Telegram Web Link
#ደብተራ_በቤተ_ክርስቲያን_እይታ
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
✍️ከአንዳንድ ሰዎች ጋር የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በተመለከተ ስንነጋገር ደብተራ የጻፈው ማለት ይቀናቸዋል🙆፡፡ ይሄ ንግግራቸው ከሁለት ስሕተቶች የመነጨ ነው፡፡ አንደኛው ስለ ደብተራ ካለማወቅ ሲሆን ሁለተኛው ስለ መጻሕፍቱ ካለመረዳት የሚመጣ ነው፡፡ #ደብተራ የሚለው ቃል ጥሬ ትርጉሙ #ድንኳን ማለት ነው፡፡ ይህም ቢሆን #ሐይመት ከሚለው ቃል ፍች ይለያል፡፡ #ሐይመት ለማንኛውም አገልግሎት የሚውለውን ድንኳን ሲያመለክት #ደብተራ ግን በዋናነት ለቤተ መቅደስነት የሚውለውን ድንኳን ያመለክታል፡፡

✍️#ደብተራ_ኦሪት የብርሃን ድንኳን እንዲል፡፡
በመካከለኛው ዘመን መጀመሪያ ላይ ነገሥታቱ ከሀገር ሀገር ሲጓዙ አብራቸው የምትጓዝ የጸሎት ታቦት ነበረቻቸው፡፡ ለዚህች ታቦት የምትሆን ድንኳን አዘጋጁ፡፡ ታቦቷ በቤተ መንግሥት ግቢ ተተክላ ትቀመጥና ንጉሡ ከቦታ ወደ ቦታ ሲንቀሳቀስ ተነቅላ ትንቀሳቀስ ነበር፡፡ በዚህች የቤተ መንግሥት የድንኳን መቅደስ ውስጥ ለአገልግሎት የሚመረጡት በዕውቀታቸውና በንጽሕናቸው የተመሰገኑ ነበሩ፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ አባት በዚህች ድንኳን ከሚያገለግሉ ካህናት ወገን ነበረ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በዚህች የድንኳን ቤተ መቅደስ ውስጥ አገልግሏል፡፡ በዚህች ቤተ መቅደስ የሚያገለግሉት ካህናት አንዱ ሥራቸው ንጉሣውያን ቤተሰቦችን ማስተማር ስለነበር አባ ጊዮርጊስ የዐፄ ዳዊትን ልጆች ሲያስተምር ነበር፡፡

✍️በዚህች የቤተ መንግሥት መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት #በማደሪያው_አዳሪው_በአዳሪውም_ማደሪያው_ይጠራልበሚባለው መሠረት በደንኳኗ (በደብተራ) እነርሱም #ካህናተ_ደብተራ እየተባሉ መጠራት ጀመሩ፡፡ ቆይቶም #ካህናት የሚለው ስም ተጎርዶ #ደብተራ እየተባሉ ብቻ ተጠሩ፡፡#ከመነሻው_ደብተራ_ማለት_በዕውቀትና_በሕይወት_ተመርጦ_የቤተ_መንግሥቱን_የደብተራ_ቤተ_መቅደስ_ለማገልገል_የተሰየመ_ሊቅ_ካህን_ማለት_ነበር፡፡

✍️ካህናተ ደብተራ ከንጉሡ ጋር የተሻለ ቀረቤታ በማግኘታቸው በኋላ ዘመን የርስትና የሹመት ተካፋዮች ሆኑ፡፡ ይህን ላለማጣት ሲሉም አንዳንዶቹ ቀኖናው ከሚያዛቸው ይልቅ ንጉሡ የሚያዛቸውን መቀበል ጀመሩ፡፡ በዚህ የተነሣም ካህናተ ደብተራ ለንጉሡ የሚያደሉና ለእውነት የማይቆሙ እየሆኑ በመምጣታቸው እንደነ አባ በጸሎተ ሚካኤል ያሉ አበው በድፍረት ወቅሰዋቸው ነበር፡፡ በኋላ ዘመን ደግሞ አንዳንዶቹ ከማኅበረሰቡ በተሻለ የተማሩ መሆናቸውን በመጠቅም ጥንቆላና አስማት እንችላለን በማለታቸው #ደብተራ የሚለው ስም የምሁርነት ስም መሆኑ ቀርቶ ከጥንቆላና መተት ጋር የተያያዘ ስም እየሆነ መጣ፡፡

✍️አንዳንዴም #ዕውቀት_ያስታብያል እንዲል መጽሐፉ ወደ መሰናክሉ የሚወስዳቸው ዕውቀታቸው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ታሪከ ነገሥቱን፣ ዜና መዋዕሉንና ለቤተ መንግሥቱ የቀረቡ ድርሳናቱን የመጻፉ ዕድል የደብተሮች ሲሆን ከገዳማዊ ሕይወት ጋር የተገናኙ የጸሎት፣ የዝማሬ፣ የገድል፣ የመልክዕና የውዳሴ ድርሳናትን የመጻፍ ዕድል ደግሞ የገዳማውያኑ ሊቃውንት ነበረ፡፡ ሁለቱንም ሊቃውንት አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር በዘመኑ ዕውቀት የበለጸጉ መሆናቸው ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ቤተ መንግሥቱንም ገዳማዊ ሕይወቱንም የሚያውቁ ሊቃውንት ይገኛሉ፡፡ መነሻቸው አንደኛው ይሆንና ወደሌላው ይሄዳሉ፡፡ ከገዳሙ ወደ ቤተ መንግሥቱ (ልክ አንደ አባ ባሕርይ) ወይም ደግሞ ከቤተ መንግሥቱ ወደ ገዳሙ (እንደ ቅዱስ ያሬድ)፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
ጌታቸው ኃይሌ፣የአባ ባሕርይ ድርሰቶች፣1995፣35)

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
#በምድር_ላይ_ሰላምን_ለማምጣት_የመጣሁ_አይምሰላችሁ_ሰይፍን_እንጂ_ሰላምን_ለማምጣት_አልመጣሁም።ማቴ 10፥34) ሲል ምን ማለቱ ነው??

✍️ኢየሱስ ወደ እዚህ ምድር በመምጣቱ ሰላም ሰፍኗል፡፡መላእክትም ይህንን ሰላም ለሰው ሁሉ አብስረዋል፡፡
#ክብር_ለእግዚአብሔር_በአርያም_ይሁን_ሰላምም_በምድር_ለሰውም_በጎ_ፈቃድ_አሉ።ሉቃ 2፥14 #እኔ_ሕይወት_እንዲሆንላቸው_እንዲበዛላቸውም_መጣሁ።ዮሐ10፥10 በማለት ለሰላምና ለሕይወት የመጣ መሆኑን ነግሮናል፡፡
#እርሱ_ሰላማችን_ነውና_ሁለቱን_ያዋሐደ_በአዋጅ_የተነገሩትንም_የትእዛዛትን_ሕግ_ሽሮ_በመካከል_ያለውን_የጥል_ግድግዳን_በሥጋው_ያፈረሰ_ይህም_ከሁለታቸው_አንድን_አዲስን_ሰው_በራሱ_ይፈጥር_ዘንድ_ሰላምንም_ያደርግ_ዘንድ ኤፌ 2፥14-15 በማለት የሰላም በለቤት መሆኑን ነገረን፡፡
በሌላ ቦታም
#ከሰው_ሁሉ_ጋር_ሰላምን_ተከታተሉ_ትቀደሱም_ዘንድ_ፈልጉ_ያለ_እርሱ_ጌታ_ሊያይ_የሚችል_የለምና።ዕብ 12፥14

✍️አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ክርስቶስ መንግሥትን ሊመሠርት አልመጣም፡፡ወንጌልንም በሠይፍ አልሰበከም አላስፋፋምም ይልቁንስ መከራ እየተቀበለ ሁሉን ወደ እርሱ ሳበው፡፡እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።ዮሐ 12፥32 እንዳለ።

✍️ኢየሱስ ሰላም ባይሆን መስቀሌን /መከራዬን/ተሸከሙ ብሎ ከሚአዘን ይልቅ ሰይፍ እንድንይዝ በአዘዘን ነበር፡፡
ለእኛ ለክርስቲያኖችስ ሰይፋችን የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡፡

#የመዳንንም_ራስ_ቁር_የመንፈስንም_ሰይፍ_ያዙ_እርሱም_የእግዚአብሔር_ቃል_ነው።ኤፌ 6፥17 በማለት ሰይፍ የእግዚአብሔር ቃል መሆን እንዳለበት ነገረን፡፡
ኢየሱስም መልሶ #መንግሥቴ_ከዚህ_ዓለም_አይደለችም_መንግሥቴስ_ከዚህ_ዓለም_ብትሆን_ወደ_አይሁድ_እንዳልሰጥ_ሎሌዎቼ_ይዋጉልኝ_ነበር_ አሁን_ግን_መንግሥቴ_ከዚህ_አይደለችም_አለው።ዮሐ 18:36
👉የኢየሱስ መንግሥት በዚህ ምድር ስላልሆነ እኛም ተከታዮቹ በዚህ ምድር ላይ መንግሥትና መደላደል ምቾትና ሰላም የለንም፡፡ዓለም ሰላማችን ብትነሳንም#ሰላምን_እተውላችኋለሁ_ሰላሜን_እሰጣችኋለሁ_እኔ_የምሰጣችሁ_ዓለም_እንደሚሰጥ_አይደለም_ልባችሁ_አይታወክ_አይፍራም።ዮሐ 14፥27 በማለት የሠላም ባለቤት እርሱ በነገረን በተስፋ ደስ ይለናል።

✍️ሰይፉ ገና በወለደችው በአናቱ #በድንግል_ማርያም ጀምሮ ነው፡፡
አረጋዊ ሰምዖን #በአንቺ_ደግሞ_በነፍስሽ_ሰይፍ_ያልፋል ሉቃ 2:35)እንዳለ የሃዘን ና የመከራ ሰይፍ አልፎባታል እርሷ ግን በዚህ አልደነገጠችም።#ነፍሴ_ጌታን_ታከብረዋለች_መንፈሴም_በአምላኬ_በመድኃኒቴ_ሐሴት ታደርጋለች ሉቃ 1፥47 እያለች በዝማሬ አምላክን አመሰገነች፡፡

#በዚያን_ጊዜ_ለመከራ_አሳልፈው_ይሰጡአችኋል_ይገድሉአችሁማል_ስለ ስሜም_በአሕዛብ_ሁሉ_የተጠላችሁ_ትሆናላችሁ።ማቴ 24፥9 እንዳለ

✍️ደቀ መዛሙርቱ በሰይፍ እየተሰየፉ ሞቱ ስለ ስሙ የተጠሉ ሆኑ ነገር ግን ደስተኞቸ ነበሩ ወደ ሞት ኢየሄዱ አልፈሩም ለሰይፉም ልባቸው አልዛለም፡፡
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን
ሮሜ 8:35 በማለት ይዘምሩ ነበር፡፡
አዎን ክርስቶሰ በመምጣቱ ሁሉን ለይቷል በክርስቶስ ምክንያት በቤተሰብ ድረስ ክርክር እና መለያየት ሆኗል፡፡
በባዓል ና በሚሰት በአባት ና ልጅ መካከል በክርስቶስ ምክንያት መለያየት መጣ፡፡በክርስቶስ ምክንያት ዱድያኖስ ሚስቱን ሰየፈ በክርስቶስ ምክንያት ወለተ ጴጥሮስ በባሏ ተገረፈች በክርስቶስ ምክንያት የሮም ባለስልጣናት ሚስቶች ከጣኦት አምላኪ ባሎቻቸው ተለይተው ሐዋርያት ጋር በወንጌል ተባበሩ።ክርስቶስን የሚከተሉት ሁሉ ሰይፍ ተከተላቸው፡፡
#በድንጋይ_ተወግረው_ሞቱ_ተፈተኑ_በመጋዝ_ተሰነጠቁ_በሰይፍ_ተገድለው_ሞቱ_ሁሉን_እያጡ_መከራን_እየተቀበሉ_እየተጨነቁ_የበግና_የፍየል_ሌጦ_ለብሰው_ዞሩ ዕብ 11፥37)እንዳለ ይህ ሁሉ ሲሆን በማንም ላይ ሰይፍ አልመዘዝንም
የመዘዝነውንም ሰይፍ #ሰይፍ_የሚያነሡ_ሁሉ _በሰይፍ_ይጠፋሉና_ሰይፍህን_ወደ_ስፍራው_መልስ።ማቴ 26፥52 በማለት ሰይፋችንን እየሰበርን እንድንከተለው አዞናል፡፡ የተቆረጠነውንም ጆሮ ፈውሶታል

👉#በምድር_ላይ_ሰላምን_ለማምጣት_የመጣሁ_አይምሰላችሁ_ሰይፍን_እንጂ_ሰላምን_ለማምጣት_አልመጣሁም_ሰውን_ከአባቱ_ሴት_ልጅንም_ከእናትዋ_ምራትንም_ከአማትዋ_እለያይ_ዘንድ_መጥቻለሁና።ማቴ 10፥35
✍️ሰውን ከአባቱ ልለይ=ሲል ከዲያብሎስ ማለቱ ነው። የሰው ልጅ የዲያብሎስን ቃል ሰምቶ የዲያብሎስ አገልጋይ ሆኗልና፡፡#እናንተ_ከአባታችሁ_ከዲያብሎስ_ናችሁ_የአባታችሁንም_ምኞት_ልታደርጉ_ትወዳላችሁ_እርሱ_ከመጀመሪያ_ነፍሰ_ገዳይ_ነበረ_እውነትም_በእርሱ_ስለ_ሌለ_በእውነት_አልቆመም_ሐሰትን_ሲናገር_ከራሱ_ይናገራል_ሐሰተኛ_የሐሰትም_አባት_ነውና።ዮሐ 8:44 እንዲል አሁን ግን ሰውን ከዲያብሎስ ልለየው መጥቻለሁ አለ፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
✍️ሴትን ልጅ ከእናቷ ሲልም==ኦሪትን ከአይሁድ መምህራን ሥርዓት ልለያት መጣሁ ሲል ነው፡፡
✍️አማትን ከምራቷ=> ምኩርብን ከካህናት ልለያት ነው ሲል ነው፡፡
✍️ለሰው የገዛ ቤተሰቦቹ ጥላቶቹ ይሆኑበታል ሲል ይህ ቃል ነፍስና ሥጋን ይመለከታል፡፡
✍️ቤተሰብ የተባሉት ውስጣዊ ብልቶቻችን ናቸው፡፡
#ሥጋ_በመንፈስ_ላይ_መንፈስም_በሥጋ_ላይ_ይመኛልና_እነዚህም_እርስ_በርሳቸው_ይቀዋወማሉ_ስለዚህም_የምትወዱትን_ልታደርጉ_አትችሉም።ገላ 5፥17

👉በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን ያዕ 4፥1

👉#እንግዲህ_በምድር_ያሉቱን_ብልቶቻችሁን_ግደሉ_እነዚህም_ዝሙትና_ርኵሰት_ፍትወትም_ክፉ_ምኞትም_ጣኦትንም_ማምለክ_የሆነ_መጎምጀት_ነው።ቆላ 3፥5
አንድም ሰይፍ የተባለ የእግዚአብሔር የሚለየው ቃል ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉#አሁን_ግን_ኮረጆ_ያለው_ከእርሱ_ጋር ይውሰድ_ከረጢትም_ያለው_እንዲሁ_የሌለውም_ልብሱን_ሽጦ_ሰይፍ_ይግዛ_ጌታ_ሆይ_እነሆ_በዚህ_ሁለት_ሰይፎች_አሉ_አሉት_እርሱም_ይበቃል_አላቸው።ሉቃስ 22፥38
👉ስለ ሰው መግደያው ሰይፍ እያለ ቢሆንስ ይበቃል ባላላቸው ነበረ፡፡
ሁለት ሰይፍ የተባሉት #ብሉይ እና #ሐድስ ኪዳን ናቸው፡፡ልብሱን ሽጦ ማለት እራሱን ክዶ ወንጌልን ቃሌን ይማር ማለት ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ #የተሳለ ነው፥ ነፍስንና #መንፈስንም ጅማትንና #ቅልጥምንም #እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ዕብ 4፥12

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
#ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ክፍል አንድ👈    
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ድንግል ማርያም የዘር ኃጢያት የለባትም ለዚህም እጅግ በርካታ ማረጋገጫዎችን መዘርዘር ሲቻል በዚህ ጽሁፍ ግን ለጊዜው የሚከተሉትን ሶስት ነጥቦች እንመለከታለን     
••●◉ ✞ ◉●••
፩. አስቀድመው ነብያት የዘር ኃጢአት #ጥንተ_አብሶ እንደሌለባት አስረግጠው ተናግረዋል ከነዚህም ጥቂቶቹ ለመመልከት ያህል፡             
••●◉ ✞ ◉●••
 ፩.፩ ነብዩ ኢሳይያስ #እግዚአብሔር_ዘርን_ባያስቀርልን_ኖሮ_እንደ_ሰዶም_በሆንን_እንደ_ገሞራም_በመሰልነ_ነበር ኢሳ 1፥9 ዘር የተባለች ዓለም የዳነባት አምላክ ሰው የሆነባት #ድንግል_ማርያም ናት ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን ክታቡ #የአብራሃምን_ዘር_ይዞአል_እንጂ_የያዘው_የመላእክትን_አይደለም ዕብ 1፥17 በማለት ጌታ ሰው የሆነባትን ዘር የአብርሃም ዘር እያለ ይጠራታል ነቢዩ ኢሳይያስም እግዚአብሔር ያስቀራት ዘር ያላት #እመቤትችንን ነው #አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሰው ሲሆን ከመርገመ አዳም ከመርገመ  ሔዋን ለይቶ በንጽሐ ሥጋ በንጽሐ ነፍስ ጠብቆ ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ለማዳን ምክንያት ያደረጋት ዘር ናት፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
፩.፪ ነብዩ ዳዊት #የወርቅ_ልብስ_ተጎናጽፋና_ተሸፋፍና_ንግስቲቱ_በቀኝህ_ትቆማለች_ልጄ_ሆይ_ስሚ_እይ_ጆሮሽንም_አዘንብይ_ወገንሽን_የአባትሽን_ቤት_እርሺ_ንጉሥ_ውበትሽን_ወዶአልና መዝ 49፥9-11 ወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ሲሆን ተጎናፅፋ የተባለው ደግሞ ንጽሓ ስጋ ላይ #ንጽሓ_ነፍስ_ንጽሃ_ነፍስ ላይ ንጽሓ ልቦና መደራረቧን የሚያስረዳ ነው ወገንሽን የአባትሽን ቤት እርሺ የተባለው ደግሞ ከሰው ዘር በሙሉ መለየቷን የዘር ኃጢአት እንዳላገኛት የሚያስረዳ ነው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እመቤታችንን ልጄ እያለ መጥራቱ ከሱ ዘር እንደምትወለድ ያስረዳናል ጌታም ከሷ ስለተወለደ የዳዊት ልጅ ተብሎ ተጠርቷል ማቴ 1፥1 ንጉሥ የተባለ ልጇ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሲሆን ውበትሽን ወዷልና ማለት ውበት ንጽሕናሽን ሊዋሃደው ወዷልና ማለት ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
 ፩.፫ ጠቢቡ ሰሎሞን #ወዳጄ_ሆይ_ሁለንተናሽ_ውብ_ነው_ነውርም_የለብሽም መኃ4፥7 ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ተቃኝቶ እመቤታችንን ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየ ንጹሕ ነው ብሎ አመስግኗታል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
፪. የቅዱስ ገብርኤል ብሥራታዊ ሰላምታ እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ #የዘር_ኃጢአት እንደሌለባት በሚገባ ያስረዳል ይህንንም እንደሚከተለው በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን
 💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
#ጸጋን_የሞላብሽ_ሆይ_ደስ_ይበልሽ_ጌታ_ካንቺ_ጋር_ነው_አንቺ_ከሴቶች_መካከል_የተባረክሽ_ነሽ"  ሉቃ 1፥28  
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
••●◉ ✞ ◉●••
፪.፩ #ጸጋ_የሞላብሽ_ሆይ እናስተውል የሰው ልጆች ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል በተባለበት ዘመን ጸጋ የሞላብሽ የሚል ልዩ ምስጋና የቀረበላት #እመቤታችን ብቻ ናት በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲህ ነበር የተባለው #ሁሉም_የእግዚአብሔር_ክብር_ጎሎአቸዋል ሮሜ 3፥24 እንግዲህ ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል የተባለው ሁሉ ኃጢአት ስለሠሩ አይደለም ነገር ግን አዳማዊ መርገም በሁሉ ስለደረሰ ነው ለዚህም ነው #ኃጢአት_ባልሰሩት_ላይ_እንኳን_ሞት_ነገሰ ሮሜ 5፥14 ተብሎ የተጻፈው ታድያ ሰው ሁሉ መረገመ አዳም ስለደረሰበት ከጸጋ በታች ከተባለ ድንግል ማርያም እንዴት ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ይህ በርግጥም #እመቤታችን የዘር ኃጢአት ፍዳ እንደማይመለከታት ያስረዳናል ድንግል ማርያም ይህ የምስጋና ቃል የቀረበላት ጌታን ገና ከመጽነሷ በፊት ነው ይህ ማለት ደግሞ ጌታችን ሰው ሆኖ ጸጋ ለጎደለው አለም ካሳ ቤዛ ሳይሆንለት  ድንግል ማርያም ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ማለት ከእናቷ ማህጸን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ጠብቋታል ማለት ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
፪.፪ #ከሴቶች_መካከል - ሁለተኛው ነጥብ #ድንግል_ማርያም ከሴቶች ተለይታ የተባረከች እንድትባል ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ በዘር ኃጢአት ምክንያት በሌሎች የደረሰ መረገም በእርሷ ስላልደረሰ ነው እንዲህ ባይሆን ኖሮ ይህ ምስጋና ባልተገባትም ነበር ስለ ሌሎች የሰው ልጆች መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጽ #ልዩነት_የለም_ሁሉ_ከበደል_በታች_ናቸው ሮሜ 3፥22 ይላል።ስለእመቤታችን ሲናገር ግን ከሴቶች መካከል ብሎ መለየቷን በግልጽ ያስቀምጣል እንግዲህ ሰው ሁሉ ያለ ልዩነት ከበደል በታች በተባለበት ዘመን እርሷ የተለየች ከተባለች በእርግጥም #ወላዲተ_አምላክን የውርስ ኃጢአት ፍዳ አይመለከታትም ማለት ነው ። #እመቤታችን ክብር ምስጋና ይግባትና የጥንተ አብሶ ፍዳ ይመለከታታል ከተባለ የእርሷ መለየት የቱ ጋ ሊሆን ነው? ስለዚህም የመልአኩ የሰላምታ ቃል ስህተት ነው እንላለን አንልም እውነታውን ይዘን ድንግል ማርያም በእውነት ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየች ንጽሕት ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን እንጂ፡፡
  ••●◉ ✞ ◉●••
፪.፫ #የተባረክሽ_ነሽ - በሶስተኛ ደረጃ ከመልአኩ የምስጋና ቃል #ድንግል_ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደሌለባት የሚያስገነዝበን የተባረክሽ ነሽ የሚለው ኃይለ ቃል ነው 
  ••●◉ ✞ ◉●••
👉በአጠቃላይ ድንግል #ድንግል_ማርያም ከላይ በመልአኩ የሰላምታ ንግግር ከብዙ በጥቂቱ እንደተመለከትነው የዘር ኃጢአት በፍጹም እንደማይመለከታት ነው ይህም አምላክ አለምን ለማዳን ከእርሷ ከሥጋዋ ሥጋ ክነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ለመሆን ያዘጋጃት በመሆኗ የእርሷ ንጽህና በሰው ልጆች መዳን ውስጥ በምክንያትነት ወደፊት በቀጣዩ ክፍላችን የምንመለከተው ይሆናል፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ክፍል 2 ይቀጥላል👈

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
#ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ክፍል ሁለት👈    
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒 
••●◉ ✞ ◉●••
👉፫. #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም የውርስ ኃጢአት አለባት ማለት #የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ንጹሐ ባሕርይውን መዳፈር ነው  #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አለምን ለማዳን ሰው ሲሆን ሥጋና ነፍስን ከሰማይ ይዞ አልወረደም ሰው የሆነው የእኛን ባሕርይ ተዋሕዶ ነው።#እንግዲህ_ልጆቹ_በሥጋና_በደም_ስለሚካፈሉ_እርሱ_ደግሞ_በሞት_ላይ_ስልጣን_ያለውን_እንዲሽር_እንዲሁ_ተካፈለ_የአብርሃምን_ዘር_ይዞአል_እንጂ_የያዘው_የመላእክትን_አይደለም ዕብ 2፥14-15
••●◉ ✞ ◉●••
👉እንግዲህ#ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሰው ሲሆን ሥጋንም ነፍስንም #ከድንግል_ማርያም ከነሳ እርሷ ደግሞ መርገም ነክቶአታል ከተባለ ክብር ምስጋና ይግባውና #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኃጢአት ያለበትን ሥጋ ተዋሐደ ልንል ነውን እንዲህማ ካልን ተረፈ አይሁድ ሆነናል ማለት ነው ምክንያቱም ደፍረው  #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ኃጢአት አለበት ያሉት አይሁድ ናቸውና  #ይህ_ሰው_ኃጢአተኛ_መሆኑን_እኛ_እናውቃለን ዮሐ 9፥24
••●◉ ✞ ◉●••
👉እኛስ #ከእመቤታችን ምንም ምን ኃጢአት ያላወቀውን ሥጋ እንደነሳ እንመሰክራለን እንደ እውነተኞቹ አባቶቻችን #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ንጽሕት ቅድስት ከምትሆን #ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን እናምናለን እንመሰክራለን #ኦ_ድንግል_አኮ_ዘተአምሪ_ርስሐተ_ከመ_አንስት_እለ_እምቅድሜኪ_ወእምድሬኪ_አላ_በቅድስና_በንጽሕና_ስርጉት_አንቲ (#ድንግል_ሆይ_ካንቺ_አስቀድመው_ካንችም_በኋላ_እንደ_ነበሩ_ሴቶች_አደፍ_ጉድፍን_የምታውቂ_አይደለሽም_በቅድስና_በንጽሕና_ጸንተሽ_ኖርሽ_እንጂ ቅዳሴ ማር 5፥42    
   ••●◉ ✞ ◉●••
👉መቼም አባቶቻችን እነ ቅዱስ ኤፍሬም እነ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የደረሱአቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት የማይቀበል ኦርቶዶክሳዊ አለ ማለት እጅግ ይከብዳል ፡፡ እንግዲህ ቅድስት ቤተክርስትያን ስለነገረ ማርያም በጥንቃቄ የምታስተምረው ስለድንግል ማርያም የምናምነው ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ #ከጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ማንነት ጋር ተያያዥነት ስላለው ነው እግዚአብሔር ይግለጥልንና #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከእመቤታችን መርገም ያለበትን ሥጋ ተዋሐደ ማለት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታዊ ተቃርኖዎችን ያስነሳል። 

👉፩. የድንግል ማርያም ሥጋ የውርስ ኃጢአት ወይም የጥንተ አብሶ ፍዳ አለበት ከተባለ #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከርሷ ሲወለድ ኃጢአት የወረሰውን ሥጋ ወሰደ ሊባል ነው ይህ ማለት ደግሞ  በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ትምህርት ነው ምክንያቱም #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ባሕርይ ኃጢአት ፈጽሞ  አይስማማውምና ኃጢአት የነካውን ሥጋ ተዋሐደ  ከተባለ መለኮት ኃጢአት ይስማማዋል እንደማለት ነው።ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወግዘው ክህደት ነው ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦች መመልከት ይቻላል

👉#ቅዱስና_ያለ_ተንኮል_ነውርም_የሌለበት_ከኃጢአተኞት_የተለየ_ከሰማያትም_ከፍ_ከፍ_ያለ ዕብ 6፥27

👉#ከኃጢአት_በቀር_በነገር_ሁሉ_እንደኛ_ተፈተነ………… ዕብ 4፥15

👉#ኃጢአት_ያላወቀውን_እርሱን_ስለኛ_ኃጢአት …………2ቆሮ5፥20

👉፪. #የድንግል_ማርያም ሥጋ የጥንተ አብሶ ፍዳ ወይም የውርስ ኃጢአት  አለበት ማለት #የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የማዳን ሥራ  አለመቀበል ነው ። ምክንያቱንም ከዚህ እንደሚከተለው ማብራራት ይቻላል ።#የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከድንግል_ማርያም መርገም ያለበትን ሥጋ ከነሳ ክብር ምስጋና ይግባውና  መርገም ባለበት ሥጋ መርገምን አራቀ ማለት በጭራሽ አያስኬድም። ይህ ደግሞ አለም እንዲድን የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበትም ምክንያት ከንቱ ሊሆን ነው ። የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበት ምክንያትኮ ሰው  ሁሉ የመረገም የእዳ የበደል ተጠያቂ ስለነበር ንጹሕ የሚያድን በመጥፋቱ ነው።ለዚህም ነው በነብዩ ኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው

👉#እግዚአብሔር_አየ_ፍርድም_ስለሌለ_ተከፋ_ሰውም_እንደሌለ_አየ_ወደ_እርሱ_የሚማልድም_እንደሌለ_ተረዳ_ተደነቀም_ስለዚህም_የገዛ_ክንዱ_መድኃኒትን_አመጣለት_ጽድቁም_አገዘው ኢሳ49፥17  
  ••●◉ ✞ ◉●••
🙏አዎን እግዚአብሔር ያጣው ንጹሕ ሆኖ ስለ ሌላው የሚማልድ ካሳ ቤዛ የሚሆን ሰው ነበር ነገር ግን ሁሉ ከእዳ ከበደል በታች ስለነበሩ ንጹሕ መርገም የሌለበት ጠፋ ስለዚህም በንጹሐ ባሕርይው #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ንጹሕ ሥጋን ተዋህዶ  ወደ እኛ መጣ ።ነብዩ የገዛ ክንዱ መድኃኒትን አመጣለት ማለቱ  እርሱ እራሱ ሰው ሆኖ አዳነን ማለቱ ነው ።  እርሱ በባሕርይው ኃጢአት ስለማይስማማው  ኃጢአት የሌለበትን ሥጋ ለመዋሐዱ ምንም ሊያከራክር አይችልም ።መርገም ያለበት መርገም ያለበትን ማዳን ቢችል ኖሮ ከብዙ ነብያት አንዳቸው አለምን  ማዳን በተቻላቸው ነበር። #የድንግል_ማርያምን ንጽሕና በጥንቃቄ ከተረዳን ነገረ ድኅነትን እንዳናፋልስ ይረዳናል ለዚህም ነው ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ስለ #የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሰው መሆን ሲገልጽ #ስለእመቤታችን  ንጽሕና አስረግጦ የተናገረው #ወለደት_ድንግል_ዘፀንሰቶ_እንዘ_ኢተአምር_ብእሴ_በሥጋ_ዘፈጠሮ_ለርእሱ_ወወለደቶ_ዘእንበለ_ደነስ_ወሕማም_ወኢረሰስሐት_በሐሪስ_ሐፀነቶ_ዘእንበለ_ፃማ_ወድካም_ወአጥበቶ_ዘእንበለ_ድካም_ወአልሐቀቶ_በሕግ_ዘሥጋ_ዘእንበለ_ትካዝ ።ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ 28፥19
••●◉ ✞ ◉●••
#ለተዋሕዶ_የፈጠረውን_ሥጋ_ያለ_ወንድ_ዘር_ያለ_ኃጢአት_ያለምጥ_ወለደችው_የአራስነት_ግብርም_አላገኛትም_ያድካም_ያለመታከት_አሳደገችው_ያለድካም_አጠባችው_ለሥጋ_በሚገባ_ሕግ_ምን_አበላው_ምን_አለብሰው_ሳትል_አሳደገችው
••●◉ ✞ ◉●••
👉ማብራሪያውን በክፍል ሶስት እንመለከታለን፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ክፍል 3 ይቀጥላል👈

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
#ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ክፍል ሶስት👈    
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒 
ከዚህ ቀደም ተከታታይ ባቀረብናቸው ጽሑፎች #ወላዲተ_አምላክ_ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደማይመለከታት ከብዙ በጥቂቱ ለማየት ሞክረናል።በክፍል ሁለት ጽሑፋችን #ወለደት_ድንግል_ዘፀንሰቶ_እንዘ_ኢተአምር_ብእሴ_በሥጋ_ዘፈጠሮ_ለርእሱ_ወወለደቶ_ዘእንበለ_ደነስ_ወሕማም_ወኢረሰስሐት_በሐሪስ_ሐፀነቶ_ዘእንበለ_ፃማ_ወድካም_ወአጥበቶ_ዘእንበለ_ድካም_ወአልሐቀቶ_በሕግ_ዘሥጋ_ዘእንበለ_ትካዝ ።ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ 28፥19
••●◉ ✞ ◉●••
#ለተዋሕዶ_የፈጠረውን_ሥጋ_ያለ_ወንድ_ዘር_ያለ_ኃጢአት_ያለምጥ_ወለደችው_የአራስነት_ግብርም_አላገኛትም_ያድካም_ያለመታከት_አሳደገችው_ያለድካም_አጠባችው_ለሥጋ_በሚገባ_ሕግ_ምን_አበላው_ምን_አለብሰው_ሳትል_አሳደገችው። ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዮስ 28፥19 ትርጉም  ማብራሪያውን በቀጣዩ ጽሁፋችን እንመለከታለን ብለን ነበር ያቆምነው።

👉ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናቴዎስ ካስተማረው ትምህርት እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት በሚገባ ማስተዋል ይቻላል ግልጽ ለማድረግም የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት ይቻላል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉፩. ያለ ኃጢአት ከሚለው ቃል ወላዲተ አምላክ ጌታን ምንም ምን ኃጢአት ሳያገኛት እንደወለደችው ያስረዳናል      
••●◉ ✞ ◉●••
፪. ያለምጥ የአራስነት ግብርም ሳያገኛት ከሚለው ደግሞ ሌሎች ሴቶች በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት በምጥ በአራስነት የሚወልዱ ሲሆን እርሷ ግን ከመርገመ ከእዳ ከበደል የተለየች በመሆኗ ምጥና አራስነት አልነበረባትም ይህም ከመልአኩ የምስጋና ንግግር ተስማሚነት ያለው ነው #ቅዱስ ገብርኤል ሲያበሥራት ከላይ ከተጠቀሱት የመርገም ምልክቶች እመቤታችን የተለየች መሆኗን ሲያስረዳ #አንች_ከሴቶች_መካከል_የተባረክሽ_ነሽ  ሉቃ 1፥28 በማለት አመሰግኖአታል።ለመሆኑ እርሷ በሌሎች ሴቶች ያለ የመርገም ፍዳ ካለባት ከሌሎች ሴቶች መለየቷ ምን ላይ ሊሆን ነው  ስለዚህ እመቤታችን የመርገም ፍዳ ይመለከታታል ብሎ ማስተማር ፍጹም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ የራቀ ትምህርት ነው ማለት ነው ። ወላዲተ አምላክ የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት ቅዱስ አትናቴዎስ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቅዱሳን አበውም መስከረዋል  

👉ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #ድንግል_ማርያም የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት ሲያስረዳ በሚደንቅ ንግግር እንዲህ ይላል #ከመገባሪ_ጠቢብ_ሶበ_ይረክብ_ግብሮ_ዘይትጌበር_ይገብር_እምኔሁ_ንዋየ_ሰናየ_ከመዝ_እግዚእነ_ሶበ_ረከበ_ሥጋሃ_ቅዱስ_ለዛቲ_ድንግል_ወነፍሳ_ቅድስት_ፈጠረ_ሎቱ_መቅደስ_ዘቦቱ_ነፍስ » ሐይ አበ ዘአፈወርቅ 66 ፡14
••●◉ ✞ ◉●••
#ጥበበኛ_ንጹሕ_አፈር_ባገኘ_ጊዜ_ጥሩ_እቃ_እንደሚሰራበት_ጌታችንም_የድንግልን_ንጹሕ_ሥጋዋን_ንጹሕ_ነፍሷን_ባገኘ_ጊዜ_ይዋሐደው_ዘንድ_ነፍስ_ያለውን_መቅደስ_ሰውነቱን_ፈጠረ 
••●◉ ✞ ◉●••
👉መቼም የቀናች የተረዳች ርትዕት የሆነች የተዋሕዶ ምዕመን ሆኖ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የማያውቅ አለ ማለት ይከብዳል ምንም በማያሻማና ግሩም በሆነ አገላለጽ ሊቁ እነዳስቀመጠልን አምላክ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነው ምንም ምን እንከን ከሌለው ሰውነቷ ነው  ሊቁ #የእመቤታችንን ነፍስና ሥጋዋን በንጹሕ አፈር መስሎታል በዚህ አገላለጹ ከሰው ወገን ተመርጣ #የለጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እናትነት የበቃች መሆኗን አስረዳን ምክንያቱም የሰው ሁሉ ተፈጥሮው ከአፈር ነውና ። #ወላዲተ_አምላክ እንደሰው ሁሉ ተፈጥሮዋ ከአፈር ቢሆንም ቅሉ ሊቁ እንደተናገረው ንጹሕ አፈር የሚለው አገላለጽ በሰዎች ከደረሰ አዳማዊ መርገም የተለየች መሆኗን ያስረዳናል

👉ቅዱስ ኤፍሬምም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም #ዘር_ያልተዘራባት_እርሻ በማለት በንጹሕ እርሻ መስሎአታል

👉ልበ አምላክ ዳዊትም #እንደ_ዝናብ_በንጹሕ_እርሻ_ላይ....ይወርዳል   መዝ 71፥6 በማለት #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን በዝናበ ሕይወት እመቤታችንን ደግሞ አረም ተዋስያን በሌሉት ንጹሕ መሬት መስሎ ትንቢት ተናግሮአል ይህም ምንም ተፈጥሮዋ ከሰው ወገን ብትሆንም የኃጢአት አረም ህዋስ ያልነካት ንጽሕት ዘር መሆኗን ያስረዳናል። ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በንጹሕ አፈር የመሰላት ።
••●◉ ✞ ◉●••
👉ሊቁ በመቀጠልም #ንጹሕ_ሥጋዋን_ንጹሕ_ነፍሷን_ባገኘ_ጊዜ  በማለት #የወላዲተ አምላክ ነፍሷ ሥጋዋ ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ ንጹሕ ቅዱስ መሆኑን ይመሰክራል ባገኘ ጊዜ አለ እንጂ ሊዋሐደው ሲል አነጻው አላለም ስለዚህም እውነተኞች ቅዱሳን አበው በጥንቃቄ የመሰከሩትን #የእመቤታችንን ንጽሕና ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊያስተባብል አይችልም ተቀባይነትም አይኖረውም ።

👉ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረን  #እኛ_ብንሆን_ወይም_የሰማይ_መልአክ_ከሰበክንላችሁ_ወንጌል_የሚለይ_ወንጌል_ቢሰብክላችሁ_የተረገመ_ይሁን።ገላ 1፥8 ባለው መሠረት ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊሽረው ወይም ሊለውጠው አይችልም። ቢሞክር እንኳን የተለየ የተረገመ ነው።#ቅድስት_ቤተክርስቲያን የምትመራው ቀደምት ቅዱሳን ባስተማሩን እውነተኛ ትምህርት እንጂ አዲስ ዛሬ የሚፈጠር ምንም የለም ስለዚህ ከአንዳንድ የዘመናችን ሰዎች የተሳሳተ ትምህርት ብንሰማ እነሱ የተለዩ ይሆናሉ እንጂ የሰማይ መልአክ ነኝ የሚል ቢመጣ እንኳን የቤተክርስቲያን አስተምሮ አይለወጥም፡፡  
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉የመጨረሻ ክፍል 4 ይቀጥላል👈

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
#ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉የመጨረሻ ክፍል 👈    
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒 
👉ከዚህ ቀደም ባቀረብኳችው ጽሁፎች  #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም  የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደ ማይመለከታት ቅዱሳን አባቶቻችን የተናገሩትን መመልከት ጀምረን ነበር በዚህ ጽሁፌም ቀጣዩን ክፍል እንመለከታለን  #አምላካችን_ልዑል_እ ግዚአብሔር የእናቱን በረከት ረድኤት ያሳድርብን አሜን፡፡ 🙏

👉ቅዱስ  ኤራቅሊስ  በሃይማኖተ  አበው ምዕራፍ  48 ቁጥር 31  ስለ እመቤታችን ንጽህና ሲመሰክር እንዲህ ይላል 
 #ኢያእመረ_እስመ_ዘተፈጥረት_እምነ_ጽቡር_ጽሩይ_ትከውን _መቅደሶ_ለእግዚአብሔር
••●◉ ✞ ◉●••
#የእግዚአብሔር_መቅደሱ_ማደርያው_ትሆነው_ዘንድ_ከንጹህ_አፈር_የተፈጠረች_መሆኗን አላወቀም።

👉ታላቁ የቤተክርስትያን አባት ቅዱስ ኤራቅሊስ  ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው አረጋዊ ካህን ዮሴፍ ለእመቤታቸን አገልጋይ ሆኖ የታጨለትን ምሥጢር በተረጎመበት ክፍል ነው  ።በእርግጥ አረጋዊ ዮሴፍ ለእመቤታችን ለምን እንደታጨ አላወቀም ነበር እርሷም ትንቢት የተነገረላት ሱባዔ የተቆጠረላት #አምላክን በድንግልና ጽንሳ በድንግልና የምትወልድ ከመርገመ አዳም  ከመረገመ ሔዋን የተለየች መሆኗን አላወቀም ነበር። ነገሮችን መረዳት የጀመረው መልአኩ ካረጋጋው በኃላ የተለያዩ ምልክቶችን አይቶ ነው ።ሊቁም ይህንን ሲያስረዳ #የእግዚአብሔር_መቅደሱ_ትሆነው_ዘንድ_ከንጹህ_አፈር_የተፈጠረች_መሆኗን_አላወቀም
••●◉ ✞ ◉●••
👉ይህም አገላለጽ #ወላዲተ_አምላክ ስትፈጠር ጀምሮ ንጽህት ቅድስት መሆኗን ያስርዳል ዮሴፍ ማንነቷን ከማወቁ በፊት እንደማናቸውም አንስት ከአዳማዊ እዳ በደል ያልተለየች ሴት መስላው ነበር ሁሉን የተረዳው ቆይቶ ነው።ድንግል ማርያም ግን ሊቁ እንደተናገረው ተፈጠሮዋን በተመለከተ #ከንጹህ_አፈር በማለት ንጽሐ ጠባይዋ ያላደፈባት ያልጎደፈባት ገና በማህጸን አጥንት  ሰክቶ ሲፈጥራት በንጸህና የጠበቃት ስለሆነች ከንጹህ አፈር የፈጠራት በማለት ተናገረ ።

👉#ድንግል_የአምላካችን_የጌታችን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አማናዊት መቅደስ ናት ።እንደ #ደንግል_ማርያም _የእግዚአብሔር ማደርያ የሆነ ማንም የለም በሌሎቹ ሁሉ ቢያድር በጸጋ ነው።  #በእመቤታችን ግን በኩነት ሰው በመሆን በተዋህዶ ነው ያደረባት ስለዚህም አማናዊት መቅደስ ናት ።
••●◉ ✞ ◉●••
👉#የእግዚአብሄር መቅደስ ደግሞ በእውነት ንጹሕ ነው።ኃጢአት የማይስማማው ንጹሐ ባህርይ የሆነ መለኮት ንጹህ ማደርያን ይፈልጋልና ።

👉ከሊቁ ከቅዱስ ኤራቅሊስ ንግግር ልናስተውለው የሚገባን መሰረታዊ ነጥብ አለ።ይህም #ድንግል_ማርያምን በንጽህና ፈጠራት አለ እንጂ ከፈጠራት በኋኃላ አነጻት አላለም ።
••●◉ ✞ ◉●••
👉አንዳንድ አደናጋሪዎች #ወላዲተ_አምላክ ክብር ምስጋና ይግባትና አዳማዊ መርገም በብስራተ መልአክ ጠፋላት እያሉ ለማሳሳት ይሞክራሉ።ይህ ግን አላዋቂነት ነው ቅዱሳን አበው በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ያስተማሩትን ትምህርት ማስተባበል ነው ደግሞስ መርገም በብስራተ መልአክ የሚጠፋ ከሆነ መላእክት ያበሰሯቸው ሁሉ መርገመ አዳም መርገመ ሔዋን ጠፍቶላቸዋል ማለት ነው ይህስ ከሆነ የአምልክ መውረድ  መወለድ ሰው መሆን ሰጋውን መቁረስ ደሙን ማፍሰስ ለምን አሰፈለገው በክርስትና አስተምሮ መሰረት  #የእመቤታችን_የቅድስት_ማርያም ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከምሥጢረ ድህነት ጋር የተያያዘ ነው ስለዚህም ነው ስለእርሷ የምንናገረውን ነገር ልንጠነቀቅ የሚገባን ።

👉ሊቁ ቅዱስ ኤራቅሊስ ከንጹህ አፈር ተፈጠረች ማለቱ የሚጠቁመን ሌላ ነጥብ ደግሞ በጥንተ ተፈጥሮ ስንመለከት ከአፈር በቀጥታ የተፈጠረ አባታችን አዳም ብቻ ነው  ሌሎቹ አዳማዊያን መሰረታቸው አፈር ቢሆንም የተፈጠሩት በውልደት ነው 

👉#ድንግልን ግን ከንጹህ አፈር ተፈጠረች አላት ይህም  ምሳሌ ነው በቁሙ አፈር ንጹህ እና ቆሻሻ ተብሎ  አይደለም።ነገር ግን  በዚህ አገላለጽ  በአፈር የተመሰለ የሰው ልጆች ሰውነት ነው።በቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ እንደተባለ #አፈር _ነህና_ወደ_አፈር_ትመለሳለህ ዘፍ 3 ፥19 
••●◉ ✞ ◉●••
👉ከሌሎች የአፈር አይነቶች ተለይቶ ተዋስያን በሌሉበት  በንጹህ አፈር የተመሰለ  መርገመ አዳም መርገመ አዳም ያልነካው የእመቤታችን ሰውነት ነው።ምንም እንኳን #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ብትወልደውም እንደ ሰው ሁሉ  ተፈጥሮዋ እንደ አዳማዊያን ከአፈር ነውና ሰለዚህም ቅድስት ቤተክርስትያን የእውነተኞቹን ደጋግ አበው ምስክርነት ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር አስተባብራ  #ወላዲተ_አምላክ መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት የጥንተ አብሶ ፍዳ የተለየች መሆኗን አበክራ ታስተምራለች፡፡

👉እመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከንጽህናዋ በረከት ረድኤት ያሳትፈን አሜን፡፡🙏🙏🙏🙏
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉በቀጣይ ነገረ ድህነትን በተመለከተ ተከታታይ ፅሁፍ ይለቃቃል።👈

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
#የመዳን_ትምህርት_ወይም_ነገረ_ድኅነት

ክፍል አንድ

👉የሰው ልጅ ለመዳን ምን ያስፈልገዋልእግዚአብሔር ሰውን ለማዳን የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ አንድም ሳይቀር ፈጽሟል አድርጓል፡፡ የሰው ልጅ ለመዳን ከሚያስፈልገው ነገር ውስጥ በእግዚአብሔር ዘንድ ሳይፈጸም የቀረ አንዳችም ነገር የለም፡፡ ያ የእግዚአብሔር ድርሻ ተፈጽሟል፡፡ #ጌታችን_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ #ወይቤ_ተፈጸመ_ኩሉ ተብሎ በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ የሰው ልጅን ለማዳን ማድረግ የነበረበትን አምላካዊ ስራ በሙሉ ፈጽመዋል ከዚህ በኋላ የሚቀረው የሰው ድርሻ ነው፡፡

የዘለዓለም ሕይወት እንዴት እንደሚገኝ፤ መዳንም እንዴት እንደሚገኝ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ እያሉ ይነግሩናል፡፡
ዮሐ 3÷36 #በልጁ_የሚያምን_የዘለዓለም_ሕይወት_አለው ተብሎ ተጽፏል፡፡ ስለዚህ ሕይወት የሚገኘው በእምነት መሆኑን ይነግረናል፡፡
👉እንደገና ደግሞ በጥምቀት የዘለዓለም ሕይወት መዳን እንደሚገኝ ይነግረናል ፡፡ ማር16÷16#ያመነ_የተጠመቀ_ይድናልይላል፡፡

👉እንደዚሁም ደግሞ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ሕይወት እንደሚገኝ ይነግረናል።ጌታችን_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ያልበላ ደሜንም ያልጠጣ የዘለዓለም ሕይወት የለውም ብሎናል።

👉እንደዚሁም ደግሞ መዳን ዘለዓለማዊ ሕይወት ቃሉን በመስማት እንደሚገኝ ይነግረናል፡፡
በዮሐ 5÷24 #እውነት_እውነት_እላችኋለሁ_ቃሌን_የሚሰማ_የላከኝንም_የሚያምን_የዘለዓለም_ሕይወት_አለው_ከሞትም_ወደ_ሕይወት_ተሻገረ_እንጂ_ወደ_ፍርድ_አይመጣም

👉በሌላ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል ደግሞ ወንጌልን በመስበክ ሕይወት እንደሚገኝ መዳን እንደሚገኝ እንዲህ ሲል ይነግረናል።#የሚያጭድ_ደሞዝን_ይቀበላል_የሚዘራና_የሚያጭድም_አብረው_ደስ_እንዲላቸው_ለዘለዓለም_ሕይወት_ፍሬ_ይሰበስባል።ዮሐ 4÷36

👉በሰማዕትነት #በጌታችን_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም በመታመን ሕይወት እንደሚገኝ ሲንገርን #ነፍሱን_የሚወድ_ያጠፋታል_ነፍሱንም_በዚህ_ዓለም_የሚጠላ_ለዘለዓለም_ሕይወት_ይጠብቃታል ዮሐ 12÷25

👉እንደገና #ምጌታችን_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ከዘመድና ከሀብት ንብረት በላይ በመውደድና በመምረጥ የዘላለም ሕይወት እንደሚገኝ ሲናገር #ስለ_ስሜም_ቤቶችን_ወይም_ወንዶችን_ወይም_እህቶችን_ወይም_አባትን_ወይም_እናትን_ወይም_ሚስትን_ወይም_ልጆችን_ወይም_እርሻን_የተወ_ሁሉ_መቶ_እጥፍ_ይቀበላል_የዘለዓለምንም_ሕይወት_ይወርሳል ማቴ 19÷29

👉በተጨማሪም የዘላለም ሕይወት የሚገኘው መዳን የሚገኘው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛቱንና ሕግጋቱን በመጠበቅም መሆኑን ሲናገር ደግሞ አንድ ባለጸጋ ቀርቦ ለጠየቀው ጥያቄ #ጌታችን_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሲመልስ ያ ባለፀጋ ወደ ጌታችን ቀርቦ መምህር ሆይ የዘለዓለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? ብሎ ጠየቀው መሰረታዊ ጥያቄ ነው ይህ ሰው የጠየቀው መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ አለው #ወደ_ሕይወት_መግባት_ብትወድ_ግን_ትዕዛዛትን_ጠብቅ_አለው፡፡ማቴ 19÷16-18

👉በሌላ በኩል ደግሞ ቅዱሳንን በመዘከር እንደምንድንም ተናግሯል ማቴ10:42

👉ስለዚህ የዘለዓለም ሕይወት የሚገኝባቸውን የተለያዩ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት እንዲህ ባለ መልኩ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፈው እናገኛቸዋለን፡፡ እንግዲህ እነዚህ አንዱን ነጥለን አንዱን ብቻ ይዘን ሳይሆን ሁሉንም በተዋሀደ መልኩ ስንገነዘብና ስንፈጽማቸው ነው የዘለዓለም ሕይወት የሚገኘው

ለምሳሌ በአንድ ቤት ውስጥ በር፣መስኮት፣ጣሪያ፣መሠረት፣ምሰሶ፣ ግድግዳ ወዘተ አለ።ያ ቤት የዚያ ሁሉ ድምር ውጤት ነው፡፡ በአግባቡ በየቦታው መስኮትን በመስኮትነቱ በርን በበርነቱ ጣሪያም እንዲሁ በየቦታው ሲቀመጥ ነው ያን ቤት ቤት የሚያደርገው ነገር ግን ከቤት ውስጥ መስኮቱ ብቻ ቤት አይደለም በሩን ብቻ ነጥለን ብናየው ቤት አይሆንም ሌላውም እንደዚሁ

👉ስለዚህ በቅዱስ መጽሐፍ በተለያየ ሁኔታ የተነገሩን ልክ አንድ ቤት ከመሠረቱ ጀምሮ በሚገባ እየወጣ እስከ ጣሪያው ድረስ ሲሄድ ሙሉ እና ትክክለኛ ቤት እንደሚሆን ሁሉ በቅዱሳት መጽሐፍት የተነገሩትን የእግዚአብሔር ቃላት የእግዚአብሔር ትዕዛዛት እንዲህ ባለ በተስማማ መልኩ ልናዳምጣቸው እና ልንረዳቸው ይገባል ማለት ነው።

👉አንድ ሰው ለመዳን የሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች አሉ እነዚህን በአራት መሠረታዊ ነገሮች ከፍለን እንመለከታቸዋለን

👉#አንደኛ ለመዳን የመጀመሪያዉ መሰረት የመጀመሪያዉ ነጥብ #ማመን ነዉ ወይም #እምነት ነዉ።እምነት በዉስጡ #ሁለት ገጽታዎች አሉት።የመጀመሪያዉ #ማመን ነዉ #እምነት ስንል ሰዉ ይህንን በእምነት መቀበል ይኖርበታል፡፡
ዮሐ 3፡14-18 #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ዓለም_በልጁ_እንዲድን_ነዉ_እንጂ_በአለም_እንዲፈርድ_እግዚአብሔር_ወደ_አለም_አላከዉም_ካለ_በኋላ_በእርሱ_በሚያምን_አይፈረድበትም_ይለናልበሚያምን አይፈረድበትም በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል፡፡

👉ስለዚህ አንድ ሰዉ ለመዳን መጀመሪያ ሊኖረዉ የሚገባዉ መሰረቱ #እምነት ነዉ፡፡ #እምነት የመጀመሪያዉ ነዉ የመጨረሻዉ ግን አይደለም

👉#በሁለተኛ አንድ ሰዉ ለመዳን #ሚስጥራትን_መፈፀም ነዉ።በቤተክርስቲያን የተለያዩ ሚስጥራት አሉ።በተለይ ደግሞ ከመዳናችን ጋር ቀጥተኛና ሊታለፍ የማይችል ግንኙነት ያላቸዉን መሰረታዊ ምስጢራት አንድ ሰዉ ለመዳን መፈፀም ይኖርበታል፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ነገረ ድህነትን ክፍል 2 ይቀጥላል።👈

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
ፌጦን፣ ዝንጅብልንና ማርን በተመለከተ
እኔ ዘመዴ ያለኝ መረጃ
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉በነጋዴዎች ምክንያት የጸኑቱ፣ እስከ አሁንም ቃሉን በመጠበቅ በተስፋ እንደ ቃሉ በቤቱ ፀንተው ያሉቱ እንዳይደናገጡ ይሄን ጻፍኩላችሁ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
#ETHIOPIA |~ እነ ፌጦን፣ ቀበርቾ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ሎሚ፣ ማር፣ ዝንጅብልና ጦስኝን በተመለከተ ማንቁርቴን አንቃችሁ ለጠየቃችሁኝ ጓደኞቼ በሙሉ ይድረስልኝ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
#ሥጋዬ_እውነተኛ_መብል_ደሜም_እውነተኛ_መጠጥ_ነውና_ሥጋዬን_የሚበላ_ደሜንም_የሚጠጣ_በእኔ_ይኖራል_እኔም_በእርሱ_እኖራለሁ_ሕያው_አብ_እንደላከኝ_እኔም_ከአብ_የተነሣ_ሕያው_እንደምሆን_እንዲሁ_የሚበላኝ_ደግሞ_ከእኔ_የተነሣ_ሕያው_ይሆናል
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉#ከሰማይ_የወረደ_እንጀራ_ይህ_ነው_አባቶቻችሁ_መና_በልተው_እንደ_ሞቱ_አይደለም_ይህን_እንጀራ_የሚበላ_ለዘላለም_ይኖራል። ዮሐ 6፥ 53-58 ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉እኔ የማውቀው የነፍስና የሥጋ መድኃኒት ይሄ ነው። እናም ጎዶኛዬ እርግጡን ልንገርህ አይደል ንስሐ ካልገባህ አትድንም። ሥጋወደሙ ካልተቀበልክ አትፈወስም። እኔ የማውቀው መድኃኒት ይሄ ነው። የእሳት ባህር የሚያሻግር፣ ከሲኦል እሳት የሚያተርፍ፣ ከገሀነመ እሳት የሚያስመልጥ፣ ከዲያብሎስና ሠራዊቱ ተረግጦ ከመገዛት ነፃ የሚያወጣህ የክርስቶስን ሥጋና ደም መብላት መጠጣት ብቻ ነው። እኔ የማውቀው፣ ቤተ ክርስቲያኔም የነገረችኝ መድኃኒት ይሄው ነው።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉በወረርሽ ጊዜ አካባቢን ማጽዳት፣ የግል ንጽሕናን መጠበቅ ሲሠራበት የኖረ ነው። እነ ፌጦ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ጎመንና ቃሪያ ወትሮም ቢሆን በቀላሉ አይገኙም እንጂ በቀላሉ ከተገኙ ለሥጋችን ሸጋ ናቸው። ከኮሮናንም ሆነ ከኮሌራ ግን የሚፈውስህ ከልብ የሆነ በእምነት የምትጸልየው ጸሎት፣ በፈጣሪ ፊት የምትንበረከከው ስግደት፣ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር በፍጹም ልብ መመለስ ናቸው እንጂ ፌጦ ቀበርቾ ዝንጅብልም ከሞት አያተርፍም።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉እናም በንስሐ ሳሙና ታጠብ ስትባል አንተ አራዳው ላክስ ሳሙና አጃክስህንና ቢ29 ሳሙናህን ይዘህ እጅህን ስትፈትግ ትውልልኛህ። ሥጋውን ብላ ደሙንም ጠጣ ስትባል አንተ ብልጡ ፌጦ በማር ይሻለኛል ብለህ ተሸብረህ ሰው ታሸብርልኛለህ። ይሄ እንደውም የማርና የቅመማ ቅመም ነጋዴዎች ሴራ እንዳይሆን እጠረጥራለሁ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ቆይ ምን እያሰብክ ነው ግን ትጦዛለህ እንዴ አሁንም እጅን በመታጠብ ቢሆን ከአውሮፓ በላይ እጁን የሚታጠብ አለ እንዴ ነጭ ሽንኩርት ፌጦና ዝንጅብልን በመመገብስ ቢሆን ጃፓንና ኮርያን ቻይናንም የሚያህል አለ እንዴእሱ አይደለም የሚያድንህ። መድኃኒቱ ንስሐ መግባት፣ ሥጋወደሙ መቀበል ብቻ ነው። ቢመርህም ቢጨንቅህም እውነቷው ይሄው ነው። አውቃለሁ ይጨንቃል። ግን ምንም ልረዳህ አልችልም።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉እናም መድኃኒቱ ይኸው ነው። ፌጦ ለመግዛት እንዲህ መከራ ከምታይ በንፁሕ ልብ አንዲት አቡነ ዘበሰማያት ብትጸልይ ባህር ትከፍላለህ፣ የመጣውን መቅሰፍት ታስመልሳለህ። እናም ወዳጄ ብዙም ብልጥ አትሁን። አራዳም አትሁን።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ሀገር ስትዘርፍ፣ ስታመነዝር፣ ስትሰርቅ፣ ስትቀጥፍ፣ ስትዋሽ፣ ስትገድል፣ ደሀ ስትላቅስ ኖረህ ከርመህ። አንተ ብልጡ፣ አንተ ስማርቱ በፌጦ ልታመልጥ እ አራዶ በቁሩንፉድ ልትሸውድ ሞኝህን ብላ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉መጀመሪያ ጨክን። ትንፋሽህን ሳብ ሰብሰብ አድርግና ጨክነህ ለንስሀ ፍጠን። ብትኖርም፣ ብትሞትም ራስህን ለካህን አስመርምር፣ ሥጋወደሙ ተቀበል፣ በጸሎት ትጋ፣ ጸበልህን ተቀባ ጠጣ፣ እምነትህን ተቀባ ተዳሰስብትም። ከዚህ በላይ መድኃኒት የለም። ጨውና የማይነቅዝ እህል ከቤትህ አይጥፋ። ደህና ሁን ብልጦ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉#በዚያን_ወራት_እግዚአብሔር_ከፈጠረው_ከፍጥረት_መጀመሪያ_ጀምሮ_እስከ_አሁን_ድረስ_ያልሆነ_ደግሞም_የማይሆን_የመከራ_ዓይነት_ይሆናልና_ጌታስ_ወራቶቹን_ባያሳጥር_ሥጋ_የለበሰ_ሁሉ_ባልዳነም_ነገር_ግን_ስለ_መረጣቸው_ምርጦች_ወራቶቹን_አሳጠረ_በዚያን_ጊዜም_ማንም_እነሆ_ክርስቶስ_ከዚህ_አለ_ወይም_እነሆ_ከዚያ_አለ_ቢላችሁ_አትመኑ
ማር 13፥10-21
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ብልጦ አንተ በገንዘብህ አንድ ማንኪያ ማር፣ በጀንጅብል ውጠህ ልትተርፍ። በንስሐ፣ በሥጋወደሙ ተወስኖ ዕድሜ ልኩን የአምላኩ ባርያና አገልጋይ ሆኖ የኖረው ምስኪኑ አማኝ ገንዘብ ስለሌለው ፌጦና ማር ስለሌለው ሊሞት። ቀልደኛ ነህ ጃል። #ከእግዚአብሔር_የተወለደ_ሁሉ_ዓለምን_ያሸንፋልና_ዓለምንም_የሚያሸንፈው_እምነታችን_ነው።1ኛ ዮሐ 5፥4።
••●◉ ✞ ◉●••
👉፩ኛ #እንግዲህ_ከወዴት_እንደ_ወደቅህ_አስብ_ንስሐም_ግባ_የቀደመውንም_ሥራህን_አድርግ_አለዚያ_እመጣብሃለሁ_ንስሐም_ባትገባ_መቅረዝህን_ከስፍራው_እወስዳለሁ።ራእ 2፥5።
••●◉ ✞ ◉●••
👉፪ኛ #እንግዲህ_እንዴት_እንደ_ተቀበልህና_እንደ_ሰማህ_አስብ_ጠብቀውም_ንስሐም_ግባ_እንግዲያስ_ባትነቃ_እንደ_ሌባ_እመጣብሃለሁ_በማናቸውም_ሰዓት_እንድመጣብህ_ከቶ_አታውቅም።” ራእ 3፥3
••●◉ ✞ ◉●•
👉፫ኛ #እኔ_የምወዳቸውን_ሁሉ_እገሥጻቸዋለሁ_እቀጣቸውማለሁ_እንግዲህ_ቅና_ንስሐም_ግባ_እነሆ_በደጅ_ቆሜ_አንኳኳለሁ_ማንም_ድምፄን_ቢሰማ_ደጁንም_ቢከፍትልኝ_ወደ_እርሱ_እገባለሁ_ከእርሱም_ጋር_እራት_እበላለሁ_እርሱም_ከእኔ_ጋር_ይበላል
ራእ 3፥19-20
••●◉ ✞ ◉●••
👉በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።
እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው። ራእ 3፣ 15-16 ይልሃልና ከወዲሁ አሁንም ቢሆን ምርጫህን አስተካክል።
••●◉ ✞ ◉●••
👉ማታ ማታ ተሰብስበህ ፊልም ከምታይ፣ የባጥ የቆጡን ከምትቀባጥር እስቲ ነጠላችሁን ለበስ አድርጋችሁ በቤተሰብ ደረጃ ሰብሰብ ብላችሁ ውዳሴ ማርያም ጸልያችሁ፣ ከመዝሙረ ዳዊትና ከወንጌል ጥቂት ቃል ተካፍላችሁ፣ ጥቂትም ሰግዳችሁ ተኙ። ወንድ ከሆንክ ይሄን ሞክር። ተነስና ጨከን ብለህ ሞክር።

ሻሎም ! ሰላም !

💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መጋቢት 8/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
👉ጎበዝ ትልቁን ነገር ለፈጣሪ እንስጥ…….ነገር ግን እኛም የአቅማችንን እንጠንቀቅ የአንድ ሰው ጥንቃቄ በኛ ኢትዮጵያውያን ኑሮ እራሱን እንኳን አያድነውም ……ሁሉም ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉ግንዛቤ ያላችሁ ደግሞ እንደ አሉቧልታ አትቁጠሩት……..ግደታ ለመንቃት 300 … 400 ሰዉ ሙቶ ማየት የለብንም……..እግዚአብሔር አለ እያላችሁ የምትዘናጉ ሰወች ተጠንቀቁ ።
••●◉ ✞ ◉●••
👉እግዚአብሔር ትሰሙበት ታዩበት አይንና ጆሮ ታገናዝቡበት ህሌና ሰጥቷችኋል…ችግር ሲፈጠር በፈጣሪ ከማዘን አባቶች የሚሉትን መንግስት የሚለዉን ስሙ እና ተግብሩ…
••●◉ ✞ ◉●••
👉እግዚአብሔር ከዚህ በላይ እንዴት ያስተምረን።አዉሮፓን ተመልከቱ እያለቁ ነው ….እኛን ተመልከቱ አሁንም በእግዚአብሄር እጅ ነን ከነሱ እንማር ዘንድ ግዜ ሰጥቶናል……..
••●◉ ✞ ◉●••
👉ሰለዚህ ጥንቃቄ ማድረግ የእምነት መሸርሸር የሚመስላችሁ ሰወች አትሳሳቱ...እኛ ማድረግ ያለብንን እናድርግ ቀረዉን ለፈጣሪ እንስጥ..
••●◉ ✞ ◉●••
👉ቢያንስ እኛ ማድረግ ያለብንን አድርገን ፈጣሪን እናማር፡፡ከቻልን እና አቅሙ ያለን ደግሞ አበል ያሰከራቸው ስብሰባ ሱስ የሆነባቸዉ ሰወችን እናዉግዝ
••●◉ ✞ ◉●••
👉ገጠር መረጃው እና እውቀቱ ለሌላቸው ወገኖቻችን የግንዛቤ ትምህርት እንስጥ……ግዴታ ሃኪም መሆን የለበትም ሰለ በሽታው መከላከያ መንገድ ጥሩ ግንዛቤው ያለዉ ሰው/ መምህራኖች ሊያደርጉት ይችላሉ
••●◉ ✞ ◉●••
በተረፈ
👉በብሄር …
👉በቋንቋ...
👉በዘር ተከፋፍለህ
➡️ሰው ስገድል
➡️ስታፈናቅል
➡️ሴት/እናት / ስደፍር
➡️ቤተ እምነት ስታቃጥል የነበርክ ኢትዮጽያዊ ምነው ያኔ የፈጣሪ መኖር ትዝ አላልህም ነበር…….እግዚአብሔር አለን እያላችሁ ለምትመፃደቁ ከንቱወች……… በአማኞች ዘንድ በደስታም በሃዘንም ቀን ሁሌም እግዚአብሔር
አለ………
ንሰሃ መግባቱ ግን እንዳይረሳ
በተረፈ እግዚአብሔር ይጠብቀን ይርዳን…..
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
ወንድማችሁ ኤፍሬም አረጋ

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
👉#ዘመናችን_ሳይፈፀም_እጁን_ወደኛ_ዘርግቶ_የሚጠራንን_እንስማው#ፈጥነን_በፊቱ_ራሳችንን_እናዋርድ#አቤቱ_እነሆ_አንተን_በድለናል_እኛን_በዐይነ_ምህረት_ተመልከተን#ፍጥረቶችህን_አትጣል_እንጅ#የእጅህ_ፍጥረቶች_ነንና_ከሞት_በኋላ_የሚያስብህ_በመቃብርስ_ተስፋ_የሚያደርግህስ_ማነው#እያልን_ፈጥነን_ንስሐ_እንግባ🔑🔑🔑
••●◉ ✞ ◉●••
(መዝ. ፮:፩-፯::፻፴፰(፻፴፱):፰::ኢሳ.፷፭፡ ፪)
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ሐይማኖት አበው ዘጎርጎርዮስ 37፥11

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
👉ኑዛዜ🙏
••●◉ ✞ ◉●••
✍️ጌታ ሆይ መኖሪያዬ መሥሪያ ቤቴ ነው አልንህ ፣ #መሥሪያ_ቤቱም_እንዳትመጡብኝ_ብሎ_ዘጋአዋቂዎች ስለ እኛ እየተመራመሩ ነው እንተኛ አልን ፣ #እነርሱም_ከአቅማችን_በላይ_ነው_አሉንሰንበትን ሽረን ትምህርት ቤቶችን ከፈትን፣ስድስት ቀን የሠራነው ሳይበቃን በሰባተኛውም ቀን እንሥራ አልን ፤ #ትምህርት_ቤቱም_ለወራት_ተዘጋ_አንድ_ሰንበትን_ሽረን_ሰባቱንም_ቀን_ሰንበት_አደረግኸው
••●◉ ✞ ◉●••
✍️ከምርጫ ግርግር ለመዳን ብለን ውጭ አገር ኮበለልን#እዚያም_ሞት_ቀድሞ_ጠበቀን ይህ መሬት የእኛ ነው ውጣልን ተባባልን ፣ #እጃችሁ_የእናንተ_አይደለም_አፋችሁን_አትንኩ_ተባልንጎዳናው ማረፍ ፈልጎ ለመነህ ፣ #አንተም_ሰምተኸው_ጸጥ_አደረግከውሰማዩን በተበከለ አየር ጋረድነው ፣ #እኛን_እቤት_ስታስቀምጥ_ውበቱ_ፈክቶ_ይኸው_እየሳቀ_ነውበሽታውን ከእንስሳ መጣብን አልን ፣ #በልተውን_ሳይሆን_በልተናቸው_መሆኑን_ረሳን
••●◉ ✞ ◉●••
✍️ጭጋጉ ያደጉ ከተሞችን ሸፍኖ ነበር ፣ #ይኸው_ከዋክብት_ሊያበሩ_መጡአንድ በሽታ ሲመጣ የሚያጠቃው ጥቁሮቹን ነው አልን ፣ #ሁሉም_የሚያቃስትበትን_በሽታ_አመጣህእግዚአብሔር አላመጣውም ሰዎች ለቀውብን ነው አልን ፣ #ክፉዎችን_በክፉዎች_እንደምትቀጣ_ረሳንህ
••●◉ ✞ ◉●••
✍️እኛን አይነካንም ብለን ተመጻደቅን ፣ #እምነታችን_ከካዱት_የተለየ_እንዳልሆነ_አሳየኸንጸሎታችን ልዩ ነው አልንህ#የወንድም_ቀባሪዎችን_ጸሎት_መስማት_መቼ_ጀምረህ_ነውያልታመመውን ካልፈወስን እያልን ነገድን#የታመመ_ሲመጣ_አዳራሹን_ለቀን_ወጣን
••●◉ ✞ ◉●••
✍️እግዚኦ ብንል አልን ቅዱሶቹን አርክሰን ፣ አማኞቹን አውግዘን ፣ ንጹሖቹን ስም ሰጥተን የምትሰማን መስሎን ተታለልን ። አቤት ፣ አቤት እያልንህ እህል እንደብቃለን ። እየጸለይን ሰውን እንዘርፋለን ። የእኔ ዘር ያልሆነ አልይ አልን#እናትና_ልጅን_የማያስተያይ_በሽታ_ተማለን_አወረድንሰው ዘቅዝቀን ሰቀልን#አየር_የሚያሳጣ_ጉድ_መጣብንያለ ፍርድ ሰውን እንደ እባብ ቀጥቅጠን ገደልን#ፍርድ_ቤት_የሚያዘጋ_የበሽታ_ባለሥልጣን_ከተፍ_አለብንየገደልነውን ሬሳ አይነሣም ብለን ፎከርን#ቀባሪ_የሚያሳጣ_ደዌ_ጎተትንጠግበን ነበረ ፣ የምንናገረውን መመጠን አቅቶን አፍስሰነው ነበረ ። በሰማይ ደመና እንጂ ዙፋን አልታየንም ነበር ። ጌታ ሆይ እንዴት ታዘብከን ።
••●◉ ✞ ◉●••
✍️በጣም ተገፋፋን ፣ አብሮ አደጎች ተካካድን ፣#በሚያራርቅ_ሕመም_አትነካኩ_ተባልንሥልጣኔአችንን የሚያቆመው ኃይል የለም ብለን ተናግረን ሳንጨርስ#ጉንፋን_አቆመን ። የአንዲት አገር በሽታ ነው ብለን ስንሳደብ #የሁሉም_አገር_እንዲሆን_አደረግንተፋፍገው የሚኖሩ ድሆች በሽታ አያጣቸውም አልን#ቤተ_መንግሥት_የሚኖሩ_ሲጠቁ_አየንፈረንጅ አገር ሂዶ መምጣት ልዩ ነገር መሰለን#ዛሬ_የሚያሳስበን_ሆነግደለኝ እያልንህ ስንለምንህ ከረምን#ዛሬ_አልኮል_ለመግዛት_ተሰለፍን
••●◉ ✞ ◉●••
✍️የዛሬውን ችግር ሳናይ የትላንቱን አደነቅን#ይባስ_እንደማያልቅ_አስተማርከን_ሁሉም_ነገር_አንድ_ቀን_ቀጥ_እንደሚል_ዋዜማውን_አሳየኸንቃልህን ለመስማት ኮራን ፣ የተማርኩት በቂ ነው አልን#ስብከተ_ወንጌል_የለም_ተባልን_ቅዳሴ_ለማስቀደስ_ተፈተንን_በየቤታችሁ_ሁኑ_ተባልንሰው ሰብስቦ ማስተማር ሰለቸኝ አልን#ባዶ_ቤት_መስበክ_ጀመርን ። ሰው ሰላም እንዳይለን እንሸሽ ነበር#በአዋጅ_አትጨባበጡ_ተባልን_የጠላነው_መነካካት_ዛሬ_ሕግ_ሆኖ_መጣመተቃቀፍ አስጠላን#የሚተቃቀፉትን_ፖሊስ_ይለይ_ተባልንጨረቃ ላይ ደርሰናል ብለን ስንኮራ ገና #እጃችሁን_ታጠቡ_የሚል_ምክር_እንሰማለንጠላት አለብኝ እያልን ስንለፈል#በእጃችሁ_ዓይናችሁን_እትንኩ_እጃችሁ_ነው_ጠላታችሁ_ተባልን
••●◉ ✞ ◉●••
✍️ለትዳራችን የሚሆን ጊዜ አጥተን ተረሳስተን ነበር#አሁን_ሃያ_አራት_ሰዓት_አብረን_ስንቀመጥ_ተፋጠጥንሥራችንን ጠልተን ጥቁር ሰኞ እንል ነበር#ዛሬ_መሥሪያ_ቤቱ_ናፈቀንሰዓቱ ሳይሞላ ከሥራ ወጥተን ነበር#ዛሬ_ትርፍ_ሰዓት_መሥራት_አማረንከሠራነው ላይ አሥራት ለመስጠት ተፈትነን ነበር#ዛሬ_ግን_ያስቀመጥነውን_ያለ_ደስታ_እንበላለን
••●◉ ✞ ◉●••
✍️ጌታ ሆይ ጣትህን ብትዘረጋ እንዲህ የሟሸሽን ክንድህን ብትዘረጋ የት ልንገባ ነው ብናኝ ልጆችህን ይቅር በለን ። አክብረኸን ማረን እንጂ አክብረኸን እንዳትጣላን ። እኛ ሰው🙏 ፣ አንተ አምላክ ነህ🙏 ። እባክሀ ይቅር በለን ። በመልካም አስበን ።
••●◉ ✞ ◉●••
✍️ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ ። ለዘላለሙ አሜን ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉Finote_kidusan
መጋቢት 21 ቀን 2012 ዓ.ም


🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
#ይድረስ_በቤት_ላለች_ቤተ_ክርስቲያን
••●◉ ✞ ◉●••
👉ሥላሴ በመዓታቸው ውስጥ ምህረት አለ! ወቅቱ ዓለም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የተዋከበ ሩጫ የበዛበት የውድድርና የፉክክር ኑሮዋን አቁማ ጸጥ ረጭ ያለችበት ጊዜ ነው፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት በእነርሱ የማይደርስ መስሎዋቸው ተዘናግተውና ቀልደው የነበሩ ሁሉ ለጸጸት እንኳን ጊዜ አላገኙም፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በእኛም ሀገር የበሽታው ተጠቂዎች በመገኘታቸው በሽታው እንዳይዛመትና የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በማሰብ መንግስት የበኩሉን እያደረገ ይገኛል፡፡ #እኛም_አምላክነሰ_አምላከ_አድኅኖ_ወፍናዊሁኒ_ለሞት_ዘእግዚአብሔር_ውእቱ_አምላካችንስ_የደኅንነት_አምላክ_ነው_ከሞት_መውጣትም_ከእግዚአብሔር_ነው መዝ 67፥20 እንደተባለ #በእግዚአብሔር ምኅረትና ቸርነት እንጂ በራሳችን ጥንቃቄ ብቻ የምንድን ባይሆንም ከወረርሽኙ ለመዳን ያስችላሉ የተባሉ ጥንቃቄዎችን ማድረግ እንደሚገባ የታመነ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉በነገረ ድኅት ትምህርታችን ቤክርስትያን እንደምታስተምረን አዳኝ መድኃኒት የሆነው አምላካችን የማዳን ሥራውን የሠራልን ቢሆንም በመዳን ሕይወት ውስጥ የሰው ልጆች ድርሻ አላቸው፡፡ በነገረ ድኅነት ትምህርት ማመን በጎ ምግባራትን መሥራት ምሥጢራትን መፈጸም የሰው ልጅ ድርሻ ነው፡፡ የነፍስ ድኅነትን ማደል ደግሞ #የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፡፡ እንደዚሁ ሁሉ በሥጋ ሕይወትም #ከእግዚአብሔር መዓትም ለመዳን የሰው ልጆች ድርሻ አላቸው፡፡ በዚህ መሠረት ነው ቤተክርስትያን ጥንቃቄዎችን እንድናደርግ የምትነግረን፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉ይህ በአሁኑ ወቅት ያለው የኮሮና ወረርሽኝ መዓት የሚመስል ጉዳይ ላስተዋለው እና ለተጠቀመበት ሰው በውስጡ ምሕረት አለው፡፡አበው ሲናገሩ #ሥላሴ_በመዓታቸው_ውስጥ_ምህረት_አለ ይላሉ፡፡ በዮናስ ሕይወት ውስጥ ከመርከብ ወደ ባሕር መጣል በአሳ ነባሪ መዋጥ መዓት ነው፤ በውስጡ ግን ለዮናስም ለነነዌ ሕዝብም ምሕረት ነበረው፡፡ ከዚህ አንጻር ከሰሞኑ ወላጆች ከሥራ ልጆች ከትምሀርት ቤት ቀርተው ቤት ውስጥ መዋል አስፈላጊ በመሆኑ በነዚህ ቤት ውስጥ በምንውልባቸው ጊዜያት እንዴት ማሳለፍ ይገባል የሚለው ብርቱ ጉዳይ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ በመገናኛ ብዙሃን የሚነገሩን የጥንቃቄ መረጃዎች እንዳሉ ሆነው የሚከተሉትን ብናደርግ መዓቱን በምኅረት ለመለወጥ ያስችሉናል፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
#ሀ_የቤተሰብ_ጸሎት
••●◉ ✞ ◉●••
👉ጸሎት የሚደረገው በቤተክርስቲያን ብቻ ይመስል በቤታችን ጸሎት ማድረግ ያልለመድን፤ የቤተሰብ ጸሎት የሌለን ቤተሰቦች ይህ ጊዜ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልሞና በጻፈው መልእክቱ ላይ #የኢየሱስ_ክርስቶስ_እስር ጳውሎስ_ወንድሙም_ጢሞቲዎስ_ለተወደደውና_አብሮን_ለሚሠራ_ለፊልሞና_ለእኅታችንም_ለአፍብያ_ከእኛም_ጋር_አብሮ_ወታደር_ለሆነ_ለአክርጳ_በቤትህም_ላለች_ቤተክርስቲያን_ከእግዚአብሔር_ከአባታችን_ከጌታም_ከኢየሱስ_ክርስቶስ_ጸጋና_ሰላም_ለእናንተ_ይሁን ፊል 1፥1-3 ብሎታል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉የክርስቲያን ቤት ጸሎት የሚደርስበት ምልጃ የሚፈጸምበት ራሱን የቻለ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በቤትህ ላለች ቤተክርስትያን ያለው፡፡ በቅዳሴ ጸሎታችን ላይ #ተዘከር_እገዚኦ_ማኅበረነ_ባርኮሙ_ወጸግዎሙ_ከመይኩኑ_ለከ_ዘእንበለ_ክልአት_ወኢጽርዓት_ይግበሩ_ፈቃደከ_ቅድስት_ወብጽዕት_ወረስዮሙ_ቤተ_ጸሎት_ወቤተ_ንጽሕ_ወቤተ_በረከት … እንደሚል አይደለም ቤታችን ሕይወታችንም የጸሎትና የበረከት ቤት እንዲሆን ያስፈልጋል።
••●◉ ✞ ◉●••
👉ብዙዎቻችን በሥራ በኑሮ ሩጫና ውጥረት የግል ጸሎታችንን ተረጋግተን ማድረስ ያቃተን፤ ከቤተሰብ ጋር አብረን የምናሳልፈው ጊዜ ያጣን ለብዙ ጉዳዮች ጊዜ አጥሮብን የከረምን ሰዎች ነን፡፡ አስበንበት በፍቅር ልናደርገው የሚገባንን የቤተሰብ ጸሎት ዛሬ በዚህ በሽታ ምክያትም እንኳን ጊዜ ስናገኝ ብንጀምረው መዓቱን ወደ ምኅረት ቀየርነው ማለት ነው፡፡ የጀመርን ደግሞ ማጽናት ይገባናል፡፡ የቤተሰብ ጸሎት በባልና ሚስት መካከል ያለን ፍቅር ያበረታል በልጆች እና ወላጆች መካከል ያለ መግባባትን ያጠናክራል ልጆችን በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲያድጉ እና ከፈተና እንዲጠበቁ የሚያስችላቸውን የጸሎት ሕይወት እንዲለማመዱ ያስችላል በአጠቃላይ የቤተሰቡን መንፈሳዊ ሕይወት በማሳደግ #ለእግዚአብሔር ምሥጋና የሚቀርብበት የቅዱሳን በረከት ያለበት እውነተኛ ቤተክርስትያን እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በሐዋ 10፥1-3 የተገለጸው ቆርኔሌዎስ በዘጠኝ ሰዓት #ጸሎትህና_ምጽዋትህ_በእግዚአብሔር_ፊት_መታሰቢያ_እንዲሆን_አረገ የሚለውን የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማው ከቤተሰዎቹ ሁሉ ጋር በነበረው የቤተሰብ ጸሎት ውስጥ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉በዚህ ሰሞን ገድለ አቡነ ሐብተማርያም ገድለ ቅዱስ ቂርቆስን አድርሱ ድገሙ የሚል መልዕክት ከገዳማት ተልኳል በሚል መግዛትና ማድረስ ጀምረናል፡፡ ከወረርሽኝ የሚታደግ ከመዓት ለመዳን ቃል ኪዳን ስላላቸው፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ቸርነትና ሥጦታው ነውና ልንበረታ ይገባናል፡፡ ወትሮ በረከታቸው እንዲያድርብን እንደነርሱ በፍቅር ወደ እግዚአብሔር ከፍ ያልን እንድንሆን በቤታችን ልንደግመው ይገባን ነበር፡፡ ሆኖም ዛሬ መጀመራችንም መልካም ነው፡፡ የምንቀጥልበት የምናጸናው ሊሆን ይገባል፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
#ለ_የአርምሞ_ጊዜ
••●◉ ✞ ◉●••
👉5አርምሞ ዝምታ ነው፡፡ ዝምታ ሲባል ከንግግር ጸጥ ማለትን ብቻ አይደለም፡፡ በልብ ካለ ትዕቢት እና ማጉረምረም ከቂምና ከበቀል ሀሳብ፤ ለዚህ ዓለም ኑሮ መሳካትና ምኞት በሀሳብ ውጣ ውረድ ከመባዘን አረፍ ማለትን ይጨምራል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አርምሞ የእግዚአብሔርን ጥብብና ቸርነት ለማድነቅ አና ለማመስገን መንፈሳዊ ምሥጢራትን ለመመርመር ይጠቅማል፡፡ ሰይጣን ዓለምን በሁካታና በጥድፊያ የሚሞላት የአርምሞን ጥቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ሰዎች በአርምሞ ውስጥ ከሆኑ የእግዚአብሔርን ቸርነት ማሰብና ፍቅሩን መገንዘብ ይችላሉ፤ የዓለምን ከንቱነት ተረድተው ወደ ንስሐ ይመለሳሉ እናም ከሰይጣን ወጥመድ ይድናሉ፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉በቅዱሳት መጽሐፍት የእግዚአብሔርን ቸርነት ከማድነቅ የተነሳ የሚመጣ አርምሞ እናያለን፡፡ #ናርምም_እስመ_ኢንክል_ፈጽሞ_ጥንቁቀ_ነጊረ_በእንተ_ዕበዩ_ለውእቱ_ገባሬ_ሰናያት_የእርሱን_የገናንነቱን_ነገር_ፈጽመን_መናገር_አንችልምና_ዝም_እንበል እንዳለ ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ፡፡ በሌላ በኩል ሰዎች ምንም ማድረግ በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ #የእግዚአብሔር_ፈቃድ_ይሁን_ብሎ_ዝም ማለት አለ፡፡ ሐዋ 21፡14
••●◉ ✞ ◉●••
👉በዚህ ወቅት በቤታችን ስንሆን የሚኖረን አርምሞ ፈጣሬ ዓለማት #እግዚአብሔር በዓይን በማይታይ ትንሽ ፍጥረቱ ሁሉን የሚችል ሁሉን የተቆጣጠረ የመሰለውን ዓለም እንዴት ጸጥ እንዳደረገው አስተውለን በእኛም ሕይወት ውስጥ ሩጫችን ብቻ፣ ገንዘባችን ብቻ፣ እውቀታችን ብቻ ሁሉን የሚሠራ መስሎን የሮጥንበትን ጊዜ ቆም ብለን የምናስተውልበት ጊዜ ቢሆን መልካም ነው፡፡ አንዳንዶቻችን የሥራ ቀናት አልበቃን ብለው ዕለተ ሰንበትን እንኩኳን ማክበር አቅቶን እንሮጥ ለነበ
ርን ፈቃድህ ይሁን ማለት ላቃተን እርሱ እንዲህ ሁሉን ማቆም የሚችል መሆኑን ስላሳየን ነገን እንዴት መኖር እንደሚገባን የምናስብበት ጊዜ ሊሆን ይገባል፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
#ሐ_የዕርቅ_ጊዜ
••●◉ ✞ ◉●••
👉ኑሮአችን እና ቤታችን እንደየመልካችን ብዙ ዓይነት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ክርስትና ግን ሁላችንን አንድ ያደርገናል፡፡ ይህ አንድነት የምንተዋወቀውን አብሮን ያለውን ብቻ ሳይሆን በአካል አብረን ያልሆነውን የማንተዋወቀውንም እንኳን አንድ በሚያደርገን #በክርስቶስ ሥጋና ደም ለአንድ መንግስተ ሰማያት የተጠራን የበጎ ሠርግ ታዳሚዎች በመሆናችን ያገኘነው አንድነት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ለዚህ አንድነት ሳይሆን ለሥጋ ጠባያችን አድልተን ያልተገባንንን ሥራ የሠራንበትንና ወደማይገባን ያዘመምንበትን ትተን ከራሳችን ጋር የምንታረቅበት ጊዜ ቢሆን መዓቱን በምኅረት ይመልሰዋል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉በሌላ በኩል በሕይወታችን ያጠራቀምናቸው ብዙ ጉዳዮች ይኖሩናል፡፡ በተለይ ባልና ሚስት ከቅዱስ ቁርባን ያራቁን ሰላማችንን የነሱን ፍቅራችንን ያቀዘቀዙብንን ጉዳዮች ልናጠራበት በመካከላችን ግድግዳ ወደመሆን እያደጉ ያሉ ትንንሽ የሚመስሉ ጉዳዮች ላይ እንድንነጋገርበት #እግዚአብሔር የሰጠን እድል አድርጎ መጠቀም ይገባል፡፡ #ሎቱ_ስብሐት_ለእግዚአብሔር ምሥጋና ይግባውና ክፉን ያርቅልን ምናልባት በሩቅ የሰማናቸው ጉዳዮች ተጠናክረው በእኛም ሀገር ከገጠሙን ለንስሐ ይቅር ለመባባል ዕድል የማናገኝ ልንሆን እንችላለን፡፡ ያ እንዳይሆን ዛሬ ደህና ሳለ የጭንቅ ቀን ሳይመጣ ራሳችንን ማየት ይገባል፡፡ ቁጭ ብለን ስለበሽታው በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የምንሰማውን ዜና እና ቀልድ ብቻ እየሰማን እያወራን ውለን የምናድር ወይም በፍርሃትና በጭንቀት የምንከርም ሰዎች መሆን አይገባንም፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
#መ_የውይይት_ጊዜ
••●◉ ✞ ◉●••
👉ልጆች ከትምህርት ቤት ወላጆችም ከሥራ ቀርተው ቤት እየዋሉ ያለበት ይህ ጊዜ ወላጆች እርስ በራሳቸውና ከልጆቻቸው ጋር የሚወያዩበት የሚያወሩበት ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ልጆቻችንን እኛ ካደንግበት አስተዳደግ ውጭ ነው የምናሳድገው፡፡ እኛ በችግር አድገን እነርሱን በምቾት ለማሳደግ የምንጥር እኛ በግርፊያ አድገን እነርሱን በልምምጥ የምናሳድግ፤ እኛ በረሃብ አድገን ልጆቻችን ምግብ ተለምነው የሚበሉ፤ እኛ ልጅ በእድሉ ያድጋል በሚል ፈሊጥ አድገን እኛ ግን ልጆቻችን ጌቶቻችን አድርገን የምናሳድግ ወዘተ አለን፡፡ ይህ ግን የራሳችንን የኑሮ ቁጭት ከመወጣት ባለፈ የምንፈልገውን አይነት ልጆች ያደርጋቸዋል ወይ የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉ለወላጆች ትልቁ የሕይወት ስኬት ሊሆን የሚገባው ልጆቻቸውን በሚገባ አሳድጎ ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ ነው፡፡ ልጆች #ከእግዚአብሔር የተሰጡን የምናተርፍባቸው መክሊቶቻችን ናቸው፡፡ በሚገባ ማሳደግ ስንልም በእውቀት፣ በጥበብ፣ በሞገስ ያደጉ አካላዊ ዕድገታቸው ከመንፈሳዊ ሕይወታቸው የአስኳላ እውቀታቸው ከመንፈሳዊ እውቀታቸው ወዘተ ተገናዝቦ ለራሳቸው ለቤተሰቦቻቸው ለሀገር ለቤተክርስትያን የሚጠቅሙ ልጆች እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ ይህ የሁሉ ወላጅ ፍላጎት ቢሆንም ብዙዎቻችን በሥራና በተለያዩ ጉዳዮች ከመጠመዳችን የተነሳ ይህን ኃላፊነት ትምህርት ቤቶች ብቻ የሚወጡልን መስሎን ጥሩ ትምህርት ቤት የምንለውን በመፈለግ የምንችለውን ብቻ ሳይሆን ከምንችለውም በላይ እየከፈልን የምናስተምር ብዙዎች ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉በዚህ ሰሞን ግን ልጆቻችን ከትምህርት ቤት ቀርተው እኛም ከሥራ ቀርተን እቤት ውስጥ አብረን የምንውልባቸው ቀናት ሆነዋል፡፡ እነዚህ ቀናት ሁላችንም የመምህራንን ኃላፊነት የምናስተውልበት እና ትልቁን የወላጅነት ሚናችንን የምንወጣበት ቢሆን ጥሩ ነው፡፡
ስለዚህም ከልጆቻችን ጋር የውይይት ጊዜ ቢኖረን ደጋግመው ስለኮሮና በመገናኛ ብዙሃን በመስማት እንዳይሳቀቁ በሌላ በኩል ልቅ አድርገናቸው ከቤት እየወጡ የጨዋታና የግድለሽነት ጊዜ አድርገውት ለበሽታ ተጋልጠው ወላጆችን አረጋውያንን እንዳያጋልጡ ጥንቃቄ ከማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ወይም ቤት ውስጥ ብቻቸውን በመዋል ለክፉ ፈቃዳትና ልማዳት እንዳይጋለጡ ጊዜያቱን በአግባቡ መጠቀም ብልህነት ነው፡፡ ስለትምህርታቸው ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው በአጠቃላይ ስለቤተሰባዊ ኑሮአችን በመወያየት ብናሳልፈው ጥቅሙ ብዙ ነው፡፡ በተለይ በልጆቻችን ሕይወት እንዲያድጉ የምንