Telegram Web Link
#ፀሃይና_ጨረቃዬ
.
.
.
በራሷ ልክ ለምታውቀኝ የኔን ናፍቆት ያቺን ድሃ፣
ላንዱ ልቤ የልቡ ራ'ብ ሆና ብትፈልቅ የፍቅር ውሃ።
ነይ ብሏታል ሰርክ ናፍቆ እዝነ ነፍሴ ተመልክቷት፣
ከሺ ልባም ከሴት መሃል ከቀይ እንቁ እሷን ሽቷት።

ትመጣለች እኔን ብላ፤
ትመጣለች ሀሳብ ጥላ፤
የምታውቀው ሩህሩህ መላዕክ በፍቅር ዘንግ እየመራት፣
መቼም እሱ ያውቅበታል፤
ከመጨከን ሳይቀላቅል ልቤ መሃል እሷን 'ሰራት ።

ከቆምኩበት ከዚያው ስፍራ፤
ባክሽ ፍጠኝ ድረሽ እያልኩ ከራሴ ጋር ሳጉረመርም፣
ከሀሳብ ባህር የወደቀን ብኩን እኔን ቆሜ ሳርም።
መጣችልኝ ያይኔ አበባ መጣችልኝ የልቤ ሰው፣
እንባና ሳግ ወንድ አንጀቴን ቁጡ ፊቴን ሳቅ ወረሰው።
( እኔ የምልሽ ? መቼ ነው ግን፤ )
( ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ከጥጋብ ደጅ የምደርሰው ? )
እንጃ'ባቴ !!!!!

ልብላ አላለች ወይ ልጠጣ፤
ልውረድ የለም ወይም ልወጣ፤
ናፍቆት ሆኖ የሷም ረሃብ ካለም ሁሉ የተለየ፤
ከወንዶቹ አስበልጦ ከህዝበ አዳም እኔን ያለ።
ፍቅር  አይኗን ከደነችው፤
ጠፍር አልጋ መሃሉ ላይ ግራ እጄን ተንተርሳው፣
ሙቅ ትንፋሿ እፍፍ ሲለኝ ወንድ አካሌ ነፍሴን ረሳው።

አጀብ መቼም ያየሁትን፤
ስትነካካኝ በጣቶቿ ስትዳብሰኝ በመዳፏ፣
ንጉስ መሆን የዛን'ለት "የኔ አባት" ሲለኝ አፏ።
በነፍሷ ጫፍ ምኑ ዳሬን የቱ ጋር ነው የነካችኝ፣
የተጣላሁ ከራሴ ጋር በምን ብልሃት አስማማችኝ ?

በአርምሞ በፀጥታ፤
አይኗን አየሁ ሽፋሽፍቷን፤
ተመለከትኩ የነፍሷን ሀቅ ተኝታለች አለም ረስታ፣
አንገቴ ስር ካገኘችው ስስ ህይወቷን ተጠግታ።
የዛን'ለታ........
እያለ
እያለ
እያለ "ልሂድ" አለኝ፤
እኛን ሲያዩ የፈገጉ ሰማይ ምድር ተላቀቁ፤
በመሄድ ውስጥ ተከርችመው ነገን ሊሉ ሲታረቁ።
እቅፍ ብርሃን ፈነጠቀ ከአፅናፍ አፅናፍ ተዘረጋ፣
ፀሃይና ጨረቃዬን፤
በአክናዴ እንዳቀፍኳት ሆነ አዲስ ቀን ሌቱ ነጋ።
.
.
.
"አይኗን ገልጣ አይኔን አየች ከኔ ማዶ የራሷን ሀቅ፣
ፈገግ ብላ አዋሰችኝ የሰጧትን የ'ግዜሯን ሳቅ።"
                     
            ስትችልበት !!!!!!


ዓቢይ ( @abiye12 )




@getem
@getem
@getem
እሱና እሷ

እሱና እሷ ከአንድ ቀን እይታ፣
ወዳጅነት ፈጥረው ፍቅር ተገንብታ፣
ተፈቃቅረው ከርመው ዓመታትን ቆጥረው፣
ጎጆ ለመቀለስ በአንድ ለመጠቅለል ሽማግሌ ልከው፣
ህይወት በአዲስ መልኩ ተጀመረ ይኸው።

የአንድ ቀን እይታ ዛሬ ፍሬ አፍርቶ፣
ሙሽሪት ፀንሳ ቤተሰብ መስርቶ፣
ሁለትነት ቀርቶ በዝተው ተበራክተው፣
ዘር የሚያስቀጥል አዲስ ትውልድ ፈጥረው፣
ባል አክብሮ ሚስቱን ሚስት ለባል ተገዝታ፣
ፍቅርና መቻቻል በእነሱ ላይ ታይታ፣
ለማየት በቅተናል ፍቅራቸው አፍርታ።

በሳምሪ የዝኑ ልጅ

@getem
@getem
@getem
ያደረግሽኝ በዝቶ.... ልቤን ያሳረረው
ጩኸቴን እንዳፍን
ምኑን ቀባብቼ ምኑን ልሞሽረው??!

ወልውዬ ሰጥቼሽ አፈር ካለበሽው
ጤነኛውን ልቤን መርዝ ካቀመሽው
በምን አማርኛ ትህትናን ጠልፌ
እንደው እንዲቀልሽ እንዴት ልበል ፅፌ??!!

አንቺ ኮ አታፍሪም ከበደልሽ በላይ
በጥሩ አማርኛ ስምሽ ገኖ ቢታይ
እንዳ-ላ-ጠፋ እንዳ-ል-በደለ
በከንቱ ንፁህ ........ እንዳልገደለ
ስጠብቂ ሳይ
                   ...... ያመኛል ብትይ!!!!

ነበረኝ ጥሩ ቃል ላንቺ ያላነሰ
ከልብ የተቀዳ ስንቱን የቦነሰ
የገፋሽው ድሮ .... ቀለለብኝ ያልሽኝ
ነበር አማርኛ ንቀሽ ያልሰማሽኝ
ከቃሉ ያደረ ... ፍፁም የከበረ
ብሰጥሽ ንፁህ ልብ ....... ያኔ ተሰበረ !!
እንደሞኝ ቆጥረሽው የተግባሬን ነገር
ባልኩት መገኘቴ ላንቺ ቀልድ ነበር

ታዲያ.............
ተመልሰሽ ዛሬ
ለምን ትይኛለሽ ተነካብኝ ክብሬ
ያኔ
አቅቶኝ ስቀጣ እያየሽኝ መራቅ
እንዴት ይገርምሻል
ደስታዬ ሲያድንሽ ፡ ሲሆንብሽ ጭራቅ!



ig & tiktok @be_Olyon


       ✍️ Olyon
                       
           
              አስተያየት (@be_Olyon)



     @getem
                   @getem
                                  @getem
               
ማያልፍ የመሰለኝ ዳምኖ ህይዎቴ
ባዘነብኩት እንባ ታጥቦ ማንነቴ
ግርዶሹ በርትቶ ነገየን ጋርዶብኝ
ፍፁም አንዳልጓጓ ህመም በርትቶብኝ
ዛሬ ነገ እያልኩኝ ሞቴን ሲጠባበቅ
ህመሜን ሳዳምጥ ስሜቶቼን ሳረቅ
.
.
.
         መኖር ማለት ስቃይ
         መኖር ምለት ህመም
         መኖር ማለት ጭንቀት
         መኖር ማለት ድካም....

ወደ ተስፋ መንደር እልፍ ጊዜ ባመራ
የ እድሌን ልሻማ ከ እኩዮቼ ጋራ
ብፈልግ... ብጠብቅ ድርሻ የለኝ ሁኖ
ጠብታ እንኳን ሳይቀር ከ እኔነቴ ተኖ
ፀሐይ የለኝ ሁና ሕይዎቴ ዳምኖ
.
.
.
       ትላንት በመኖሬ ተስፋ እንኳን ሳይኖረኝ
       ምንም ያህል ባዝን የሚያልፍ ባይመስለኝ
       ቀን እየቆጠረ ቀን እየጨመረ
       የደመናው ጥቁረት መጠኑ ቀንሶ
       የስቃይ ዉርጅብኝ ከነበረው አንሶ
       ከ ሕይወቴ ጠፋ ቀስ በቀስ ጨርሶ...
.
.
.
የ ፀሐይ ዉበቷ
የፀሐይ ድምቀቷ
የዉበት ፍካቷ
ዛሬ ላይ ብሸፈን
ደመናው ሲገፈፍ ወደጎን ሲበተን....
.
.
.
       ህመም ብርድ ሁኖ ያገረጣው ትናንት
       ተንፏቆ እየዳሀ ዛሬን በመጠጋት
       አንድ ቀን ልጨምር ብዬ በመኖሬ
       ተስፋ ፀሐይ ሁኖ ከች አለልኝ ዛሬ!!
           
           📆ሚያዚያ 25 - 2016
                ዘይድ ሁሴን

@getem
@getem
@paappii
በጥራት የተዘጋጀ   መሳያ ሸራ ይዘዙ
የዋጋ ለውጥ
20 x 20 cm ,,,200 ብር
25x25 cm. ..200 ብር
20*40cm.....300 ብር
30 x30  cm ....300 ብር
30*40cm ...300
30*60....350
40*80...500
40x 50 cm....400 ብር
40 x60 cm... 400 ብር
50 x60 cm....450 ብር
50 x70cm....450 ብር
60*80cm...550 ብር
100*60cm..750ብር
80*100...800 ብር
100*100cm  850ብር
80*120...900ብር
100*120....1100 ብር

Canvasochin እና የ ስዕል ማስዋቢያ frame ይዘዙን በ ጥራት እንሰራለን
ለበለጠ መረጃ በ 0934039346 ይደውሉልን
የቀረው

ቤት ሙሉ ዕቃ
ግቢ ሙሉ አበባ
ጠፈር ሙሉ ሰማይ
ተስፋን የተቀባ

ወንበሩ ሁሉ ሰው
ጠረጴዛው ምግብ
ቀኑ ሁሉ ድግስ
ሆድ ሁሉ ሲጠግብ

አፍ ሁሉ ፈገግታ
እጅም የሰላምታ
በጊዜ እሽሩሩ
ስቃይም ሲረታ

በምቾቱ ጭጋግ
ሲሸፈን ያለፈው
እንዳይከፈት አርጎ
ልቤን የቆለፈው

አንድ አለ
የረጋ ባዶነት
የቢሆን ጥያቄ
የምናልባት ውጋት!

ቅር ቅር የሚያሰኝ
በጩኸቶች ሁሉ ፤ ዝምታን ሚቀኝ
ከሳቅ የሚያርቀኝ
ያፈራሁት ሁሉ ፤ አልዋጥ እንዲለኝ
ምን ይሆን ያነቀኝ?

አምናን ለፍርሀት ፤ ትላንትን ለኩራት
የገበርኳትን ልብ ፤ ብለምን ብጠራት
ካስቀመጥኳት የለች ፤ ብፈልግ አጣኋት
እሷ ትሆን... መሰለኝ
ያዳፈንኩት እሳት ፤ እኔን አበሰለኝ
ሰም እና ወርቁንም ፤ ለይቶ አስተማረኝ።

አሁን የተረፈኝ...
በሞቀው ድባብ ውስጥ
ቀዝቀዝ ያለ እውነት
በፈካው ቀንም ላይ
ድብዝዝ ያለ እምነት

ድብዝዝ ያለ ተስፋ
በር በር እያየ አርቆ የጠፋ
በመጣው ስው ብዛት እጥፍ የተከፋ

ኮቴዋን የለየ እሷን የፈለጋት
የረጋ ባዶነት
የቢሆን ጥያቄ
የምናልባት ውጋት!!!



✍🏽✍🏽✍🏽... E.Z(@EZpoemandfiction)

@getem
@getem
@getem
አባቶች እናቶች
በፍቅር ተጋግዘው ፣ ያቆሙልን እውነት
በዘመን ጠልሽቶ...
ለእኛ ለልጆች ፣ ይመስለናል ተረት፡፡
።።።።።።
የኛ ትልቅ ችግር ፣ የኛ ትልቅ ህመም
"ተረት ተረት"ሲባል
መሰረት ሳንይዝ
"የመሰረት" ብሎ ፣" እሺ" እያሉ ማዝገም፡፡
።።።።።።፣
ተረት ተረት
"የመሰረት"
አንድ ሀገር ነበረች
"እሺ"
እምነትን ከፍቅር ፣ ገምዳ ያስተማረች፡፡
"እሺ"
አናም በዚች ሀገር...
ሙስሊሞች በእምነት ፣ መስጅድ ሲገነቡ
ክርስቲያኖች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ምሶሶ ሲያቀርቡ፡፡
"እሺ"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም በዚች ሀገር...
ክርስቲያኖች በምነት ፣ ቤተስኪያን ሲያንፁ
ሙስሊሞች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ጉልላት ሲቀርፁ፡፡
"እሺ"
እናም በዚ መልኩ ፣ ሲኖሩ ሰኖሩ
እንደተዋደዱ እንደተፋቀሩ
እንደተጋገዙ እንደተባበሩ
መሰረት እንድናይ...
አንዋር ከራጉኤል ፣ ተጎራብተው ቀሩ
"እሺ"
"እሺ" ማለት ጥሩ
መሰረት ሳይዙ ...
የመሰረት ብሎ ፣ መኖር ነው ችግሩ!!!
።።።።።

By Belay Bekele Weya

@getem
@getem
@paappii
( እግዚአብሔር ያመርራል .. )
=====================

ትዝ ይልሻል አይደል
ያኔ ሌላ ለምደሽ ስትሄጂ ትተሽኝ
በምጸት በውሸት ቃል
" ከኔ የተሻለች ሴት ይገባሀል " ያልሽኝ
ባይዋጥልኝም በዓለም የማፈቅረው
ካንቺ ሌላ እንዳለ ....
ውስጤን እየበላኝ አንጀቴ እያረረ
በየዋህ ልቡና .. መልሴ ' አሜን ' ነበረ

ታዲያ ዛሬ ሳያት ያሁኗ ወዳጄን
ቤቴን የምትሞላ ምታሞቀው ደጄን
ፍቅሯ ህሊናዬን ነፍሴን ሲያስደንቃት
ውልብ ይልብኛል የዛኔው ምርቃት

ለካ እምነት እስካለ ሁሉ ይቆጠራል
ሰው ገፍቶ የናቀውን እግዚአብሔር ያከብራል
ለካ ከሀሰት እጥፍ ... እውነት ሺ ያበራል
ሰው የቀለደውን እግዚአብሔር ያመርራል !!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
.............😇ህልሟ😇.............

ከደስታ በር ቆሜ
ወደእኔ መጣች ፤ ሳታልፈኝ አስቆምኳት
ጠየኳት

ምን ትፈልጊያለሽ ፤ ህልምሽን ንገሪኝ?
ትንሽ አመንትታ
መኪና ቤት አለች ፤ የቀደመን አይታ

ከዛም አለፈችኝ
ስትሄድ ሸኘኋት ፤ ዞራም አላየችኝ።

ከደስታ በር ቆሜ
ወደእኔ መጣች ፤ ሳታልፈኝ አስቆምኳት
ጠየኳት

ምን ትፈልጊያለሽ ፤ ህልምሽን ንገሪኝ
ትንሽ አመንትታ
ትዳር ከዛም ልጆች .... የቀደመን አይታ

ከዛም አለፈችኝ
ስትሄድ ሸኘኋት ፤ ዞራም አላየችኝ

ከደስታ በር ቆሜ
ወደእኔ መጣች

ደክማለች
መሮጡ ታክቷታል
ያፍላነት እሳቷ ፤ በጊዜ ተረቷል

ሳታልፈኝ አስቆምኳት
ጠየኳት

ምን ትፈልጊያለሽ
ህልምሽን ንገሪኝ?

ዝም አለችኝ ላፍታ ፤ አየችኝ በአንኩሮ
ከሳሁ ጠቆርኩ ፤ ልበን ደርሻለሁ ፤ የለሁም ዘንድሮ
የነፍሷ ጥሪ ፤ የመንፈሷ ለቅሶ ... ነበርኩ
ስጋዋ የከዳኝ ፤ በስሜት የታሰርኩ

አነባች ለአፍታ
በሀዘኗ እውነት ፤ እውር አይኗ በራ
ይሉኝታም ተረታ

ለአፍታ ህይወቷ ፤ ትላንት ለኖረችው
ሞተ ገደለችው
አነባች አዘነች ፤ ከዛም ቀበረችው።
ዳግም ተወለደች
እኔን ያዘችና ፤ አይኖቿን ጨፈነች።


በህይወት ሸራዋ ፤ እጇ ላይ ታች አለ
ልቧም ደም አነባ ፤ አለም ተነከረ
ማንም አላያትም
ዳኝነት ይሉኝታም ፤ ተኝተው ነበረ

ጊዜዋም ሲያበቃ
አይኗን ገልጣ ፤ ፈገግ አለች
መጨረሻም ህልሟን ሳለች

እሱም ውብ ነበር!


✍🏽✍🏽✍🏽... E.Z(@EZpoemandfiction)

@getem
@getem
@getem
ተምታቶብኝ አይደል
ሺህ ጊዜ ብመርጣት ... ሺህ ቦታ ልሰጣት
ረስቼ አይደል
የሷን አለመሙላት ...... ወዳጄ ነሽ ብላት
.............................. አቃለው ሲጎድላት!
መቼ ረስቼ
ምን ብታስቀይም ብዙ ብታስለፋኝ
እሷን ትቶ መሄድ ለኔ መቼ ጠፋኝ
.................... አቀለው ሲከፋኝ!
እንደሱ አይደለም
ብዙ ደጋግሜ ደስታዬን ልለቅም
ስንቴ ብርቃትም
ሲከፋኝ ነው እንጂ ሲደላኝ አላቅም!!
አይቻለውና
የምችለው መስሎኝ
ናፍቆቷ ሲቀጣኝ ምኞቴ ነጥሎኝ
ታምሚያለውና
ህይወቴ ሲጨልም ተስፋ ሲሄድ ጥሎኝ
............................... እረ ምኑን ቀሎኝ!!!
እድሌ ናት በቃ
ሁሌ ምታፈላኝ .... የልቤ ሞቅታ
ሁሌ የምታመኝ የነብሴ ስቅታ
ብትደላም ባትደላም
የኔ ገፅ ብቻውን ያለ'ሷ አይሞላም!
              

   
Follow my IG & Tiktok @be_Olyon

       ✍️ Olyon
                       
           
              አስተያየት (@be_Olyon)


     @getem
                   @getem
                                  @getem
የሞተ ፍቅር

ፍቅር ሲፈርስ
ከኮዳው ሲፈስ
ከጆንያ ሲበተን
ከገንዳው ላይ ሲተን
ፍቅርን አዬሁት
እንዳልተ መኘሁት


ውሀ እንዳጣ ተክል  መንምኖ
እንደ ሀምሌ ሰማይ  ዳምኖ
እንደ ወራጂ ውሀ ድፍርስ ብሎ
እንዳልመጣ ሁሉ  ተንበልብሎ
ጠራርጎ ሲያልፍ እሱም ያልቃል
ከታተመበት  ልብ ላይ ይፋቃል

ነፍስ የዘራው ነፍስ ሲያጣ
እያወዛ  ያደመቀው  ሲገረጣ
እርቆ ሊሄድ  ለሞት ዳና ያቃጥራል
ስንገድለው  ለነፍስ ውጭ ያጣጥራል
እንደዘበት ትዝታ ሆኖ ይቀራል

By kerim

@getem
@getem
@paappii
ከከፍታ የሚልቅ ዝቅታ
==============

የሰማይ ዳስ ተሰርቶላት፣
ማማለዱ ሆኖ ግብሯ
እመቤቲት የሁሉ እናት፣
የባሪያ ነው ንግግሯ
ሳይቸግራት ፈውስ መሆን፣
ፍምን ያህል አድሮ ሆዷ
በማነሷ ነው ማርያም፣
ከፍ ካሉት መወደዷ


ዘማርቆስ
28/07/2016
By GIZE

@getem
@getem
@getem
ገንፎ

ሀገሬስ ገንፎ ናት
በስልጣን ማንኪያቸው የሚቆራርሷት
ቂቤ ወሬያቸውን በርበሬ ስራቸው
ጨመር አርገውባት
እሷ ያዝኩት ስትል
የስጧትን ሁሉ አጣቅሰው አላውሰው
በዛ ስልጣን ማንኪያ በህብረት አብረው
ያውም ክብ ሰርተው
እንደ ጉድ ሚበሏት የሚጎራረሷት
ሀገሬ ለእነርሱ ገንፎ ብቻ እኮ ናት
@topazionnn
@getem
@getem
ያውቃል የልቦናን መልስ አለው በጊዜው
አያደርግ ይመስል ለምን ነው ትካዜው?
በእኛ ጊዜ ላይሆን የፈጣሪ መልሱ
ባለበት እስኪሰጥ አምናቹ ታገሱ

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@paappii
የአባይን ልጅ...

አባይ ተገድቦ
                  ሆኖ ከደጃፌ

ሠፊው ጣናም ሞልቶ
                    ሳለ ከበራፌ

አዋሽና ጊቤ
               ተከዜና ባሮ

ማግኘት እየቻልኩኝ
                    ከሀገሬ ጋሮ

በዚህ ከባድ ኑሮ
                 ሁሉን ነገር ትቼ

እኔ በጥም ብዛት
                አለውኝ ገርጥቼ

ከድፍን ሀገሩ አንዲት ውሀ አጣጭ
               ለራሴ አጥቼ::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
Audio
👆👆👆 አሪፍ ግጥም በአሪፍ አቀራረብ ተጋበዙልኝ::    
        
               በቃሉ ሹምዬ
                🎙 ያኔት
Editor: @begitimenawga


🤰መልካም የእናቶች ቀን

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

@getem
@getem
@getem
❤️አልጎደልኩም❤️

አንዲት ትንሽ አጥንት
ከጎኔ አንስቶ

አምላክ ህይወት ሰጠኝ
አንቺን ለኔ ሰርቶ

ምንም ብባዝንም
ለጎደለው ጎኔ

ሙሉ አርገሺኛል
ስትመጪ ወደኔ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
እንባማ ወንዝ ነው ያልፋል እንደዘበት
ቢያብሱት ይደርቃል አፅናኝ በሞላበት
ክፉ የውስጥ ነው የማይደርቅ በሽታ
እንባ የማይመልሰው ልብ ያዘነ ለታ!


   
Follow my IG & Tiktok @be_Olyon

       ✍️ Olyon
                       
           
              አስተያየት (@be_Olyon)


     @getem
                   @getem
                                  @getem
2024/05/15 05:17:00
Back to Top
HTML Embed Code: