Telegram Web Link
በጀርመንኛ ከተጻፈ “Das Licht seiner Geburt“ (የልደቱ ብርኃን) ከሚል መጽሐፍ ያገኘኋቸውን ሥእሎች እዩማ። ሥእላቱ ከተለያዩ አብያተ ክርስትያን እና የብራና ማስቀመጫዎች የተወጣጡ ናቸው (እነ ማኅደረ ማርያም — ደብረ ታቦር፣ ደብረ ብርኃን ሥላሴ — ጎንደር፣ የSTUB Frankfurt/Main ብራናዎች ወዘተ)።
እመብርኃን ጥጥ ስትፈትል ያለው ነው በጣም ያማረኝ። ዳዊት በበገናንም ሹፉ:

(እዚህ ላይ
ዕዝራ በመሰንቆ ዳዊት በበገና፣
እግዜርም እንደሰው ይወዳል ምስጋና። የሚለውን የቀኛ/ች ምስጋናው አዱኛ ግጥም ትዝ አለኝ)
Unconquered_States_Non_European_Powers_in_the_Imperial_Age_H_E_Chehabi.pdf
8.2 MB
ይሄን አዲስ መጽሐፍ ያላያችሁ፡ ኢትዮጵያ ብቻ ወደ ሦስት ምዕራፎች አሏት።
For friends in Addis Abeba:

“In honor of Black History Month, we will be screening the groundbreaking romance/drama film Losing Ground (1982) directed by Kathleen Collins who is often cited as being the first African American woman to write and direct a feature length film, even preceding the likes of Julie Dash’s Daughters of the Dust.

Losing Ground revolves around a summer in the life of a married scholar and artist couple who are at a crossroads. It stars Seret Scott as the lead and her husband is played by the legendary cult filmmaker Bill Gunn (Ganja & Hess, Personal Problems).

Losing Ground never got distribution and was lost in obscurity for more than 30 years; it finally got a theatrical release in 2015 and is now considered one of the most important films of the 80s. Come join us on February 20, 2025 for a night of celebrating cinema!”

RSVP here: https://posh.vip/e/losing-ground-film-screening

Losing Ground film screening
Century Cinema
Thu, Feb 20 at 6:00 PM - 8:00 PM (EAT)
Organised by Video-Bet
ነገ ጃንሜዳ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል ከቀኑ 9፡30 ላይ The Lost Wax: Light Up Lalibela's Church የተባለ ዶክዩመንተሪ ፊልም ይታያል ከዚያም ውይይት ይከተላል። እንደምታውቁት የፈረንሳይ መንግሥት የላሊበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያን ለማሳደስ ብዙ ገንዘብ አውጥቷል። ብዙ ኢትዮጵያዊ እና የውጭ ምሁራንም ሲያግዙ ነበሩ/አሉ። ከሱ ጋር የተገናኘ ፊልም ነው።

ለበለጠ መረጃ እዚህ ተመልከቱ፡ https://cfee.hypotheses.org/11455
በድጋሚ የቀረበ፡

የአደባባይ ችሎት እና የተጠየቅ ሙግት

የጥንቱ ችሎት በተነሳ ቁጥር . . . የሚነገርለት አንድ ነገር አለ። ይኸውም ተውኔታዊ ባህርይ የነበረው የከሳሽና የተከሳሽ አለባበስ፥ አቋቋም፥ ዘንግ አያያዝ፥ የሰውነት እንቅስቃሴ፥ የነገር አቀራረብና ባጠቃላይም ሞቅና ደመቅ ያለው ጥምር የአሞጋገቱ ስልት ነው። ተሟግቶ ለመርታት፥ ረትቶም እርካታ፥ ዝናና ክብርን ለመቀዳጀት በቅድሚያ የተሟጋቹን ንቃት፥ ብልህነትና ብርታት ይጠይቃል። ከዚህም የተነሳ ከሰውነት እንቅስቃሴው ሌላ፥ በተለይ የመሟገቻው ቋንቋ በተዋቡ ቃላት፥ በምሳሌያዊ አነጋገር፥ በተረት፥ በአፈታሪክ፥ በእንቆቅልሽና በመሳሰሉት ዘዴዎች የበለፀገና ለዛማ መሆን ይገባው ነበር። የነዚህ ሁሉ ውሁድ የችሎት ነፃ ትርኢት ነው እንግዲህ፥ ወጪ ወራጁን፥ አላፊ አግዳሚውን ሁሉ ይማርክና ያማልል የነበረው።

ሁሉንም ተሟጋቾች አይመለከት ይሆናል። ይህም ቢሆን የክት ልብስን ለብዞ፥ ድግድጋትን አሳምሮ (አደግድጎ)፥ ጎራዴም ሆነ ሽጉጥ በወገብ ላይ ገንደር አድርጎ፥ ረዢም ዘንግ ይዞ ግርማ ሞገስ በተቀላቀለበት ሁኔታ እችሎት ላይ መቅረቡ፥ ቀርቦም ወቅቱ ሲደርስ እየተንቆራጠጡና ነገርን እያራቀቁ መሟገቱ፥ ከአንድ ጥሩ ተሟጋች የሚጠበቅ ልማድ ወይም ወግ ነበር።

አንድ ተጓዥ እንዲህ ሲል የዛፍ ስር ሙግት ተሟጋቾችን ገልጿል «በተመልካቾች መካከል ተቀምጦ የነበረው ዳኛም የከሳሽን ጉዳይ በጥሞና አዳምጦ ካበቃ በኋላ፥ ተከሳሽ መልስ እንዲሰጥ ይጋብዘዋል። ተከሳሽም ተስፈንጥሮ ወደላይ በመዝለልና ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ በመዘርጋት፥ ክሱ የማይመለከተውና ንፁህ መሆኑን ለመግለፅ ይጥራል። ከዚያም በአንድ ጉልበቱ በርከክ ቀጥሎም ብድግ በማለትና በእግር ጣቶቹ ብቻ በመቆም ወደ ባላጋራው ሌባ ጣቱን ቀሰር ያደርጋል። ወዲያውም ሁለት እጆቹን በደረቱ ላይ ለጥፎ በአሳዛኝ መልክ ወደ ዳኛው ጠጋ ይላል። ይህ ሰው እነዚህን ሁሉ ድርጊቶች ሲፈፅም ከንፈሮቹ የማያቋርጡ ቃላትን እያነበነቡ ነበር።

ለነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ ግን ይኽ ከንቱ ነበር፡ «አንዳንድ የውጭ ሀገር ስደተኞችም በልተን እንደር ሲሉ ያገራችን ሹማምንት ዛሬ የያዙትን የስህተት መንገድ እንዳይለቁ ያጠናክሩታል። አይዟችሁ እያሉም ከየመፃህፍቱ የለቀሙትን፥ —-አንዳንድ የተሰብሩ ቃላት ያስጠኗቸዋል። ያገራችንም ሹማምንት ሩቅ እንዳያዩ. . . አይናቸውን ሸፍነው ይከለክሏቸዋል። እውቀት አለንም ብለው ራሳቸው ይዞራል። ውሏቸውም ስራን ትተው በክርክርና በሙግት ብቻ ነው» ይላል።

«እመንደር ከዋለ ንብ አደባባይ የዋለ ዝንብ» እየተባለ ይተረታል - አደባባይ የፍርድ ችሎትን ይወክላል። ችሎት ለማየት በሚውል እና በማይውል ሰው ላይ ያለውን ማኅበራዊ ግምት ከተረዳን የገ/ሕይወት ባይከዳኝ ትችት የምር ሊያሳስበን ይችላል። ስራ ተፈቶ ክርክር ሲታይ ይዋል ነበር ማለት ነው? ፡)

ደግሞ ችሎት የአሞጋገትና የአነጋገር ስልትን የመቅሰሚያ፥ ህግና ዳኝነትን የመማሪያ፥ ከሹማምንትና ከመሳሰሉት ከፍተኛ ሰዎች ጋር የመተዋወቂያና ለዳኝነትም ሆነ ለሌላ ስልጣን የመመረጫ ቦታም ጭምር በመሆኑ አዳማቂዎቹ ወይም ደንበኞቹ ሙግት ያላቸውም፥ የሌላቸውም ነበሩ።

ባንድ ወቅት ከሳሽና ተከሳሽ እዳኛ ፊት ግራና ቀኝ ተቋቁመው ሲሟገቱ፤ አንደኛው የሌላውን ደካማ ጎን (እንከን) አውቆ ኖሯል። እንከኑም አደባባይን አላማዘውተሩና ከድህነቱም የተነሳ ሚስቱን ነጠላ እንጂ ኩታ አልብሷት እንደማያውቅ መሆኑ ነበር። ይህንን የተረዳው ጮሌ ተሟጋችም በዘመኑ የነበረውን የችሎት ላይ ያነጋግር ነፃነትና የአሞጋገት ስልትን በመጠቀም እንዲህ ብሎ ይሰድበዋል።

በላ ልበልሃ!
ያጤ ስርአቱን የመሰረቱ፡
አልናገርም ሀሰቱን፡
ሁሌ እውነት እውነቱን!
ላምህ ብትወልድ ዛጎላ፡
ሚስትህ ብትለብስ ነጠላ፡
አንተ ብትውል እጥላ!

ተሰዳቢው ተሟጋችም ምንም እንኳን አደባባይን የማያዘወትርና የኑሮ ደረጃውም ዝቅ ያለ ቢሆንም ቅሉ፥ ነገር አዋቂና አራቃቂ ነበርና፤ እሱም በበኩሉ በ’በላ ልበልሃ’ የአሞጋገት ስልት እንዲህ ብሎ መለሰለት ይባላል።

በላ ልበልሃ!
ያጤ ስርአቱን የመሰረቱን፡
አልናገርም ሀሰቱን፡
ሁሌ እውነት እውነቱን!
ላሜ ብትወልድ ዛጎላ
አውራውን አስመስል ብላ።
ሚስቴ ብትለብስ ነጠላ
ቀን እስቲያልፍ ብላ።
እኔ ብውል እጥላ፥
ያንተን ብጤ ነገረኛ ብጠላ!

😂 ዛሬ ይሄ ባህል ቢኖር እኔም ስራ ፈትቼ አደባባይ ፍርድ ሳይ ነበር የምውለው እምዬን።
***
‘የሞራል ውድቀት ዝንባሌ በትምህርት እድገት በኢትዮጵያ ላይ’ በሚለው መጽሐፋቸው ሀይሌ ወ/ሚካኤል እንዲህ ይላሉ፡ «በመካሰስና ነገር ካለበት ስፍራ በመዋል የኢትዮጵያ ህዝብ የታወቀ ሆኗል። ትልቅ ገበሬ ከመሆን አነስተኛ ጠበቃ መሆን ክብር ነው። ከአደባባይና ከትችት ቦታ መዋል የጨዋ ልጅ ምልክት ነው። የሰው ልጅነትህን በአንደበትህ ርቱዕነት ማረጋገጥ አለብህና»

ተሟጋችነት ከመከበሩ የተነሳ አንድ ተሟጋች ብቃት የሌለውን እንዲህ ብሎ ሰድቦታል፡ እዛው ችሎት አደባባይ

በላ ልበልሃ!
ያጤ ስርአቱን የመሰረቱ፡
አልናገርም ሀሰቱን፡
ሁሌ እውነት እውነቱን!
በሳማ ሲበላ ጣቱን የሚልሰው፥
አደባባይ ቆሞ አንድ እማይመልሰው፥
ሚስቱ ስትቆጣው እጓሮ እሚያለቅሰው፥
አንተም ከኔ ጋራ እኩል ሰው እኩል ሰው። 😄

ከሺበሺ ለማ ፡ ተጠየቅ
ገጽ 15 - 46
Call for Papers:

ሐዋሳ ለሚደረገው 22ኛው የኢትዮጵያ ጥናት ጉባኤ እኔ እና ዶ/ር ሰለሞን ገብረየስ የምናዘጋጀው ፓኔል አለ። ርእሱ የኢትዮጵያ ታሪክ አጻጻፍ ነው (historiography)። ማንኛውንም አይነት ጽሑፍ በዚህ ርእስ ሥር ማቅረብ የምትፈልጉ ከሥር ባለው መጥሪያ መሠረት ካሁን ጀምሮ ማመልከት ትችላላችሁ። የቁጥር ገደብ የለም እና ሁላችሁም ማመልከት ትችላላችሁ። እናበረታታለን።

መጥሪያውን እዚህ ተመልከቱ፡
ሰሞኑን አባት ሀገር ጀርመን ምርጫ ተካሄዶ አልነበር? በኢትዮጵያ እንዴት እንደተዘገበ እንጃ ግን በ1923 ዓ.ም. አእምሮ ጋዜጣ «መሴ ሒትለር» የተባሉ ሰው ምርጫ አሸነፉ ብሎ የዘገበውን ላሳያችሁ።

ርዕሱ፡ የውጭ አገር ፖለቲካ መመርመር። የጀርመን አገር ምርጫ በኋላ የሶሺያሊስት ወገን የሙሴ ሒትለር ማሸነፍ
አእምሮ ጋዜጣ፣ 1923 ዓ.ም. ጥቅምት 1 ቀን።
አድዋ፡ የመጨረሻው ውጊያ

« ከዚህ ቀጥሎ አጼ ምኒልክ ጦራቸውን ወደ አድዋ በመምራት የአድዋ ሸለቆ ከሚታይበት ከፍታ ላይ ሰፈሩ። ራስ መኮንን፣ ራስ መንገሻ እና ራስ ሚካኤልን ከመሃል ወራሪ፤ እራሳቸውን እና እቴጌን ከመካከል፣ ንጉሥ ተክለሃይማኖትን በስተቀኛቸው፣ ራስ አሉላን በስተግራ አደረጓቸው።

ጀነራል ባራቴሪ ከቅርብ ርቀት ላይ ቢሆንም የስንቅ እና ቁሳቁሶች እጥረት እየገጠመው ነበር። ስለዚህ በጥር ወር የምኒልክም ጦር ስንቅ እስኪያልቅ ጣልያኖች እንዲጠብቁ አዞ ነበር። ነገር ግን የጣልያን መንግሥት እርምጃ ውሰድ ዝምብለህ ከምትጠብቅ የሚል ትእዛዝ ስለላከ ሊተገብረው አልቻለም።

በየካቲት 23 ጥዋት ላይ ሊያጠቃ የነበረው ባራቴሪ ሦስት ሻለቃ ጦሮችን አሰለፈ። ጀነራል አልበርቶን በስተግራ፣ ጀነራል ዳቦርሚዳ በስተቀኝ እና ጀነራል አሪሞንዲ ከመካከል አድርጎ ደጀን ላይ ደግሞ ጀነራል ኢሌናን አስቀመጠ። አልበርቶን ራሱን ኪዳነምሕረት በምትባል ከፍታ ላይ አስቀምጦ የኢትዮጵያውያኑን እንቅስቃሴ ለመከታተል አስቦ ነበር።

ነገር ግን እሱ እንዳቀደው ሳይሆን ጀነራል አልበርቶን ዘው ብሎ ራስ አሉላ በሠፈሩበት አካባቢ ገባ። ሯጮች አጼ ምኒልክ ጋር ገስግሰው ጣልያን በጠዋት እንዳጠቃ ነገሯቸው። ዘበኞች ውጊያ ጀምረው ነበር። 25 ሺህ ሰዎችን ሲልኩላቸው አሪሞንዲን ከነበረበት ነቅለው እንዲሸሽ አደረጉት። 12 ሰዓት ላይ አልበርቶንን እና አስካሪዎቹን ወደ አሪሞንዲ ጦር ገፍተው አልበርቶንን ምርኮኛ ያዙት። የዳቦሪሚዳ ጦር እንኳን አልበርቶንን ሊያድን እራሱ ሳያስበው በራስ ሚካኤል ሰፈር ውስጥ ገብቶ ስለተከበበ ተደመሰሰ። የቀሩት የባራቴሪ ጦረኞች በንጉሥ ተክለሃይማኖት ተቆርጠው ተገደሉ። ቀን 6 ሰዓት ሲሆን በምኒልክ ሥር የዘመቱት የጦር መሪዎች በጦር ሜዳው ተሳትፈው ራሳቸውን አስመስክረዋል። የተረፉት ጣልያኖች ወደ ኤርትራ እግሬ አውጪኝ ሸሹ። እነሱም በኢትዮጵያ ገበሬዎች እየተጠቁ ኤርትራ የገቡት በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።

የአድዋ ጦርነት እንዲህ ተፈጸመ። ከ4 እስከ 5 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሞተው ወደ 8 ሺህ ያህል ቆስለዋል። ጀነራል አልበርቶን እና 3ሺህ ጣልያናውያን ምርኮኛ ተወሰዱ። ከእነዚህ 200 የሚሆኑት በቁስሎቻቸው ምክንያት ሲሞቱ ወደ 800 አስካሪዎች ግራ እግራቸውን እና ቀኝ እጃቸውን ተቆረጡ። ከጠላት ጋር አብራችኋል በማለት። ጣልያኖች ወደ 7ሺህ ሰዎች ሲሞቱባቸው፣ 1500 ያህል ቆስሏል። 11 ሺህ ጠመንጃዎቻቸውም ተማርከዋል። »

ከፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት Ethiopian Warriorhood
ገጽ 234
2025/10/23 02:44:34
Back to Top
HTML Embed Code: