"ዘጠነኛው ሺ" ድራማ በአዲስ ምዕራፍ ሊጀምር ነው
በአብርሆት ኢንተርቴይመንት ተዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ብሮደካስቲግ ኮርፖሬሽን የሚቀረበው "ዘጠነኛው ሺ" አስቂኝ የቴሌቪዥን ድራማ በአዲስ ምዕራፍ በቅርቡ እንደሚጀመር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
ለተጨማሪው: @firtunamedia

"የማስረዳት ሸክም" መጽሐፍ ለንባብ በቃ
በህግ ባለሞያው እና ደራሲ ዳዊት በዛብህ የተዘጋጀው "የማስረዳት ሸክም" የተሰኘ መጽሐፍ ከሰሞኑ ለንባብ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
"የማስረዳት ሸክም" የአመክንዮ ሳይንስ (Logic) ፣ ሥነእውቀት (epistemology) እና የማስረጃ እና የሥነሥርዓት ሕግ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ነው።
ጸሐፊው "የሀገራችን ችግር ለመወያየት እና ለመከራከር ፍላጎት ከማጣትም በላይ መሠረታዊ የሙግት መርሆዎችን ከሕግና ፍልስፍና አንጻር ያለመረዳት ነው። ተሟጋች ማህበረሰብ (Litigant society) ቢኖረንም እውነት እና እውቀትን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የመረዳት ችግር አለብን። ይህንንም መሰረታዊ የሙግት ችግር ለመፈታትና መንገድ ለማመላከት የተጻፈ መጽሐፍ ነው"ብሏል።
"የማስረዳት ሸክም" መጽሐፍ በሰባት ምዕራፍ የተከፈለ ሲሆን በ225 ገፆች የተቀነበበ መጽሐፍ ነው።
በ400 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።በጃፋር፣ሀሁ እና እነሆ መጻሕፍት መደብሮችም ይገኛል ተብሏል።
የህግ ባለሞያው እና ደራሲ ዳዊት በዛብህ አስቀድሞ የሕግ ፍልስፍና፣ ኢትዮጵያ ሥነ ሕግ የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።
ለተጨማሪው: @Firtunamedia

📍 የሥነጽሑፍ ውይይት
የጁፒተር ብራና የንባብ ክበብ አባላት በአንጋፋው ደራሲ ፍቅርማርቆስ ደስታ "የሚሳም ተራራ" መጽሐፍ ላይ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:45 እስከ 12:00 በጁፒተር ሆቴል ውስጥ ሥነጽሑፋዊ ውይይት ያካሄዳሉ።
ለተጨማሪው: @firtunamedia
የጁፒተር ብራና የንባብ ክበብ አባላት በአንጋፋው ደራሲ ፍቅርማርቆስ ደስታ "የሚሳም ተራራ" መጽሐፍ ላይ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:45 እስከ 12:00 በጁፒተር ሆቴል ውስጥ ሥነጽሑፋዊ ውይይት ያካሄዳሉ።
ለተጨማሪው: @firtunamedia
ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ በጋራ የተሰሩት ገሚስ አልበም ዛሬ ይመረቃል
ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ በጋራ የተሰሩት "አዲስ ቀለም" የተሰኘ ገሚስ አልበም ዛሬ ሐምሌ 18 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ቦሌ ዓለም ሲኒማ አካባቢ በሚገኘው "The Jungle" ውስጥ እንደሚመረቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።የዚህ ገሚስ አልበም ምርቃት መግቢያ በነፃ ተብሏል።
"አዲስ ቀለም" ገሚስ አልበም በውስጡ ምንድነው ፣ ኤሌክትሪክ፣ ማዕዘን፣ተው ተው፣አንድ ሰሞን የተሰኙ አምስት ሙዚቃዎችን የያዘ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
የገሚስ አልበሙ ግጥም ፣ ዜማ፣ እንዲሁም ከሙዚቃው ቅንብር እስከ ማስተሪንጉ ድረስ በያምሉ ሞላ ተሰርቷል።
በተጨማሪም በከበሮ አገረሰላም ሻፊ ፣ በመሰንቆ ሀዲንቆ፣በክራራ ፋሲካ ኃይሉ ተሳትፈዋል።
"አዲስ ቀለም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና የሙዚቃ አቀናባሪው ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ የተጣምሩበት ገሚስ(EP) የሙዚቃ አልበም በዩቲዩብ እና ስፖቲፋይ መተግበሪያዎች በኩል ባሳለፍነው አርብ እንደተለቀቀ ይታወሳል።

"ጥቁር አደይ" ፊልም በሲኒማ ቤት ሊታይ ነው
"ጥቁር አደይ" ፊልም ለተወሰነ ጊዜ ከነገ ሐምሌ 19 2016 ዓ.ም ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ብቻ ለእይታ ሊቀርብ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"ፊልሙ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የፊልም ሽልማቶች ላይ እጩ ሆኖ እንዲቀረብ የግድ ሲኒማ ቤት መታየት አለበት።ስለዚህም ከሐምሌ 19 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ብቻ ለተወሰነ ጊዜ ለእይታ ይበቃል"ሲል ተዋናይ ነብዩ እንድሪስ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግሯል።
በፊልሙ ላይ ኤደን አይሸሹም፣ካሣሁን ፍስሐ (ማንዴላ)፣ናታን ጌታቸው፣ነቢዩ እንድሪስን ጨምሮ ከ186 በላይ ተዋናያን ተሳትፈውበታል።
"ጥቁር አደይ" ፊልም አንድ ሰዓት ከሐምሳ ደቂቃ ረዝመት ያለው ሲሆን ከ6.7 ሚሊየን ብር በላይ ውጪ እንደወጣበት ተነግሯል።ሦስት ዓመታትን የፈጀው ፊልሙ 1 ሰዓት ከ51 ደቂቃ ርዝመት ያለው ነው ተብሏል።
ፊልሙ ከአገር ውጪ እንደተመለሰ በኔትፍሊክስ እና አፕል የፊልም መተግበሪያዎች እንደሚሰራጭ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
በደራሲ እና ዳይሬክተር ፍፁም ካሣሁን የተሰራው "ጥቁር አደይ" ፊልም ሐምሌ 10 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

መቅደስ ፀጋዬን ምን መጠየቅ ይፈልጋሉ?
በመጪው ዝግጅታችን ተወዳጇን አርቲስት መቅደስ ፀጋዬን በእንግድነት በ አሜሪካን ኢምባሲ የምንጋብዝ ሲሆን የመድረኩ አንድ አካል ይሆኑ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ጋብዘነዎታል ።
ስለ ፊልም ፣ እንዲሁም የሕይዎት ዘይቤዋ ሙያዊ የሆኑ ጥያቄዎችን መጠየቅ የምትፈልጉ ከዚህ በታች ኮሜንት /ሀሳብ/ መስጫው ላይ በማስፈር የመድረኩ አካል ይሁኑ!
ለአዳዲስ መረጃዎች ሶሻል ሚዲያዎቻችንን ይከታተሉ.
@prestigeaddis
@firtunamedia

📌በእረፍት ቀንዎ ፊልም ይመልከቱ !
እነዚህ አራት የፊልም ማሳያዎች(ሲኒማ ቤቶች) ዛሬን ጨምሮ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት እነዚህን ፊልሞች ለተመልካቾች ያቀርባሉ: ምስሎቹን ይመልከቱ።
የሲኒማ ቤቶቹ አድራሻ:
✔️ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ : ጋስት ሲኒማ
✔️ለም ሆቴል አካባቢ: ቫምዳስ ሲኒማ
✔️ጉርድ ሾላ አካባቢ : ሴንቸሪ ሲኒማ
✔️ቦሌ አካባቢ : ዓለም ሲኒማ
መልካም የእረፍት ቀናት ይሁንላችሁ !
ለተጨማሪው :@Firtunamedia

📌የደራሲ ሄኖክ በቀለ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
ከዚህ ቀደም "ሀገር ያጣ ሞት" በተሰኘው የልቦለድ መጽሐፉ የምናውቀው ደራሲ ሄኖክ በቀለ "ይናፍቀኛል" የተሰኘ የግጥም ስብስቦች መጽሐፍ ዛሬ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን አቅርቧል።
"ይናፍቀኛል" የተሰኘው የግጥም መጽሐፉ 88 የግጥም ስብስቦችን የያዘ ሲሆን በ128 ገፆች ተቀንብቦ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለንባብ በቅቷል።
መጽሐፉን ለማዘዝ የምትፈልጉ ከሆነ በዚህኛው የቴሌግራም አድራሻ https://www.tg-me.com/ynafkegnal ማዘዝ እንደምትችሉ ተገልጿል።
ለተጨማሪው :@firtunamedia

📌የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ አዲስ መጽሐፍ
የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ " ሲ ጥ ል" የተሰኘ ረጅም ልቦለድ አዲስ መጽሐፍ ሐምሌ 27 2016 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከደራሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የሚከተለውን ብሏል"ሲ ጥ ል" የተሰኘ ረጅም ልቦለዴን ከሐምሌ 27/2016 ጀምሮ ገበያ ላይ ይውላል::
አሳታሚው ዋልያ መጻሕፍት ሲሆን በመጽሐፉ ጀርባም የሚከተለው ጽሁፍ ሰፍሮበታል::
ከዚህ ቀደም፣ ‹ዛጎል›፣ ‹ደርሶ መልስ›፣ ‹እምቢታ (የቃቄ ወርድወት)› እና ‹ምሳሌ› በተሰኙ ረጃጅም ልቦለዶቹ የምታውቁት፤ በጭብጥ አመራረጡና በአጻጻፍ ስልቱ የተወዳጃችሁት እንዳለጌታ ከበደ፣ አሁን ደግሞ ‹ሲጥል› የተሰኘ ልቦለድ አበርክቶልናል፡፡
‹ሲጥል› የመንገደኞች ታሪክ ነው፤ መንገደኞቹ ለየጉዳዮቻቸው ከቤታቸው ወጥተው አንድ ላይ ቢሳፈሩም፣ በአንድ ባልታሰበ ሰበብ አብረው የሚሰነብቱበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ መንገደኞቹ፣ የየራሳቸው የሕይወት ፍልስፍና እና መርሆ ያላቸው ናቸው፡፡ እናም፣ በረገጡት ሥፍራ እንግዳ የሚሆኑት እነሱ ብቻ አይሆኑም - ሃሳቦቻቸውም ጭምር እንጂ፡፡"
" ‹ሲጥል› እንደ ከዚህ ቀደም የእንዳለጌታ መጻሕፍት ከራሳችን ጋር የሚያጨዋውቱ፣ ለሙግትም የሚጋብዙ ሃሳቦች የተስተናገዱበት ኪናዊ ማዕድ ነው፡፡ የድኅረ ዘመናዊ ደራስያንን የአጻጻፍ መንገድ በከፊል ተከትሎ፣ የትረካ ስልቱን ደግሞ እንደ ጃዝ ሙዚቃ አድርጎታል፡፡"

📌“ናዋዥ” የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ
በደራሲ እያዩ ዳኛው የተሰናዳውና “ናዋዥ” የተሰኘው አዲስ የግለ ታሪክ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በዋናነት በደራሲው የግል ህይወት ላይ የሚያጠነጥን ቢሆንም፤ ኢትዮጵያዊያን በሱዳንና በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚያደርጉትን አስከፊና አስቸጋሪ የስደት ህይወት የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡
ነዋሪነቱን በጀርመን ያደረገው ደራሲ እያዩ ዳኛው፤ መፅሐፉ ከደቡብ ጎንደር ክምር ድንጋይ እስከ ጣሊያን የወደብ ከተማ ትራፓኒ የዘለቀውን የስደትና የውጣ ውረድ ጉዞ የሚዳስስ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡
“ናዋዥ”፤ደራሲው ልጅነቱን የአፍላ ወጣትነቱን፣ የኢትዮጵያውያንን የስደት ኑሮ፣ በሱዳንና በሰሃራ በረሃ ለማቋረጥ ስደተኞች የሚከፍሉትን መስዋዕትነት እንዲሁም በመንግሥት አልባዋ ሊቢያ የነበረውን ኑሮና በሜድትራንያን ባህር የሚያጋጥምን ፈተና ያስቃኛል፡፡
በ470 ገፅ የተቀነበበው “ናዋዥ”፤ የግለ ታሪክ መፅሐፍ በ500 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
📍መረጃው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው

በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

Forwarded from Prestige Addis
Beyond the Screen: A Special Event with Mekdes Tsegaye
Join us for an unforgettable afternoon with the legendary Mekdes Tsegaye, one of Ethiopia's most celebrated artists!
📅 Date: Tuesday, July 30
⏰ Time: 2 PM (8:00 PM Ethiopian Time)
📍 Location: U.S. Embassy, Addis Ababa
Please remember to bring your ID and arrive on time, as seats are limited and reserved. Secure your spot now by registering at the link below and be a part of this incredible experience! Don’t miss out on this unique opportunity to experience the magic of Mekdes Tsegaye live!
📋 Register Here: https://lnkd.in/eRwjBt7H

ሰላም እንደምን አላችሁ !
በየሁለት ሳምንቱ ተወዳጅ ዝግጅቱን ይዞላችሁ የሚቀርበዉ ፕርስቲጅ አዲስ ፤ ዛሬም እጅግ ተወዳጅ እና አንጋፋ የፊልም ባለሙያ የሆነችው አርቲስት መቅደስ ፀጋዬን ጋብዟል::
መቅደስ የሥራ እና የህይወት ተሞክሮዋን የምታካፍለን ሲሆን ከወዳጅ እና ድናቂዎቿ ለሚቀርቡላትን ጥያቄዎችም የፊታችን ነገ ማክሰኞ ሀምሌ 23 ,2016 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል።
በዕለቱ የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃ-ግብር ይኖራል::
ፕርስቲጅ አዲስ ከ መቅደስ ፀጋዬ ጋር አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ እንድታደርጉ ይጋብዛል።
አድራሻ ፡ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 ( ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )
ሰዓት- 8:00 🕘
⌚️ 🎯 ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩ። ⏰
መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ 🪪
📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱️
https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

የኢቢኤስ መዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጁ ትንሳኤ ብርሃን በ1 ሚሊየን ብር የባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ አምባሳደር ሆነ
ባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት (Balli Food Processing) ለሚያመርታቸው በማር ወለላ የተቀመመ QQ yammy snack እና በኦቾሎኒ ጣዕም ለሚያመርተው QQ coated peanut የኢቢኤስ የመዝናኛ እና የቁምነገር አዘጋጅ የሆነውን ትንሳኤ ብርሃንን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በዛርው እለት ሾሟል
ባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ (Balli Food Processing) የሚያመርታቸው በማር ወለላ የተቀመመ QQ yammy snack እና በኦቾሎኒ ጣዕም የሚያመርተው QQ coated peanut ሕጻናት፣ ወጣቶች እና አዋቂዎች በየትኛውም ሰዓት እና ሁኔታ እያጣጣሙ ዘና ብለው የሚመገቧቸው ጣፋች ምግቦች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ የብራንድ አምባሳደር የሥራ ስምምነት ፊርማ ለ1 አመት እንደሚቆይ ተነግሯል
ተቋሙ እነዚህን ጣፋጭ ምግቦች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በከፍተኛ ጥራት ለገበያ እንደሚያቀርብ የተገለፀ ሲሆን ይህን ምርት ለማስተዋወቅ የኢቢኤስ የመዝናኛ እና የቁምነገር አዘጋጁ ትንሳኤ ብርሃን በአምባሳደርነት ተመርጧል!!
ባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ (Balli Food Processing) ከተመሰረተ 4 አመትን ያስቆጠረ ሲሆን በማር ወለላ የተቀመመ QQ yammy snack እና በኦቾሎኒ ጣዕም የሚያመርተው QQ coated peanut በማምረት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው
(በድሬ ትዩብ ሪፖርተር)

📌የድምጻዊ አብዱ ኪያር "ፓፓፓ" የሙዚቃ አልበም በዩቲዩብ በተለቀቀ አንድ ወር ውስጥ ብቻ ከ18 ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ በላይ ተመልካቾችን እንዳገኘ ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ከአሰራጨው መረጃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ለአድናቂዎቹና አድማጮቹ የምስጋና መልዕክቱን አስተላልፏል።
በአልበሙ ላይ በቅንብር ስማገኘሁ ሳሙኤል፣ ኪሩቤል ተስፋዬ፣ ካሙዙ ካሳ እና ዳዊት ቦስኮ ተሳትፈዋል። ሚክሲንጉን የሰሩት ስማገኘሁ ሳሙኤል እና ኪሩቤል ተስፋዬ ሲሆኑ ማስተሪንግ ደግሞ በአበጋዝ ክብረወርቅ ተሰርቷል።
"ፓፓፓ" የሙዚቃ አልበም ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ነበር ለአድማጮች የደረሰው።