Telegram Web Link
በሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ስም የተሰየመው የሮያሊቲ ክፍያ ማስገኛ ሥርዓት ይፋ ሆነ

በተወዳጁ የሙዚቃ ባለሙያ ኤልያስ መልካ ስም የተዘጋጀው የሙዚቃ ሮያሊቲ መሰብሰቢያ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በይፋ ተዋውቋል።

ሥርዓቱ ኤልያስ መልካ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ሮያሊቲ መሰብሰቢያ ወይም (EMEMRC) የሚል መጠሪያ የተሰጠው ነው።

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር የሮያሊቲ ክፍያ አሰባሰብን አስመልክቶ በጋራ ያዘጋጁትን የሮያሊቲ ክፍያ ቀመር ለማፅደቅ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የቀረበለትን ቀመር ለማፅደቅ ከሚዲያ አመራሮችና ከፈጠራ ባለሙዎች ጋር እየተወያየ ሲሆን፥ ተቋማት የሚከፍሉት የሮያሊቲ ክፍያ የገቢ አቅማቸውን መሰረት በማድረግ 24 ሠአት የሙዚቃ ውጤቶችን ይጠቀማሉ ተብሏል።

የሙዚቃ ተጠቃሚዎች በዓመትና በጊዜያዊነት ክፍያ መፈፀም እንደሚችሉም ተሰምቷል።

ለአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በቀረበው ቀመር መሰረት ተቋማቱ በ24 ሠአት ውስጥ 360 እነዲሁም በዓመት ደግሞ 131 ሺህ 400 ሙዚቃዎችን እንደሚያጫውቱ ተመላክቷል።

የሙዚቃ ባለሙያውም በተጫወተለት የሙዚቃ መጠን የሚከፈለው ሲሆን፥ ባለስልጣኑና ሁለቱ ማህበራት በዛሬው ዕለት የሮያሊቲ ክፍያ ቀመርን ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ዘግቧል።

@Firtunamedia
የአስቻለው ፈጠነ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው

በእናትዋ ጎንደር፣ካሲናው ጎጃም፣ አሞራው ካሞራ በተሰኙ ነጠላ ዜማዎች ተወዳጅነትን ያተረፈው "አስቻለ"የተሰኘው አልበም ከአንድ ዓመት በፊት ለሙዚቃ አፍቃሪው ያደረሰው ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ( አርዲ) የሙዚቃ ኮንሰርት በእስራኤል ሀገር  ሊያቀርብ እንደሆነ ገልጿል።

አርትስ ስፔሻል ከድምጻዊ እንዳገኘው መረጃ ከሆነ የሙዚቃ ዝግጅቱ ከፋሲካ በኃላ በፈረንጆቹ ሜይ 15 2025 በቴላቪብ  እንደሚካሄድ ተነግሯል።

ድምጻዊ አስቻው ፈጠነ የሙዚቃ ኮንሰርት በእስራኤል ካቀረበ በኃላ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት የሙዚቃ ዝግጅቱን እንደሚያቀርብ ድምጻዊው ለአርትስ ስፔሻል ገልጿል።

@firtunamedia
Forwarded from Prestige Addis
Our Guest: Anteneh Haile 🎬

Prestige Addis is honored to welcome the acclaimed writer and director, Anteneh Haile, to our next Beyond the Screen session!

From powerful screenplays to unforgettable productions, his work has helped shape the Ethiopian film scene.
Got something you’ve always wanted to ask him? Now’s your chance!

Stay tuned for an inspiring conversation.

@prestigeaddis
ሰላም እንደምን አላችሁ !

ፕሪስቴጅ አዲስ በተወዳጅ የፊልም ስራዎቹ የሚታወቀውን ስመ-ጥሩ እና አንጋፋው የፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር አንተነህ ሀይሌ ጋብዟል::

ከአንተነህ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን  ማክሰኞ ሚያዚያ 7, 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል።

በዕለቱ ከደራሲ እና ዳይሬክተር አንተነህ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃ-ግብር ይኖራል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከአንተነህ ሀይሌ ጋር  አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ እንድታደርጉ ይጋብዛል።
                                                                                                  
አድራሻ ፡ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 (  ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )
ማክሰኞ ሚያዚያ 7, 2017 ዓ.ም
ሰዓት- 8:00 🕘

⌚️ 🎯 ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩ።  

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ  🪪
                                                                                                                                     
📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱

https://jazzio.land/register

የፕሪስቴጅ አባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱

https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA


@prestigeaddis
ሰይፍ ፋንታሁን ህመም ገጥሞት እንደነበረ ተናገረ

ዝነኛው የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ፕሮግራሞች አቅራቢ ሰይፉ ፋንታሁን ትንሽ ህመም ገጥሞት እንደነበረ  በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታወቀ።

ሰይፉ ፋንታሁን በማህበራዊ ትስስር ገፁ"ቀለል ያለውን አድርጎልኛል።እግዚአብሔር ይመስገን።በዚህ ሳምንት ወደ ስራ እመለሳለሁ" ብሏል።

@firtunamedia
ሙዚቀኛው ሞቶ ተገኘ!

የቀድሞ ሮሀ ባንድ ሳክስፎኒስቱ በመኖሪያ ቤቱ ሞቶ ተገኘ

ከቀደምት ሮሀ ባንድ አባላት መካከል ተጠቃሹ አርቲስት ስምኦን ሊባኖስ በመኖሪያ ቤቱ ሕይወቱ አልፎ እንደተገኘ ጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ የአርቲስቱን የቀድሞ ስራ ባልደረባና ጓደኛ ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

" ከደቂቃዎች በፊት ጋሽ ዳዊት ይፍሩ እንዲህ አለኝ.. "እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነን። የዛን ዘመን የሮሃ ባንድ ሳክስፎኒስት የቀድሞ የስራ ባልደረባዬና ጓደኛዬ የነበረው አርቲስት ስሞኦን ሊባኖስ ( ዮናስ ደገፉ) ዛሬ ህንድ ኢንባሲ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።
ለምርመራው የአዲስ አበባ ፖሊስ አስክሬኑን ወስዷል"አለኝ።

ግን ሌላው የሚያሳዝነው ቤተሰቦቹን ማግኘት አልተቻለም ። እና ቤተሰቡ ወይም ወዳጆቹ አዲስ አበባ ፖሊስ መጠየቅ ትችላላችሁ። " ሲል መረጃውን አጋርቷል።



ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ቤተሰብ ይሁኑ።

"""""""""""***""""""""""
@firtunamedia
አርቲስት ሰላም ተስፋዬ የፖፕላር ኤሌክትሮኒክስ ትሬዲንግ ብራንድ አምባሳደር ሆነች

አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ከፖፕላር ኤሌክትሮኒክስ ትሬዲንግ ጋር የብራንድ አምባሳደርነት የስራ ውል ስምምነት ዛሬ ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ተፈራርማለች።

አርቲስት ሰላም ተስፋዬ በፖፕላር ኤሌክትሮኒክስ ትሬዲንግ ለቴሌቪዥን፤ ቢል ቦርድ እና ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎችን የምትሰራ ይሆናል።

ፖፕላር ኤሌክትሮኒክስ ትሬዲንግ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ከውጭ በማስመጣት የሚታወቅ ድርጅት ሲሆን በዛሬው እለትም አዲስ በከፈተው ሾው ሩም አርቲስት ሰላም ተስፋዬን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።

የአርቲስቷ የአምባሳደርነት ስምምነት ለአንድ ዓመት የሚቆይ ይሆናል።

@firtunamedia
የፈረጃ ፊልም ቀረፃ ሚያዝያ 20 ይጀምራል

በህዝብ መዋጮ የሚሰራዉና በኢትዮጵያ የመጀመርያው (Crowdfunding) ፊልም የሆነው ፈረጃ የተሰኘዉ የቦክስ ፊልም ከብዙ ዝግጅትና አድካሚ ጉዞ በኋላ የታሰበዉ በጀት ባይሞላም ቀረፃዉ ሚያዝያ 20 ሊጀመር ነዉ።

አርቲስት ሄኖክ ወንድሙ ሂደቱ ከባድ እንደነበር ተናግሮ የቦክስ ፊልም እንደመሆኑ ለቀረፃዉ ብዙ ሰው እንደሚያስፈልግና በተሳትፎ እንዲያግዙት ወጣቱን ኃይል ጠይቋል።

በገንዘብና በሀሳብ ላገዙት ሰዎች በሙሉ ትልቅ ክብርና ምስጋናዉንም አቅርቧል።

@firtunamedia
ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ከእስር ተፈታ

በእጮኛው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ እስር ቤት የቆየው ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሶስት ወራት ከተጠጋ ጊዜ በኋላ ከእስር ቤት መውጣቱን ፋስት መረጃ አስነብቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ የህግ ባለሙያው አበባየው ጌታ "ከአርቲስት አንዷለም ጎሳ ጠበቃ ጋር በስልክ ባደረኩት ንግግር አርቲስቱ ከእስር የመፈታቱ ዜና እውነት መሆኑን አረጋግጦልኛል" ሲል ጽፏል።

@firtunamedia
📌የአንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ የ60ኛ ዓመት የልደት በዓል ነገ ቅዳሜ በድምቀት ሊከበር ነው

ከጦር ሃይሎች ራድዮ አስከ ኢትዮጵያ ሬድዮ ከቅዳሜ መዝናኛ፣ ከነፃ ፕሬስ እስከ አርትስ ቲቪ፣ ከ97.1 ራዲዮ እስከ ሸገር ኤፍ ኤም ድረስ ተወዳጅ ሥራዎቹን ያቀረበው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከ11:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ በሚደረግ የእራት ፕርግራም የልደት በዓሉ ይከበራል ተብሏል።

በሃይሌ ግራንድ ሆቴል በሚከበረው የደረጀ የልደት በዓል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን፣ የልደት በዓሉን ለማድመቅ የሙዚቃ ዝግጅትም እንደተሰናዳ ተገልጿል።

@firtunamedia
2025/07/05 04:57:59
Back to Top
HTML Embed Code: