Telegram Web Link
❗️Ukrainian militants shell civilian district in Russia’s Belgorod

There is no official information about the number of injuries yet, Governor Gladkov said.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Local media publishes moment Belgorod apartment building roof collapses — Unverified footage
Enormous blaze engulfs shopping mall in Polish capital

Warsaw firefighters have extinguished the blaze that took hours to put out.

Local media reports no major casualties at this time, however an investigation is underway.
15 Confirmed Killed, And Missing After Ukrainian Missile Attack On Russian Civilian Zone - Local Officials

Rescuers had to take cover as Kiev repeated attacks on Belgorod & Belgorod region, despite the massive strike hours earlier.

29 people were injured with 12 hospitalised, emergency services continue to search for survivors having evacuated the building, the region's Governor reported.
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
🟢🟡🔴 ግንቦት 5 | #ቅዱስ_ኤርምያስ_ነቢይ ዐረፈ። እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕጻንነቱ ነበር። "ከእናትህ ማሕጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ፤ ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል። (ኤር. 1፥5) ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም። ከ70 ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና። ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" (ባለ እንባው ነቢይ) ይሉታል። እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ…
#የቅዱስ_ኤርምያስ_ነቢይ ትንቢት
ምዕራፍ 23

¹ የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።

² ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል። በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጎበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጎበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

³ የመንጋዬም ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ያፈራሉ፤ ይበዙማል።

⁴ የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ። ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነሱም አንድ አይጎድልም፥ ይላል እግዚአብሔር።

⁵ እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።

⁶ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።


⁷ ስለዚህ፥ እነሆ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

⁸ ነገር ግን የእስራኤልን ቤት ዘር ከሰሜን አገርና ካሰደድኋቸውም አገር ሁሉ ያወጣና የመራ ሕያው እግዚአብሔርን! ይባላል፤ በምድራቸውም ይቀመጣሉ።

⁹ ስለ ነቢያት ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል፤ አጥንቶቼም ሁሉ ታውከዋል፤ ከእግዚአብሔር የተነሣ ከቅዱስ ቃሉም የተነሣ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈው እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ።

¹⁰ ምድር ከአመንዝሮች ተሞልታለችና፥ ከመርገምም የተነሣ ምድር አልቅሳለች፤ የምድረ በዳ ማሰማርያ ደርቆአል፤ አካሄዳቸው ክፉ ነው፥ ብርታታቸውም ቅን አይደለም።

¹¹ ነቢዩና ካህኑም ረክሰዋልና፥ በቤቴም ውስጥ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

¹² ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች እንደ ድጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች፥ እነርሱም ፍግምግም ብለው ይወድቁባታል፤ እኔም በምጎበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።

¹³ በሰማርያ ነቢያት ላይ ስንፍናን አይቻለሁ፤ በበኣል ትንቢት ይናገሩ ነበር፥ ሕዝቤንም እስራኤል ያስቱ ነበር።

¹⁴ በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።

¹⁵ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኵሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና እሬትን አበላቸዋለሁ፤ የሐሞትንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።

¹⁶ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ፤ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል፤ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።

¹⁷ ለሚንቁኝ ሁልጊዜ እግዚአብሔር ሰላም ይሆንላችኋል ብሎአል ይላሉ፤ በልቡም እልከኝነት ለሚሄድ ሁሉ ክፉ ነገር አያገኛችሁም ይላሉ።

¹⁸ ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነውና? ቃሉንስ ያደመጠ የሰማስ ማን ነው?

¹⁹ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፥ እርሱም ቍጣው፥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፍስ ወጥቶአል፤ የዓመፀኞችን ራስ ይገለባብጣል።

²⁰ የእግዚአብሔር ቍጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም፤ በኋለኛው ዘመን ፈጽማችሁ ታስተውሉታላችሁ።

²¹ እኔ ሳልልካቸው እነዚህ ነቢያት ሮጡ፤ እኔም ሳልነግራቸው ትንቢትን ተናገሩ።

²² በምክሬ ግን ቢቆሙ ኖሮ፥ ለሕዝቤ ቃሌን ባሰሙ ነበር፥ ከክፉም መንገዳቸው ከሥራቸውም ክፋት በመለሱአቸው ነበር።

²³ እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም።

²⁴ ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።

²⁵ አለምሁ አለምሁ እያሉ በስሜ ሐሰትን የሚናገሩትን የነቢያትን ነገር ሰምቻለሁ።

²⁶ ትንቢትን በሐሰት በሚናገሩ፥ የልባቸውንም ሽንገላ በሚናገሩ በነቢያት ልብ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?

²⁷ አባቶቻቸው ስለ በኣል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያንዳንዱ ለባልንጀራው በሚናገራት ሕልማቸው ሕዝቤ ስሜን ለማስረሳት ያስባሉ።

²⁸ የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፤ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው?

²⁹ በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር።

³⁰ ስለዚህ፥ እነሆ፥ እያንዳንዱ ከባልንጀራው ዘንድ ቃሌን በሚሰርቁ ነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።

³¹ እነሆ፥ ከምላሳቸው ትንቢትን አውጥተው። እርሱ ይላል በሚሉ ነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።

³² እነሆ፥ ሐሰትን በሚያልሙ በሚናገሩም በሐሰታቸውና በድፍረታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አልላክኋቸውም አላዘዝኋቸውምም። ለእነዚህም ሕዝብ በማናቸውም አይረቡአቸውም፥ ይላል እግዚአብሔር።

³³ ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን የእግዚአብሔር ሸክም ምንድር ነው? ብሎ ቢጠይቅህ፥ አንተ ሸክሙ እናንተ ናችሁ፥ እጥላችሁማለህ፥ ይላል እግዚአብሔር ትላቸዋለህ።

³⁴ የእግዚአብሔር ሸክም የሚለውን ነቢይንና ካህንን ሕዝቡንም ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ።

³⁵ አንዱም አንዱ ለባልንጀራው፥ አንዱም አንዱ ለወንድሙ እንዲህ ይበል፦ እግዚአብሔር የመለሰው ምንድር ነው? እግዚአብሔርስ ምን ነገር ተናገረ?

³⁶ ለሰው ሁሉ ቃል ሸክም ይሆንበታልና የእግዚአብሔር ሸክም ይሆንበታልና የእግዚአብሔር ሸክም ብላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ አትጥሩ! የሠራዊትን ጌታ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን የሕያውን አምላክ ቃል ለውጣችኋልና።

³⁷ ለነቢዩ እግዚአብሔር ምን መለሰልህ? እግዚአብሔርስ የተናገረው ምንድር ነው? ትላለህ።

³⁸ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሸክም ብትሉ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ የእግዚአብሔር ሸክም አትበሉ ብዬ ልኬባችኋለሁና፥ እናንተም ይህን ቃል

³⁹ የእግዚአብሔር ሸክም ብላችኋልና ስለዚህ፥ እነሆ ፈጽሜ እረሳችኋለሁ። እናንተንም ለእናንተና ለአባቶቻችሁም የሰጠኋትን ከተማ ከፊቴ እጥላለሁ።

⁴⁰ የዘላለምንም ስድብ ከቶም ተረስቶ የማይጠፋውን የዘላለምን እፍረት አመጣባችኋለሁ።

  _🔥_🔥_🔥_
🟢🟡🔴
ግንቦት 7 | #ቅዱስ_አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ዐረፉ፨

አትናቴዎስ ማለት ‹‹ሞት ሕልፈት የሌለበት ሕይወት›› ማለት ነው፡፡ ሐናፊ ከሚባል የእስላም ነገድ የተገኙ እንደሆኑ መጽሐፈ ስንክሳሩ ይጠቅሳል።

በኋላም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 20ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የሆኑ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ ናቸው፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ትውልዳቸው ግብፅ እስክንድርያ ሲሆን ወላጆቻቸው ከማያምኑ ከአረማዊያን አሕዛብ ወገን ናቸው፡፡

በወጣትነታቸው ከመሾማቸው በፊት ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሄደው ከእሳቸው ጋር ለተወሰነ ጊዜ አብረው ኖረዋል፡፡ በ325 ዓ.ም በጉባኤ ኒቂያ ላይ መምህራቸውንና ሊቀ ጳጳሳቱን እለእስክንድሮስን ተከትለው ሄደው አርዮስ ከክህደት ትምህርቱ እንዲመለስ 318ቱ ሊቃውንት ቢመክሩትና ቢያስተምሩት አልመለስ ቢላቸው አርዮስን አውግዘውታል፡፡ አፈ ጉባኤውም አቡነ አትናቴዎስ ነበሩ።

አባታችን በማርቆስ መንበር 20ኛው ፓትርያርክ ሆነው በሹመት 47 ዓመት ሲኖሩ 15ቱን ዓመት በስደትና በእስራት ነው ያሳለፉት፡፡ አረማውያኑ በኃይል አምስት ጊዜ እንዲሰደዱና ሦስት ጊዜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ አድርገዋቸዋል።

ከሃዲዮች ከሹመታቸው አውርደው በግዞት በመርከብ ጭነው ወስደው በባሕር ውስጥ ቢጥሏቸውም የታዘዘ መልአክ ከባሕሩ አውጥቶ ቅድስናቸውን ለገዳዮቻቸው መስክሮላቸዋል፡፡

ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያ ትምህርተ ሃይማኖትን ያስፋፉ ጸሎተ ሃይማኖትን ያረቀቁልን ናቸው፡፡

ለእኛ ለኢትዮጵያም የመጀመሪያውን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃንን የሾሙልን እሳቸው ናቸው፡፡

ግንቦት 7 ቀን 374 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈው ወደሚናፍቁት አምላካቸው ዘንድ የሄዱበት ዕለት ነው፡፡

T.me/Ewnet1Nat
❗️ህንድ በአዋራማ አውሎ ንፋስ ተመታለች ❗️

እስካሁን 64 ሰዎች ተጎድተዋል፤ 4 ሰዎች ሞተዋል።
የበዓል መልእክት፦
፩ኛ ለኢ.ዓ.ብ ቤተሰቦች
፪ኛ በፊት የኢ.ዓ.ብ ቤተሰብ ለነበራችሁ


በስተመጨረሻም በጊዜውም ያለጊዜውም ጸንተን ታምነን እንቁም! ሁሉም ዕጣ ፈንታውን ያገኛል። ግድም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይፈጸማል!

ጽኑ! በርቱ! በጸሎትም በጾምም ትጉ!
በሀገር ውስጥም ያላችሁ በውጪውም ያላችሁ ቤተሰቦቻችን ኹሉ አይዟችሁ! ጽናትን ገንዘባችሁ አድርጉ!

አሁን ጊዜው የሚጠይቀው በእምነት መጽናትን ነው። የሚፈትናችሁ ነገር ብቅ ሲል ወደ ፈጣሪያችሁ።

የተገባላችሁን ተስፋ እንዳትተዉ፣ እንዳትጥሉ ተጠንቀቁ!


የደከማችሁ የጠፋችሁ ቀድሞ የእኛ ቤተሰብ የነበራችሁ ደሞ ዛሬ ጊዜው ያው እንደምታዩት ኾኗል። እየተገለጠ ብርሃኑ ብቅ እያለ ስለሆነ እኛ ለምን እንዲህ አደረጋችሁ ብለን የምንወቅሳችሁ ሰዎች አይደለንም።

እኛ የምንሻው ተጸጽታችሁ፣ ንስሐ ገብታችሁ፣ እውነቱን ተረድታችሁ፤ ትላንት ስለተቻችሁን ስለናቃችሁን ብዙ ስላላችሁን እኛ ያንን ቦታ አንሰጠውም። እኛ በዛ ምንም የምንጠቀመው ነገር የለም። እኛ የቂም ሰዎች አይደለንም፤ የክፋት ሰዎች አይደለንም። እግዚአብሔር ያስተማረን ሁሉንም በፍቅር እንድንቀበል ነው።

በንስሐ ብትመለሱ ግን ደስታችን እጥፍ ነው የሚሆነው። በንስሐ ተመለሱ። ጊዜ አታባክኑ፣ ሰዓቱ አልቋል። የምታዩት ነው። አልቋል! ምክራችን ይሄ ነው።

በዚህ በትንሣኤው ዘመን ከተጫናችሁ መጥፎ አካሄድ እንደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸሩ መድኃኔዓለም መቃብራችሁን እየፈነቀላችሁ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር ሩጡ፤ ፍጠኑ፤ ጊዜ አታጥፉ። ጊዜ በእግዚአብሔር እጅ ናት ያለችው። እናንተ ቀጠሮ ሰጥታችሁ የምታቆዩት ጊዜ አይደለም ያለው። መሽቷል!

በቃ! ያለፈው ክፋቱ ይበቃዋል። አዎ ወደ እውነቱ ወደ ብርሃኑ ብትመለሱ እንመክራለን።

የአባቶች የ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል መግለጫ (26/8/16)
Audio
ገድለ አቡነ ኪሮስ ዘወርኃ ግንቦት
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 9 | #አቡነ_ብፁዓ_አምላክ ዐረፉ።

እኚህ ጻድቅ አባታቸው ቅዱስ አፍቅረነ እግዚእ፣ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርያም ዘመዳ ሲባሉ በ1425 ዓ.ም መስከረም 1 በትግራይ ልዩ ስሙ መከዳ በተባለ ቦታ ተወለዱ።

በስምንት ዓመታቸው ወደ ደብረ ቢዘን ገብተው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲማሩ፣ በገዳማዊ ኑሮ ሲያገለግሩ ቆይተው በ25 ዓመታቸው መነኵሰዋል።

በመሠረቱት ገዳም ደብረ ኰዳዱ ሔደው በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብተው ሕማማተ መስቀልን በማሰብ በአንድ ሺህ ችንካሮች እራሳቸው ቸክረው ለ30 ዓመታት ሲጋደሉ ኖሩ።

በዛው እግዚኣ ዓለማት ሥላሴ ለአብርሃም እንደተገለጹ ለእርሳቸውም በአንድነትና በሦስትነት ታኅሣሥ አንድ ቀን ተገለጡላቸው። እርሳቸው ሥላሴ መሆናቸው ለማረጋገጥ የቆሙበት ድንጋይ ለሦስት ቦታ ተከፈለ፤ እንደ ገና ደግሞ ተመልሶ ወደ አንድ ተለወጠ። ቃል ኪዳን ከገቡላቸው በኋላ መጨረሻ የሚያርፉበት ቦታ ነግረዋቸው ተሰወሩ።

ከዚያም ሁለተኛ ወደ መሠረቱት ገዳም ደብረ ምዕዋን ገብተው ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ግንቦት 9 ቀን 1501 ዓ.ም በ76 ዓመታቸው ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተቀብለው ዐርፈዋል።

አቡነ ብፁዐ አምላክ የተገነዙባት ጨርቃቸው አስቀድመው ይለብሷት የነበረች ናት። ይኸውም አንድ ቀን መንገድ ሲሔዱ ወንበዴዎች ያራቆቷት ሴት አገኙ።

አባታችንም ደንግጠው ሰው ነሽን ወይስ ሰይጣን? ብለው ሲያማትቡ እርሷም ፊቷን በመስቀል ምልክት አማትባ አባቴ ሆይ! ቀማኞች ልብሴን በጉልበት የወሰዱብኝ ክርስቲያን ነኝ አለቻቸው።

በዚኽም ጊዜ ሳያዩዋት አንዲቷን መጎናጸፊያቸውን ሰጥተዋት ሔዱ። ወዲያውም እግዚአብሔር ልዩ የሆነች መልካም ልብስ ሰጣቸውና “ይኽች ልብስ እስከ ዕለተ ዕረፍትህ አትለቅ” አላቸው።

ያችም ልብስ ሳታድፍና ሳታልቅ እስከ ዕረፍታቸው ቀን ድረስ ኖረች።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
እግዚአብሔር ቃሉን አክባሪ ነው

እኛ ስላልታመንን፣ ተስፋ ስለቆረጥን፣ ስለወደቅን፣ በትካዜ ስለተዋጥን፣ ለጊዜው ጠላት በሚሠራው ሴራ የተሳካለት መስሎን እጅግ በኅሊና በአካል ብንቆስልም እግዚአብሔር አምላካችን ለቃሉ የታመነ ነው። የማይዘገይ መሆኑን አውቀን ልንጸና፣ ልንጽናና እንደገናም በንስሐ ራሳችንን ልናድስ ይገባል።


የአባቶች የ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል መግለጫ (26/8/16)
2024/06/16 01:59:37
Back to Top
HTML Embed Code: