Telegram Web Link
📌 ድርሹ ዳና ተሸለመች

የሬድዮ ፕሮግራም አቅራቢና የማስታወቂያ ባለሙያ የሆነችው ድርሻዬ ዳና(ድርሹ) በኢምሬትስ ዱባይ በተካሄደው 2ኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ፓርላማ  ጉባኤ ላይ ተሸልማለች።

ድርሹ ዳና በማህበራዊ ትስስር ገጿ"አሸናፊ ሆነናል።ደጉ አባቴ የልጁን ድካም ቆጥሮ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ዳግም አሸልሞኛል" ብላለች።

ድርሹ ዳና በ2ኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ፓርላማ ላይ በሚዲያና ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ከኢትዮጵያ ተመራጭ እጩ ሆና እንደቀረበች ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ኢራን ኢትዮጵያን አመሰገነች

የኢራን መከላከያ ጦር ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ደጋፊ ከኢትዮጵያ ፣ ከጋና፤ ከሶማሊያ፣ ኬኒያ እና ደቡብ ሱዳን አግኝተናል ብሏል።

ጦሩ በፌስቡክ ገጹ የሚለጥፋቸውን መረጃዎች የሚከታተሉ እና ገጹን የሚከታተሉ ዜጎች ቁጥር በመጨመሩ ነው ምስጋናውን ለሃገራቱ ያቀረበው።

በመቀጠልም ሁሌም ቢሆን የአፍሪካ እና የአፍሪካውያን ነፍስያ ከኢራን በኩል ነው ብሏል ጦሩ።

በተያያዘ ለአፍጋን ወንድም እህቶቻችን ከጎናችን ስለሆናችሁ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ዛሬ ዓለምአቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ቀን ነው

የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች ቀን ሐምሌ 2 ቀን የስፖርት ጋዜጠኞች ስፖርትን ለማስተዋወቅ የሚያገለግሉትን አገልግሎት ለማክበር በሚል በዓለምአቀፍ ደረጃ ተከብሮ ይውላል።

ይህ ቀን በ1924ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ የዓለም አቀፍ ስፖርት ፕሬስ ማህበር የተመሰረተበት ቀን በመሆኑ በይፋ "የዓለምአቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ቀን" ተብሎ ተወስኗል።

በህትመት (ጋዜጣና መጽሔት ) ፣በሬድዮና ቴሌቪዥን፣በዲጂታል የሚዲያ አማራጮች ከልባችሁ የምትሰሩ ውድ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ጋዜጠኞች እንኳን አደረሳችሁ እንላለን።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌን ያስለቀሰው ሰርፕራይዝ

ኮሜዲያን/ተዋናይ ደረጀ ኃይሌ በኮሜዲ ስራዎቹም
ሆነ በኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ ለበርካታ ዓመታት
በጥሩ ዲሲፒሊን ትንሽ ትልቁን አክብሮ ለዘመናት
ሙያውን አክብሮና አስከብሮ የኖረ ታላቅ አርቲስት እንደሆነ ይነገርለታል።

ኮሜዲያን ደረጀ ኪነጥበቡ ላይ ላሳረፈው ትልቅ አሻራና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ወዳጆቹ ፣ የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በአድዋ ባንድ ባለቤት አቶ ሞገስ ሀሳብ አመንጪነት ቦሌ በሚገኘው የመሣይ በቀለ ሆቴል ውስጥ ፕሮግራም አዘጋጅተውለት በሽልማት አንበሽብሸውታል።

ከሽልማቶቹ መካከል ደረጃውን የጠበቀ ሙሉ የቤት ዕቃዎች ፣ ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት፣ከሀብቴ ጋር አንድ ላይ የተነሱትን ፎቷቸውን እና ሌሎች ሽልማቶችም ይገኙበታል።

ደረጀም ባልጠበቀው ድንገተኛ ሰርፕራይዝ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት በደስታ ዕንባ ሲታጠብ ተመልክተነዋል።

Via ዘሪሁን ተዝናኑ

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በኒውሮሳይንስ ላይ ያተኮረ ልዩ ዝግጅት ሊካሄድ ነው

