Telegram Web Link
📌ሐጫሉ አዋርድ የአንዱዓለም ጎሳን ሽልማት ነጥቆ ይቅርታ እንዲጠይቅ ተጠየቀ

የሐጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ አዘጋጅ የሆነው ሐጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳን ከሸለመ በኋላ በህዝቡ ቅሬታ አጋጥሞታል። በተለይ የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ህይወቷ ከማለፉ በፊት ጥቃት ይደርስባት እንደነበር የሚያመለክቱ ምስሎች ከወጡ በኋላ በህዝቡ ዘንድ ቁጭት እና እልህ የታከለበት እንደ አዲስ ጉዳዩ እንዲነሳ ሆኗል።

የሞዴል ቀነኒ አዱኛ እጮኛ የነበረው ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ የተሸለመው ሽልማት ተነጥቆ ፋውንዴሽኑ በ24 ሰዓት ውስጥ ለህዝቡ መግለጫ እንዲሰጥ ዘመቻም ተጀምሯል።

Via FastMereja

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌እንጦጦ ላይ ያሉ ባህር ዛፎች ሙሉ በሙሉ ይነሳሉ ተባለ

በአዲስ አበባ ተራራማ ቦታ በእንጦጦ ላይ የሚገኙት ባህር ዛፎች በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚነሱ እና በሀገር በቀል ዛፎች እንደሚተኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ገልጸዋል።

ባህር ዛፍ ውሃ የመምጠጥ አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ እና መዲናዋ የከርሰ ምድርን ውሃ በአግባቡ ለመጠቀም እየሠራች በመሆኑ ዛፎቹን መተካት አንዱ መፍትሔ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።

ባህር ዛፎቹ ሲነሱ ግን በእጥፍ በሀገር በቀል ዛፎች እና ስነ ምህዳሩን ለማስተካከል በሚችሉ ዛፎች እየተተኩ መሆኑንም መገለጻቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከተጀመረ ወዲህ ከእንጦጦ ተነስተው ወደ መሀል ከተማ የሚፈሱት ወንዞች የውሃ መጠን መጨመሩንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በእንጦጦ ፓርክ ከሚገኙ የዛፍ አይነትቶች ባህር ዛፍ አብዛሃኛው ቦታ ይሸፍናል።

ይህ ደግሞ ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ እንዳልሆነ በብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች የተረጋገጠ በመሆኑ፤ በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ እየተካሄደ ካለው የወንዞች መልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ትግበራ ጋር ተሳስሮ ባህር ዛፍን በአገር በቀል ዝርያዎች ለመተካት እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

በዚህም መሠረት በፖርኩ የሀበሻ ጽድ፣ ዝግባ፣ ወይራ የመሳሰሉት አገር በቀል ዛፎች ባህር ዛፍን እንዲተኩ እንደሚደረግ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:

1.ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ በድንገተኛ ፈንጠዝያ በደስታ የተፈከነከነበትና በወዳጆቹ የተመሰገነበት ልዩ ዝግጅት ተካሄደ። ደሬ ምን ተሰማው? ጠይቀናል።

2.የቲቤታዊያን ሙዚቃዎች ነገር ከሰሞኑ በኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ትስስር ገፆች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። የቲቤታዊውያንን ሙዚቃ ከእኛ ሙዚቃ ምን አንድ አደረገው? ምንስ ይለየዋል? የሙዚቃ ባለሙያዋን ብሌን ዮሴፍን ጠይቀናል። በአርትስ ስፔሻል በዝርዝር ትሰማላችሁ።

3.በልጄስ ተከታታይ ድራማ ላይ ባሳየው የትወና ብቃት በርካቶች እያደነቁት የሚገኘው አርቲስት ዳንኤል አሸናፊ (ገዛኸኝ) በትወና የተሳትፈበት "ማ-ዘንድ" ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/31bXR7MFiV0?si=Kl14vuSBwUSXye1j

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሽልማቱን ተነጠቀ

ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት አንዱአለም ጎሳ የሰጠውን ሽልማት እንደነጠቀ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

ፋውንዴሽኔ ሽልማቱን እንዲያነሳ የሚጠይቅ ድምጽ ከሰሞኑ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲስተጋባ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከቀድሞው ባለቤቱ ከሞዴል ቀነኒ ህልፈት ጋር ተያይዞ ስሙ እየተነሳ ያለው ድምጻዊ  አንዷለም እስካሁን  በጉዳዩ ላይ ያለው የሰጠው ምላሽ  የለም፡፡

ድምጻዊው በሞዴል ቀነኒ  ድንገተኛ ህልፈት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ቢሆንም፣ በፍ/ቤት ጥፋተኛነቱ አለመረጋገጡ ይታወቃል፡፡

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ከመጋረጃው ጀርባ" ተውኔት ነገ ይመለሳል

የቶፊቅ ኑሪ ድርሰት የሆነውና በዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ተዘጋጅቶ ለህዝብ ሲታይ የቆየው “ከመጋረጃ ጀርባ” ኮሜዲ ተውኔት ከአንድ ዓመት በኃላ ነገ እሁድ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በ12:00 ሰዓት አለም ሲኒማ ዳግም ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

ወቅታዊ ጉዳዮችን እያዋዛ በማቅረብ የሚታወቀው "ከመጋረጃ ጀርባ" ቴአትር ቀድሞ የነበረውን ይዘት ሳይለቅ እንዲሁም ከገሊላ ርዕሶም በስተቀር የነበሩትን ተዋናዮች በሙሉ ይዞ ዳግም ወደ ተመልካች ይደርሳል ተብሏል።

ተዋናይት ገሊላ ርዕሶም  የምትጫወታትን ገፀባህሪ የምስራች ግርማ  ተክታ እንደምትጫወትም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌 ሁሉ ስፖርት መኪና ሸለመ!

"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል"ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ የቆይታ ጊዜው ከሰኔ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ አዲስ አበባን ጨምሮ በተመረጡ አራት የክልል ከተሞች ይካሄዳል።

እንዲሁም የተለያዩ የስፖርት ሁነቶችን ለማከናወን ከፍተኛ በጀት መመደቡ ታወቀ። በዛሬው እለትም ሁለገብ online solution በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተዘጋጀውን መተግበሪያ ይፋ ሆኗል ፣ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ልዩ የሁለገብ ቤተሰብ ለሆኑ ተሳታፊዎች ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በተሰጠው ፍቃድ መሰረት ይፋ ተደርጓል።

1- አቶ ለአለም ገብረኪዳን ገብረ መስቀል የBYD SEAGULLየኤሌክትሪክ መኪና
ከመቀሌ
2- አቶ ይብራህ ፈተዊ የኤሌክትሪክ ሳይክል
ከአድዋ
3- አቶ ጫላ ኦላኒ የስማርት ስልክ
ከጋንቤላ
4- አቶ አማኑኤል እዮብ ፕሌይ ስቴሽን
ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ

5- አቶ ምናየው ንጉሴ የስማርት ቴሌቪዥን ሽልማት
ከአርባምንጭ(ጎፋ ወረዳ) ተበርክቶላቸዋል።

የዘንድሮው የ"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል" ሲጀመር በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ሚድያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሲሆን፤ ለደንበኞቹ ይበልጥ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ የሆነው አዲስ ዌብሳይትም ተዋውቋል።

ዌብሳይታችንን ይጎብኙ
ሁሉ ስፖርት ቤተሰብ ይሁኑ!

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በልጁ መጽሐፍ ተጻፈለት

ከጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተና በልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

ይኸ በሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀው መጽሐፍ በአማርኛ "የኃይሌ ኃይሎች"በእንግሊዝኛ "Dissecting Haile" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቶታል።

መጽሐፉ የኢትዮጵያዊውን የረጅም ርቀት አትሌት እና ስራ ፈጣሪ የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከእረኝነት ዘመኑ አንስቶ ያለውን ድንቅ ሕይወት፣መርሆች እና ዘላቂ ትሩፋት የሚዳስስ ከመሆኑ ባሻገር ከኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተ መጽሐፍ መሆኑን ደራሲዋ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናግራለች።

አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መጽሐፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነም ተነግሯል።

ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ኃይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ገልጻለች።

በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ለማሰናዳት አንድ ዓመት እንደፈጀ ተነግሯል።

መጽሐፉ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በብሬል የተሰናዳ እንደሆነም ተገልጿል።

"የኃይሌ ኃይሎች" ወይም "Dissecting Haile" መጽሐፍ የፊታችን ነሐሴ 2017 ዓ.ም በይፋ ለአንባቢያን የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ማስጀመሪያ ዝግጅት፣ በመቀጠልም ዓለም አቀፍ ደረጃ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

በአማዞን፣ በቴሌብር፣ በተለያዩ የኦንላይን አማራጮችና እንዲሁም መጽሐፍት መሸጫ መደብሮች መፅሀፉ በኤሌክትሮኒክ አማራጮችና በሀርድ ኮፒ ከነሐሴ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በትዕዛዝ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
2025/07/07 04:33:46
Back to Top
HTML Embed Code: