📌ያሬድ ነጉ የሙዚቃ አልበም ሊለቅ ነው
ያሬድ ነጉ "ዳታን" የተሰኘ የመጀመሪያ የዘፈን አልበሙን የፊታችን አርብ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም ሊለቅ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"ዳታን" አልበም 11 የዘፈን ስብስቦች ያሉት አልበም ነው። ከአልበሙ ላይ ሦስት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ተሰርቶ የተጠናቀቁ ሲሆን ይህ አልበም በያሬድ ነጉ ፕሮዲዩስ ተደርጓልም ተብሏል፡፡
ይህ "ዳታን" የተሰኘው አልበም በግጥም ወንደሰን ይሁብ፣ ፍሬዘር አበበወርቅ፣ ኃ/ማርያም መንግስቴ ፣ ጃሉድ አወል፣ሄኖክ ክብሩ(ጎፈር)መልእቲ ኪሮስ እና ፈለቀ ማሩ በዜማ በኩል ፋኑ ጊዳቦ ፣ ፀጋው ተክሉ (ቹቹ) ፣ኤሊያስ ግዛቸው ፣ጃሉድ አወል፣ሙሉአለም ታከለ እና ዮሃና ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ፣ስማገኘው ሳሙኤል፣ፋኑ ጊዳቦ፣ ጊልዶ ካሣ፣ሱራፌል የሺጥላ እና ሃይፐር በሚክሲንግ ይትባረክ ክፍሌ ማስተሪንግ ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል፡፡
"ዳታን" የተሰኘው አልበም የፊታችን አርብ ጥር 09 በያሬድ ነጉ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በዞጃክ ወርልድ አማካኝነት ይገኛል፡፡
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1

📌የኤመረተስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ የአክብሮትና የምስጋና ልዩ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል።
ፕሮፌሰር ኤመረተስ ሽብሩ ተድላ የሥነ ሕይወት መምህር፣ ተመራማሪ እንዲሁም የአካባቢ ሳይንስ ጥናት ባለሙያ ናቸው::
የሥነፅሁፍና ታሪክ አዋቂና ደራሲ ናቸው:: እኚህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር የማክበርና የማመስገኛ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል::
በዚህ ፕሮግራም ላይ የፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ቤተሰቦች፣የክብር እንግዶች፣የስነፁሑፍ ባለሙያዎች፣ጋዜጠኞች፣የሥራ ባልደረቦች፣ የቀድሞ ተማሪዎች ብሎም አድናቂዎች ይገኛሉ::
ዲስኩሮች የመፅሐፍ ፊርማና የተለያዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉ መርሐግብሩ ዛሬ ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በዋሊያ መፅሐፍት (4ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ዝቅ ብሎ ) ይካሄዳል።

📌"አስትሮ ፎቶግራፊና የከዋክብት ምልከታ" የተሰኘ ልዩ ዝግጅት ነገ አርብ ይካሄዳል።
(መግቢያው በነፃ ነው)
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሥነጥበብና የሳይንስ ማዕከላት ጋር በመተባበር ነገ አርብ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም "የአስትሮ ፎቶግራፊና የከዋክብት ምልከታ" ዝግጅት አሰናድቷል፡፡
መርሐገብሩ ከቀኑ 11፡30 እስሰ 12፡00 ስለ አስትሮ ፎቶግራፊ አውደርዕይና ገለጻ የሚኖር ሲሆን ከምሽቱ 12፡00 እስከ 1፡30 የከዋክብት ምልከታ ይከናወናል ተብሏል።አቅራቢ ክብረት አፅባሓ (አስትሮ ፎቶግራፈር) ናቸው።
አድራሻ: ከፒያሳ ወደ ውንጌት በሚወስደው ዋና መንገድ - ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ አለፍ እንዳሉ በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ወይንም በተለምዶ ወረዳ ስምንት እየተባለ የሚጠራው ቦታ ላይ ሲደርሱ መለስተኛውን አስፓልት ይዘው 500 ሜትር ገባ ቢሉ ግቢውን ያገኙታል።
በዊንጌት መስመር የሚመጡ ከሆነ ደግሞ መድኃኒያለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን አለፍ እንዳሉ ወረዳ ስምንት ሲደርሱ በስተግራ የሚገኘውን መለስተኛ አስፓልት ይዘው 500 ሜትር ከፍ እንዳሉ ሙዚየሙን ያገኙታል።
ጎግል ማፕ፥
https://maps.app.goo.gl/GwKfjcwg1jmqsfG76
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
https://www.tg-me.com/+VZQIhKm-NoAwYjM0

📌የአዲስ ጌራ "ወዳጅ" ሙዚቃ ዛሬ ይለቀቃል
የወጣቷ ድምጻዊት አዲስ ጌራ "ወዳጅ" የተሰኘ አዲስ ሙዚቃ ዛሬ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም በራሷ የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል ተብሏል።
የሙዚቃው ግጥምና ዜማ በራሷ በድምጻዊዋ የተሰራ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር ሀብታሙ ነጋሽ በሚክሲንግና ማስተሪንግ ኤንዲ ቤተ ዜማ ተሳትፈውበታል።
የሙዚቃ ቪዲዮው ዳይሬክተር ዘመን እሸቱ ነው።
ድምጻዊት አዲስ ጌራ ከዚህ ቀደም "ማን ያውቃል " እና "መስከረሜ" የተሰኙ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች አድርሳለች።

📌የአስቻለው ፈጠነ አዲስ ሙዚቃ በተለቀቀ በአጭር ቀናት ውስጥ ከአንድ ሚሊየን በላይ እይታን አገኘ
የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ(አርዲ) "አሞራው ካሞራ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ሙዚቃ በብርቧክስ ሪከርድስ ዩቲዩብ ቻናል በተለቀቀ በሁለት ቀናት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን እይታ እንዳገኘ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።
አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ከዚህ ቀደም "እናትዋ ጎንደር" እና "ካሲናው ጎጃም" በተሰኙ ሙዚቃዎች ከፍተኛ ተደማጭነትን አግኝቷል።
በተጨማሪም ባሳለፍነው ዓመት ጥር ወር በለቀቀው "አስቻለ" የሙዚቃ አልበም ተወዳጅነትን አትርፏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ(አርዲ) "አሞራው ካሞራ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ሙዚቃ በብርቧክስ ሪከርድስ ዩቲዩብ ቻናል በተለቀቀ በሁለት ቀናት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን እይታ እንዳገኘ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።
አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ከዚህ ቀደም "እናትዋ ጎንደር" እና "ካሲናው ጎጃም" በተሰኙ ሙዚቃዎች ከፍተኛ ተደማጭነትን አግኝቷል።
በተጨማሪም ባሳለፍነው ዓመት ጥር ወር በለቀቀው "አስቻለ" የሙዚቃ አልበም ተወዳጅነትን አትርፏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ተወዳጁ "ዘ-ገሊላ" ሙዚቃ 20 ዓመት ሞላው
የበርካቶች ትዝታ የሆነውና የጥምቀት ሰሞን የቴሌቪዥንና ሬድዮ ጣቢያዎች የሚቀባበሉት የድምጻዊ ይሁኔ በላይ "ዘ-ገሊላ" ሙዚቃ ዘንድሮ ድፍን 20 ዓመት ሞልቶታል። ይህ ተወዳጅና ዘመን አይሸሬ ሙዚቃ ለአድማጮች የደረሰው በ1997 ዓ.ም ነበር።
"ወርዉሬ መታሁት ጥላሽን በእምቧይ፣
ደሞ ባንች በኔ ከልካይ አለን ወይ።
ወደአንች ስመጣ ተመለስ የሚለኝ፣
ማን ይሆን ወገኛዉ የሚከለክለኝ።
***
ወንዞ አይፈሬዉ ቀሚስ የተሸነሸነዉ፣
ትፍትፉ መቀነት ወገቧን የዞረዉ፣
ልቤን በጉንፏ አዉሎ አሳደረዉ።
***
እንኳን ዛጎል ማርዳዉ አምባሩም መስቀሉ፣
ሽርብት አደሬ ማተብሽ ድንግሉ፣
አንችን ለማሳመር መች አነሰ ባሉ።"
ርዕስ: ዘገሊላ
ድምጻዊ: ይሁኔ በላይ
ግጥም: አቤል መልካሙ
ዜማ: አስቻለው አየለ
ሙዚቃ ቅንብር: ዳዊት ጥላሁን

📌"ዛኘ" ነጠላ ሙዚቃ ተለቀቀ
የድምፃዊ ፈለቀ ማሩ ''ዛኘ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የጉራጊኛ ነጠላ ሙዚቃ በሪቦ አዲስ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ደርሷል።
የሙዚቃው ግጥም በፈለቀ ማሩ የተሰራ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር በኩል በኃይሉ ዘርይሁን ተሳትፏል።

📌"የሕይወት ታሪክ" ተውኔት በልዩ ፕሮግራም ዛሬ ይቀርባል።
ድርሰቱ እና ዝግጅቱ የነብዩ ባዬ እና የቢንያም ወርቁ የሆነው "የሕይወት ታሪክ" አዲስ ተውኔት ዛሬ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በልዩ ዝግጅት ይቀርባል።
ይህ ተውኔት ከዚህ ቀደም በሸገር ራዲዮ በሬድዮ ድራማ መልክ ቀረቡ የነበረ ሲሆን አሁን በመድረክ ተውኔት ቅርጽ ተሰርቷል ተብሏል።
በ"ሕይወት ታሪክ" በተውኔት ላይ ቢንያም ወርቁ እና ፀደይ ፋንታሁን ለሁለት ይተውናሉ።
ተውኔቱ በነባ ጥበባት እና ኮምኒኬሽን የቀረበ ነው።

📌አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ አረፈ
አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
አርቲስት እንቁስላሴ 30 በሚሆኑ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አገኝቷል፡፡

📌በፎቶግራፍ ጥበብ ላይ ሙያዊ ውይይት ተከናወነ
በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ከአዲስ አበባ ፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር "በፎቶግራፍ ጥበብና በለውጥ ሰበዞች" ዙሪያ ሙያዊ ውይይት ጥር 9 2017 ዓ.ም በአካዳሚው ውስጥ አከናውኗል።
በሙያዊ ውይይቱ ላይ የሥነጥበብ ባለሙያና ኲሬተር ቆንጅት ሥዩም፣ ማኅደረ ኃይለሥላሴ፣ ሙሉጌታ አየነ፣ አንቶኒዮ ፊዮሬንቴ እና ሚካኤል ፀጋዬ የተሳተፉ ሲሆን፣ ወ/ሮ ቆንጅት የውይይት ሐሳቦችን በማንሳትና ጥያቄዎችን በማጫር ውይይቱን አጋፍራለች።
ከታኅሳስ 12 2017 ዓ.ም አንስቶ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ በቆየው "የለውጥ ሰበዞች" የተሰኘውን የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ መነሻ በማድረግ አራቱም ፎቶግራፈሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ስላገኟቸው ዕውቅናዎችና በሙያቸው ስላጋጠሟቸው ፈተናዎች በማንሳት ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
አካዳሚውና ማኅበሩ ከታህሳስ 12 እስከ ጥር 9-2017 ድረስ ያሰናዱት ዐውደ ርዕይና ውይይት የፎቶግራፍ ጥበብ በሀገሪቱ እንዲጎለብት መሰል ዝግጅቶች እንዲቀጥሉ የሚያበረታታ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎችና ተወያዮች ሰፊና ጥልቅ ሙያዊ ሀሳቦችን በማንሳት ደማቅ ተዋስዖ አድርገዋል።
Via የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

📌የኢትዮ ጃዝ ፈጣሪ የሆነው ሙላቱ አስታጥቄ ‹‹ሙዚቃ ሳይንስ ነው ስለዚህም ሳይንቲስቶቹን ማክበር ይገባናል›› ሲል ተናገረ፡፡
ሙላቱ ከፎርቹን ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደገለፀው ሙዚቃ ልክ እንደኬሚስትሪ ሁሉ የተለያዩ ድምፆች ተደባልቀውና ተዋህደው ጣእመ ዜማን ይፈጥራሉ፡፡
ሲናገርም ‹‹አውሮፓዊያን ሙዚቃን እንደሳይንስ ይመለከቱታል፡፡ አስፕሪንን ለመፍጠር የተለያዩ ኬሜካሎችን እንደሚያዋህዱት ሁሉ ሙዚቃንም እንደሳይንስ ቆጥረው ጥልቅ ምርምር በማድረግ ሙዚቃን ያመርታሉ፡፡ ስለዚህም በሳይንስና በሙዚቃ መካከል ምንም ልዩነት የለም፡፡›› ብሏል፡፡ ጨምሮም አፍሪካዊያን ደግሞ ለሙዚቃ ግብአት የሚሆኑትን ለአውሮፓ እንደሚያበረክቱ አስረድቷል፡፡
በአንድ ወቅት የድሮው አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ከፍቶ እንደነበር ያወሳው ሙላቱ በተለያዩ ምክንያቶች መቀጠል እንዳልቻለ ጠቅሷል፡፡ ይሁንና በርካታ ልጆች በትክክለኛው መንገድ ላይ መሄድ አለመቻላቸው እንደሚያሳዝነው አስረድቶ ‹‹ሙዚቃ ሳይንስ ቢሆንም አፍሪካዊያን ግን እንደጊዜ ማሳለፊያና ለዳንስ ብቻ ይጠቀሙበታል›› ካለ በኋላ ሙዚቃ እንደማንኛውም ጥበብ የትምህርት ስርአቱ ውስጥ መካተት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ሙዚቃ በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ቢካተት ወጣቶች የሙዚቃን ሳይንስነት እንደሚረዱትም አስታውቋል፡፡
Via ዘሀበሻ

📌ተወዳጁ ጋዜጠኛና ደራሲ ገነነ መኩሪያ ሊብሮ በሞት ከተለየ ዛሬ አንድ አመት ሆነው ።
ጋዜጠኛ ፥ ፀሀፊ ፥ ደራሲ ፥ ታሪክ አሻጋሪና ፥ የተራማጅ ሀሳብ ባለቤት ፥ እንዲሁም የአዲስ ሀሳቦች አፍላቂ የሆነው ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) በሞት ከተለየን ዛሬ አንድ ዓመት ሆነው።
የገነነ ቤተሰቦቹም " የገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ሞት ለታሪክ አድማጭና ፥ ለታሪክ አንባቢው ፥ ለታሪክ ነጋሪና ለታሪክ ተረካቢው እንዲሁም ሁሌም አዲስ ሀሳብና መንገድን ለሚናፍቀው ለሀገራችን የእግር ኳስ ስፖርት ትልቅ ሞት ሲሆን ከሁሉ በላይ ደግሞ ለእኛ ለቤተሰቦቹ ሀዘኑ በቃል የማይገለፅ እጅግ ከባድ ሀዘን ነው" ብለዋል።
የጋዜጠኛና ደራሲ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የአንደኛ የሙት ዓመት መታሰቢያንም ነፍሱ ባረፈችበት በዛሬዋ ዕለት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ አካሄድ መሠረት በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በፀሎት እንደታሰበ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ቤተሰቡ በተጨማሪ " እኛ ቤተሰቦቹ እርሱን ለማሰብም በቁስቋም ጌርጌሴኖን የመርጃና ማገገሚያ ማዕከል የሚገኙ ወገኖቻችንን በመመገብም እንዘክረዋለን" ብለዋል።
"የገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) እልፈት ከተሰማ ጀምሮ ሀዘናችንን ሀዘናችሁ አድርጋችሁ ከሀገር ውስጥም ይሁን ከውጪ ሀገር ያፅናናችሁን ወዳጆቹ በሙሉ ስለሁሉም ነገር በፈጣሪ ስም እጅግ አድርገን ዛሬም እናመሰግናችኋለን" ሲሉም ምስጋናቸውን አቅረበዋል።

📌የአርቲስት እንቁስላሴ የቀብር ሥነሥርዓት ተፈፀመ
የአርቲስት እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ የቀብር ሥነሥርዓት ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም በቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እንደተፈጸመ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአርቲስት እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ በተወለደ በ71 ዓመቱ ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 11/2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡
አርቲስት እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ ከአባታቸው ከአቶ ወ/አገኘሁ ኃይሌ እና ከእናታቸው ወይዘሮ ዘውድነሽ ብሩ በጥቅምት 27/1946 በአዲስ አበባ ከተማ መወለዱን የህይወት ታሪኩ ያትታል።
ከባለቤቱ ወይዘሮ አይናለም ወርቁ 3 ሴቶች እና 3 ወንድ ልጆች ያፈራ ሲሆን እንዲሁም 12 የልጅ ልጆችን አፍርቷል፡፡

📌የአስትሮ ፎቶግራፊና የከዋክብት ምልከታ ተካሄደ
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሥነ - ጥበብና የሳይንስ ማዕከላት ጋር በመተባበር የአስትሮ ፎቶግራፊና የከዋክብት ምልከታ አከናውኗል፡፡
በፀሐይ ምልከታ መርሐግብር ቴሌስኮፕን በመጠቀም የፀሐይን ፎቶስፊር እንዲሁም የፀሀይን ስፖቶች ታዳሚያን መመልከት ችለዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም አስትሮ ፎቶግራፈር ክብረት አፅባሓ በቴሌስኮፕ ታግዘው የተነሱ የሰማይ አካላት ፎቶግራፎችን ያሳዩ ሲሆን ስለአስትሮ ፎቶግራፊ ሙያ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በማታው መርሐግብር በሶሳይቲው ባለሙያ ሊዲያ ዲንሳ አስተባባሪነት ተሳታፊዎች ቬነስን እና ጁፒተርን ከአራት ጨረቃዎችዋ ጋር መመልከት እንዲሁም ሌዘር ፖይንተር/ የብርሃን መጠቆሚያ በመጠቀም ስለተለያዩ የሰማይ አካላት አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።
ይህም ተሳታፊዎችን የሚያስተምር እንዲሁም የተማሩትን በተግባር ለማስደገፍ ያገዘ መርሐግብር ሆኖ አልፏል፡፡
ጥር 9/2017 በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎችና ታዳሚያን ተገኝተዋል፡፡
©️መረጃው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ነው።

📌"የሎሚ ጭማቂ ትዝታ" አርብ ይመረቃል
በደራሲ አህመድ ሁስ የተዘጋጀው "የሎሚ ጭማቂ ትዝታ" የተሰኘ የረጅም ልቦለድ መጽሐፍ አርብ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።
በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ላይ አርቲስት ሚካኤል ታምሬ፣ደራሲ ህይወት እምሻው፣ ገጣሚ ሚካኤል ምናሴ፣ ገጣሚ ኪሩቤል ዘርፉ ፣ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።