በኒውሮሳይንስ ላይ ያተኮረ ልዩ ዝግጅት ሰኞ ሀምሌ 14 2017 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ ልዩ መርሐግብር ላይ ሲናፕስ ኢትዮጵያ በይፋ ሊጀመር እንደሆነም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።"ሲናፕስ" በኒውሮሳይንስ አለም እጅግ መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ ነው። የሁለት ነርቭ ሴሎች ተገናኝተው መረጃ የሚለዋወጡበት ድልድይ ማለት ነው።

ይህንን መነሻ በማድረግ፣ ሲናፕስ ኢትዮጵያ በአገራችን የመጀመሪያው በኒውሮሳይንስ ላይ ያተኮረ የህዝብ ንግግር መርሃ ግብር ሲሆን ስለ ኒውሮሳይንስ የቅርብ ጊዜ ዕውቀቶችና ምርምሮች ይቀርባሉ።

አዘጋጆቹ የኒውሮሳይንስ ዕውቀት በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎችም የህይወታችን ዘርፎች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እንመለከታለን ብለዋል።

በተጨማሪም በተመራማሪዎችና በዝግጅቱ ታዳሚዎች መካከል የልምድ ልውውጥና አዲስ ግንኙነት ይፈጠራል ተብሏል።

እንዲሁም ስነ-ጥበብ: የሳይንስና የኪነ-ጥበብ ውህደት በፈጠረው ልዩ ድባብ እንዝናናለን ሲሉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ 300 ብር ነው።


ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በሐኪም የሚዘጋጁ ጤናማ የታሸጉ ምግቦች የሚቀርቡበት ልዩ ሁነት የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል።

በናዶራ ዌልነስ ሴንተር የተዘጋጀው " Beyond the stethoscope" የተሰኘ ልዩ ሁነት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 28 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ጀምሮ ቦሌ ኣትላስ ሶሻል አዲስ(ሴሎ) ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ሁነት ላይ በሃኪም የሚዘጋጁ ጤናማ የታሸጉ ምግቦቸ -የጤፍ ኩኪሶች - ኬኮቸ እና የተፈጥሮ ማር ይቀርባሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በእጅ የተሰሩ ጌጣ ጌጦች፥ ሌዘር ምርቶች ፥ ሠዓሊያንና እና ሥዕሎቻቸው፥ የተቀመሙ ሽቶዎች፥ አልባሳት፥ ፎቶግራፎች፥ እና ሌሎችም በዝግጅቱ ይቀርቡበታል ተብሏል።

Open mic- ኮሜዲያኖች እና ገጣሚዎች አሉም።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ 200 ብር ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የዋሸንት ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ይደገማል

የዋሽንት ተጫዋቹ ጣሰው ወንድም "የትንፋሽ ውበት" 2 ሲል የሰየመውንና ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የዋሽንት ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 28 2017  ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በመሶብ የሙዚቃ ማዕከል ውስጥ ያቀርባል።

በዚህ ኮንሰርት ላይ የዋሽንት ተጫዋቹ ጣሰው ወንድምና የፒያኖ ተጫዋቹ አብይ ወ/ማርያም ይጣመራሉ ተብሏል።

"የትንፋሽ ውበት" የዋሽንት ሙዚቃዊ ዝግጅት መግቢያ ዋጋውም 300 ብር እንደሆነ ተገልጿል።

በመሶብ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ ውስጥ በዋሽንት ተጫዋችነቱ የምናውቀው ጣሰው "የትንፋሽ ውበት" የተሰኘ የዋሽንት የሙዚቃ አልበም ከአንድ ዓመት በፊት ለአድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ሐጫሉ አዋርድ የአንዱዓለም ጎሳን ሽልማት ነጥቆ ይቅርታ እንዲጠይቅ ተጠየቀ

የሐጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ አዘጋጅ የሆነው ሐጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳን ከሸለመ በኋላ በህዝቡ ቅሬታ አጋጥሞታል። በተለይ የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ህይወቷ ከማለፉ በፊት ጥቃት ይደርስባት እንደነበር የሚያመለክቱ ምስሎች ከወጡ በኋላ በህዝቡ ዘንድ ቁጭት እና እልህ የታከለበት እንደ አዲስ ጉዳዩ እንዲነሳ ሆኗል።

የሞዴል ቀነኒ አዱኛ እጮኛ የነበረው ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ የተሸለመው ሽልማት ተነጥቆ ፋውንዴሽኑ በ24 ሰዓት ውስጥ ለህዝቡ መግለጫ እንዲሰጥ ዘመቻም ተጀምሯል።

Via FastMereja

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌እንጦጦ ላይ ያሉ ባህር ዛፎች ሙሉ በሙሉ ይነሳሉ ተባለ

በአዲስ አበባ ተራራማ ቦታ በእንጦጦ ላይ የሚገኙት ባህር ዛፎች በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚነሱ እና በሀገር በቀል ዛፎች እንደሚተኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ገልጸዋል።

ባህር ዛፍ ውሃ የመምጠጥ አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ እና መዲናዋ የከርሰ ምድርን ውሃ በአግባቡ ለመጠቀም እየሠራች በመሆኑ ዛፎቹን መተካት አንዱ መፍትሔ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።

ባህር ዛፎቹ ሲነሱ ግን በእጥፍ በሀገር በቀል ዛፎች እና ስነ ምህዳሩን ለማስተካከል በሚችሉ ዛፎች እየተተኩ መሆኑንም መገለጻቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከተጀመረ ወዲህ ከእንጦጦ ተነስተው ወደ መሀል ከተማ የሚፈሱት ወንዞች የውሃ መጠን መጨመሩንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በእንጦጦ ፓርክ ከሚገኙ የዛፍ አይነትቶች ባህር ዛፍ አብዛሃኛው ቦታ ይሸፍናል።

ይህ ደግሞ ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ እንዳልሆነ በብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች የተረጋገጠ በመሆኑ፤ በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ እየተካሄደ ካለው የወንዞች መልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ትግበራ ጋር ተሳስሮ ባህር ዛፍን በአገር በቀል ዝርያዎች ለመተካት እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

በዚህም መሠረት በፖርኩ የሀበሻ ጽድ፣ ዝግባ፣ ወይራ የመሳሰሉት አገር በቀል ዛፎች ባህር ዛፍን እንዲተኩ እንደሚደረግ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:

1.ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ በድንገተኛ ፈንጠዝያ በደስታ የተፈከነከነበትና በወዳጆቹ የተመሰገነበት ልዩ ዝግጅት ተካሄደ። ደሬ ምን ተሰማው? ጠይቀናል።

2.የቲቤታዊያን ሙዚቃዎች ነገር ከሰሞኑ በኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ትስስር ገፆች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። የቲቤታዊውያንን ሙዚቃ ከእኛ ሙዚቃ ምን አንድ አደረገው? ምንስ ይለየዋል? የሙዚቃ ባለሙያዋን ብሌን ዮሴፍን ጠይቀናል። በአርትስ ስፔሻል በዝርዝር ትሰማላችሁ።

3.በልጄስ ተከታታይ ድራማ ላይ ባሳየው የትወና ብቃት በርካቶች እያደነቁት የሚገኘው አርቲስት ዳንኤል አሸናፊ (ገዛኸኝ) በትወና የተሳትፈበት "ማ-ዘንድ" ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/31bXR7MFiV0?si=Kl14vuSBwUSXye1j

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሽልማቱን ተነጠቀ

ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት አንዱአለም ጎሳ የሰጠውን ሽልማት እንደነጠቀ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

ፋውንዴሽኔ ሽልማቱን እንዲያነሳ የሚጠይቅ ድምጽ ከሰሞኑ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲስተጋባ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከቀድሞው ባለቤቱ ከሞዴል ቀነኒ ህልፈት ጋር ተያይዞ ስሙ እየተነሳ ያለው ድምጻዊ  አንዷለም እስካሁን  በጉዳዩ ላይ ያለው የሰጠው ምላሽ  የለም፡፡

ድምጻዊው በሞዴል ቀነኒ  ድንገተኛ ህልፈት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ቢሆንም፣ በፍ/ቤት ጥፋተኛነቱ አለመረጋገጡ ይታወቃል፡፡

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ከመጋረጃው ጀርባ" ተውኔት ነገ ይመለሳል

የቶፊቅ ኑሪ ድርሰት የሆነውና በዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ተዘጋጅቶ ለህዝብ ሲታይ የቆየው “ከመጋረጃ ጀርባ” ኮሜዲ ተውኔት ከአንድ ዓመት በኃላ ነገ እሁድ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በ12:00 ሰዓት አለም ሲኒማ ዳግም ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

ወቅታዊ ጉዳዮችን እያዋዛ በማቅረብ የሚታወቀው "ከመጋረጃ ጀርባ" ቴአትር ቀድሞ የነበረውን ይዘት ሳይለቅ እንዲሁም ከገሊላ ርዕሶም በስተቀር የነበሩትን ተዋናዮች በሙሉ ይዞ ዳግም ወደ ተመልካች ይደርሳል ተብሏል።

ተዋናይት ገሊላ ርዕሶም  የምትጫወታትን ገፀባህሪ የምስራች ግርማ  ተክታ እንደምትጫወትም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌 ሁሉ ስፖርት መኪና ሸለመ!

"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል"ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ የቆይታ ጊዜው ከሰኔ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ አዲስ አበባን ጨምሮ በተመረጡ አራት የክልል ከተሞች ይካሄዳል።

እንዲሁም የተለያዩ የስፖርት ሁነቶችን ለማከናወን ከፍተኛ በጀት መመደቡ ታወቀ። በዛሬው እለትም ሁለገብ online solution በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተዘጋጀውን መተግበሪያ ይፋ ሆኗል ፣ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ልዩ የሁለገብ ቤተሰብ ለሆኑ ተሳታፊዎች ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በተሰጠው ፍቃድ መሰረት ይፋ ተደርጓል።

1- አቶ ለአለም ገብረኪዳን ገብረ መስቀል የBYD SEAGULLየኤሌክትሪክ መኪና
ከመቀሌ
2- አቶ ይብራህ ፈተዊ የኤሌክትሪክ ሳይክል
ከአድዋ
3- አቶ ጫላ ኦላኒ የስማርት ስልክ
ከጋንቤላ
4- አቶ አማኑኤል እዮብ ፕሌይ ስቴሽን
ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ

5- አቶ ምናየው ንጉሴ የስማርት ቴሌቪዥን ሽልማት
ከአርባምንጭ(ጎፋ ወረዳ) ተበርክቶላቸዋል።

የዘንድሮው የ"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል" ሲጀመር በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ሚድያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሲሆን፤ ለደንበኞቹ ይበልጥ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ የሆነው አዲስ ዌብሳይትም ተዋውቋል።

ዌብሳይታችንን ይጎብኙ
ሁሉ ስፖርት ቤተሰብ ይሁኑ!

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በልጁ መጽሐፍ ተጻፈለት

ከጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተና በልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

ይኸ በሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀው መጽሐፍ በአማርኛ "የኃይሌ ኃይሎች"በእንግሊዝኛ "Dissecting Haile" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቶታል።

መጽሐፉ የኢትዮጵያዊውን የረጅም ርቀት አትሌት እና ስራ ፈጣሪ የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከእረኝነት ዘመኑ አንስቶ ያለውን ድንቅ ሕይወት፣መርሆች እና ዘላቂ ትሩፋት የሚዳስስ ከመሆኑ ባሻገር ከኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተ መጽሐፍ መሆኑን ደራሲዋ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናግራለች።

አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መጽሐፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነም ተነግሯል።

ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ኃይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ገልጻለች።

በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ለማሰናዳት አንድ ዓመት እንደፈጀ ተነግሯል።

መጽሐፉ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በብሬል የተሰናዳ እንደሆነም ተገልጿል።

"የኃይሌ ኃይሎች" ወይም "Dissecting Haile" መጽሐፍ የፊታችን ነሐሴ 2017 ዓ.ም በይፋ ለአንባቢያን የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ማስጀመሪያ ዝግጅት፣ በመቀጠልም ዓለም አቀፍ ደረጃ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

በአማዞን፣ በቴሌብር፣ በተለያዩ የኦንላይን አማራጮችና እንዲሁም መጽሐፍት መሸጫ መደብሮች መፅሀፉ በኤሌክትሮኒክ አማራጮችና በሀርድ ኮፒ ከነሐሴ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በትዕዛዝ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
2025/07/06 02:19:11
Back to Top
HTML Embed Code: