Telegram Web Link
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 29 | ከተሰዓቱ ቅዱሳን የሆኑ #አቡነ_አፍጼ እና #አቡነ_ጉባ በዓላቸው ነው፡፡

ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አራቱ በምድር ላይ ሞትን ሳያዩ የተሰወሩ ናቸው፡፡ እነዚህም አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ሊቃኖስና አቡነ አፍጼ ናቸው።

☘️ አቡነ አፍጼ ☘️

አቡነ አፍጼ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ፡፡

ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር ‹‹አፍፄ-አፈ ዐፄ›› ብሏቸዋል፡፡ ይኽም የዐፄ/የንጉሥ አንደበት ያለው›› ወይም ‹‹ንግግር አዋቂ›› ማለት ነው፡፡

አቡነ አፍጼ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው ግንቦት 29 ቀን በ684 ዓ.ም በሞት ፈንታ ተሰውረዋል፡፡

☘️ አቡነ ጉባ ☘️

እርሳቸውም የተወለዱት ታኅሣሥ 29 ቀን 336 ዓ.ም በመንፈቀ ሌሊት ነው፡፡ አባታቸው ጌርሎስ እናታቸው ቴዎዶክስያ የተባሉ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡

አቡነ ጉባ በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር፡፡ ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው አመስግነዋል። በዚህም ቀን ዐረፉ።
🍀

#አቡነ_መዝራዕተ_ክርስቶስ
አባታቸው ለባሴ ክርስቶስ የዐፄ ፋሲል የቅርብ ወዳጅ የነበረ የጦር አዛዥ ደጃዝማች ሲሆን እናታቸው ሚላንያ ትባላለች፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 29 ቀን በጎንደር ተወለዱ፡፡

ዓፄ ፋሲል ሴት ልጃቸውን ሊድሩላቸው ሲሉ ሸሽተው መነኮሱ። ከዛም በአርማጭሆ ደብረ ሙጅና፣ በዋልድባ፣ በጉንዳጉንዲ ማርያም፣ በመጠራ በምንኩስና ሲጋደሉ ኖሩ።

በዋልድባ ገዳም ሥዕለ ማርያምን በጎኑ ታቅፎ ሲያዝን ለብዙ መናንያን የተሰወረችው ደብረሲና የተባለች ቅድስት ቦታ ተገልጣላኋለች።

በኋላም በመሠረቷት በማይ ዱር ገዳም በ93 ዓመታቸው ግንቦት 29 ዐረፉ።

T.me/Ewnet1Nat
33
🇨🇬🇨🇬

#_ተግሣጽ-፰ (ለኢ.ዓ.ብ ቤተሰብ ብቻ)
#_አጥፊዎች_ስለ_ቅድስና_የሚያውቁት_ነገር_የለም

🇨🇬 የኢ.ዓ.ብ የሐዋርያት ሥራ ትምህርት ፭
| 🕛 | ከ ፱:፶፭ - ፲: ፵፬

አጥፊዎች ስለ ቅድስና የሚያውቁት ነገር የለም። ትላንት ቤተ ክርስቲያንን በልምድ ኖሩባት፤ ለጥፋቷ ተመልካች ኾነው አሳለፉ፤ ዛሬ ለደረሰችበት ጥፋት አስተዋጽኦ አደረጉ።

ዛሬም #_በጽዋ_ማኅበር_መሳተፍ_ብቻ_በቂ_ነው የሚል ስሜት ያደረባቸው ኾነው ንስሐ የማይገቡ፣ በእውነት መለወጥ፥ በእምነት ሳይጸኑ፣ በእውነትና በመንፈስ ጸንተው ሳይቆሙ፣ ጉድለታቸውን ሳያርሙ፣ በሌሎች ወንድም እኅቶቻቸው ላይ ነቀፋን፥ ትችትን፥ ሐሜትን የሚያስፋፉ ላይ #_እግዚአብሔር_ይገሥጻል_እርምጃም_ይወስዳል

www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
25
ንስሐ —> ንስሐ —> ንስሐ —> መንግሥተሰማያት
31👏1
" ሰዎች ሞተዋል ፤ ንብረትም ወድሟል " - ነዋሪዎች

➡️ " ጥቃቱን ከፈፀሙ በኃላ ለቀው ወጥተዋል " - የዞን ሰላምና ፀጥታ ቢሮ


በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ቡለንከተማ  ዛሬ ጠዋት 12:00  እስከ እረፋዱ 4:00 ድረስ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ ማርፈዱን እና በዚህም ሰዎች መሞታቸውንና ንብረት መውደሙን የቡለን ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ነዋሪዎቹ ፥ ጥቃቱን ያደረሰው በአካባቢው ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው የ' ሸኔ '  ታጣቂ ኃይል እንደሆነ ተናግረዋል።

ታጣቂው ኃይል ዛሬ ከማለዳው 12:00 ጀምሮ ወደ ከተማው ዘልቆ በመግባት የመንግስት የፀጥታ ሀይሎችንና ንፁሀኖችን መግደሉን እንዲሁም በርካታ ንብረት መዝረፉን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ስለ ሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተማው ገና ስላልተረጋጋ  ማወቅ አለመቻላቸውን ተናግረዋል።
11😭8🔥5👍1
Audio
AudioLab
🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አራት (4)

በድምፅ ንባብ (በትረካ)

(📌 ክፍል 1ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማዳመጥ 👈)

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማነው?

🌿 ሕይወቱና ተጋድሎው
🌻 ቃልኪዳኑና
🌹 ሰማዕትነቱ
...

📌 ቁጥር 1) ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወቱንና ከመድኃኔዓለም የተቀበለውን ልዩ ቃልኪዳን በፅሑፍ ያንብቡ👇

🫴 https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/14510

PDF ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ (በ1988 ዓ.ም የታተመ)👇

https://www.tg-me.com/kidusan_page/50
21
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
42
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ከተማ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ 

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በመተከል ዞን፣ በቡለን ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 10 ሰላማዊ ሰዎች እና የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

የመተከል ዞን እና የቡለን ወረዳ አስተዳደር በከተማይቱ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን፣ ባንክ ቤትን ጨምሮ በተቋማት ላይ ዝርፊያ እና ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል።
11😭2
ዜና እገታ‼️

በትላንትናው እለት 47 ኢትዮጲያውያን እና 3 ቻይናውያን ከደርባ ሲቢንቶ ፋብሪካ ታግተው ተወስደዋል።
8
የሟቾች ቁጥር 18 ደርሷል‼️
በትናንትው ዕለት በመተከል ዞን በቡለን ከተማ በነበረው ጥቃት ህይወታቸውን ካጡት መካከል በጥቂቱ ከላይ በፎቶ የተያያዙት ይገኙበታል።
ጥቃት አድራሾቹ የቡለን ንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅን በግድ በር እንዲክፍተላቸው ካደረጉ በኋላ በርካታ ብር ይዘው ሄደዋል።
በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ18 በላይ ደርሷል።
ነፍስ ይማር❗️
😭10🔥51👍1
❗️ 1 ሺህ 212 የዩክሬን ወታደሮች አስከሬን በረድፍ ወደ ልውውጥ አካባቢ መድረሳቸውን የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ሹም ዋና ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አሌክሳንደር ዞሪን አስታወቁ

እንደ እርሳቸው ገለጻ ተጨማሪ አራት 1 ሺህ 200 የዩክሬን ወታደሮች አስከሬን በየደረጃው ለማስተላለፍ ዝግጅት ተጠናቋል።
11🔥5
2025/07/13 03:35:24
Back to Top
HTML Embed Code: