📌አብርሆት ቤተመጻሕፍት በጊዜያዊነት ተዘጋ

የአብርሆት ቤተመጻሕፍት በ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ምክንያት መደበኛ አገልግሎቱ በጊዜያዊነት ተቋርጧል።ለሳምንታትም በጊዜያዊነት ዝግ ሆኖ እንደሚቆይም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ቤተመጻሕፉም ስለዚህ ጉዳይ ተከታዩን ብሏል"አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሚሰጥባቸዉ ተቋማት አንዱ መሆኑ ይታወቃል።ስለሆነም ተቋሙ ከሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለዝግጅት እና ለፈተና አገልግሎት ስለሚውል የወትሮ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን በአክብሮት ልናሳውቅ እንወዳለን"።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ የተማሪዎች ምርቃት ስነ-ስርዓት እና የተቋሙን የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ያከብራል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን 75ኛ ባች ተማሪዎች ያስመርቃል።

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት በትምህርት ልህቀት፣ በአመራር ልማት እንዲሁም በሀገር ግንባታ ያደረገው ዘላቂ እና ዘርፈ ብዙ አበርክቶ ይዘከራል ተብሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከ75 ዓመታት በፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመባል ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤ የፈጠራ፣ ምርምር እና የዕውቀት መፍለቂያ በመሆን በርካታ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ምሁራንን አፍርቷል፡፡

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ የጃንቦ ሪል ስቴት አምባሳደር መሆኑን ሪል ስቴቱ ይፋ አድርጓል።

በቅርቡ 60ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከበረው ጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ በቅርቡ ከዚሁ ሪል ስቴት የመኖሪያ ቤት እንደተበረከተለት ይታወሳል።

ጋዜጠኛውና የሪልስቴት ተቋሙ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።

የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ደበበ ሰይፋ ጃምቦ ሪል ስቴት በጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ መወኩሉ ትርፋማ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሪልስቴት ተቋሙ እስካሁን 700 የሚሆኑ ቤቶችን ለቤት ባለቤቶች ገንብቶ ማስረከቡን ስራ አስፈፃሚው መናገራቸውን አራዳ ሰምቷል።

የሪል ስቴት ተቋሙ እና የጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ የሥራ ስምምነት ለሦስት ዓመት ይቆያል ተብሏል።

የአምባሳደርነት ሥምምነት መፈረሜ ቀጣይ ሥራዎቼ ላይ ትኩረት አድርጌ እንድሰራ ያደርገኛል ያለው ደግሞ ጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ ነው።

በህይወት ዘመኔ የምችለው እና የማውቀው ሥራ ጋዜጠኝነት ብቻ ነው ያለው ጋዜጠኛው ሙያው ግን የልፋትን የሚከፍል ባለመሆኑ ብዙ ሊሰራበት ይገባል ሲል አሳስቧል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ሱፐር ስፖርት ልዩ ቻናል የፊታችን ሰኞ ይዘጋል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ጨምሮ የተለያዩ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ በቀጥታ ስርጭት ለተመልካቾች ሲያሰራጭ የቆየው ዲ ኤስ ቲቪ ሱፐር ስፖርት ልዩ ቻናል ከፊታችን ሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርጭቱን እንደሚያቋርጥ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከቻናሉ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ቻናሉ የተለያዩ የስፖርት ይዘቶችን በሌሎች የሱፐር ስፖርት ቻናሎች መከታተል ትችላላችሁ ብሏል።

በያዝነው ዓመት ከወራት በፊት ካናል ፕላስ ቻናልም ከኢትዮጵያ የሚዲያ ዘርፍ ስርጭቱን አቋርጦ መውጣቱ ይታወሳል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ጋዜጠኛ ዳዊት አለሙና ውቢት ያረጋል የክብር እንግዳ የሆኑበት ልዩ ዝግጅት የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

(መግቢያው በነፃ ነው)

በሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በፒያሣ ካምፓስ የሰለጠኑ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክታቸውን የፊታችን እሑድ ሰኔ 22 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚያቀርቡ ሲሆን በዕለቱም ጋዜጠኛ ዳዊት አለሙ እና ጋዜጠኛ ውቢት ያረጋል በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት የጋዜጠኝነት ሕይወታቸውን እና ልምዳቸውን የሚያካፍሉ ይሆናል።

በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት የተመራቂ ተማሪዎችን የመመረቂያ ስራዎች እንዲከታተሉ እንዲሁም ለጋዜጠኛ ዳዊት አለሙ እና ጋዜጠኛ ውቢት ያረጋል መጠየቅ የሚፈልጉትን በማንሳት በልምድ ልውውጡ ላይ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ቢራቢሮ" ተውኔት የፊታችን ሰኞ ለመድረክ ይበቃል

በኤልያስ ቤተማርያም ተፅፎ በዘካርያስ ረታ የተዘጋጀው “ቢራቢሮ” የተሰኘው ተውኔት ለእይታ ሊበቃ ነው።

"ቢራቢሮ" ሙዚቃዊ ተውኔት ሲሆን የፊታችን ሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

በተውኔቱ ላይ ሩሐማ ኃ/ሚካኤል ፣ ዮናታን መኮንን፣ እየሩሳሌም ገ/ስላሴና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

የተወኔቱ ፕሮዳክሽን ማናጀሮች ሀና ታዬ(እርጎዬ) እና ሔኖክ ተሾመ ናቸው።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የደጃዝማች ከበደ ተሰማ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

የክቡር ደጃዝማች ከበደ ተሰማ ‹‹ነበር እንዳይረሳ - ከታሪክ ማስታወሻ ባሻገር›› የሚል ርዕስ የተሰጠው  መጽሐፍ በራሳቸው በደጃዝማች ከበደ ተሰማ ተዘጋጅቶ ከ52 ዓመታት በኋላ ነገ ለአንባቢያን ይቀርባል።

የመጽሐፉ የምርቃት ሥነሥርዓት በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር) ፣በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ አዳራሽ ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ  አራት ሰዓት (4፡00) ጀምሮ ይካሄዳል ።

ደራሲው ከዚህ በፊት በብዙ አንባቢያንና የታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ተወዳጅ በነበረው ‹‹የታሪክ ማስታወሻ›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ይታወሳሉ፡፡

በአዲሱ መጽሐፋቸው፣ ደራሲው በሕይወተ ሥጋ እያሉ  ባለፉባቸዉ  ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ኹነቶች ውስጥ የዐይን እማኝ የነበሩባቸውን ጉዳዮች ጨምሮ፣ ስለ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት  የአስተዳደር ዘይቤዎችና ልምዶች ፣ ስለ ልጅ ኢያሱ ምኒልክ አነሳስና ፍፃሜ ፣ ሰለ አፄ ኃይለሥላሴ የንግሥና ክብረ በዓል ሥርዓትና  በ1953 ዓ.ም ተሞክሮ ስለከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት  ያዩትን ፣የነበሩበትንና የታዘቡትን ለአንባቢያን  አቅርበዋል ።

በዚሁ  ወቅት በመጽሐፉ አርትዖት ላይ በቀጥታ የተሳተፉት ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለና ዶክተር  የራስወርቅ አድማሴ ግንዛቤያቸውን ያቀርባሉ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች ፣ የደራሲው ቤተሰቦችና ወዳጆች የሚታደሙ ሲኾን  ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዉ አጠር ያለ  ውይይት ይደረጋል፡፡

መጽሐፉ በዕለቱ ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለገበያ የሚውል ሲሆን በሁሉም የመጻሕፍት መደብሮች ይገኛል፡፡

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል ሊመስገን ነው

ዘንድሮ 75ተኛ ዓመት የልደት በዓሉን የሚያከብረው ተወዳጁና ተከባሪው ደራሲና መምህር ኃይለመለኮት መዋዕል ነገ በሚካሄድ ልዩ መርሐግብር ይመሰገናል።

ይህ መርሐግብር በስብሐቲዝም አዘጋጆች የተሰናዳ ሲሆን ነገ እሁድ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊው ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም ደራሲያኑ ሣህለስላሴ ብርሃነ ማርያምና ዘነበ ወላ ሀሳቦቻቸውን የሚያጋሩበትን ጭምሮ ልዩ ልዩ መርሐግብሮች እንደሚካሄዱ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ቃል እና ቅኔ" ልዩ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

ሙሉ ገቢው ለበጎ ዓላማ የሚውለው "ቃል እና ቅኔ" የተሰኘ ልዩ መርሐግብር ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ዘነበ ወርቅ (ኢቢሲ ማሰልጠኛ ተቋም ) ኦሮሚያ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ልዩ መሰናዶ ላይ ትላልቅ የኪነጥበብ ባለሞያዎች የሚገኙ ሲሆን የግጥም፣ ወግ፣ መነባንብን ጨምሮ የተለያዩ መሰናዶዎች ይቀርባሉ ተብሏል።

ትኬት መሸጥ ተጀምሯል!!
በቴሌብር
0929521135 ዳግም
0913742370 ፉአድ

በንግድ ባንክ 1000345483679 Dagim Sisay
እያስገባችሁ ደረሰኙን በዚሁ ስልክ በቴሌግራም ላኩልን።

◈ ወዳጅዎን በመጋበዝ ዓላማውን ይደግፉ!!

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

    መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌በዓለም ሲኒማ በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

    መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌አፍሪካዊቷን ጋዜጠኛ “ቆንጆ ነሽ” በማለት ያደነቁት ዶናልድ ትራምፕ መነጋገሪያ ሆነዋል

በነጩ ቤተ -መንግስት  ለዘገባ  የተገኘችውን አፍሪካዊት ጋዜጠኛ ቆንጆ ነሽ በማለት አድናቆታቸውን የገለጹት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት መነጋሪያ ሆነዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ  ዴሞክራቲከ ሪፐብሊክ ኮንጎንና ረዋንዳን  ለማስታረቅ  በተሰናዳው ስነ-ስርዓት ላይ በነጩ- ቤተ መንግሰት  ለዘገባ የተገኘችውን አንጎላዊት ጋዜጠኛ  ሃርያና ቬራስን ነው  ቆንጆ ነሽ ሲሉ ያደነቋት፡፡

እንዳንች ያሉ ቆነጃጀት ጋዜጠኞች ቢበዙ እንዴት መልክም ነበር ሲሉም  ምኞታቸውን  ገልጸዋል፡፡

"ይህን ማለቴ ትክክል ላይሆን  ይችላል”  ቢሆንም “በጣም ውብ ናት" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

Via ebcdotstream

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
በቀነኒ የቲክቶክ ገፅ የተለቀቀው ፎቶ መነጋገሪያ ሆነ

ከወራት በፊት ህይወቷ ያለፈው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ በሕይወት እያለች ትጠቀምበት በነበረውና ከ636 ሺ በላይ ተከታይ ባለው የቲክቶክ አካውንቷ ጥቃት እንደደረሰባት የሚያሳይ ፎቶ ተለቋል::

በሟች የቲክቶክ ገፅ ጥቃት እንደሚደረስባት የሚያሳይ ፎቶ ከተለቀቀ በኃላም በርካቶች እየተነጋገሩበት እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

በቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ እስር ቤት የቆየው እጮኛዋ አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ በትላንትናው ዕለት በተካሄደው የሀጫሉ አዋርድ ተሸላሚ እንደነበረ የሚታወስ ነው::

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌 ድርሹ ዳና ተሸለመች

የሬድዮ ፕሮግራም አቅራቢና የማስታወቂያ ባለሙያ የሆነችው ድርሻዬ ዳና(ድርሹ) በኢምሬትስ ዱባይ በተካሄደው 2ኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ፓርላማ  ጉባኤ ላይ ተሸልማለች።

ድርሹ ዳና በማህበራዊ ትስስር ገጿ"አሸናፊ ሆነናል።ደጉ አባቴ የልጁን ድካም ቆጥሮ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ዳግም አሸልሞኛል" ብላለች።

ድርሹ ዳና በ2ኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ፓርላማ ላይ በሚዲያና ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ከኢትዮጵያ ተመራጭ እጩ ሆና እንደቀረበች ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ኢራን ኢትዮጵያን አመሰገነች

የኢራን መከላከያ ጦር ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ደጋፊ ከኢትዮጵያ ፣ ከጋና፤ ከሶማሊያ፣ ኬኒያ እና ደቡብ ሱዳን አግኝተናል ብሏል።

ጦሩ በፌስቡክ ገጹ የሚለጥፋቸውን መረጃዎች የሚከታተሉ እና ገጹን የሚከታተሉ ዜጎች ቁጥር በመጨመሩ ነው ምስጋናውን ለሃገራቱ ያቀረበው።

በመቀጠልም ሁሌም ቢሆን የአፍሪካ እና የአፍሪካውያን ነፍስያ ከኢራን በኩል ነው ብሏል ጦሩ።

በተያያዘ ለአፍጋን ወንድም እህቶቻችን ከጎናችን ስለሆናችሁ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ዛሬ ዓለምአቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ቀን ነው

የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች ቀን ሐምሌ 2 ቀን የስፖርት ጋዜጠኞች ስፖርትን ለማስተዋወቅ የሚያገለግሉትን አገልግሎት ለማክበር በሚል በዓለምአቀፍ ደረጃ ተከብሮ ይውላል።

ይህ ቀን በ1924ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ የዓለም አቀፍ ስፖርት ፕሬስ ማህበር የተመሰረተበት ቀን በመሆኑ በይፋ "የዓለምአቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ቀን" ተብሎ ተወስኗል።

በህትመት (ጋዜጣና መጽሔት ) ፣በሬድዮና ቴሌቪዥን፣በዲጂታል የሚዲያ አማራጮች ከልባችሁ የምትሰሩ ውድ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ጋዜጠኞች እንኳን አደረሳችሁ እንላለን።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌን ያስለቀሰው ሰርፕራይዝ

ኮሜዲያን/ተዋናይ ደረጀ ኃይሌ በኮሜዲ ስራዎቹም
ሆነ በኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ ለበርካታ ዓመታት
በጥሩ ዲሲፒሊን ትንሽ ትልቁን አክብሮ ለዘመናት
ሙያውን አክብሮና አስከብሮ የኖረ ታላቅ አርቲስት እንደሆነ ይነገርለታል።

ኮሜዲያን ደረጀ ኪነጥበቡ ላይ ላሳረፈው ትልቅ አሻራና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ወዳጆቹ ፣ የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በአድዋ ባንድ ባለቤት አቶ ሞገስ ሀሳብ አመንጪነት ቦሌ በሚገኘው የመሣይ በቀለ ሆቴል ውስጥ ፕሮግራም አዘጋጅተውለት በሽልማት አንበሽብሸውታል።

ከሽልማቶቹ መካከል ደረጃውን የጠበቀ ሙሉ የቤት ዕቃዎች ፣ ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት፣ከሀብቴ ጋር አንድ ላይ የተነሱትን ፎቷቸውን እና ሌሎች ሽልማቶችም ይገኙበታል።

ደረጀም ባልጠበቀው ድንገተኛ ሰርፕራይዝ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት በደስታ ዕንባ ሲታጠብ ተመልክተነዋል።

Via ዘሪሁን ተዝናኑ

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በኒውሮሳይንስ ላይ ያተኮረ ልዩ ዝግጅት ሊካሄድ ነው

በኒውሮሳይንስ ላይ ያተኮረ ልዩ ዝግጅት ሰኞ ሀምሌ 14 2017 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ ልዩ መርሐግብር ላይ ሲናፕስ ኢትዮጵያ በይፋ ሊጀመር እንደሆነም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።"ሲናፕስ" በኒውሮሳይንስ አለም እጅግ መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ ነው። የሁለት ነርቭ ሴሎች ተገናኝተው መረጃ የሚለዋወጡበት ድልድይ ማለት ነው።

ይህንን መነሻ በማድረግ፣ ሲናፕስ ኢትዮጵያ በአገራችን የመጀመሪያው በኒውሮሳይንስ ላይ ያተኮረ የህዝብ ንግግር መርሃ ግብር ሲሆን ስለ ኒውሮሳይንስ የቅርብ ጊዜ ዕውቀቶችና ምርምሮች ይቀርባሉ።

አዘጋጆቹ የኒውሮሳይንስ ዕውቀት በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎችም የህይወታችን ዘርፎች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እንመለከታለን ብለዋል።

በተጨማሪም በተመራማሪዎችና በዝግጅቱ ታዳሚዎች መካከል የልምድ ልውውጥና አዲስ ግንኙነት ይፈጠራል ተብሏል።

እንዲሁም ስነ-ጥበብ: የሳይንስና የኪነ-ጥበብ ውህደት በፈጠረው ልዩ ድባብ እንዝናናለን ሲሉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ 300 ብር ነው።


ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በሐኪም የሚዘጋጁ ጤናማ የታሸጉ ምግቦች የሚቀርቡበት ልዩ ሁነት የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል።

በናዶራ ዌልነስ ሴንተር የተዘጋጀው " Beyond the stethoscope" የተሰኘ ልዩ ሁነት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 28 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ጀምሮ ቦሌ ኣትላስ ሶሻል አዲስ(ሴሎ) ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ሁነት ላይ በሃኪም የሚዘጋጁ ጤናማ የታሸጉ ምግቦቸ -የጤፍ ኩኪሶች - ኬኮቸ እና የተፈጥሮ ማር ይቀርባሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በእጅ የተሰሩ ጌጣ ጌጦች፥ ሌዘር ምርቶች ፥ ሠዓሊያንና እና ሥዕሎቻቸው፥ የተቀመሙ ሽቶዎች፥ አልባሳት፥ ፎቶግራፎች፥ እና ሌሎችም በዝግጅቱ ይቀርቡበታል ተብሏል።

Open mic- ኮሜዲያኖች እና ገጣሚዎች አሉም።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ 200 ብር ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የዋሸንት ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ይደገማል

የዋሽንት ተጫዋቹ ጣሰው ወንድም "የትንፋሽ ውበት" 2 ሲል የሰየመውንና ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የዋሽንት ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 28 2017  ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በመሶብ የሙዚቃ ማዕከል ውስጥ ያቀርባል።

በዚህ ኮንሰርት ላይ የዋሽንት ተጫዋቹ ጣሰው ወንድምና የፒያኖ ተጫዋቹ አብይ ወ/ማርያም ይጣመራሉ ተብሏል።

"የትንፋሽ ውበት" የዋሽንት ሙዚቃዊ ዝግጅት መግቢያ ዋጋውም 300 ብር እንደሆነ ተገልጿል።

በመሶብ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ ውስጥ በዋሽንት ተጫዋችነቱ የምናውቀው ጣሰው "የትንፋሽ ውበት" የተሰኘ የዋሽንት የሙዚቃ አልበም ከአንድ ዓመት በፊት ለአድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
2025/07/03 21:16:00

❌Photos not found?❌Click here to update cache.


Back to Top
HTML Embed Code: