Telegram Web Link
📌የተለያዩ ስልጠናዎች ለስልጠና ፈላጊዎች

(ያልተከፈለበት ማስታወቂያ )

በዚህ ክረምት በጋዜጠኝነት፣ በፊልም፣ በሥነጽሑፍ፣ በግራፊክስና ዲዛይን፣ በስብዕና ግንባታ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች አጫጭር ስልጠናዎችን መውሰድ ከፈለጋችሁ በእዚህ ተቋማት መሰልጠን ትችላላችሁ።

ኤቨንት አዲስ ሚዲያ መልካም የክረምት ስልጠና ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኝላችዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
🙏132🔥1👏1
📌ድምጻዊ ምስክር አወል "አዲሱ አልበሜ ያለፈቃዴ ነው የተለቀቀው" ሲል እንባ እየተናነቀው ተናገረ

የድምጻዊ ምስክር አወል አስር የሙዚቃ ስብስቦችን የያዘና "ልቻለው"  የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ አልበም ከወራት በፊት ሀርመኒ መልቲሚዲያ በተባለ የዩቲዩብ ቻናል እንደተለቀቀ ይታወሳል።

ትላንት ሰይፉ ሾው ላይ የቀረበው ድምጻዊ ምስክር አወል "አዲሱ አልበሜ ያለፈቃዴ ነው የተለቀቀው" በማለት እንባ እየተናነቀው ሲናገር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

በተጨማሪ ከዓመታት በኋላ ብዙ ለፍቶ ሙሉ አልበም ቢሰራም ድምጻዊው "ፕሮውዲሰሮቹ" ሲል የሚጠራቸው አካላት ግጥሙን ቆረጠው፣ ጥራት በጎደለው ቅንብር ፣ ያለምንም ማስታወቂያ (ፕሮሞሽን) በአጠቃላይ አልበሙ ሳያልቅ እንደለቀቁበትም ገልጿል።

ድምጻዊ ምስክር አወል ኢትዮጵያ ፣ እያመነሽ ፣ መንታዎቹ በሚሉት ዘፈኖቹ በበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
😢179💔3👍1
📌የሰርፀ ፍሬስብሐት አዲስ ሹመት

የሙዚቃ ባለሙያ ሰርፀ ፍሬስብሐት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆኖ እንደተሾመ ታወቀ።

ሰርፀ ፍሬስብሐት ከሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ይፋዊ ትውውቅ ማድረጉን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በፌስቡክ ገጹ ያሰራጨውን መረጃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

ሰርፀ ፍሬስብሐት አስቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ የባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ማገልገሉ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
10👏6🔥3👍2😁1
📌በዓለም ሲኒማ በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

እሁድ በ12:00 "ከመጋረጃ ጀርባ" ተውኔትም ይቀርባል።

    መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
2
📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

    መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
👍61
📌የበጎ ሰው ሽልማት በበጀት እጥረት ሊቋረጥ ተባለ

ላለፉት 12 ዓመታት በዓመቱ መጨረሻ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች ላይ በጎ አስተዋፅኦ ላደርጉ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት ድርጅቱን በሚደግፉ ተቋማት የፋይናንስ እጥረት ሳቢያ የመቋረጥ አደጋ እንዳጋጠው ተነግሯል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ላለፉት 10 ዓመታት ስፖንሰር በማድረግ ሽልማቱን ሲደግፍ የቆየው ሄኒከን ኢትዮጵያ የቢራ ማስታውቂያ በብሮድካስት ሚዲያዎች እንዳይተላለፍ መታገዱን ምክንያት በማድረግ የበጎ ሰው ሽልማት መርሃ ግብር በቀጥታ ስርጭት በቴሌቪዥን በሚተላለፍበት ወቅት ሽልማቱን ስፖንስር ከሚያደርግበት በጀት ጋር የማይመጣጠን ማስታስታወቂያ ሽፋን በመሰጠቱ የተነሳ የስፖንሰር ድጋፉን ማቋረጡ ታውቋል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማትን እንደ ቴሌና ንግድ ባንክ ባሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ስፖንስር ለማስደረግና ለማስቀጠል የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ የዘንድሮ የበጎ ሰው ሽልማት ላይካሄድ እንደሚችል ታውቋል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተመዘገበና በበጎ ፈቃደኛ የቦርድ አባላት የሚተዳደር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ዓመታዊ የሽልማት በጀቱን አሁንም በለጋሾች ድጋፍ ነው የሚያካሂደው፡፡

Via ቁምነገር  ሚዲያ

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
4😁4🤔1
📌"የበርበሬ አውሎንፋስ" የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

የደራሲ አበረ ሽፈራው"የበርበሬ አውሎንፋስ” የተሰኘ መጽሐፍ ትላንትና ሀሙስ ሀምሌ 3 2017 በዋልያ መጸሀፍት ቤት አዳራሽ ተመርቋል።

የደራሲ አበረ ሽፈራው “የበርበሬ አውሎንፋስ”፣ የመጀመሪያ መጽሐፉ ሲሆን፣ በስነጽሁፍ መንገድ ላይ ለረጅም ዓመታት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አሻራውን ያኖረ ሰው ነው።

በተጨማሪም ከደራሲ ህይወት እምሻው (ባለቤቱ ናት) ስራዎች ጀርባ የሚደግፋትና የሚያግዛት ቁልፍ ሰው እንደሆነ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
👍4
📌"ቆይታ ከትዕግስት ዋልታንጉስ ጋራ"

"ቆይታ ከትዕግስት ዋልታንጉስ ጋራ" የተሰኘ በስነ-ልቦና ያተኮረ ልዩ የውይይት ዝግጅት ሊካሄድ ነው።

ይህ ውይይት የሚካሄደው ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሲሆን ጀምሮ የሚካሄድበት ቦታ ደግሞ አዲስ አበባ እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኘው ከቤት እስከ ከተማ ከተማ ማዕከል ውስጥ ነው።

ትዕግስትም ዋልተንጉሥ የስነ ልቦና ባለሙያ ስትሆን ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በአዕምሮ ቁስለት (trauma focused therapy) ላይ በማተኮር ንቁ አገልግሎት  እየሰጠች ያለች ባለሙያ ናት። በ2016 ዓ.ም ለንባብ የበቃው እና 10ኛ ዕትም ላይ የደረሰው  የ "ምን ሆኛለሁ?” መጽሐፍ ተባባሪ ጸሐፊም ናት።

የዚህ ዘግጅት መግቢያው 300 ብር ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
6👍3👎2
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:

1.ጀግና አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ "የኃይሌ ኃይሎች" የተሰኘ መጽሐፍ በልጁ ተጽፎለታል።የኃይሌን ብዙውን የሕይወት ታሪክ ሕዝብ የሚያውቀው ቢሆንም ይሄን መጽሐፍ ምን ለየት ያደርገዋል ? ከልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረስላሴ ያገኘውን መልስ እንነግራችኋለን።

2. ተወዳጁ ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ በትወና የተሳተፈባቸው ሁለት የተለያዩ ፊልሞች በአንድ ሳምንት ውስጥ ለእይታ ሊበቁ ነው።

3. ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ"ለካ ሰርቻለሁ፣የሀገሬ ሥነጽሑፍ ውስጥ አለሁበት" ሲል የተናገረበትና ሶስት ተከታታይ ድርሰቶቹ በአንድ የተሰበሰቡበት "ዝይን" መጽሐፍ ለአንባቢያን ሊቀርብ ነው።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/D96pVJBAZuY?si=GaREQolLqIOpDB3L

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
6👍2👏1
📌ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ነገ ይካሄዳል።

ልዑልሰገድ በየነ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 92ተኛ መድረክ "ፍለጋችን በዘመናችን ውስጥ" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ ነገ ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
1
📌የገጣሚ መላክ ማሩ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

የገጣሚ መላክ ማሩ "መንታ ነፍስ"የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ ነገ ሐምሌ 6 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ታኦስ የባህል አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዕለቱም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በመጽሐፉ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
1
📌የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "እንደ አመሌ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ትላንት አመሻሹን በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ በኩል ለአድማጮች ቀርቧል።

በ"እንደ አመሌ" ሙዚቃ ላይ በግጥምና ዜማ አብዲ እንዲሁም በቅንብር ብሩክ ተቀባ ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
👍3
📌የአለማየሁ ገላጋይ ሦስት ድርሰቶች ተሰበሰቡ

የደራሲ አለማየሁ ገላጋይ ሦስትያ ድርሰቶች በአንድ የተካተቱበት መጽሐፍ ለአንባቢያን ቀረበ።

በፍቅር ስም ፣ ታለ በእውቀት ስም፣ ሀሰተኛው በእምነት ስም  የተሰኙ ሶስት ተከታታይ ድርሰቶች "ዝይን" በተሰኘ ርዕስ ውስጥ በአንድ እንደተሰባሰቡም ተነግሯል።

የመጽሐፍ አሳታሚ ዋልያ መጽሐፍ ሲሆን በጠንካራ ወረቀት፣ ለማንበብ በሚያመች መልኩ እንደተዘጋጀም ተገልጿል። በተጨማሪም በሀርድ ከቨር 200 መጻሕፍት ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።

ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ በማህበራዊ ትስስር ገፁም “ዝይን" ን ዳጎስ ብላ ስመለከት " ለካ ሰርቻለሁ፣ የሀገሬ ሥነ ጽሁፍ ውስጥ አለሁበት" የሚል ምስክርነት ለራሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰማኝ። አይጣበቅብኝ ፣ ለእብሪት አይዳርገኝ እንጂ አንዳንዴ ይሁን" ሲሉ ተናግሯል።

መጽሐፉ በቅርቡ በተለይ ዝግጅት እንደሚመረቅም አርትስ ስፔሻል ከዋልያ መጻሕፍት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
🔥73👍2
📌ኢቫንጋዲ የኢንቴርየር ዲዛይን ስልጠና ጀመረ

ከተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ የሚገኘውና በሁለት ወጣት  ሴት ባለሞያዎች ሜሮን መኮንን እና ህብረወርቅ ገለታ የሚመራው ኢቫንጋዲ ኮንስትራክሽንና ቤተ-ውበት በዚህ ክረምት የኢንቴርየር ዲዛይን ስልጠና በይፋ ጀምሯል።

በተጨማሪም ኢቫንጋዲ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች -

ኢንቴርየር ዲዛይን እስከ ግንባታው

ላንድስኬፕ/የገፀ ምድር/ ዲዛይን

አርክቴክቸራል ዲዛይን

3D Rendering & Modeling

Physical modeling እና ሌሎችም አገልግሎቶች ይገኙበታል።

አድራሻቸው: ሾላ ገበያ ቡና ባንክ ያለበት ህንፃ  አንደኛ ፎቅ ላይ ነው።

ስልኩ ቀጥራቸው ደግሞ

0915416410
0938218123

በቴሌግራም አድራሻቸው @Evangadiconstruction ሊያገኟቸውም ይችላሉ።

የቲክቶክ ቻናል: merryevangadi_interiors

የቴሌግራም ቻናል:https://www.tg-me.com/Evangadiconstruction1
📌ከጋዜጦችን ጀርባ ያለ ያልተነገረለት ታታሪ ሰው

የሕትመት ዋጋ መናር ብዙ ጋዜጦችና መፅሔቶችን ከሕትመት ውጪ አድርጓል። እጅግ ተወዳጅ የነበረው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከወር በፊት ሹልክ ብሎ ከገበያ ብዙ ሰው አላስተዋለም።

ያሉትም ጋዜጦች አዲስዘመን፣ ሄራልድ፣ ፎርቹን፣ ካፒታል በገበያ ውስጥ እየተንገዳገዱ ቢቀጥሉም ኮፒያቸውን በመጨመር ተደራሽነታቸውን ለማሳደግ የሕትመት ዋጋ ንረቱ አስሮ አስቀምጧቸዋል።

አንድ ጋዜጠኛ ወዳጄ ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች ለታይታ ያህል እንጂ ኮፒ ጨምሮ ማሳተም ገንዘብን አትሞ ሜዳ ላይ የመርጨት ያህል እንደሚቆጠር አጫውቶኛል።

እንደብርሐኑ ዮሐንስ ዓይነቱ ጋዜጣ አከፋፍሎ ሕይወቱን ለሚገፋ ሰው ይኸ ጉዳይ ይበልጥ አሳሳቢ ነው።

ብርሐኑ የሕመት ኢንደስትሪው በከባድ ወጀብ ውስጥ ባለበትም በዚህ ወቅት ተስፋ ባለመቁረጥ ጋዜጦችን ተሸክሞ ከመነሻው 4 ኪሎ፣ በ 22 ፣በ መገናኛ፣ በቦሌ በእግሩ አቆራርጦ ደንበኞቹ ጋር ያደርሳል።

ጠዋት ማልዶ ተነስቶ እስከ ቀኑ 10:00 አንዳንዴም 11:00 ሰዓት ድረስ መጓዝ የዕለት ተዕለት ሥራው ነው። በዚህ መንገድ ከሚያገኛት በወር 5 ሺህ ብር ገደማ ገቢ ሁለት ልጆቹን እያስተማረ ይገኛል።

ሥራ እንዴት ነው አልኩት።
መጥፎ ነው ብሎ ማማረር አልፈለገም። በአጭሩ "ቀዝቅዟል" አለኝ።
"መቀዝቀዙ ገቢህን ጎድቶታል?"
"አዎን እንደበፊቱ አይደለም" የሚል አጭር ምላሽ ሰጠኝ።

አዎ ብርሐኑ ለዓመታት ከእጅ ወደአፍ በሆነ የጋዜጣ ማዞርና ማከፋፈል ሥራ ውስጥ ቆይቷል። ዛሬም ግን አልደከመውም። ዛሬም ሥራውን ስለማሳደግ አብዝቶ ያስባል።

"ሳይክል ወይንም ሞተር ሳይክል ባገኝ ሥራዬን ለማስፋትና ገቢዬን ለማሳደግ እችላለሁ" አለኝ።

(ፍሬው አበበ)

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
10😢4
📌ድምጻዊ አዲስ ለገሠ አዲስ ሙዚቃ ሊለቅ ነው

የድምጻዊ አዲስ ለገሠ "እቱ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ሐምሌ 5 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል ለሙዚቃ አድማጮች ይደርሳል።

በዚህ የድምጻዊ አዲስ ለገሠ ነጠላ ሙዚቃ ላይ በግጥም ናትናኤል ግርማቸው በዜማ እሱባለው ይታየው (የሺ) እንዲሁም በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ተሳትፈዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
👍31
2025/07/13 16:05:22
Back to Top
HTML Embed Code: