Telegram Web Link
የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ የሕይወት ታሪክ

#ውልደት
የቀድሞው አባ ኃይለ ማርያም መለሰ የኋላው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ከአባታቸው ከሊቀ መዘምር መለስ አየነው ደስታና ከእናታቸው ከወ/ሮ ፀሐይ ገብረ አብ በሰሜን ጎንደር ደብረ ሰላም ሎዛ ማርያም አካባቢ በ1961 ዓ.ም ተወለዱ።

#ትምህርት
• ፊደል፥ ንባብ፥ ዳዊትና ቅዳሴ ከመርጌታ ሙሴ ብፅዐ ጊዮርጊስ ተምረዋል።
• ቅኔ፥ ከግጨው መንከር ምንዝሮ ተክለ ሃይማኖት፥ ሐዲሳት፥ ከመጋቤ ሐዲስ ወልደ ሰንበት ግምጃ ቤት ማርያም ተምረዋል።
• 1ኛና 2ኛ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዐፄ ፋሲል፡ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በዳግማይ ደብረ ሊባኖስ አዘዞ ተክለ ሃይማኖት ት/ቤቶች ተምረዋል።
• ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ በቴዎሎጂ ዲፕሎማ፥
• ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቴዎሎጂ ዲግሪ፥
• ከኖርዌይ ስታቫንገር ስፔሻላይዝድ ዪኒቨርስቲ የማስተርስ ዲግሪ፥
• ከፕሪቶርያ ዩኒቨርስቲ በፍልስፍና የፒኤችዲ ዲግሪ አግኝተዋል።

#ቋንቋ
• ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ የኖርዌይ፥ የስዊድንና የዴንማርክ ቋንቋዎችን ይችላሉ፡፡

#መዐርገ_ክህነት
• ዲቁና - በ1968 ዓ.ም. ከብፁዕ አቡነ እንድርያስ (ቀዳማዊ) በወቅቱ የሰሜን ጎንደር ሊቀ ጳጳስ ተቀብለዋል፥
• ምንኵስና - በ1984 ዓ.ም. በታዋቂውና ጥንታዊው ገዳም ጎንድ ተከለ ሃይማኖት ተቀብለዋል፥
• ቅስና - ከብፁዕ አቡነ ያዕቆብ (ኤርትራዊ) በወቅቱ የሰሜን ጎንደር ሊቀ ጳጳስ ተቀበለዋል፥
• ቁምስና - ከብፁዕ አቡነ ገብርኤል በወቅቱ የምዕራብ ሸዋ ሊቀ ጳጳስ ተቀብለዋል።
#አራቱ_ጉባኤያት_የሚባሉት_ለመሆኑ_ምን_ምን_ናቸው??

#አራቱ #የመጻሕፍት #ጉባኤያት
፩ ብሉይ ኪዳን
፪ ሐዲስ ኪዳን
፫ መጽሐፈ መነኮሳት
፬ መጻሕፍተ ሊቃውንት
መጽሐፈ መነኮሳት የሚባሉት 3 ናቸው እነዚህም፦
            ፩ ማር ይስሐቅ
            ፪ ፊልክስዩስ
            ፫ አረጋዊ መንፈሳዊ
መጽሐፈ ሊቃውንት የሚባሉት 7 ናቸው እነዚህም፦
             ፩ ሃይማኖተ አበው
             ፪ ድርሳነ ቄርሎስ
             ፫ ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ
             ፬ ተግሣጸዮሐንስ አፈወርቅ
             ፭ ፍትሐ ነገሥት
             ፮ 14ቱ መጽሐፈ ቅዳሴ
             ፯ አቡሻህር
በብሉይ ኪዳን ያስመሰከረ መጋቤ ብሉይ ይባላል። በሐዲስ ኪዳን ያስመሰከረ ደግሞ መጋቤ ሐዲስ ይባላል። በመጽሐፈ ሊቃውንት ያስመሰከረ ሊቀ ሊቃውንት ይባላል። 4ቱንም ያስመሰከረ ዓራት ዓይና ይባላል።

ብሉይ ኪዳን የሚባሉት 46 ናቸው እነዚህም፦
               ፩ ኦሪት ዘፍጥረት
               ፪ ኦሪት ዘጸዓት
               ፫ ኦሪት ዘሌዋውያን
               ፬ኦሪት ዘኁልቊ
               ፭ ኦሪት ዘዳግም
               ፮ መጽሐፈ ኢያሱ
               ፯ መጽሐፈ መሳፍንት
               ፰ መጽሐፈ ሩት
               ፱ መጽሐፈ ሲራክ
               ፲ መጽሐፈ ሱቱኤል ዕዝራ
               ፲፩ መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ
               ፲፪ ዜና መዋእል 1ኛ
               ፲፫ ዜና መዋእል 2ኛ
               ፲፬ መጽሐፈ አስቴር
               ፲፭ መጽሐፈ ጦቢት
               ፲፮ መቃብያን 1ኛ
               ፲፯ መቃብያን 2ኛ
               ፲፰ መቃብያን 3ኛ
               ፲፱ መጽሐፈ ኢዮብ
               ፳ መዝሙረ ዳዊት
               ፳፩ መጽሐፈ ምሳሌ
               ፳፪ መጽሐፈ ተግሣጽ
               ፳፫ መጽሐፈ መክብብ
               ፳፬ መኃልየ ሰሎሞን
               ፳፭ ዜና አይሁድ
               ፳፮ መጽሐፈ ነገሥት
               ፳፯ መጽሐፈ ሳሙኤል
               ፳፰ ትንቢተ ዳንኤል
               ፳፱ ትንቢተ ኤርምያስ
               ፴ ትንቢተ ሕዝቅኤል
               ፴፩ ትንቢተ ኢሳይያስ
               ፴፪ ትንቢተ ሐጌ
               ፴፫ ትንቢተ ዮናስ
               ፴፬ ትንቢተ ናሆም
               ፴፭ ትንቢተ ዘካርያስ
               ፴፮ ትንቢተ አብድዩ
               ፴፯ ትንቢተ ኢዩኤል
               ፴፰ ትንቢተ ሚልክያስ
               ፴፱ ትንቢተ ሚክያስ
               ፵ ትንቢተ አሞጽ
               ፵፩ ትንቢተ እንባቆም
               ፵፪ ትንቢተ ሆሴእ
               ፵፫ ትንቢተ ሶፎንያስ
               ፵፬ መጽሐፈ ሄኖክ
               ፵፭ መጽሐፈ ኩፋሌ
               ፵፮ መጽሐፈ ዮዲት
ሐዲስ ኪዳን የሚባሉት ደግሞ 35 ናቸው እነዚህም፦
                      ፩ የማቴዎስ ወንጌል
                      ፪ የማርቆስ ወንጌል
                      ፫ የዮሐንስ ወንጌል
                      ፬ የሉቃስ ወንጌል
                      ፭ የሐዋርያት ስራ
                      ፮ ራእየ ዮሐንስ
    ፯ የጳውሎስ መልእክት ወደሮሜ ሰዎች
    ፰ የጳውሎስ መልእክት ወደ ገላትያ
    ፱ የጳውሎስ መልእክት ወደ ኤፌሶን
    ፲ የጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ
    ፲፩ የጳውሎስ መልእክት ለቆሮንቶስ 1ኛ
    ፲፪ የጳውሎስ መልእክት ለቆሮንቶስ 2ኛ
    ፲፫ የጳውሎስ ምልእክት ለዕብራውያን
    ፲፬ የጳውሎስ መልእክት 1ኛ ጢሞቴዎስ
    ፲፭ የጳውሎስ መልእክት 2ኛ ጢሞቴዎስ
    ፲፮ የጳውሎስ መልእክት ወደ ቲቶ
    ፲፯ የጳውሎስ ማልእክት ወደ ፊልሞና
    ፲፰ የጳውሎስ መልእክት ለቆላስይስ
    ፲፱ የጳውሎስ መልእክት ለተሰሎንቄ 1ኛ
    ፳ የጳውሎስ መልእክት ለተሰሎንቄ 2ኛ
              ፳፩ መልእክተ ይሁዳ
              ፳፪ መልእክተ ያእቆብ
                            ፳፫ መልእክተ ዮሐንስ 1ኛ
              ፳፬ መልእክተ ዮሐንስ 2ኛ
              ፳፭ መልእክተ ዮሐንስ 3ኛ
              ፳፮ መልእክተጴጥሮስ 1ኛ
              ፳፯ መልእክተጴጥሮስ 2ኛ
              ፳፰ ዲድስቅልያ
              ፳፱ አብጥሊስ
              ፴ ሥርዓተ ጽዮን
              ፴፩ መጽሐፈ ኪዳን 1ኛ
              ፴፪ መጽሐፈ ኪዳን 2ኛ
              ፴፫ ግጽው
              ፴፬ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
              ፴፭ ትእዛዝ
አራቱ ጉባኤያት የሚባሉ እነዚህ ናቸው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ምንጭ👉መ/ር በትረማርያም አበባው

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ
#Share_Please

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
#፮ኛው_ሳምንት_ምንይባላል??

​​​​​​የዐብይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡

ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ስለ ታማኝ አገልጋይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ስንኖር ለፈጣሪያችን ያለንን ታማኝነትና የምናገኘውን ዋጋ በመዋዕለ ሥጋዌው
አስተምሯል፡፡

ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያነት የዐብይ ጾምን ሳምንታትን ሲከፍል ገብርኄርን ተጠቅሟልና እኛም ስለ ገብር ሄር ጥቂት እንበል፡፡ ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን በነቢዩ አንደበት አድሮ፤ “እከሥት በምሳሌ አፉየ፤ ወእነግር አምሳለ ዘእምትካት፤ አንደበቴን /ነገሬን/ በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ
ታሪክና ምሳሌ እናገራለሁ” አለ፡፡

ይህም ማለት ወንጌልን በምሳሌ አስተምራለሁ፤ በመልከ ጼዴቅ ዘመን አስቀድማ የተሠራችና ታይታ የጠፋችውን ወንጌልን እናገራለሁ፡፡ ይህን ታላቅ ምሥጢር ሐዋርያው ሲያብራራ “ከመ በአሚን ያጸድቆሙ እግዚአብሔር ለአሕዛብ አቅደመ አሰፍዎቶ ለአብርሃም ከመ ቦቱ ይትባረኩ ኲሎሙ አሕዛብ ፤  በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ” ብሏል፡፡ /ገላ. ፫፥፰፣ መዝ. ፸፯፥፪

በዚሁ መሠረት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ለልዩ ልዩ ወገኖች በልዩ ልዩ ምሳሌ አስተምሯል፤ ከላይ በተገለጠው ኃይለ ቃል መነሻነት ሁለት ምሳሌያትና አንድ ቃለ ትንቢት ቀርበዋል፡፡ ከምሳሌያቱ
የመጀመሪያው በዐሥሩ ደናግል አንጻር የቀረበው ምሥጢር ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ወጥተው ወርደው ነግደው ያተርፉበት ዘንድ ገንዘቡን ስለሰጠ አንድ ነጋዴ የሚናገረው ነው፡፡

የትንቢቱ ምሥጢራዊ ይዘት የሚያስረዳውም ስለ ኅልቀተ ዓለም አይቀሬነት ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ዕትማችን ወጥተው ወርደው ነግደው እንዲያተርፉበት ከጌታቸው የተሰጣቸውን መክሊት ስለተቀበሉት አገልጋዮች ሕይወት እንመለከታለን፡፡ ፈጣሪያችን አእምሮውን ለብዎውን /ማስተዋሉን/ ያድለን፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማራቸው ምሳሌያዊ ትምህርቶች በቅዱስ መጽሐፋችን በሰፊው ተጽፈው እናገኛለን፡፡ የእነዚህ ትምህርታዊ ምሳሌዎች መሠረታዊ ሀሳብና ዓላማም የእግዚአብሔርን መንግሥት የምናገኝበትን የታማኝነትን ሥራ እንዴት መሥራት እንደሚገባንና መሥራትም እንደምንችል ማስተማር ነው፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመንግሥተ ሰማያት ምሥጢር ያስተማራቸው ብዙ ምሳሌዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ብዙ ምሳሌያዊ ትምህርቶች መካከልም እንዲያተርፉበት መክሊት ስለተሰጣቸውና ስለተመሰገኑት መልካም አገልጋዮች፣ እንዲሁም መክሊቱን በመቅበሩ ምክንያት በጌታው ስለተወቀሰውና ፍርድን ስለተቀበለው ሰነፍ ሰው ታሪክ፣ የታሪኩም ምሥጢር ምን እንደሚመስል የተጻፈው ትምህርት ነው።

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ምሳሌ የተናገረው /ያስተማረው/ በሚከተለው መልኩ ነበር፤ ‹‹ወደ ሌላ ሀገር የሚሔድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ ሀገር ወዲያውኑ ሔደ፡፡

አምስት መክሊትም የተቀበለው ሔዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፣ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ፣ አንድ የተቀበለው ግን ሔዶ ምድርን ቆፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ፡፡

ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ፡- ጌታ ሆይ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ፡፡
ጌታውም፡- መልካም አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡

ሁለት መክሊት የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡- ጌታ ሆይ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፡፡ እነሆ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ፡፡
ጌታውም፡- መልካም አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡- ጌታ ሆይ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሔጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት ፤ እነሆ መክሊትህ አለልህ አለው፡፡
ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፡- አንተ ክፉና ሐሰተኛ ባሪያ ካልዘራሁበት እንዳጭድ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር።

እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር፡፡ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት ዐሥር መክሊትም ላለው ስጡት። ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል። ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል፡፡

የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል የሚል ነው፡፡

መክሊት ጥንት የክብደት መለኪያ ነበር:: አንድ መክሊት 30 ኪሎ ግራም ያህል ነው፡፡ በዚህ ምሳሌ ላይ እንደተገለጸውም መክሊት የሚለው ቃል ገንዘብን ያመለክታል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምሳሌ ውስጥ እርሱን የምናገለግል ሁላችን እንደየዓቅማችን ማድረግ የሚገባንን መንፈሳዊ የአገልግሎት ሥራንና በአገልግሎታችን ውጤታማ በመሆናችንም ከእርሱ የምናገኘውን ዘለዓለማዊ ክብርና ዋጋን እንዲሁም መሥራት የሚገባንን ባለማድረጋችንም ምክንያት የሚገጥመንን መለኮታዊ ቅጣትን አመልክቶናል፡፡

በዚህ ምሳሌ ውስጥ ባለ አምስት የተባለው በቂና ፍጹም ትምህርት ተምሮ ሌላውን መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ የተካ ያወጣ ነው፡፡

በተመሳሳይም ባለ ሁለት የተባለው እንደ መጀመሪያው ሁሉ ተምሮ ሌላውን መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ያወጣ ሲሆን ባለ አንድ የተባለው ደግሞ ተምሮ ሳያስተምር የቀረ በስንፍና በቸልተኝነት በማን አለብኝነት ሕይወት ተገድቦ የቀረ ሰው ነው።

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
ፍኖተ ቅዱሳን ꜰɪɴᴏᴛᴇᴋɪᴅᴜsᴀɴ pinned «#፮ኛው_ሳምንት_ምንይባላል?? ​​​​​​የዐብይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡ ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ስለ ታማኝ አገልጋይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ስንኖር ለፈጣሪያችን ያለንን ታማኝነትና የምናገኘውን ዋጋ በመዋዕለ ሥጋዌው አስተምሯል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያነት የዐብይ ጾምን ሳምንታትን ሲከፍል ገብርኄርን ተጠቅሟልና እኛም ስለ ገብር ሄር ጥቂት…»
​​የቀጠለ 👆

በመሆኑም የባለ አምስትና የባለ ሁለት መክሊት ባለቤቶች የሆኑት ወጥተው ወርደው ደክመው፣ መከራ መስቀልን ሳይሳቀቁና ሳይፈሩ፤ ወድደው ፈቅደው የጀመሩትን አገልግሎት በማክበር ሕይወታቸውን ለታመነው አምላክ አደራ በመስጠት የተማሩትን ፍጹም ትምህርት ለሌላው አስተምረው፣ ሠርተው ያገኙትን ለሌላው አካፍለው ወገናቸውን እንደራሳቸው አድርገው ሲመለከቱ

ባለ አንድ መክሊት የተባለው ግን ዓላውያን እሳት ስለት አሳይተው ሃይማኖቴን ሲያስክዱኝ መናፍቃን ተከራክረው ምላሽ ቢያሳጡኝ ብሎ ፈርቶ ሃይማኖቱን በልቡ ከመደበቅና ከመሠወር በቀር የተማረውን ትምህርት ሠርቶ ያገኘውን ሀብት ንብረት ለሌላው ሊያካፍልና የተሰጠውን አደራም ሊወጣ አልወደደም፡፡

ይህ የመክሊቱ ባለቤት የተባለው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የተሰጣቸውን ሓላፊነት በአግባቡና በጽንአት ለተወጡት ሁሉ እርሱ ፍጹም ዋጋን የሚሰጣቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡

ይህም ሁኔታ “አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” በሚል ታላቅ የምስጋና ቃል ተገልጧል፡፡ ይህ ቃል በሃይማኖትና በበጎ ምግባር ለእግዚአብሔር የታመኑ ሁሉ ዘለዓለማዊና ፍጹም ደስታ ወደሚገኝበት መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ለሚያደርጉት የእምነት ጉዞ እጅግ ተስፋ የሆነ ቃል ነው፡፡

በዚህ ምንባብ ላይ እንደተገለጸው እግዚአብሔር አምላክ ለሁላችንም እርሱን የምናገለግልበትንና ለእርሱ በመታመን ዘለዓለማዊ ክብርን የምናገኝበትን ዕውቀትን፣ ማስተዋልን፣ እምነትን፣ ተስፋን፣ የሥነ ምግባር ሀብትን፣ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን እንጠቀምባቸው ዘንድ ለእኛ ለሰው ልጆች እንደየዓቅማችን መጠን ሰጥቶናል፡፡

እነዚህ ሁሉ ነገሮች የሥጋችንን ምኞት
ለማስፈጸም የተሰጡ ሳይሆኑ ነፍሳችን የምትከብርበትን መልካም ሥራን የምንሠራባቸው መሣሪያዎቻችን ናቸው። በመሆኑም እርሱ በሰጠን የአገልግሎት በር ጸጋ በታማኝነት በማገልገል በሕይወት ዘመናችን ሁሉ መንፈሳዊውን ሀብት የምናተርፍ እንሆን ዘንድ የተላለፈልን አምላካዊ ምክር ነው፡፡

ምክንያቱም እኛ የተጠራነው ፍሬ ልናፈራና ሌላውንም ልናተርፍ መልካም ሥራን ልንሠራ እንጂ የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል የኃጢአት ባሮች ልንሆን አይደለም፡፡ መጽሐፍ እንዲህ አለ “ወኲሉ ዘከመ ተጸውአ ከማሁ ለየሀሉ፤ ሁሉ እንደተጠራ እንዲሁ ይኑር” /፩ኛ ቆሮ. ፯፥፳/

ከላይ እንደተመለከትነው በልዑል አምላክ በእግዚአብሔር አንደበት አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ መባልን የመሰለ አስደሳችና አስደናቂ ነገር የለም፡፡

ይህ ደግሞ የሚገኘው ሃይማኖትን በሥራ በመግለጥ እንጂ ሃይማኖትን በልቡና በመያዝ ብቻ /ሙያ በልብ ነው/ በማለት ብቻ የሚገኝ አይደለም፡፡ ከእነዚህ እንደ አቅማቸው መጠን መክሊት ተሰጥቷቸው በትጋታቸውና በቅንነታቸው ሌላ መክሊት ካተረፉት በጎና ታማኝ አገልጋዮች የምንማረው እውነታም ይህ ነው፡፡

በብዙ ለመሾም ለማደግ ለመጽደቅ በጥቂቱ መታመን መፈተን መጋደል ግድ ነው፡፡ አንድ መክሊት የተሰጠውን ሰው ስንመለከተው ጌታውን ጨካኝና ፈራጅ አድርጎ ከመቁጠር ውጪ በተሰጠው መክሊት ወጥቶ ወርዶ ሊያተርፍ አልወደደም፡፡

መክሊቱንም ባስረከበ ጊዜ በጌታው ላይ የተናገራቸው ቃላት የእርሱን አለመታዘዝና አመጸኝነት ይገልጡ ነበር፡፡ በመሆኑም ይህ ሰው በጥቂቱ መታመን ያቃተውና በአስተሳሰቡ ደካማነት እጅግ የተጎሳቆለ ሰው ነው፡፡

በዚህ ምሳሌ መሠረት ይህ ባለ አንድ መክሊት የተባለው ሰው ዓላውያን ነገሥታት እሳት ስለት አሳይተው ቢያስክዱኝ መናፍቃን ተከራክረው መልስ ቢያሳጡኝ በማለት ሃይማኖቱን በልቡ ሸሽጎና ቀብሮ በተቀደሰ ተግባር ሳይገልጠው ከመያዙ ባሻገር በጌታ ፊት በድፍረት ቆሞ አንተ ሕግ ሳትሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ፤ መምህራንንም ሳትመድብ በሥነ ፍጥረት ተመራምራችሁ በሠራችሁ ብለህ የምትፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆንክን አውቃለሁና ፈርቼ ሃይማኖቴን በልቡናዬ ይዠዋለው በአዕምሮዬ ጠብቄዋለሁ የሚል ሃይማኖቱን ግን በሥራ የማይገልጥ ሰነፍ ሰውን ያመለክታል፡፡

ለዚህ ዓይነት ሰው የጌታ መልስ ደግሞ በምሳሌው መሠረት የሚከተለው ነው። እኔ ሕግ ሳልሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ ፤ መምህር ሳልሰጥ በሥነ ፍጥረት ተመራምራችሁ አውቃችሁ በሠራችሁት ብዬ የምፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆኔን ታውቃለህን? እንዲህስ ካወቅህ ሹመትክን ልትመልስልኝ ይገባኝ ነበር፡፡

ወጥቶ ወርዶ ለሚያስተምር በሰጠሁት ነበር፡፡ አሁንም የእርሱን መምህርነት ሹመት ነሥታችሁ (ወስዳችሁ) ለዚያ ለባለ ዐራቱና ለባለ ዐሥሩ ደርቡለት!

እርሱን ግን አውጡት የሚል ነው። ምክንያቱም ከበጎ ምግባር የተለየች እምነት የሞተች እንደሆነ ተጽፏልና። ዛሬም እያንዳንዳችን በዓቅማችን መጠን መክሊት ተሰጥቶናል፡፡ ነገር ግን መክሊቱን እንደቀበረው እንደዚያ ሰው የተሰጠንን ቀብረን ለወቀሳና ለፍርድ እንዳንሰጥ በአገልግሎታችን ልንተጋ ይገባናል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህንኑ ሲገልጥ “ወዘሂ ይትለአክ በመልእክቱ፤ ወዘሂ ይሜህር በትምህርቱ. . .፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ የሚያስተምርም በማስተማሩ ይትጋ የሚሰጥም በልግሥና ይስጥ›› (ሮሜ. ፲፪፥፯) በማለት ተናግሯል፡፡

ለመሆኑ አሁን ባለንበት የስግብግብነት ወቅት ዛሬ ‹‹አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ…›› ተብሎ በእግዚአብሔር ሊመሰገን የሚችል ሰው ማን ይሆን? በእውነት እንዲህ ተብሎ የሚመሰገን በጎና ታማኝ ካህን በጎና ታማኝ መምህር በጎና ታማኝ ምእመን ታማኝ ሰባኪና ታማኝ ዘማሪ ማግኘት ይቻል ይሆንን?

ነገር ግን መቼም አምላካችን ቸር ነውና በየዘመናቱ አንዳንድ ታማኝ አባቶችን እንደማያሳጣን ተስፋ አለን። ምክንያቱም ዛሬም ቢሆን እንደአባቶቻችን እንደቅዱሳን ሐዋርያት በእምነት፣ በትዕግሥት በፍቅር በተጋድሎ በየውሐት በትሕርምት በጸሊዓ ንዋይ በትሕትናና በትጋት በማገልገል የተሰጣቸውን መክሊት የሚያበዙ አገልጋዮች አሉ፡፡

የእነዚህ ክብራቸው በምድርም በሰማይም እጅግ የበዛና ራሳቸውን አስመስለው በትምህርት የወለዷቸው ልጆቻቸውም ለቤተ ክርስቲያን የተወደዱ የተከበሩ ልጆች ናቸው፡፡

ለምሳሌ ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ ነቢየ እግዚአብሔር ኢያሱን ፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀሌምንጦስን፣ ቅዱስ ጳውሎስም ቅዱስ ጢሞቴዎስን ለቤተ ክርስቲያን አበርክተዋል፡፡ ሌሎችም አበው ቅዱሳን በወንጌል ቃል መንፈሳውያንና ትጉሃን የሆኑ ምእመናንን በሚገባ አፍርተዋል፡፡

ያላመኑትንም አሳምነው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመመለስ ለዘለዓለማዊ ክብር የበቁ እንዲሆኑ አስችለዋቸዋል። በተሰጣቸው ጸጋም አትርፈው አትረፍርፈው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንድትጎበኝ አድርገዋል፡፡ የእነርሱም በረከታቸው ረድኤታቸው ቃል ኪዳናቸው ለሌሎች እንዲተርፍ ሆኖላቸዋል፡፡

በመሆኑም ክርስቶስ በደሙ የከፈለውን ወደር የሌለውን ዋጋ ዓለም አምኖና ተቀብሎ በክርስትና ሃይማኖት እንዲድንበትና እንዲጠቀምበት በማድረግ እንዲሁም በታማኝነትና በበጎነት አገልግሎታቸው ጥንትም ዛሬም ላለችዋና ወደፊትም ለምትኖረዋ ቅድስት ቤተክርስቲያን ድምቀትም ውበትም የሆኑት ቅዱሳን አበው ሊገኙ የቻሉት ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን ደስ ለማሰኘት በመድከማቸው ሳይሆን የተጠሩበትን ዓላማና የጠራቸውን እርሱን በሚገባ አውቀውና ከልብ ተረድተው ለዘለዓለማዊ ሕይወት ተግተው በመሥራታቸው ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ከቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 የቀድሞ አባቶች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር  አስገብተዋል።

  ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ ወደ ጸበል መሄዳቸውን ገልጸው ደብዳቤአቸውን በተወካይ አስገብተዋል። በጥቅሉ ደብዳቤ ያስገቡት18 ሲሆኑ ቀሪዎቹ  6 የቀድሞ አባቶች በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ በዛሬው ዕለት የተገኙት የቀድሞ አባቶች ገልጸው በቅርብ ጊዜ ቀሪዎቹ ግለሰቦች ማመልከቻቸውን ይዘው እንደሚመጡ ገልጸዋል።
ምንጭ፡ የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
#ኒቆዲሞስ

ሰው ሥልጣን ቢኖረው ዕውቀት ሊጎድለው እንዲሁም ሀብት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ማካበት ያዳግተዋል፡፡ ሀብት ቢኖረውም እንኳን ዕውቀት ይጎድለዋል፤ ሥልጣንም አይኖረውም፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ሦስቱንም አንድ ላይ አስተባብሮ የያዘ የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡
 
ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነው ኒቆዲሞስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያስተማረውን ወንጌልን ለመማር ከአይሁድ ሁሉ ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ይሄድ ነበር፡፡ ፈሪሳውያን ማመን በተሳናቸው በዚያን ጊዜ ጆሮውን ለቃለ እግዚአብሔር፣ ልቡን ለእምነት የከፈተ ሰው ነው፡፡
 
እናውቃለን በማለት የሚመካኙ በርካታ ሰዎች ከመልካም ነገር ሲከለከሉ እርሱ ግን “ዐዋቂ ሳለ ራሱን ዝቅ አድርጎ፣ እምነት በማጣት የነጠፈችውን የፈሪሳውያንን ኅብረት ጥሎ፣ ሐዋርያትን መስሎ ጌታውን አግኝቶታል፡፡” ቀርቦም እንዲህ አለው፤ ‹‹መምህር ሆይ፥ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርግ የሚችል የለምና፡፡›› ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም›› አለው፡፡
 
ነገር ግን ኒቆዲሞስ ምሥጢሩ ስላልተገለጠለት ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?›› በማለት ጌታን መልሶ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡››
 
አሁንም ግን ኒቆዲሞስ ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና ‹‹ይህ ሊሆን እንዴት ይቻላል?›› በማለትም ጌታን ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ፤ ነገር ግን እንዴት ይህን አታውቅም? በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም…›› በማለት አስረድቶታል፡፡ (ዮሐ.፫፥፪-፲፭)
 
የዓለም መድኃኒት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በለየባት በዚያች ሰዓት፣ ሐዋርያት በተበተኑባትና አይሁድ በሠለጠኑባት ጊዜ እንኳን ከጌታችን ሳይል በድፍረት ከእግረ መስቀሉ የተገኘ እንዲሁም ቅዱስ ሥጋውን በድርብ በፍታ ገንዞ የቀበረ ሰው ኒቆዲሞስ ነው፤ ስለዚህም ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት በእርሱ ስም ተሰይሟል፡፡
 
ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን ገልጾ ያዳነውና ያከበረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛም ምሥጢሩን ይገልጽልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን፡፡
 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
 

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
#በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጣ

ኒቆዲሞስ በውድቅት ሌሊት ወደ ጌታችን መጣ። ሌሊት እንግዲህ በቂ ብርሃን የሌለበት ፣ እንቅፋት የሚበዛበት ፣ ጭልም የሚልበት ፣ ግራ ቀኝ ቢያዩ ሰው የሚታጣበት ፣ ማጅራት ከሚመቱ ወንበዴዎች በቀር በመንገድ ሌላ ሰው የማያጋጥምበት ፣ ብርድና ቆፈን ሰውነትን የሚያስጨንቅበት ሰዓት ነው። ይህ የአይሁድ መምህር በሌሊት የመጣበት ምክንያቱ ብዙ ሲሆን ለእምነት ማነስ ማሳያ የሚሆን ሰው ነው።

ዛሬ ደግሞ ለአፍታ ኒቆዲሞስን "በሌሊት ወደ ኢየሱስ በመምጣቱ" በጥቂቱ እናመስግነው።  ብዙ እግሮች ወደ ኃጢአት በሚሮጡባት ሌሊት ወደ ክርስቶስ የሮጠውን ይህንን ሰው እስቲ እናድንቀው!  ይህንን የሌሊት ግርማ ሳይበግረው ወደ ኢየሱስ የተጓዘ የጨለማ ተጓዥ ፣ ይህንን ሰዓታት ቋሚ ፣ ይህንን ማሕሌት ቋሚ በጥቂቱ ብናመሰግነው ምን አለ? ከጌታ ፊት ቆሞ ቅኔ የተመራውን ፣ ስለ ልደት እየተናገረ ስለ ጥምቀት የሚያመሰጥረውን የፈጣሪን ቅኔ ተቀብሎ ሊያዜም ከጀመረ በኋላ መቀበል ሲያቅተው ጌታችን  "አንተ የአይሁድ መምህር ስትሆን ይህንን አታውቅምን?" ብሎ የገሠፀውን ኒቆዲሞስን እስቲ ዛሬ በበጎነቱ አርኣያ እናድርገው።

በሕይወታችን ውስጥ የተስፋ ብርሃን ጭልም ባለብን ጊዜ ፣ እንቅፋት በበዛብን ወቅት ፣ ግራ ቀኝ አይተን ሰው ባጣንበትና ብቸኝነት በዋጠን ሰዓት ፣ ክፉ ከማድረግ በማይመለሱ ጨካኞች በተከበብን ሰዓት እኛስ ወዴት እንሔዳለን?

ሕይወቱ "ሌሊት" የሆነበት ሰው ሁሉ  ወደ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ቢሔድ እንደሚሻለው ከኒቆዲሞስ የተሻለ ምሳሌ የለም። ሕይወቱ የጨለመ ባይሆን እንኳን ልቡ የጨለመበት ፣ በኃጢአት ጠል የጠቆረ ፣ በበደል ብርድ ቆፈን እጅ እግሩ የታሰረ ከእኛ መካከል ስንት አለ?

እመነኝ ፣ ተስፋ ቆርጠህ ቁጭ ብለህ እስከሚነጋልህ ብትጠብቅ አይነጋም። ይልቅ ተነሥና "በሌሊት ወደ ክርስቶስ ሒድ" እርሱ ተስፋ ለቆረጠው ማንነትህ ዳግመኛ መወለድ እንዳለም ይነግርልሃል። ኒቆዲሞስ ጌታችንን ሊያየው ሔዶ  ራሱ ታይቶ እንደመጣ አንተም ወደ እርሱ የቀረብህ እንደሆነ ራስህን ታያለህ።

በ"ሌሊት" ውስጥ ለሚኖር ሰው ነግቶ ፀሐይ ትወጣልኛለች ብሎ ከሚጠባበቅ ይልቅ በሌሊት እንደ ኒቆዲሞስ ተነሥቶ ወደ ጽድቅ ፀሐይ ወደ ክርስቶስ ቢሔድ ይሻለዋል።  ወደ እርሱ ለሚሔድ ሰው ሌሊቱ ይነጋል ፣ ክርስቶስ ያለበት ሌሊት ከቀን ይልቅ ብሩሕ ነው ፣ እውነተኛው ብርሃን ያለበት ጨለማም ጨለማ አይደለም። ስለ እርሱ "ጨለማም በአንተ ዘንድ አይጨልምም" ተብሎ ተጽፎአልና።


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
ፍኖተ ቅዱሳን ꜰɪɴᴏᴛᴇᴋɪᴅᴜsᴀɴ pinned «#ኒቆዲሞስ ሰው ሥልጣን ቢኖረው ዕውቀት ሊጎድለው እንዲሁም ሀብት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ማካበት ያዳግተዋል፡፡ ሀብት ቢኖረውም እንኳን ዕውቀት ይጎድለዋል፤ ሥልጣንም አይኖረውም፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ሦስቱንም አንድ ላይ አስተባብሮ የያዘ የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡   ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነው ኒቆዲሞስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያስተማረውን ወንጌልን…»
በተጨማሪም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ “ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ትሰመይ (ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት” በማለት በቤተ መቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን አስወጥቷል። (ማር.፲፩÷፲፭-፲፯) ይህ ዕለት አንጽሖተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት መታሰቢያ ነው፤ ስለዚህም ዕለተ ሰኑይ “አንጽሖተ ቤተ መቅደስ” ይባላል። ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበረውን የአዳም ልጆች ኃጥአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአትን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው።
ሰሙነ ሕማማት

ሰሙነ ሕማማት የሚባለው ሳምንት በዐቢይ ጾም መጨረሻ ከሆሣዕና ዋዜማ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ባሉት ቀናት ውስጥ ያለው ነው። ሰሙነ ሕማማት የተባለበት ምክንያት ነቢዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ የጌታችንን ምሥጢረ ሕማማቱን ነገር በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት “ውእቱ ነሥአ ደዌነ ወፆረ ሕማምነ” እርሱ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ ሲል እንደተናገረው የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ድኅነት በፍቃዱ ሕማማተ መስቀልን በትዕግሥት በመሸከም ማህያዊ ሞቱ በመስቀሉ የተፈፀመበት በመሆኑ እኛም መከራ መስቀሉን የምናስብበት ስለሆነ ሰሙነ ሕማማት ተብሏል። (ኢሳ.፶፫፥፬፣ማቴ.፰፡፲፣፯፣ዮሐ ፩፥፳፱)

ዕለተ ሰኑይ መርገመ በለስ ወአንጽሖተ ቤተ መቅደስ

በዚህ ዕለት ሰኑይ (ሰኞ) አዳምና ሔዋን ከገነት እንደተባረሩ፣ የበለስ ቅጠል እንዳገለደሙ ይታሰባል። ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ እንደጻፈው (ማር.፲፩፥፲፪-፲፬) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በበዓለ ሆሣዕና በመሸ ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ። በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ። ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ። የበለስ ወራት አልነበረምና ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። በዚያን ጊዜ “ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ” ብሎ ረገማት። ስለዚህም በሰሙነ ሕማማት የሚገኘው ሰኞ “መርገመ በለስ” የተፈጸመበት ዕለት መታሰቢያ ነው። የዚህም ትርጉም ወይም ምሥጢሩ ከበለስ ፍሬ መሻቱ ከሰው ፍቅር ተርቦ ለማጣቱን ለመግለጽ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ከእኛ መልካም የሃይማኖትና የምግባር ፍሬ ሽቶ ይመጣልና ፍሬ አልባ ሆነን እንዳያገኘን፣ ፍሬ የማያፈራ ዛፍ እንደሚቆረጥና ቅጠሎቹም እንዲቃጠሉ ለእሳት እንደሚሰጡ የተነገረውን አስታውሰን መልካም ፍሬን ልናፈራ ይገባል።
#መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ዕለት_ነው

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡

በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

#አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦

ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
ሕማማት_በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ_@eotc_books_by_pdf_pdf.pdf
42.3 MB
📚⛪️ሕማማት📚⛪️

ጸሐፊ ፦ ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ
አቅራቢ ፦ @finote_kidusan 📚

✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ
#Share_Please

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ
#Share_Please

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
2024/05/16 03:49:32
Back to Top
HTML Embed Code: