Telegram Web Link
Firtuna
Photo
📌ከድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ እጮኛ ቀነኒ አዱኛ ህልፈት ጋር በተያያዘ እስካሁን ያሉ መረጃዎች

የድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ እጮኛ ሞትን በተመለከተ በርካታ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

ከመሞቷ አንድ ቀን በፊት የት ነበረች? የድምጻዊው ማናጀር ስለልጅቷ ተናግሯል።

በኢንጂነሪንግ ድግሪ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀችው ቀነኒ በሞዴሊንግ በማስታወቂያ ሥራዎች በማኅበራዊ ሚድያ ዝናን አትርፋለች።

በሚቀጥለው ቅዳሜ ልደቷን ለማክበር በሚል ፎቶዎች እየተነሳች እንደነበር ከቅርብ ሰዎቿ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ልጅቱ ከመሞቷ አንድ ቀን በፊት የት ነበረች?

ልጅቱ ከመሞቷ አንድ ቀን በፊት ለልደቷ ፎቶ ስትነሳ እንደነበር በወቅቱ ፎቶ ያነሳት የነበረው የወንዴክስ ስቱዲዮ ባለቤት ወንድወሰን ጋሻው ተናግሯል ።

ፎቶግራፈሩም "በፎቶግራፍ  ስራዎች ካፈራዋቸው ወዳጆቼ መካከል የቀኝ እጄ የምላት እህቴ ቀነኒ አዱኛ መካሪዬ ጎደኛዬ የክፉ ቀን ወዳጄ ነበረች።

ትላንት መጋቢት 1 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ  የልደት ፎቶዎች ሳነሳት ነበር ማታ 1:00 በሰላም ተለያየትን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 2 2017 ዓ.ም ጠዋት ማረፏን አረዱኝ" ብሏል።

በተጨማሪም ትላንትና መጋቢት 1 2017 ዓ.ም አመሻሹን ቀነኒ አዱኛ ከእጮኛዋ ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ ጋር  በመዝናኛ ስፍራ አብረው እንዳሳለፉም ከተለያዩ ምንጮች ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ማናጀር የሆነው ለሊሣ እንድሪስ የተፈጠረውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግሯል።

"ንጋት 11:00 ሰዓት ስልክ ተደውሎ «ቀነኒ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች ቶሎ ድረስ» እንደተባለ የሚናገረው ለሊሳ እሱ ሩቅ በመሆኑ በሰዓቱ መድረስ እንዳልቻለ ይናገራል።

ቦሌ አራብሳ ከዓመት በላይ በጋራ ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው ከአምስተኛ ፎቅ እንደወደቀች እና ምን እንደተፈጠረ ፖሊስ እያጣራ መሆኑ ተነግሯል።

ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ በቅርብ በሚገኘው ያኔት ሆስፒታል ከገባች በኋላ ጠዋት ፖሊስ መጥቶ ሬሳዋን ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ከወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት እስኪወጣ አስክሬኗ ወደ ቤተሰቦቿ ሱሉልታ መሄዱ ነው የተገለፀው።

ድምፃዊ አንዱዓለም ጎሳ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከሆስፒታል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እዛ የሚገኝ ሲሆን እኛ የምናውቀው እስካሁን አለመታሰሩን ነው ምርመራ እናድርግ ብሎ ነው ፖሊስ የወሰደው ሲል ማናጀሩ ይናገራል።

ለሁለት አመታት በፍቅር ከቆዩ በኋላ በቅርቡ ጋብቻቸውን ለመፈፀም እየተዘጋጁ እንደሆነ አውቃለሁ ሲል ለሊሳ ይናገራል።

ፖሊስም ምን አለ?

የልጅቱ አሟሟት ምን እንደሆነ የምርመራ ስራ ተሰርቶ እስኪገለጹ ድረስ ህብረተሰብ  በትዕግሥት ይጠብቅ።አንዳንድ ግለሰቦች ተገቢ ካልሆነ ትንታኔ ይታቀቡ ብሏል።

📸ፎቶው ትላንት ለልደቷ ተነሳችው ፎቶ ነበር።

@firtunamedia
📌"ባቢሎን በሳሎን"ተውኔት ወደ መድረክ ይመለሳል

በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተስፋዬ ገ/ሐና የተዘጋጀውና በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው "ባቢሎን በሳሎን" ተውኔት ከሁለት ዓመት በኃላ ለአጭር ጊዜ ወደ መድረክ ሊመለስ እንደሆነ አርትስ ስፔሻል ከደራሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

"ባቢሎን በሳሎን" ተውኔትን በአውሮፓ ለሁለተኛ ጊዜ ለማሳየት እንቅስቃሴዎች እንደተጀመሩ የተገለፀ ሲሆን ተውኔቱ ወደ አውሮፓ ከመጓዙ በፊት ለአጭር ጊዜ በዓለም ሲኒማ እንዲታይ ከሲኒማ ቤቱ አስተዳደር ጋር ንግግር እንደተጀመረ እና በቅርቡ በድጋሚ ለመድረክ እንደሚበቃ ውድነህ ክፍሌ ለአርትስ ስፔሻል ተናግሯል።

ተውኔቱ ወደ መድረክ መቼ ይመለሳል የሚለው ጥያቄ የበርካታ ቴአትር አፍቃሪን ጥያቄ እንደሆነ የገለፀው ደራሲው "ባቢሎን በሳሎን" ወደ መድረክ እንዲመለስ "የዓለም ሲኒማ ኃላፊዎችም ያሻነውን ቀን እንደሚሰጡን ቃል ገብተውልናል" ብሏል።

"ባቢሎን በሳሎን" ተውኔት ወደ መድረክ ሲመለስ አርቲስት አለማየሁ ታደሰን ጨምሮ ሁሉም ተዋናዮች እንደሚኖሩም ተገልጿል።

ለ22 ዓመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ሲቀረብ የቆየው "ባቢሎን በሳሎን" ተውኔት ከሁለት ዓመት በፊት ከመድረክ መሰናቱ ይታወሳል።

@firtunamedia
Forwarded from Prestige Addis
An inspiring evening with journalist Etsegenet Yilma at the U.S. Embassy’s Satchmo Center! 🎙 Etsegenet shared her journey, insights, and passion for media, inspiring the next generation of storytellers.

Thank you to @yango.ethiopia for supporting this impactful event!

Stay tuned for more!

#PrestigeAddis #EtsegenetYilma #BeyondTheScreen #USEmbassy #Yango #WomenInMedia #JournalismMatters

@prestigeaddis
Forwarded from Prestige Addis
Good catch! Here's the revised version with the audience included:

A memorable evening with Etsegenet Yilma! 🎙 She connected with the audience, shared her journey, and inspired future storytellers through engaging discussions.

Thanks to everyone who joined us at the U.S. Embassy’s Satchmo Center and special thanks to Yango for supporting this event!

Stay tuned for more!

#PrestigeAddis #EtsegenetYilma #USEmbassy #Yango #WomenInMedia #Storytelling

@prestigeaddis
2025/07/14 13:50:08
Back to Top
HTML Embed Code: