Telegram Web Link
የፈረጃ ፊልም ቀረፃ ሚያዝያ 20 ይጀምራል

በህዝብ መዋጮ የሚሰራዉና በኢትዮጵያ የመጀመርያው (Crowdfunding) ፊልም የሆነው ፈረጃ የተሰኘዉ የቦክስ ፊልም ከብዙ ዝግጅትና አድካሚ ጉዞ በኋላ የታሰበዉ በጀት ባይሞላም ቀረፃዉ ሚያዝያ 20 ሊጀመር ነዉ።

አርቲስት ሄኖክ ወንድሙ ሂደቱ ከባድ እንደነበር ተናግሮ የቦክስ ፊልም እንደመሆኑ ለቀረፃዉ ብዙ ሰው እንደሚያስፈልግና በተሳትፎ እንዲያግዙት ወጣቱን ኃይል ጠይቋል።

በገንዘብና በሀሳብ ላገዙት ሰዎች በሙሉ ትልቅ ክብርና ምስጋናዉንም አቅርቧል።

@firtunamedia
ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ከእስር ተፈታ

በእጮኛው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ እስር ቤት የቆየው ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሶስት ወራት ከተጠጋ ጊዜ በኋላ ከእስር ቤት መውጣቱን ፋስት መረጃ አስነብቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ የህግ ባለሙያው አበባየው ጌታ "ከአርቲስት አንዷለም ጎሳ ጠበቃ ጋር በስልክ ባደረኩት ንግግር አርቲስቱ ከእስር የመፈታቱ ዜና እውነት መሆኑን አረጋግጦልኛል" ሲል ጽፏል።

@firtunamedia
📌የአንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ የ60ኛ ዓመት የልደት በዓል ነገ ቅዳሜ በድምቀት ሊከበር ነው

ከጦር ሃይሎች ራድዮ አስከ ኢትዮጵያ ሬድዮ ከቅዳሜ መዝናኛ፣ ከነፃ ፕሬስ እስከ አርትስ ቲቪ፣ ከ97.1 ራዲዮ እስከ ሸገር ኤፍ ኤም ድረስ ተወዳጅ ሥራዎቹን ያቀረበው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከ11:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ በሚደረግ የእራት ፕርግራም የልደት በዓሉ ይከበራል ተብሏል።

በሃይሌ ግራንድ ሆቴል በሚከበረው የደረጀ የልደት በዓል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን፣ የልደት በዓሉን ለማድመቅ የሙዚቃ ዝግጅትም እንደተሰናዳ ተገልጿል።

@firtunamedia
ሰላም እንደምን አላችሁ?

በሁለተኛው የcreative lab ዝግጅታችን  ደራሲ እና ዳይሬክተር ሰማኝጌታ አይችሉህምን ይዘንላችሁ ቀርበናል። 

በዚህ ስልጠና ሰማኝጌታ  ስለ "ልጄስ?" ተከታታይ ድራማ አፃፃፍ እንዲሁም ዳይሬክቲንግ ጥበብን ያካፍላናል። ይህንን ተወዳጅ ደራሲ እና ዳይሬክተር ልምዱን እና መርሆቹን የሚያካፍልበት መድረክ ላይ እንዲታደሙ ተጋብዘዋል።

ጀማሪ የስክሪፕት ፀሀፊዎች ዳይሬክተሮች በፊልሙ አለም ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ወጣት ጀማሪ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው።


በዕለቱ እጅግ ተወዳጅነት ያተረፈውን  የተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ   "ልጄስ?" ፓይለት ኤፒሶድ እናቀርባለን። በዚህም ከፊልሙ ጀርባ ያለውን ራዕይ እንዲሁም የስራሂደት
በተመለከተ ውይይት ይኖራል።

📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 (  ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

📅 ቀን: ሃምሌ 8 ፣ 2017

🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00 

🎟 መግብያ: ነፃ

አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር

በ ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ኢንስታግራም ገፃችንን ፎሎ ማድረግ እንዳይረሱ


📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

@prestigeaddis
2025/07/12 16:35:56
Back to Top
HTML Embed Code: