Telegram Web Link
#updated
በህንድ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 270 ደረሰ።

‎ከተከሰከሰ ሶስተኛ ቀኑን የያዘው አውሮፕላኑ የ270 ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ አንድ ተሳፋሪ በህይወት መትረፉ አይዘነጋም፡፡

‎በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት መካከል 29 ሰዎች አደጋው በደረሰበት ስፍራ የነበሩ መሆናቸውን ገልፍ ቱዴይ ዘግቧል።

‎በአህመዳባድ በሚገኘው የሲቪል ሆስፒታል ዶ/ር ዳቫል ጋሜቲ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ 270 አስከሬኖችን አግኝቷል።

‎ከአውሮፕላኑ 242 መንገደኞች መካከል በህይወት የተረፈው ብቸኛው ሰው የህክምና ክትትል ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

‎በመቶዎች የሚቆጠሩ የአደጋው ተጎጂ ቤተሰቦች በሆስፒታሉ ውስጥ የዲኤንኤ ናሙና የሰጡ ቢሆንም የዲኤንኤውን ውጤት ለማወቅ እስከ 72 ሰዓታት እንደሚፈጅ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

‎ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ቦይንግ 787- 8 የሚል ስያሜ ያለው አውሮፕላን በሰሜን ምዕራብ ህንድ ከሚገኘው አህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ለንደን በረራ በጀመረ በሴኮንዶች ውስጥ የመከስከስ አደጋ እንዳጋጠመው ይታወሳል።
10😭4🔥3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእሳት ሲነድ ያደረው መካከለኛው ምስራቅ‼️
ትናንት ምሽት ኢራን በፕሮጀክታይል ሚሳይል የእስራኤልን የሃይፋን የነዳጅ ማከማቻ በመታችበት ሰዓት እስራኤል በሻህራን የሚገኘውን የኢራን የነዳጅ ማከማቻ ላይ ጥቃት አድርሳለች።
በዚህ የተነሳ የሻህራን የነዳጅ ዲፖ ለሰዓታት ሲነድ ነው ያመሸው።
የሻህራን የድፍድፍ ነዳጅ ማከማቻ ሲነድ የሚያሳየው ምስል ከላይ ተያይዟል።
10
በናይጄሪያ በተፈፀመ ጥቃት የ102 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ ቤኑ ግዛት ትጥቅ በታጠቁ የእንስሳት አርቢዎች ተፈፀመ በተባለ ጥቃት የ102 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በናይጄሪያ በውሃ እና መሬት የተነሳ በገበሬዎች እና በከብት አርቢዎች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየው ግጭት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ መጥቷል።

ከሞቱት 102 ሰዎች በተጨማሪ ከ100 የሚበልጡ ሰዎች አሁን ላይ አስጊ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ተብሏል።

ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ ቤታቸው ላይ ነዳጅ በማድረግ ቤተሰቦቻቸው በተኙበት በእሳት ማቃጠላቸውን ገልፀዋል።

ጥቃቱ ለሁለት ሰዓታት መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ሲናገሩ ፖሊስ ጥቃት አድራሾችን ለመያዝ እየሰራ ነው ተብሏል።
12🔥2
10😭5🔥1
🟩🟨🟥 ሞዓ፡ አንበሣ፡ ዘእምነገደ፡ ይሁዳ

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
41
ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ተከትሎ እስራኤል ዜጎቿን ወደ ጥብቅ መጠለያ እንዲያመሩ መልዕክት አስተላለፈች‼️
🔥93
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Israel strikes IRGC Tehran HQ — Yediot claims

Footage shows massive thick smoke engulfing mountain
🔥74
ከአርብ ዕለት ጀምሮ በትንሹ 14 የኢራን የኒውክሌር ሳይንቲስቶች በእስራኤል ጥቃቶች መገደላቸውን ሪፖርቶች አመላከቱ
🔥165
Audio
ልዩ ማሳሰቢያ
ከራዕይ ዮሐንስ 20
8/10/2017 ዓ.ም
44
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የስለላ ድርጅት (IRGC) ሃላፊ የሆኑት መሀመድ ካዚሚ እና ምክትላቸው ሀሰን ሞሃቅ በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን ድርጅቱ አረጋግጧል።
8
አሳዛኝ ዜና‼️

በትራፊክ አደጋ 5 ሰዎች ህይወታቸውን አጡ ‼️

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ሰቆጣ ወረዳ ውስጥ ባጋጠመ አሳዛኝ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ ሌሎች 11 ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል።

አደጋው የደረሰው ከደሴ ወደ ሰቆጣ አስከሬን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሰሌዳ ቁጥር አማ 30336 ኮድ 3 ሚኒባስ መኪና ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. በ07 ቀበሌ፣ ዳብል ማሪያም ዲብር ሳይል አፈራ ጎጥ ሲደርስ በመገልበጡ ነው።

በዚህ አደጋ 3 ወንድ እና 2 ሴት የአምስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፣ 7 ወንድ እና 4 ሴት በድምሩ አስራ አንድ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

የሰቆጣ ፖሊስ ጽ/ቤት የመንገድ ደህንነት ትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው እንደገለጹት፣ የአደጋው መንስኤ በምርመራ ላይ ነው።

ለሟቾች ነፍስ ይማርልን፣
ለተጎጂዎች ፈጣን ማገገም እንመኛለን።
12😭7🔥2
በቴል አቪቭ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በኢራን ጥቃት ጉዳት ደረሰበት

ትናንት እሁድ ምሽት ኢራን ባስወነጨፈቻቸው ሚሳዔሎች በቴል አቪቭ በሚገኘው የኤምባሲያቸው ቅርንጫፍ “መጠነኛ ጉዳት” መድረሱን በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር አስታውቀዋል።

ማይክ ሃካቢ በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ቆንስላው “በኢራን ሚሳዔሎች ንዝረት” ጉዳት ስለደሰበት ዝግ ሆኖ ይቆያል ብለዋል።

የአሜሪካ ኤምባሲ በቴል አቪቭ እና በኢየሩሳሌም የሚገኙ ሠራተኞቹ መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ በትናንትናው ዕለት አሳስቦ ነበር።

በሚሳዔል ጥቃቱ የተጎዳ የኤምባሲው ሠራተኛ እንደሌለም አምባሳደሩ ተናግረዋል።
23🔥3
እስራኤል የኢራን ብሄራዊ ጣቢያ ላይ ጥቃት ሰነዘረች።

እስራኤል በእስላሚክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኢራን ብሮድካስቲንግ (IRIB) ዋና መስሪያ ቤት ላይ በሰነዘረችው ጥቃት ዋና መስሪያ ቤቱ በእሳት ሲነድ ታይቷል።

ጥቃቱ ሲሰነዘር የቀጥታ ስርጭት ላይ የነበረ ሲሆን በጥቃቱ ምክንያት ስርጭቱ ተቋርጧል።

ጣቢያው የኢራንን የመንግስት ቴሌቪዥን እና የሬዲዮ አገልግሎቶች የሚቆጣጠር ሲሆን ዋነኛ የመረጃ ምንጭም ነበር።

በጥቃቱ የተነሳ ተቋሙ ስርጭቱ በበርካታ ቦታዎች ሲቋረጥ እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ከወታደራዊ ቦታ ውጪ ያጠቃችው ትልቁ ስፍራም ነው ተብሏል።

የተቋሙ ከፍተኛ መሪዎች በጣቢያው ላይ ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ "እስራኤል በወታደራዊ ኦፕሬሽን ታላቋን ኢራን እና እስላማዊ አብዮቱን ዝም ልታስብል አትችልም" ብለዋል።

ኢራን በሚዲያ ተቋሟ ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ በእስራኤሎቹ ቻናል 12 እና 14 አካባቢ ያሉ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች።

ቪዲዮ: ማኅበራዊ ሚዲያ
19🔥1
2025/07/12 16:52:03
Back to Top
HTML Embed Code: