Telegram Web Link
📌በአርቲስት ዘነበች ታደሰ"ጭራ ቀረሽ" ህይወትና ሥራ ላይ ያተኮረ መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል።

በሀገራችን በቴያትርና ሙዚቃ ዘርፍ በሁለገብ ሙያተኛነት ደምቀው ሲያበሩ ከነበሩ ከያኒያኒን መካከል አንዷ የነበረችው አርቲስት ዘነበች ታደሰ (ጭራ ቀረሽ) ሕይወትና ስራዎች ላይ የሚያጠንጥን መጽሐፍ ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

በዶ/ር ጌታቸው ተድላ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ አርቲስት ዘነበች ታደሰ ማን ነች? ለምንስ ጭራ ቀረሽ የሚል ስያሜ ተሰጣት? ለጥበብ ምን አበረከተች? የሚሉ ጥያቄዎችን ሊመልስ የሚችል በፅሁፍና በምስል የተደራጀ መፅሐፍ  እንደሆነ ተገልጿል።

አርቲስት ዘነበች ታደሰ  'ሎሚ ብወረውር' በሚለው ዘፈኗና በመድረክ ላይ ውዝዋዜዋ ይበልጡን በህዝብ ልብ ውስጥ የምትታወስ ትሁን እንጂ ጥቂት በማይባሉ የመድረክ ቴያትሮችና የቴሌቪዥን ድራማ ብሎም ፊልም ላይ  በመሳተፍ አቅሟን አሳይታለች።

ለአብነት ያህል (Shaft in Africa) ላይ ከታዋቂው የሆሊዉድ ተዋናይ ሪቻርድ ራውንድትሪ ጋር የመተወን እድል ሲገጥማት በጥሩ ብቃት የተሰጣትን ሚና ለመወጣት የቻለች ብቁ ሙያተኛ ነበረች።

'ጭራ ቀረሽ' የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ መፅሀፍ  ዛሬ ታህሳስ 12 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመርቆ ለንባብ ይበቃል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
"የለውጥ ሰበዞች" የፎቶግራፍ አውደርዕይ ተከፈተ

የአምስት ፎቶ ባለሞያዎች የፎቶግራፍ ስራዎች የሚቀርብበት "የለውጥ ሰበዞች" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የፎቶግራፍ አውደርዕይ ቅዳሜ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ውስጥ ተከፍቷል።

ዝርዝሩን በድረገጻችን ያንብቡ: http://surl.li/egtnqg

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ብስክሌት በአዲስ" ፌስቲቫል

"ብስክሌት አዲስ" የተሰኘ የብስክሌት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ ነው።

ዝርዝሩን ያንብቡ:http://surl.li/egtnqg

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የሀዲንቆ የማሲንቆ አልበም ነገ ይለቀቃል

በመስንቆው ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቹ ሀዲስ አለማየሁ በመድረክ ስሙ (ሀዲንቆ) የተዘጋጀው የመስንቆ አልበም ነገ ታህሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።የሙዚቃ አልበሙ "Streets of haddis" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቷል።

ተጨማሪውን ያንብቡ:http://surl.li/jsqasd

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የድምጻዊት ኢሪ ዲ "ሰላም ነው" ሙዚቃ ተለቀቀ

የወጣቷ ድምጻዊት ኢሪ ዲ "ሰላም ነው" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ሙዚቃ በተለያዩ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ለአድማጮች ደርሷል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በጋዜጠኛ ተስፋ ፈሩ የተፃፈው "አንሶላ ውስጥ ሟች እና ሌሎችም ወጎች" ለንባብ በቃ

መጽሐፉ 57 ወጎች እና ሽሙጦች የተካተቱበት ሲሆን በ207 ገፆች ተቀንብቧል። ደራሲው ጋዜጣ ላይ በሚጽፋቸው ቁምነገር አዘል አዝናኝ ጽሑፎች ይታወቃል።

የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ  ጉዳዮችን የሚዳስሱ ወጎች በተካተቱበት መፅሐፍ ጀርባ ላይ አቶ ሙሼ ሰሙ፣ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን እና ዶክተር መስፍን ፈቃዴ አስተያየታቸውን አስፍረዋል።

መጽሐፉ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌6ኛው የወር ወንበር ዝግጅት ቅዳሜ ይካሄዳል

በዕለቱ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ይኩኖአምላክ መዝገቡ “ኪን እና ስየማ፡ ኢትዮጵያዊ የትምህርት ዘይቤ በለቀማ” በሚል ርእስ ሃሳባቸውን ያቀርባሉ። ከታዳሚዎች ጋርም ውይይት የሚደረግ ይሆናል።

በዝግጅቱ እንትትሳተፉ ሁላችሁም በአክብሮት ተጋብዛችኋል።


📌 በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ

ከ10፡00-12፡00

📝በዝግጅቱ ላይ የሚገኙ ከሆነ ይህንን ቅፅ በመሙላት ይመዝገቡ
https://bit.ly/3BFVvGS

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አዲስ የቪዲዮ ሥነጥበብ ፌስቲቫል ዛሬ ይከፈታል።

ለአምስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የአዲስ ዓለም አቀፍ የቪዲዮ ስነ-ጥበብ ፌስቲቫል ዛሬ ሐሙስ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ስድስት ኪሎ በሚገኘው በገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ስነ-ጥበብ ማዕከል በምሽቱ 12:00 ጀምሮ  ይከፈታል።

ፌስቲቫሉም ለ 5ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ቦታዎች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ይህ አምስተኛው  ፌስቲቫልም በቅርቡም ህይወቱ ላለፈው ሠዓሊና የቪዲዮ ስነ-ጥበብ ሙያተኛ ሙሉጌታ ገ/ኪዳን መታሰቢያ እንዲሆን ተሰይሟል ተብሏል።

የዘንድሮው መሪ ቃልም "የማንሰራሪያ ተረኮች" ወይንን"Re(Cover) Story" ሆኗል።

ለዚህ ፌስቲቫል 350 ሠዓሊያን ከ 84 ሀገራት ያመለከቱ ሲሆን የመጨረሻወቹ 12 ስራዎች ተመርጠዋል ተብሏል።

በዚህ ፌስቲቫል እነዚህ የተመረጡ ስራዎችና የተጋበዙ 4 ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ፕሮግራሞች ለእይታ ይቀርባሉ።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 ጎዶ'ን ጥበቃ

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር


📍 ዋዋጎ

ድርሰት: ታረቀኝ ብርሃኑ
አዘጋጅ: ጥላሁን ዘውገ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍የሕይወት ታሪክ

ድርሰትና ዝግጅት ነብዩ ባዬ እና ቢንያም ወርቁ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
📌"ኢትዮ ኮሊውድ" የተሰኘ ግዙፍ የፊልም መንደር በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው።

ልክ "ሆሊዩድ፣ፖሊዩድ እና ኖሊዩድ" የፊልም መንደሮች ያለ ግዙፍ የሆነ "ኮሊውድ ኢትዮጵያ "የተሰኘ የፊልም እና ኢኮ ቱሪዝም መንደር  በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በኮንታ ዞን ኤላ አንቻኖ ወረዳ  በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ከሪበላ ሀይቅ ዙሪያ ሊገባ እንደሆነ ተሰምቷል።

መንደሩ 43,000 ሺ ካሬ ካርታ በመረከብ አስገራሚ  በሆነው የዘንባ ጫካን ለዚህ አገልግሎት ለማዋል ስራ መጀመሩን አርቲስት  ወንድዬ ኮንታ ይፋ አድርጓል።

ይህ የፊልም መንደር እና የኢኮ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ መንደር በውስጡ ፣የአርቲስቶች መኖሪያ መንደር፣ታላላቅ የፊልም አክተሮች እና የዘርፉ ሙያተኞች የሚገለገሉበት ሎጅ እና ማረፊያ ገስቶች ሀውሶች፣ አርት ስኩል የሙያ ኮሌጅ ፊልድ ሆስፒታል እና የባህላዊ ህክምና መስጫ ዞን፣ የሀይቅ ላይ የጀልባ መዝናኛ፣ የቱሪስት ካምፒንግ ሳይት እና መናፈሻ፣ የክሮማ ፣ የኤዲቲንግ፣ የሳውንድ ትራክ መቅረጫ እና ማቀነባበሪያ ስቱዲዮዎች የሲኒማ አዳራሾች፣ብሮድካስት የቴሌብዥን እና የሬድዮ ጣቢያ ፣ የሰርከስ ፣ የስዕል ጋለሪ እና የቅርፃቅርፅ  ፣ የመጻሕፍት ገበያ ማዕከል፣የባህላዊ አልባሳት ማምረቻዎች፣የዲዛይነሮች የጥበብ ውጤቶች፣የገበያ ማዕከልን ጨምሮ ሌሎችም ዘርፈ ብዙ  አገልግሎት መስጫን ያካተተ ነው ተብሏል።

አርቲስቱ የሚቆጠር ገንዘብ ሳይኖረው ትውልድን በሚያንፅ ሀገርን በሚያሻግር ድንግል ሀሳቡ የተማረኩ በገንዘብ የሚያግዙትን ባለሀብቶች ፣ ወዳጅ ጓደኞች ፣ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ከጀርባው በማሰለፍ   ግዙፉ ካምፓኒው በሁለት እግሩ እንዲቆም አስፈላጊውን ሁሉ ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

አርቲስት ወንድዬ ኮንታ ይህ ትልቅ ሀሳብ እንዲሳካ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ያሉ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስተርን እና የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ፐብሊክ ሰርቪስን ጨምሮ ሁሉንም ከልብ አመስግኗል።

ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚል ስያሜ የኢንቨስትመንት ሰርተፊኬት በማግኘት እና ሰፊ ይዞታ በመያዝ  ወደ ስራ ገብቷል ተብሏል።

ይህ ፕሮጀክት የኮንታ አከባቢን እንደብራዚሉ አማዞን ጫካ ከፍተኛ የዶላር ምንዛሪን እንዲያመጣና ዓለምአቀፍ የፊልም እና የቱሪዝም የገበያ ውድድር ውስጥ ለመግባት የሚያስችል ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር  የታሰብ ነው ተብሏል።

ለተጨማሪው: @EventAddis1
2025/07/12 08:38:23
Back to Top
HTML Embed Code: