Telegram Web Link
📌ግንቦት 9 እና 10 ደም ለመለገስ ተዘጋጅተዋል ?

8ኛው ዙር የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች የደም ልገሳ መርሃግብር የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ግንቦት 9 እና 10 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ወላይታ ሶዶን ጨምሮ 20 የሀገራችን ከተሞች ላይ ይካሄዳል።

በዋናትም አዲስ አበባ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የብሔራዊ ደም ባንክ ግቢ ውስጥም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ይካሄዳል።በዕለቱም ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ይገኙበታል ተብሏል።

ስለዚህም የደም ልገሳ መርሐግብር አዘጋጆችም"ኑ በደማች አዲስ ታሪክ እንስራ። በሚተካውን ደም የማይተካውን የሰው ልጅ ህይወት እናድን። ለካንሰር ታማሚ ህፃናት የነገን የማየት ተስፋ ምክንያት እንሁን "ብለዋል።በዚህኛው ዙር ደም ልገሳ ከሁለት ሺ በላይ በጎ ፍቃደኞችን ደም ለማስለገስ እቅድ እንደተያዘም ተናግረዋል።

ይህን ታላቅ የደም ለገስ መርሐግብር ላይ ከ15 በላይ የግል ድርጅቶች፣10 የበጎ አድራጎት ማህበራት፣ከ10 በላይ የሚሆኑ የሚዲያ ተቋማት በጋራ በመተባበር ከተስፋ አዲስ ቤተሰቦች ጋር አዘጋጅተውታል።
📌"ወኸየ" መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል

በደራሲ ዘላለም ሞትባይኖር የተዘጋጀው "ወኸየ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ይመረቃል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይም አንጋፋና ወጣት ከያኒያን ሀሳቦቻቸውን እንደሚያጋሩ ተገልጿል።

"ወኸየ" መጽሐፍ ሙሉ ገቢው ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል ይውላል ተብሏል።የመጽሐፉ የቅጃ መብትም ለማዕከሉ ተሰጥቷል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌፤
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ:

1.ድምጻዊ ቀመር የሱፍ በ50 ዓመታት የሙዚቃ ሕይወት ጉዞዬ "የመጨረሻዬ ነው" ያለውን የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ሊያቀርብ ነው።

2."ሐሙስ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ተውኔት ከ20 ዓመታት በኃላ በድጋሚ በዕለት ሐሙስ ለመድረክ በቃ።

3.ድምጻዊው ይሁኔ በላይ ግለ- ታሪኩ ላይ ትኩረት ያደረገ መጽሐፍ ጽፏል።ከመጽሐፉ ለንባብ መብቃት በኃላም የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች እንደሚያደርስ ተናግሯል።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/5nERJHhoZlo?si=431EHlBAGViVDJ81

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌"ቍናማት" የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

በገጣሚና ደራሲ ሐዋዝ የሻነህ የተዘጋጀው "ቍናማት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ግንቦት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በዋልያ መጻሕፍት ይመረቃል።

በዕለቱም አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን በዝግጅቱ ላይ ያጋራሉ ተብሏል።

መጽሐፉ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ205 ገፆች ተቀንብቦ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚና ደራሲ ሐዋዝ የሻነህ ከዚህ መጽሐፍ አስቀድሞ "ኢካቦድ"የግጥም ስብስብ)፣ "የአዳም ፊርማ" እና "ሰውነት" የተሰኘ ረጅም ልቦለድ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቷል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
"ሕይወት እንደ መንገድ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

በገጣሚ ጋሻው የኃላሸት (ዘቢደር) የተዘጋጀው "ሕይወት እንደ መንገድ " የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ በቅደመ ክፍያ ሽያጭ ሊበቃ እንደሆነ ተሰምቷል።

ስለመጽሐፉም ገጣሚ ጋሻው የኃላሸት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ተከታዩን ብሏል:-

"እነሆ የህትመት ብርሃንን ዘመኑ በዋጀው ዘይቤ ልንቋደስ <<ሕይወት እንደ መንገድ>> ብለን የቅድመ ክፍያ አማራጭን ተከተልን።

ስለዚህ የስነ-ጹሑፍ ወዳጆች የዚች መንገድ ምርኩዝ ትሆኑኝ ዘንድ ልባዊ ቀረቤታዬ እነሆ! ...እንግዲህ እንደ ውዴታችሁ ይህቺን መድብለ ግጥም በነጠረ ወዳጅነት፣ ሚዛኑን በጠበቀ ውዴታ፣ በፍቅር ስለፍቅር ኑ እናሳትማት!

የመጽሐፏ ዋጋ 300 ብር

Tell birr፦ 0911279718
CBE፦ 1000591706137
አቢሲኒያ፦ 221613295
Gashaw yehualasht mekonen

ክፍያ ስትፈጽሙ ስክሪን ሹት አድርጋችሁ
@zebider21 ቴሌግራም ላይ መላክዎን አይርሱ!

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ድምጻዊ ብስራት ሱራፌል በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል

(መግቢያው በነፃ ነው)

የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር ብስራት ሱራፌልን ጋብዟል::

የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች"ከብስራት ጋር በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን ማክሰኞ ግንቦት  12 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ ገለጸዋል።

በዕለቱ ከድምጻዊው ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከብስራት ሱራፌል ጋር  የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ  ማክሰኞ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:

📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱

 https://jazzio.land/register

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ተሸለመ

ሰርቢያ ቤልግሬድ ውስጥ የሚገኘው የአውሮፓ የቤተሰብ ንግድ ማሕበር በየዓመቱ ለተለያዩ ሀገራት ሰዎች እንደየሙያቸው እንዲሁም አገልግሎታቸው ተመዝኖ "Family BIZ AWARDED" የተሰኘ እውቅና እና ሽልማት ይሰጣል።

የዚህ ዓመት ሽልማት ከተሰጣቸው ውስጥ አንዱ ኢትዮጵያዊው አንጋፋ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ሆኗል።

ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠም "በጣም ደስ ብሎኛል አመሰግናለሁ "ብሏል።

ቤልግሬድ ሰርቢያ ተገኝቶ ሽልማቱን እንዲወስድ በክብር ተጋብዟል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
ጉዞ ወደ ተወዳጁ ቦታ ዶሆ ሎጅ እና አዋሽ ፓርክ

📅 Date: May 24-25 / 2025 / ግንቦት 16 እና 17/ 2017 E.C
Duration: 2 Days & 1 Night
🚌 Departure:
📍 mexico wabi shabele hotel
⌚️ 6:00 AM / 12:00 LT

Price(💵): 7700 ETB for Locals

Package includes:
ትራንስፖርት / Transportation
ቁርስ / Breakfast /X2/
ምሳ / Lunch /X2/
እራት / Barbecue Dinner
የታሸገ ውሃ / Bottled Water
የመግቢያ ዋጋ / Entrance Fees
የአስጎብኚ / Local Guide
የፓርክ ክፍያ / Park Fees

የምሽት እሳት ዳር ጨዋታ / Campfire
የተፈጥሮ ፍል ውሀ ዋና / Hot Spring Water Swimming
ማደሪያ ድንኳን / Tent
የፎቶግራፍ / Photography

For more info call on ☎️ 0919874598
@dembel tours
📌"ስካርፍ፣ ቡና ና ጢስ" መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል

የገጣሚ አንዱ ጌታቸው "ስካርፍ፣ቡና ና ጢስ" የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ሞ ከቀኑ 8:30 ጀምሮ በመሶብ የሙዚቃ ማዕከል ውስጥ ይመረቃል።"ስካርፍ፣ቡና ና ጢስ" መጽሐፍ በቅድመ ሽያጭ በ300 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌"ሻሞ" መጽሐፍ የፊታችን አርብ ይመረቃል

በደራሲ ብሩክ በቀለ የተዘጋጀው "ሻሞ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ የፊታችን አርብ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከ11:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።

በዕለቱም ልዩ ልዩ የሥነጽሑፍ ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን በመድረኩ ያጋራሉ ተብሏል።

"ሻሞ" መጽሐፍ 16 ታሪኮች ያሉት ሲሆን በ400 ገፆች ተቀንብቧል 550 ብር የጀርባ ዋጋም ለአንባቢያን ቀርቧል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌የኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ እና ኦዲዮ ቡክ የተሰኘ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

የመሰናዶው አዘጋጆች" የኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ እና ኦዲዮ ቡክ በሚል ርዕስ ከ"ኢትዮጵያ ቡክ ፎረም" አሰናኝ ዳዊት ብርሃኑ፣ ከ "በተለይ አሥራ አንደኛው" እና "ወድቆ የተገኘ ሐገር" መፅሐፍት ደራሲ ይፍቱስራ ምትኩ፣ ከ "ለምንን ፍለጋ" መፅሐፍ ተርጓሚ ቴዎድሮስ አጥላው እንዲሁም ከ"ተራኪ አፕ" መስራች እና ስራ አስኪያጅ ናሆም ጸጋዬ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ስነ-ጽሁፍ እና ኦዲዮ ቡክ የምንዳስበበት ዝግጅት ይኖረናል" ብለዋል።

https://forms.gle/LGk4PnfL6uKXSogv6

ቀን፡ ዓርብ ግንቦት 15፣ 2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 11፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት
ቦታ፡ ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌ዝሆኑን በሴራ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው

በኢትዮጵያ የቀድሞ ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸውና ከሰሜን እስከ ምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ድረስ በነበራቸው ወታደራዊ ሃላፊነት እና ሚና የሚታወቁት ሌተናንት ኮሎኔል በላይነህ ታዬ የጻፉትና እና በኢትዮጵያ ሠራዊት ምስረታ እና ውድቀት እንዲሁም በደርግ ውስጥ ሰለነበሩ ሴራዎች እና ሌሎች አዳዲስ መረጃዎችንና ያልተሰሙ ታሪኮችን አካቷል።

ዝሆኑን በሴራ የተሰኘ መጽሃፍ ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡00 በኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማህበር አዳራሽ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ከፍተኛ የጦር መሪዎችና የመንግስት ባለስልጣናች ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ፣ጥሪ የሚደረግላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ያስመርቃሉ፡፡

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌የግጥም ግጥሚያ ለሁለተኛ ጊዜ ሊካሄድ ነው

የኢትዮጽያ የግጥም ግጥሚያ ሁለተኛ ጊዜ ነገ ቅዳሜ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በመሶብ የሙዚቃ ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

በተጨማሪም የገጣሚ አንዱ ጌታቸው "ስካርፍ፣ቡና ና ጢስ" የተሰኘ መጽሐፍ  ይመረቃል ተብሏል ።

አዘጋጆቹም ስለዚህ መሰናዶ ተከታዩን ብለዋል"የመጀመሪያው የግጥም ሲጥም ዝግጅት ላይ፤ ምግባር ሲራጅ ራስ በነበረበት እሱ ቀጣይ ባለተራ ስለነበር ዝግጅቱን አጋፍሮ በሁለተኛው ዝግጅታችን ደሞ headliner poet (ራስ) በመሆን በዲበኩሉ ጌታ አጋፋሪነት “ባዶ ሰው በባዶ ቤት” የተሰኘች መጽሐፉ ተነበበች፣ ቀረበች፣ በወዳጆቿ ተዘየረች።

አሁን እኛም ሁለተኛውን ኢትዮጽያ  የግጥም ግጥሚያ ስናዘጋጅ እሱም ሁለተኛ መጽሐፉን “ስካርፍ፣ ቡና’ና ጢስ “ን ያስመርቃል! እልል እንጂ ምን ይባላል!!! ለመጽሐፍ ምርቃቱ ኑ! የግጥም ግጥሚያውንም ታደሙ! ግጥም በቡናም በጢስም ታጅባ በሞሰብ የሙዚቃ ማዕከል ትነግሳለች። የ2017 የኢትዮጽያ የግጥም ግጥሚያ ቻምፒዮን እንሰይማለን"

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

60ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ዶ/ር ይሁኔ አየለ "ቡዳ! እውነት ወይስ ሀሰት" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ግንቦት 17  2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ አባቶች ቀን ዛሬ ይከበራል

የኢትዮጵያ አባቶች ቀን ኢትዮጵያውያን በራሳችን ወግና እሴት ብሎም የመከባበር ባህል መሰረት ኢትዮጵያዊ ቀለም ባለው መልኩ "ክብር ለአባትነት" በሚል ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ ግንቦት 15 በሃገር አቀፍ ደረጃ መከበር የጀመረ ቀን ነው።

ግንቦት 15 የተመረጠበት ምክንያት የጣልያን ወራሪ ኃይልን አድዋ ላይ መክተው ያሸነፉት ጀግኖች አባቶቻችን በድል አድራጊነት ወደ መናገሻ ከተማቸው የተመለሱበት በመሆኑ ብዙሃኑ አባቶች ከቤተሰብ ባሻገር ለሃገር መፅናት ላደረጉት ተግባር የሚታወሱበትና ምስጋና የሚቀርብበት ዕለት እንዲሆንም በማሰብ ነው፡፡

ላለፉት 17 አመታት በኢትዮጵያ የአባቶች ቀንን ግንቦት 15 ላይ ሲያከብር በቤተሰባቸው፣ በአካባቢያቸው፣ በወዳጆቻቸው እና በዙሪያቸው ባሉ ሁሉ ስማቸው በመልካም የሚነሳ፣ አርአያ መሆን የቻሉ፣ ከቤተሰብ እስከ ሃገር በመልካም አባትነትና አበርክቶ የሚነሱ አባቶችን፤ የኢትዮጵያ አባቶች የክብር መገለጫ የሆነውን ጋቢ በመደረብ፣ ዝቅ ብሎ እግር በማጠብ፣ የዕውቅና ምስክር ወረቀት በመስጠትና ታሪካቸውን በመሰነድ ሲያመሰግን እና ሲያከብር ቆይቷል።

ግንቦት 15 እንደሌላው ዓለም ሁሉ ኢትዮጵያዊ መልክ የያዘ፣ ኢትዮጵያውያን አባቶች የሚመሰገኑበት፣ በኢትዮጵያ ካላንደር ኢትዮጵያዊ ምክንያት ኖሮት የሚከበር "የኢትዮጵያ አባቶች ቀን" ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌"ሥዕልና ጃዝ" የተሰኘ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል

(መግቢያው በነፃ)

"ሥዕልና ጃዝ" የተሰኘ ዝግጅት ነገ ቅዳሜ ግንቦት 16 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ መካኒሳ አካባቢ በሚገኘው ጃዝ ኮፊ ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም የሥዕልና ጃዝ ፌስቲቫል እንዲሁም ሌሎች አሳታፊና አዝናኝ ዝግጅቶች ይኖራሉ ተብሏል። መግቢያው በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌ኢቢኤስ ቁጥር አንድ ብራንድ ሆኖ ተመረጠ

ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚዲያ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ተቀባይነት ያለው ቀዳሚ ብራንድ ተብሎ የተመረጠው መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገው ብራንድ አፍሪካ የተሰኘው ተቋም ባዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡

በዚሁ የእውቅና ዝግጅት ላይ  ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ተቀባይነት ካላቸው የመገናኛ ብዙኃን ብራንዶች መካከል ቁጥር 1 የሆነው ቢቢሲና አልጀዚራን በማስከተል መሆኑን ነው ብራንድ አፍሪካ ያሳወቀው፡፡

ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚዲያ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ብራንድ ስለመሆኑ እውቅና በተሰጠበት በዚህ መድረክ ላይ የሀገርን አርማ ይዞ በመላው አለም የሚበረው አንጋፋውና ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ10 ተከታታይ ዓመታት በላይ ግዙፍ ስማቸውን ይዘው ከዘለቁ 5 ብራንዶች መካከል አንዱ በመባል እውቅና ተችሮታል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን አየር መንገዱ በአፍሪካ በአቪዬሽን ዘርፍ ካሉ ተመራጭ ብራንዶች ውስጥ ቀዳሚው በመሆን ኤምሬትስና ኳታር አየር መንገዶችን አስከትሎ የአፍሪካ ተመራጭ አየር መንገድ ስለመሆኑ ነው በዝግጅቱ ላይ የተነገረው፡፡

Via EBS

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

1.ድምጻዊት ሀይማኖት ግርማ "ጅንኑ" ስትል የሰየመችውን የሙዚቃ አልበም ከ12 ዓመታት በኃላ ዛሬ ለሙዚቃ አድማጮች አቀረበች።ድምጻዊት ኃይማኖት "ተረስቻለሁ የሚል ስጋት አለኝ፣አደጋ አጋጥሞኝ ነበር። ሙዚቃ ባቆምኩበት ሰዓት ተመልሼ የምመጣ አልመሰለኝም ነበር" ስትል ተናገራለች ስለጉዳዩ በአርትስ ስፔሻል ትሰማላችሁ።

2.በአሜሪካውያን የተሰራው "ኢትዮጵያ" የተሰኘ ተውኔት ከ88 ዓመታት በኃላ ከሰሞኑ በዋሽንግተን ዲሲ ለመድረክ በቅቷል። ተውኔቱ በ1930ዎቹ ከተዘጋጀ በኋላ በጊዜው የአሜሪካ ፕሬዚደንት በነበሩት ቴዎዶር ሩዝቬልት አስተዳደር አማካኝነት ለህዝብ ለዕይታ እንዳይቀርብ በይፋ ታግዶ የቆየ እንደሆነ ተነግሯል።በዝርዝር እንነግራችኋለን።

3.በአዲስ አበባው የጣይቱ የባህል እና ትምህርት ማዕከል ውስጥ የፊታችን ሰኞ በማዕከሉ ታሪክ የመጀመሪያው ግዙፍ የሥነጥበብ አውደርዕይ ለእይታ ሊበቃ ነው።

4.የ"ድንቅነሽ" ወይንም "ሉሲ" አጽም የተገኘበት 50ኛ ዓመት ተከበረ። እንዲሁም  በእድሳት ምክንያት ተዘግቶ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/8zfvUnde4nA?si=YcyoId-NFm08fa_g

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የሸገሩ ስንክሳር ፕሮግራም መጽሐፍ ሆነ

በጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ የተዘጋጀውና በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበት "እነሆ ስንክሳር" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

በሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬድዮ ለዓመታት ሲተላለፈ የቆየው "ስንክሳር" የሬድዮ ፕሮግራም አሁን በመጽሐፍ መልክ እንደተዘጋጀም ተነግሯል።

"እነሆ ስንክሳር"መጽሐፍ የፊታችን ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጀ ያመለክታል።

መጽሐፉ በጃፋር እና በዕውቀት በር መጻሕፍት መደብሮች በኩል ለአንባቢያን ይከፋፈላም ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አንድ እና ተከታዩን ቅጽ ሁለት መጻህፍትን በተከታታይ ከዚህ ቀደም ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

Telegram: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ወደ አየር ተመለሰ

ተወዳጁ የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ጣቢያ ለተወሰነ ጊዜ ከአየር ወርዶ እንደቆየ ይታወሳል።

ቴሌቪዥን ጣቢያው ከትላንት ጀምሮ ወደ አየር እንደተመለሰም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን በDstv ቻናል 468 እና በኢትዮሳት 11605 አሁን በስርጭት ይገኛል ተብሏል።

ትኩረቱን ልጆች ላይ አድርጎ የሚሰራውና በጥቂት ጥሪት፣ የሰው ሀይል እዚህ የደረሰው የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ጣቢያ በልጆችና በቤተሰብ ዘንድ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሆነ በርካቶች ይመሰክራሉ።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
2025/07/07 04:30:41
Back to Top
HTML Embed Code: