለእምዬ እናቴ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያኔ እመሰክራለሁ፣ እሟገታለሁ፣ እታገላለሁ። ከዚህ በኋላ ቀሪ ዕድሜዬን አላውቀውም። በህይወት እስካለሁ ድረስ ግን ትንፋሼ እስኪቋረጥ ድረስ ላልከዳት፣ ላላቆም ከወሰንኩም ቆይቻለሁ።

•••
እኔ ዘመዴ ትናንት እንኳን አላረፍኩም። አዲስ አበባ ውዬ ነበር የመጣሁት። ከአእምሮ በላይ የሆኑ ዕፁብ ድንቅ የሆኑ የምሥራቾችን ስሰማ፣ ሳይ ስመለከትም ነበር የዋልኩት። ከደስታ ብዛት እያለቀስኩ ነው የዋልኩት። ነገርየው የፌሴቡኬ በማይረባ ምክንያት መዘጋቱ ቢያናድድኝም እኔ ግን ሥራዬን አላቋረጥኩም። “ ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ 95% አልቋል። የሚቀረው ሰኔና ሰኞ መግጠሙ ብቻ ነው። ህልማችን ዕውን ይሆናል።

•••
አይሁድ ክርስቶስን ሰቅለው፣ ገድለው፣ ኩንታል ድንጋይ በመቃብሩ ላይ ቢጭኑም፣ እሳት የላሱ ነብር የሆነ የመቃብር ጠባቂዎችን በመቃብሩ ላይ ቢመድቡም ክርስቶስን ከመነሣት እንዳልከለከለው ሁሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ የኢትዮጵያን ትንሣኤ የፈለገ ተራራ ቢከመር ከመነሣት የሚያግድ፣ የሚከለክልብንም የለም። አንድስ እንኳ የሚከለክልብን የለም። አንዳችም አልኳችሁ። አንዳችም የሚያስቆመን ኃይል የለም። እኔ በበኩሌ የማይሞት፣ የማይደክም፣ የማይሸነፍ፣ የማይፈራ የይሁዳ አንበሳ ልብ ነው ያለኝ። እናም አታሸንፉኝም። ፈሪ ወሀቢይና ፈሪ መናፍቅ መቼም ቢሆን አያሸንፉኝም።

•••
እንደ ንሥር ታድሼ፣ እንደ አንበሳ እያገሳሁ፣ ኃይልና ሞገስ፣ ጉልበትም ጨምሬ እንደ አቦሸማኔ እየተመዝገዘግኩ እመለሰላሁ። እመጣለሁም። ትናንት 1500 የወሀቢይ እስላም ከፔጄ ለቅቆ ውልቅ ብሎ ወጥቶ ነበር። ዛሬ ሳየው ደግሞ ተመልሶ ቁጥሩ ከፍ እያለ ነው። የፌስቡኩ ቢቀር የቴሌግራም ቻናሌ ብቻ ራሱ ያለው ህዝብ ከበቂ በላይ ነው። ፌስቡክ የሚያዛልቅ አይመስልም። ወይም ደግሞ የእኛ የአይቲ ቡድን አባላት ፌስቡክን የሚተካ አፕ ፈጥረው እስኪያስረክቡን ድረስ በትእግስት መጠበቅ ነው። ያም ባይሆን አሁን በቴሌግራም ያለው ህዝብም ከበቂ በላይ ነው።

200 ሺ የማዕዶት ግሩፕ።
111 ሺ የራሴ የዘመዴ ቻናል
69 ሺ የማዕዶት ቻናል። ላይ ያለው ህዝብ ብቻውን በቂ ነው። ማዕዶታችን አልቋል። ከአየር ላይ ወደ ምድር መውረድ ብቻ ነው የሚቀራት። በርቱ ። እናንት ጥቂቶች በርቱ። መንጋውን እርሱት። መንጋ ዋጋ የለውም። አከተመ።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 28/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
ትክክለኛውን የቅዳሴ ስርዓት በደብረ አባይ ጣዕመ ዜማ ከነ ሥነ-ስርዓቱ እግዚአብሔር እንደፈቀደ ምስክር ባላቸው በመምህራኑ አንደበት እንማማራለን። ከዚያም ወደቀጣዩ ወንበር እንሸጋገራለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Siriate_Kidase_Wetesetio_Hizb
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
2024/06/01 02:44:22
Back to Top
HTML Embed Code: