ከዋኪብ
👉 ከዋኪብ በሚል መጠሪያ በመልካም ወንድማዊ ትስስር በአይነቱ ልዩ የሆነ
የጥበብ መድረክ ይዘንላቹ ወደ እናንተ ለመምጣት መሰናዶ ከጀመርን ወራት ተቆጥረዋል
ዐላማችንን አዉቀን :ራዕይ ለይተን
ግባችን መዳረሻችን እሩቅ መሆኑን ተገንዝበን
ከአላህ ሱብሀነ ወተዐላ በተሰጠን
የኪነ ጥበብ ተሰጥኦ ዘርፍ ዑማዉን ለማገልገል የድርሻችንን አሻራ ለማሳረፍ ዲኑን ለመኻደም እንሆ በጀመዐ ሆነን ለመስራት በአላህ ፈቃድ በመልካም እሳቤ እና በጥሩ ኒያ ተጣምረን ለመስራት በአብሮነት ተነስተናል
በዚህ ከዋኪብ አባላት ማእቀፍ ዉስጥ ሶስቱ ማዲሆች
👉 ሰልሀዲን ሁሴን
👉 አሚር ሁሴን
👉 ፉአድ ሸምሱ
እንዲሁም ሁለቱ ገጣሚያን
👉 ዑስታዝ ሰኢድ አህመድ እና
👉 አብዱልመሊክ ላሊ (ጎራዉ)
በአንድነት ተጣምረዋል
ይህ ልዩ የጥበብ መድረክ ፕሮግራም በአላህ ፈቃድ በቅርብ ግዜያት ወደ እናንተ ይደርሳል ።

Forwarded from አሚር ሁሴን//AMIR HUSSEN
Watch "ኹዝ ቢየዲ ያ ረሱለሏህ || በ ፉአድ ሸምሱ አዲስ መንዙማ || Fuad shemsu khuz biyedi ya resullah @AL Faruq Tube" on YouTube
https://youtu.be/kF8H56jr9Kg
https://youtu.be/kF8H56jr9Kg
YouTube
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሱለሏህ || በ ፉአድ ሸምሱ አዲስ መንዙማ || Fuad shemsu khuz biyedi ya resullah @ALFaruqTube
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
Like እና Share በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
የYoutube ቻናላችንን Subscribe በማድረግ በየጊዜው የሚለቀቁ Videoዎችን ይመልከቱ ||
https://www.youtube.com/c/ALFaruqTube
የፌስቡክ ገፅ ||
https://www.facebook.com/FALfaruuq/...
ቴሌግራም ||
https://www.tg-me.com/alfaruqtube
።።።።።።
ያ ሰይዲ …

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Jumma Mubarak 🕋🕌😍
Forwarded from አሚር ሁሴን//AMIR HUSSEN
Watch "አሚር ሁሴን አዲስ መንዙማ (#ሙሀመድ ነብዬ)2015 Amir hussen new memzuma 2022#አሚርሁሴን" on YouTube
https://youtu.be/U9Bw-ezHYsM
https://youtu.be/U9Bw-ezHYsM
YouTube
አሚር ሁሴን አዲስ መንዙማ (#ሙሀመድ ነብዬ)2015 Amir hussen new memzuma 2022#አሚርሁሴን
ድንበር አልባ ፍቅር ያዘኝ መዉደድ
ካንቱ ሙሀመድ
በናፍቆት ወጥመድ መጓዝ አልቻልኩም
❤ሙሀመድ ነብዬ ሰላም ዐለይኩም❤
አሚር ነኝ ለ አላህ ብዬ አወዳቹሀለዉ።
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️
@AMIR HUSSEN - official
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️
@Selehadin Hussen - official
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️
@Ethio Neshida…
ካንቱ ሙሀመድ
በናፍቆት ወጥመድ መጓዝ አልቻልኩም
❤ሙሀመድ ነብዬ ሰላም ዐለይኩም❤
አሚር ነኝ ለ አላህ ብዬ አወዳቹሀለዉ።
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️
@AMIR HUSSEN - official
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️
@Selehadin Hussen - official
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️
@Ethio Neshida…
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!
የመካ መኳንንት ግፍ በነብዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እና ባልደረቦቻቸው ላይ በርትቷል። ዱላ እና ግርፋቱ ያለማባራት እየዘነበ ነው። ያኔ ነብያችን ባልደረቦቻቸውን ከሀበሻ ቀጥሎ ወደ መዲና ይጓዙ ዘንድ አዘዙ። ትዕዛዛቸውም ተፈፀመ። በመዲና የሰፈሩት ሶሀቦች "ሙሐጂር" ተሰኙ። ታዲያ ከእነዚህ ሙሐጂሮች አንዱ የነብያችን ወዳጅ ፣ አጎት እና የጥቢ ወንድም የሆኑት ሰይዱና ሐምዛ (ረ.ዐ) ነበሩ። እንዲያ ከሚሳሱላቸው ተወዳጅ ሠው ተለይተው በመዲና መቀመጣቸው አክስቷቸዋል፣ በጀግንነት ጀብዳቸው ላይ የናፍቆት ካባ ተደርቦ ሸፍኖባቸዋል፤ እጅጉን በናፍቆት ይንከላወሳሉ። ሌት ተቀን ከመዲና ሰዎች እና ሶሀቦች ጋር በመሆን የመዲናን መግቢያ ተራሮች ያማትራሉ። ነብያችንን ናፍቀው ዛፍ እና ቆጡን እየወጡ ይጠባበቃሉ። ጊዜው ራቀባቸው።
ይህ የሰይዱና ሐምዛ ፍቅር በዓይናቸው ባላዯቸው የመዲና ነዋሪዎችም ላይ በርትቶ ታይቷል። "የአሏህ መልዕክተኛ አለ" ተብሎ ተነገራቸው እንጂ በዓይናቸው አልተመለከቷቸውም ፣ ውብ እጆቻቸውን አልዳበሷቸውም ፣ ጨረቃ መልካቸውን አላዩም ፣ ጣፋጭ ንግግሮቻቸውን አላደመጡም። ይህም ሆኖ የፀሀይን መውጣት ተከትሎ ቀድመው የከተማዋ ጫፍ ላይ በመውጣት ይጠብቋቸው ነበረ። በእንዲህ ያለ ሁኔታ በሰኞ ቀትር ላይ ከሩቁ ሁለት ሰዎች የመዲናን ጎራ እያቆራረጡ ብቅ ሲሉ አንድ የመዲና አይሁድ ወጣት ይመለከታል። ናፋቂዎቹ ፀሀዩ ስለበረታባቸው ወደየቤታቸው እየተመለሱ ነበረ። በዚህ ጊዜ "እናንተ የቂላህ ልጆች ሆይ! በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው ነብይ መጥቶላችኋል" እያለ ጮኸ። አንድ ወጣት አማኝም ድምፁን ከፍ አደረገና
"ها هو الرسول. اقبل الهادي البشير"
"እኚያው የአሏህ መልእከተኛ ፣ ቀጥተኛውን መንገድ አመላካቹ እና በመልካም አብሳሪው ነብይ መጡ" ሲል አዋጁን አወጀ። ታዲያ ይህ ወጣት ነብያችን የትኛው ፣ ሰይዲና አቡበክርም የትኛው እንደሆኑ አያውቅም ነበር። ግና ምፃታቸው በራሱ አንዳች የፍቅር መግነጢስ አሳረፈበትና በፍቅር ጥሪ ይጣራ ዘንድ ሳበው። እነዚያ ሳያዯቸው የናፈቋቸው ሰዎች በፍጥነት ወደ እርሳቸው ይገሰግሱ ጀመረ ፣ ሰይዳችንም ወደእነርሱ መጠጋታቸውን አፈጠኑት። ሰይዱና አቡበክር የፀሀዩን ሀሩር ሊከላከሉላቸው ሰይዳችንን በካባቸው አስጠልለዋል። በዚህ ነበረ ጉጉዎቹ የመዲና ሰዎች የሰይዳችንን እና የሰይድ አቡበክርን ማንነት ለይተው ለማወቅ የቻሉት። ሁሉም ወደ ነቢ ተጠጋ። ሰይዱና ሐምዛ ተጠግተው የናፍቆት ጥማቸውን በእቅፍ ጠጅ አረገቡት።
አንሷር ከሙሐጂር በአንድነት ተቀኝተው
طلع البدر علينا
እያሉ አሞገሷቸው። እርግጥም በዚያ ጠራራ ፀሀይ ውብ ጨረቃ ተፈልቅቃ መዲና ላይ ዘልቃለች። በእልልታ ተቀበሏቸው። ናፍቆታቸውን አቀዘቀዙ። በፍቅር ተገርፈው ፣ በናፍቆት ታስረው ከርመው በእይታ ታከሙ፣ በሰላምታ ተፈወሱ።
እጅግ ናፍቆት፣ እጅግ ፍቅር፣ ፍቅር ይህ ነው። ሳያዩ መናፈቅ።
#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!
✍️ Atiqa Ahmed Ali

(100 ሺ ሰብስክራይብ አመሰግናለሁ🙏)
https://youtube.co/@AMIRHUSSENofficial
[ لا يَشْكُرُ اللَّهَ مَنْ لا يَشْكُرُ النَّاسَ]
👉[ሰዎችን የማያመሰግን ሰው አሏህን አያመሰግንም።]
አሰላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዐ እንዴት ናቹ አልሀምዱሊላህ ዩቲዩብ ፔጅ በከፈትኩ በ አጭር ጊዜ ዉስጥ 100 ሺህ ሰብስክራይብ መግባት ችያለዉ። አሌሀምዱሊላህ እዚህ ደረጃ ለመድረሴ የ አንበሳዉን ድርሻ
የምቶስዱት እናንተ ናችሁ። ይህ ደስታ የ እኔ ብቻ ሳይሆን የ ሁላችንም ነዉ!! subscribe ላደረጋችሁኝ፣ ላበረታታችሁኝ ጭምር ነዉ 😍🙏ለዚህም ከልብ አመሰግናቹሀለዉ።
እንዲሁም ከ ጎኔ ሆናችሁ በብዙ ነገር ስታግዙኝ ሆነ ስደግፉኝ ለነበራችሁ ወንድምቼ ፣ የ ስራ ባልደረቦቼ በ እኔም እንዲሁም በ ወዳጅ አድናቂዎቼ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።🙏
😍አመሰግናለሁ😍
-ቤተሰቦቼን በተለይ እናቴን እንዲሁም ወንድሜ ሰለሀዲንን
-ለ ገጣሚ እና ዜማ ደራሲ አብዱል ማሊክ ላሊ (ጎራዉ)
-ኢትዮ ነሺዳ እና መንዙማ አባላት
- ለ ፉአድ ሸምሱ እና ለመላዉ የ ከዋኪብ አባላት በሙሉ
እንዲሁም ለ እኔ ስኬት ደፋ ቀና ስትሉ ለነበራችሁ ወንድም እህቶች በሙሉ ...🙏
ይህ ደስታ የእኔ ብቻ ሳይሆን የ ሁላችንም ነዉ።
↪️አዲስነትና ለውጥ የኛ አንጻራዊ እውቀት ነው።
አንተ የቻልከውን ካደረስክ በኃል ለውጤቱ አትጨነቅ ።
ከጥረትህ ውጭ ሆኖ ለሚከሰተው ነገርም በሐሳብ ወደኃላ እየተመለስክ '''በሆነ ኖሮ,,, በማለት አትብሰልሰል።
ሰበቡን አድርስ አላህ ያሳካልሀል።
እጅህን ወደ አላህ ዘርጋ እሱ ይቀበልሀል።
አሚር ሁሴን ✍
መልካም ቀን ተመኘሁ!!

Ethio Neshida & Menzuma
Photo
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!
የታመመ ሀኪሙን ይከጅላል። የተራበ ቀላቢውን ይሻል። የተጠማ የውሃ ጉድጓዱን ይምሳል። የጨለመው ኩራዙን ይለኩሳል። ያፈቀረ ተፈቃሪውን ያሳድዳል። እንዲህ ሆነና አንድ ዕለት ሰይዳችን ከመስጂዳቸው ጎራ ብለው ፀጉራቸውን ሊላጩ ተቀመጡ። ለዚህ የታደለ ሰው ፀጉራቸውን ሊቆርጥ ተሰየመ። ሶሀቦች ሁሉ ታደሙ። አፍጥጠው መጠባበቅ ጀመሩ። ለዘመናት ያልሙት የነበረ ይመስላል። ነብር ታዳኟን አሰፍስፋ የምትጠብቀውን ያህል እነርሱም የረሱልዬን ፀጉር ይጠባበቁ ጀመረ። ሁሉም ለራሱ ከጅሎታል። ሰይዲ ይህንን ጉጉታቸውን ያስተውላሉ። በእያንዳንዱ የፀጉር ዘለላቸው ላይ የተለያዬ ምስጢር አደረጉበት። ለእያንዳንዱ ሶሀባ ነሲቡን ከፈሉለት።
ፀጉር ቆራጩ ሲጨርስ ሰይዲዋ "በሶሀቦቼ መሀል አከፋፍለው" ሲሉ። አዘዙት። ሶሀባው ሁሉ መሻማት ጀመረ። አንድ ዘለላ ፣ ሁለት ዘለላ አንዳንዱ ከዚያም በላይ የደረሰው ነበረ። ከፊሉ ያሸተው ጀመረ። እኩሌታውም ይስመዋል። ሌላው እያየው ያነባል። በተወደደ እቃ ላይ አስቀምጠውታል። ይህንን ሁኔታ ከሩቅ ሆነው ሰይዱና አቡበክር ይመለከታሉ። ከነዚህ ውስጥ እጅግ አስደናቂ ነገር ተመለከቱ። ቀልባቸውን ገዝቷቸውል። በእርግጥ የአሏህ ስራ እያስገረማቸው ነው። የነብዪ የፍቅር መግነጢሳዊ ሀይል እያደነጋገራቸው ነው። ከእነዚያ ፀጉሩን ከሚሻሙት ሶሀባዎች መሀል አንዱ ሱሀይል ቢን አምር ሆኖ ተመለከቱት። አንድ ፀጉር ሲደርሰው ወዲያውኑ ወደ ዓይኑ አስጠግቶት ተንሰቀሰቀ። ይህንን በተመለከቱ ጊዜ እጅግ አለቀሱ። ቀልባቸውን አንከላወሱ። ምላሳቸውን አላወሱ።
"ትላንት ላይ በሁደይቢያ ስምምነት የነብዩን መልእክተኝነት መቀበል ተስኖት ስማቸውን ከነ ማዕረጋቸው ለመፃፍ የተፀየፈው ሱሀይል ዛሬ ከሶሀቦቻቸው ጎራ ሆኖ በፍቅራቸው ይገረፋል።" አሉ። በእርግጥ መድሀኒቱን አግኝቶ ነው። ለዘመናት የታመመውን ህመም ያሻሩለትን ሀኪሙን አፍቅሮ ነው። ትላንት ሊዋጋቸው ያሰፈሰፈ ሰው ዛሬ ነፍሱን ሊሰጣቸው ተማርኮ ነው። የፍቅር ማዕበል ተማቶት ነው። ከዚህ የበለጠ የፍቅር ምች አላስተዋልንም። የለይላ እና መጅኑንን ታሪክ አልናቅንም ሆኖም እጅጉን የበለጠው አለ። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሰው ሰውን ሲያፈቅር ሶሀባዎች ነብዩን ሲወዱ አየን። በጆሮ የሰማነውን ታድመን ያየን ያህል ተማርከን በልባችን አመንን። አንድ እናክልና የበለጠ እንተዓጀብ!
ሰይዱና ኻሊድ ቢን ወሊድ በአንድ ዘመቻ ከጦር ቆባቸው ውስጥ ያስቀመጡት የሰይዲ ፀጉር ከቆባቸው ጋር ይጠፋባቸዋል። በተፋፋመ ጦር፣ በተጋጋመ ውጊያ ውስጥ ሆነው ባዘኑ። ትዕዛዝ ለጓዶቻቸው አስተላለፉ። ፈልገው ያመጡላቸው ዘንድ አዘዙ። እስኪመጣላቸው ድረስ ታመሙ፣ በጠና ደከሙ። በማይወጡት ለቅሶ ተዋጡ። ጓዶቻቸው ፈልገው አገኙና አመጡላቸው። እርሳቸውም ተደስተው ፈገግ አሉ። "ይህንን ፀጉር ከእኔ ጋር ይዤ በተገኘሁበት ዘመቻ ሁሉ ድል የእኔ ነበረ" ሲሉ ተናገሩ። ህመማቸውን ተፈወሱ። ሀዘናቸውን ተካሱ። ይህ ነው የፍቅር ህክምናው።
#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚

اَللَّهُمَّ صَلِّ عَلى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ اَلْفَاتِحِ لِمَا أُغْلِقَ وَ اَلْخَاتِمِ لِمَا سَبَقَ نَاصِرِ الْحَقِّ بَالْحَقَّ وَ الْهَادِي إلى صِرَاطِكَ الْمُسْتَقِيمِ وَ عَلَى آلِهِ حَقَّ قَدْرِهِ و مِقْدَارِهِ الْعَظِيم
ﷺ💚💚💚
Allahumma salli
💚💚💚ﷺ
ﷺ💚💚💚
Allahumma salli
alaa Sayyidinaa Muhammadini 'l-faatihi limaa ughliq, wa 'l-khaatimi limaa sabaq, naasiri 'l-haqqi bi 'l-haqq, wa 'l-haadi ilaa Siraatika 'l-Mustaqeem, wa
alaa aalihi haqqa qadrihi wa miqdaarihi 'l-`azheem.💚💚💚ﷺ