Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የቅድመ አንደኛ ት/ቤት የአስተባባሪዎች ስልጠና
Forwarded from Addis Ababa Education Bureau (Abebe Chernet)
በትምህርት ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ለሚያካሂዱ ሱፐርቫይዘሮችና የኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ።

(ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም) የክትትልና ቁጥጥር መርሀ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ የተዘጋጀ ቼክ ሊስትን መሰረት አድርጎ የሚካሄድ ሲሆን ክትትሉ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀን በሁሉም የመንግስትና የዕቅና ፍቃድ ባላቸው የግል ትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ አድማሱ ደቻሳ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በትምህርት ቤቶች ተደጋጋሚ የድጋፍና ክትትል ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸው በአሁኑ ቁጥጥርና ክትትል እስካሁን የተካሄዱ የድጋፍ ሂደትን መሰረት በማድረግ የተሰጡ ግብረ መልሶች ተቋማቱን ምን ያህል ውጤታማ እንዳደረጉ በማየት የትውልድ ግንባታ ሂደቱ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።
Forwarded from Addis Ababa Education Bureau (Abebe Chernet)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳኘው ገብሩ በበኩላቸው የቁጥጥር መርሀ ግብሩ ትምህርት ተቋማቱ ስርአተ ትምህርቱን ምን ያህል በአግባቡ ተግባራዊ እያደረጉ እንደሚገኙ በማየት ለ2017ዓ.ም ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን ጠቁመው ቁጥጥሩን ለማካሄድ የተመደቡ ባለሙያዎች ተልኳቸውን በቼክሊስቱ መሰረት በመወጣት ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ በበይነ መረብ ኦን ላይን እንደመሰጠቱ ትምህርት ቤቶች በተለይም የግል ትምህርት ተቋማት ፈተናውን በአግባቡ ለመስጠት ግብአቶችን ከማሙዋላት ጀምሮ እያደረጉ የሚገኙትን የቅድመ ዝግጅት ስራ ማየት የቼክሊስቱ አካል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል አስታውቀዋል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://www.tg-me.com/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- [email protected]
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአ/አ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የስፖርት ውድድርን በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ተማሪዎች ራሳቸውን ከሱስ እንዲጠብቁ የተካሄደ ስልጠና
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአ/አ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የስፖርት ውድድር መክፈቻ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአ/አ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የስፖርት ውድድር መክፈቻ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
Forwarded from Addis Ababa Education Bureau (Abebe Chernet)
የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) የበይነ መረብ (Online) ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆነ፡፡


(ግንቦት 10/2016 ዓ.ም) የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በበይነ መረብ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሠረት በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከዚህ በታች በተገለጸው አድረሻ ብቻ የሚፈተኑ ይሆናል፡፡


ስለሆነም ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድርግ አስፈላጊ በመሆኑ ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚከተለዉ አድራሻ ተፈታኞች በሚገኙበት ክልል የተደለደሉ ስለሆነ ልምምድ ማድረግ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡


ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል/ከተማ አስተዳደር ቀድሞ የተላከውን የይለፍ ቃልና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡ በዚሁ መሠረት መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡


ማሳሰቢያ፡-ተፈታኞች ከተደለደሉበት ክላስተር ዉጪ ሲሰትሙን መጠቀም የማይችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡



የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://www.tg-me.com/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
ውድ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከላይ ባለው ቪዲዮ የኦንላይን ፈተና አወሳሰድን መለማመድ ትችላላችሁ... መልካም ውጤት!
2024/05/20 03:59:38
Back to Top
HTML Embed Code: