Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጊዜ የማይገልጠው እውነት የለም‼️

"በሲኖዶስ ውስጥ ከተሰበሰቡት ጳጳሳት ከአሥራ ሰባት(17) የማያንሱ የደህንነት ሰራተኞች መሆናቸውን ለመሆኑ ወገኖቼ ታውቃላችሁ!? ለስለላ የተሰማሩ፡ ለፖለቲካው ሰራተኛ የሆኑ በድፍረት የክብር ልብስ የሆነውን የክብር፣ ሰውን የመባረኪያ፤ ከኀጢአት ከእስራት የመፍቻ ሃይል የሆነውን መስቀል በእጃቸው  የጨበጡ ደፋሮች የዲያብሎስን ስራ የሚሰሩ፤ ቀሚሱን ለብሰው ስለፖለቲካው  የሚተጉእነዚህ በሲኖዶስ ውስጥ ተሰግስገው ህይወት እንዴት ነው  የሚገኘው??

ዛሬ ዓለም እንደ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ ጥር 7/2012  እንደታዘዘው ስትበጠር ይኸው ሲኖዶስ ወይም የዓለም አብያተ ክርስቲያን  ጉባኤ ለምን አቤት ብሎ አያስቆመውም? አዎን! ህይወት የላቸውም። ከሃዲዎች ናቸው። ፈጣሪያቸውን የካዱ። በሳይንስ፡ በምርምር፡ በጥንቆላ፡ በትብተባ የተሸፈኑ ናቸው።..."

ፅሑፉ ሚያዝያ 11/2012ዓ.ም ዕለተ ትንሣኤ በድምፅ ከተላለፈው
ከመግለጫ 3 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የተወሰደ ነው።

ሙሉውን ፅሑፍና መግለጫ ለማግኘት፦
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/1921
#ለታሪክ_ትቀመጥ ‼️
ሰኔ 3፥2016
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Ankara swamped by powerful flooding - again

Just a month after the Turkish capital suffered torrential downpours that left streets completely submerged, severe rainfall on Saturday has swept away cars and left a chaotic center.

Many streets remain all but impassable as several transport routes - including the metro - have been paralyzed.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Lava flow covers road to Grindavik - Drone Footage

Iceland's active volcano has stabilised since its fifth and most powerful eruption last month.

Authorities say the lava flow has started to slow as it moves across the Reykjanes Peninsula, but it has again engulfed a road which had recently been repaired and reopened.
#Update

የማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን ይዞ ሲጓዝ የነበረውን ከራዳር እይታ የተሰወረው አውሮፕላን #ስብርባሪ ተገኘ።

አውሮፕላኑ መከስከሱ ተረጋግጧል።

ምንም የተረፈ ሰው የለም።

በአውሮፕላኑ ውስጥ ምክትል ፕሬዜዳንቱ ሳውለስ ቺሊማን እና የቀድሞው ፕሬዜዳንት ባኪሊ ሙሊዚ ባለቤት / የቀድሞ ቀዳማዊ እመቤት ሻኒል ዲዚምቢሪን ጨምሮ 10 ሰዎች ነበሩ።

ሁሉም መሞታቸው ነው የተሰማው።

Photo Credit - Hopewell
አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ዜጎች የሆኑ  ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ከ #የመን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ለነፍስ አድን ሠራተኞች እንደተናገሩት ጀልባዋ 250 የሚጠጉ ሰዎችን አሳፍራ የነበረ ሲሆን፣ ለመገልበጥ የበቃችውም በካበድ ነፋስ ምክንያት ነው ተብሏል።

መሞታቸው ከታወቀው 38 ሰዎች ውጪ ሌሎች 100 ሰዎች የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን፣ እነሱን ለማግኘት ፍለጋ እየተደረገ ነው። እስካሁን 78 ሰዎች መትረፋቸውም ታውቋል ሲል
ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
📌እርግጥ ይሄ ሰአት አሁን ዝም እንድንል የሚያስገድደን ሰአት ላይ መጥተናል፡፡
ያው የፍርድ ሰአትና እጅግ እየከበደ የሚሄድ ወዲያ ወዲህም ለመንቀሳቀስ የሚከለከልበት ሰአት ሁሉ  ይመጣል፡፡ምክንያቱም ያው ግልጽ ነው፡
፡ፍርድ ነው ፡፡ክንዋኔ ነው ፡፡የእግዚአብሔር እውነት ትከናወለናለች፡፡ፍርዱ ይከናወናል ግድ ነው፡፡
⚡️ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
የሉቃስ ወንጌል ትምህርት ክፍል-- 8  ላይ የተወሰደ፡፡
Audio
መልክአ ቅዱስ ገብረ መንፈስ ቅዱስ .
☀️ ውድ እና ዕንቁ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን !
             ሰኔ ፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
☀️ ውድ እና ዕንቁ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን !              ሰኔ ፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
🍀🍀
ከዘጠኙ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው፡፡ በዓለ ዕርገት ከትንሣኤ በዓል በኋላ በ40ኛው ቀን ስለሚውል ሐሙስን አይለቅም፡፡

ዕርገት ማለት ዐርገ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ወደ ላይ መውጣት ከምድር ከፍ ከፍ ማለት... እስከ ሰማየ ሰማያት መምጠቅ ማለት ነው፡፡ የጌታ ዕርገት እንደ ኤልያስ እንደ ሔኖክ እንደሌሎቹም ቅዱሳን ያይደለ በገዛ ሥልጣኑ የሆነ ነው ሌሎቹ አጋዥ አስነሽ ይሻሉና ነው፡፡

ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ቅዱስ ዳዊት «አምላክ በዕልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ» (መዝ 46፥5) በማለት በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ በመንፈስ ዘምሯል። ይህም ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቢታንያ ይዟቸው ሄዷል። (ሉቃ 24፥50)

ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ በተለያየ ቦታ ተገልጾ ታይቷቸዋል። ትምህርትም አስተምሯቸዋል። «ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ዐርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግስት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ህያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው» (ሐዋ 1፥3)

በነዚህ ቀናት ውስጥ ጌታችን ሥርዓትን አስተምሯቸዋል። ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ትምህርት ኪዳን ብላ ትጠራዋለች። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያት የነገራቸው መጽሐፈ ኪዳን ይባላል፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀናት በምድር ቆይታ ባደረገበት ወቅት በግልጽ ተገልጦ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና መጽሐፈ ኪዳንን አስተምሯቸዋል፡፡ ጉባኤ ዘርግቶ ያስተማራቸው ለሦስት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ዮሐ.21፤14

እነሱም፦
1. ሞትን ድል አድርጎ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በተነሳበት በትንሣኤ ዕለት
2. ምሳ ባበላቸው /በአግብኦተ ግብር/ ዕለት
3. በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ናቸው፡፡

በዚህ በዕርገቱ ዕለት ቅዱስ ጴጥሮስ ታላቁን ሹመት የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻን ቁልፍ ተሰጥቶታል ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ሞትን ሳይቀምስ እስከ እለተ ምፅአት እንደሚቆይ ተገልጿል ዮሐ. 21፤15-23

#እንዴት_ዐረገ?
ሐዋርያትን ከባረካቸው በኋላ ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው ሥጋ በማነስ፣ በመርቀቅ፣ በመጥፋት ሳይሆን በመራቅ ሐዋርያት በዓይናቸው እየተመለከቱት በጥቂት በጥቂት ምድርን ለቆ ከፍ ከፍ እያለ በፍጹም ምሥጋና ፈጽሞ ወደ አልተለየው ወደ ባሕሪ አባቱ ዐርጓል፡፡

በሥጋና በነፍስ፣ በአጥንትና በደም፣ በጅማት፣ በጸጉርና በፂም እንዳለ በጥንተ አኗኗሩ በአብ ቀኝ ተቀመጠ በሰማይ በምድር ያሉትን ረቂቁም ግዙፉም ሁሉ ተገዙለት፡፡ 1ኛጴጥ. 3፤22 ክርስቶስ የሰውን አካል የሰውን ባህሪ ገንዘቡ አድርጎ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ሲገለጥ ሰውም የአምላክን ገንዘብ ገንዘብ አድርጎ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በዘባነ ኪሩቤል የመላእክትንም ምሥጋና ለመቀበል በቃ፡፡

#ለምን_ዐረገ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብሩ ማረጉ፥ በሙሴ የሕግ መጽሐፍት በነቢያትም የትንቢት መጽሐፍ እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት የተነገረው ትንቢት አለና ይህ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ መዝሙረኛው ልብ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለጌታችን ዕርገት እንዲህ በማለት ጽፏል፡፡

መዝ. 47፥5 ‹‹…. አምላክ በእልልታ በእግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ››
መዝ. 67፥18 ‹‹ወደ ላይ ዐረግህ ፣ምርኮን ማረክ ፣ ስጦታን ለሰዎች ሰጠህ››
መዝ. 16፥10 ‹‹ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፣ በነፋስም ክንፍ በረረ….›› በማለት በትንቢት መነጽር ተመልክቶ የዘመን ግድግዳ ሳያግደው የተናገረው ኃይለ ቃል ነው፡፡

#ዕርገቱን_ለምን_በተነሣ_በ40ኛው_ቀን_አደረገ?

◦ አዳም በ40 ቀን አግኝቶ ያጣትን ልጅነት እንደተመለሰለት ለማጠየቅ፣

◦ አንድም ጌታ በረቀቀ ጥበቡ ተሸብሮ የነበረውን የሐዋርያትን ልቡና እያረጋጋና እያጽናና መቆየቱን መርጦ ነው፡፡

◦ አንድም ለአይሁድ ምክንየት ለማሳጣት ነው ዕርገቱን ከትንሣኤው አስከትሎ ወዲያው ቢያደርገው ዕርገቱ ምትሐት ናት እንዳይሉ በእርግጥ በሞቱ ሞት ድል አድረጎ የተነሣው ወልደ እግዚአብሔር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ መሆኑን እንዲረዱ እንዲገነዘቡበ የጥርጣሬ መንፈስ በአዕምሯቸው እንዳይሰርጽ ነው፡፡

◦ አንድም ላላመኑት ለእስራኤላውያን (ለአይሁድ) የንስሐ ጊዜ ሲሰጣቸው ነው ብዙዎች በክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት አምነው የተመለሱ አሉና፡፡

#ዕርገት_በዓል_መቼ_ነው?
ጥንተ ዕርገቱ በወርሐ ግንቦት ስምንት ኀሙስ ቀን በ34 ዓ.ም በዘመነ ማርቆስ ነው፡፡

የዕርገት በዓል አከባበር እስከ አራተኛው መቶ ዓመት ድረስ እንደ ዛሬው ሐሙስን ሳይጠብቅ በጥንተ ዕርገቱ ግንቦት ስምንት ቀን ብቻ ይከበር ነበር፡፡ በአራተኛው ምዕተ ዓመት ወዲህ ግን ትንሣኤ በዋለ በአርባኛው ቀን ብቻ እንዲከበር ቅዱስ ዲሜጥሮስ በባሕረ ሐሳብ ቀመሩ ስሌት መሠረት ይከናወን ዘንድ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተወስኖ በሥራ ላይ ውሎ ይገኛል፡፡
🍀🍀
🟢🟡🔴
ሰኔ 7 | #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ የዕረፍቱ በዓል ነው።

ይህም ቅዱስ አባት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ነው።

ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው። ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር።

አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ገና በ3 ዓመቱ እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው። ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ። ሊቀ ጳጳሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው።

የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ። ጳጳሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት።

እርሱም፦
፩- ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ፣
፪- ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ
፫- እንዲሁም ከፈጣሪዬ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው።

ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ጳጳሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሐ በቅተዋል።

ቅዱስ ያዕቆብ በዘመኑም የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል፣ ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል፣ በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል።

ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል።

☘️☘️☘️
T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 8 | #_የእመቤታችን_ማርያም ቅዳሴ ቤት ተከናወነ፨

በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም በስደቷ ወቅት ልጇ ያፈለቀው የውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ ክርስቲያንዋ ቅዳሴ ነው።

ይኽም ከእመቤታችን 33ቱ ዋነኛ በዓላት አንዱ ነው።

ይህም እንዲህ ነው፦ ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ አለው። ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ።

ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ። በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ። የእመቤታችን ስደት የጀመረው ግንቦት 24 ቀን ነው። ለ3 ዓመት ከ6 ወርም ተወዳጅ መድኃኒት ልጇን ይዛ በስደት ቆይታለች።

ሄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት። ወደ እስራኤልም አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ አዘዘው።

በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ። ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት። እርሷም እስከ ዛሬ አለች።

ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ። ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ። በዛሬዪቱ ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ።

እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

                🌹
T.me/Ewnet1Nat
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/06/15 19:58:50
Back to Top
HTML Embed Code: