Telegram Web Link
ሙዚቀኛው ሞቶ ተገኘ!

የቀድሞ ሮሀ ባንድ ሳክስፎኒስቱ በመኖሪያ ቤቱ ሞቶ ተገኘ

ከቀደምት ሮሀ ባንድ አባላት መካከል ተጠቃሹ አርቲስት ስምኦን ሊባኖስ በመኖሪያ ቤቱ ሕይወቱ አልፎ እንደተገኘ ጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ የአርቲስቱን የቀድሞ ስራ ባልደረባና ጓደኛ ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

" ከደቂቃዎች በፊት ጋሽ ዳዊት ይፍሩ እንዲህ አለኝ.. "እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነን። የዛን ዘመን የሮሃ ባንድ ሳክስፎኒስት የቀድሞ የስራ ባልደረባዬና ጓደኛዬ የነበረው አርቲስት ስሞኦን ሊባኖስ ( ዮናስ ደገፉ) ዛሬ ህንድ ኢንባሲ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።
ለምርመራው የአዲስ አበባ ፖሊስ አስክሬኑን ወስዷል"አለኝ።

ግን ሌላው የሚያሳዝነው ቤተሰቦቹን ማግኘት አልተቻለም ። እና ቤተሰቡ ወይም ወዳጆቹ አዲስ አበባ ፖሊስ መጠየቅ ትችላላችሁ። " ሲል መረጃውን አጋርቷል።



ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ቤተሰብ ይሁኑ።

"""""""""""***""""""""""
@firtunamedia
አርቲስት ሰላም ተስፋዬ የፖፕላር ኤሌክትሮኒክስ ትሬዲንግ ብራንድ አምባሳደር ሆነች

አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ከፖፕላር ኤሌክትሮኒክስ ትሬዲንግ ጋር የብራንድ አምባሳደርነት የስራ ውል ስምምነት ዛሬ ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ተፈራርማለች።

አርቲስት ሰላም ተስፋዬ በፖፕላር ኤሌክትሮኒክስ ትሬዲንግ ለቴሌቪዥን፤ ቢል ቦርድ እና ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎችን የምትሰራ ይሆናል።

ፖፕላር ኤሌክትሮኒክስ ትሬዲንግ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ከውጭ በማስመጣት የሚታወቅ ድርጅት ሲሆን በዛሬው እለትም አዲስ በከፈተው ሾው ሩም አርቲስት ሰላም ተስፋዬን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።

የአርቲስቷ የአምባሳደርነት ስምምነት ለአንድ ዓመት የሚቆይ ይሆናል።

@firtunamedia
የፈረጃ ፊልም ቀረፃ ሚያዝያ 20 ይጀምራል

በህዝብ መዋጮ የሚሰራዉና በኢትዮጵያ የመጀመርያው (Crowdfunding) ፊልም የሆነው ፈረጃ የተሰኘዉ የቦክስ ፊልም ከብዙ ዝግጅትና አድካሚ ጉዞ በኋላ የታሰበዉ በጀት ባይሞላም ቀረፃዉ ሚያዝያ 20 ሊጀመር ነዉ።

አርቲስት ሄኖክ ወንድሙ ሂደቱ ከባድ እንደነበር ተናግሮ የቦክስ ፊልም እንደመሆኑ ለቀረፃዉ ብዙ ሰው እንደሚያስፈልግና በተሳትፎ እንዲያግዙት ወጣቱን ኃይል ጠይቋል።

በገንዘብና በሀሳብ ላገዙት ሰዎች በሙሉ ትልቅ ክብርና ምስጋናዉንም አቅርቧል።

@firtunamedia
ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ከእስር ተፈታ

በእጮኛው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ እስር ቤት የቆየው ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሶስት ወራት ከተጠጋ ጊዜ በኋላ ከእስር ቤት መውጣቱን ፋስት መረጃ አስነብቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ የህግ ባለሙያው አበባየው ጌታ "ከአርቲስት አንዷለም ጎሳ ጠበቃ ጋር በስልክ ባደረኩት ንግግር አርቲስቱ ከእስር የመፈታቱ ዜና እውነት መሆኑን አረጋግጦልኛል" ሲል ጽፏል።

@firtunamedia
📌የአንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ የ60ኛ ዓመት የልደት በዓል ነገ ቅዳሜ በድምቀት ሊከበር ነው

ከጦር ሃይሎች ራድዮ አስከ ኢትዮጵያ ሬድዮ ከቅዳሜ መዝናኛ፣ ከነፃ ፕሬስ እስከ አርትስ ቲቪ፣ ከ97.1 ራዲዮ እስከ ሸገር ኤፍ ኤም ድረስ ተወዳጅ ሥራዎቹን ያቀረበው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከ11:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ በሚደረግ የእራት ፕርግራም የልደት በዓሉ ይከበራል ተብሏል።

በሃይሌ ግራንድ ሆቴል በሚከበረው የደረጀ የልደት በዓል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን፣ የልደት በዓሉን ለማድመቅ የሙዚቃ ዝግጅትም እንደተሰናዳ ተገልጿል።

@firtunamedia
ሰላም እንደምን አላችሁ?

በሁለተኛው የcreative lab ዝግጅታችን  ደራሲ እና ዳይሬክተር ሰማኝጌታ አይችሉህምን ይዘንላችሁ ቀርበናል። 

በዚህ ስልጠና ሰማኝጌታ  ስለ "ልጄስ?" ተከታታይ ድራማ አፃፃፍ እንዲሁም ዳይሬክቲንግ ጥበብን ያካፍላናል። ይህንን ተወዳጅ ደራሲ እና ዳይሬክተር ልምዱን እና መርሆቹን የሚያካፍልበት መድረክ ላይ እንዲታደሙ ተጋብዘዋል።

ጀማሪ የስክሪፕት ፀሀፊዎች ዳይሬክተሮች በፊልሙ አለም ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ወጣት ጀማሪ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው።


በዕለቱ እጅግ ተወዳጅነት ያተረፈውን  የተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ   "ልጄስ?" ፓይለት ኤፒሶድ እናቀርባለን። በዚህም ከፊልሙ ጀርባ ያለውን ራዕይ እንዲሁም የስራሂደት
በተመለከተ ውይይት ይኖራል።

📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 (  ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

📅 ቀን: ሃምሌ 8 ፣ 2017

🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00 

🎟 መግብያ: ነፃ

አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር

በ ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ኢንስታግራም ገፃችንን ፎሎ ማድረግ እንዳይረሱ


📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

@prestigeaddis
ነፃ የሞዴሊንግ እስኮላርሺፕ ዕድል

ሞዴል መሆን ይፈልጋሉ ?

ፕሪስቴጅ አዲስ ከ ሌጋሲ ሞዴሊንግ ኤጀንሲ ጋር በጋራ በመሆን ነፃ የ ሞዴሊንግ ስልጠና ለ እናንተ ይዞላችሁ መቷል።

የዚህ እድል ተካፋይ መሆን የምትፈልጉ ከታች ያለውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባችኋል።


የፕሪስቴጅ አዲስ እና ሌጋሲ ሞዴሊንግ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ቻናል ፎሎ ያድርጉ ።

ይሄንን ፖስት የተደረገውን ሼር በማድረግ ኢንስታግራም ስቶሪ ላይ ያጋሩ ፣ ሁለቱንም ቻናሎች ታግ ያድርጉ ።

ኮሜንት ላይ ፍላጎት ያላቸውን ሶስት ሰዎችን ታግ ያድርጉ።

በ ኮሜንት ሃሳብ መስጫ ላይ ሌጋሲ ሞዴሊንግ መማር ለምን እንደምትፈልጉ እና ይሄንን እድል ላንቺ / ላንተ ለምን እድሉ መሰጠት እንዳለበት ግለፅ/ጪ ።

ይሄ እድል ከ 16 ዓመት እስከ 30 ዓመት ለሆኑት ክፍት ነው።

ምንም አይነት የሞዴሊንግ ልምድ አይጠይቅም - ለጀማሪዎች ክፍት ነው ።

#ፕሪስቴጅአዲስ እና #ሌጋሲሞዴኒንግ ሃሽታጎችን ይጠቀሙ ።

የዚህ እድል ተካፋይ ለመሆን የ @prestigeaddis ኢንስታግራም ገፅ ላይ በመግባት ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት ማሟላት መሳተፍ ይችላሉ።

መልካም ዕድል

@prestigeaddis
Forwarded from Prestige Addis
ሰላም እንደምን አላችሁ?

በ አሁኑ የ CREATOR LAB ዝግጅታችን ላይ የቴያትር እና የፊልም ደራሲ እና አዘጋጅ የሆነችው መዓዛ ወርቁን ይዘንላችሁ ቀርበናል። 

በዚህ ዝግጅት ላይ ሰለ ድርሰት እና ዝግጅት እንዲሁም የራሷን የሂዎት ተሞክሮ ለ እናንተ ታካፍላለች። ሰለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

ደራሲ እና አዘጋጅ የመሆን ፍላጎት ያላችሁ፤ እንዲሁም በ ሙያው ላይ ልምድ ያላችሁ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው።


📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 (  ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

📅 ቀን: ሰኞ - ሃምሌ 28 ፣ 2017

🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00 

🎟 መግብያ: ነፃ

አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር

በ ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ኢንስታግራም ገፃችንን ፎሎ ማድረግ እንዳይረሱ


📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

@prestigeaddis
Forwarded from Prestige Addis
CREATOR LAB with Abenezer Alemayehu

We’re thrilled to welcome Abenezer Alemayehu — AI filmmaker and creative visionary — as our next guest for Creator Lab!

In this exciting session, Abenezer will explore the world of AI Filmmaking, showing how generative AI, cinematic storytelling, and African cultural narratives come together to shape the future of film.

Whether you’re a filmmaker, digital creator, or just curious about the role of AI in storytelling, this is your chance to gain insights from a true innovator at the crossroads of culture and technology.

📅 Date: Monday, August 11, 2025
🕙 Time: 10:00 PM (Ethiopian Time)
💻 Virtual Event – Join from anywhere!

Want to attend in person?
📍 Location: Col. John C. Robinson American Corner,
Inside St. Mary’s University Graduate Campus

🎟️ Entry: FREE

Presented by: Prestige Addis
In collaboration with: American Center

Register now: https://bit.ly/Cjcrac-Prestigeaifilm

Stay connected: @PrestigeAddis

Let’s explore the future of storytelling — together.
2025/09/17 22:50:57
Back to Top
HTML Embed Code: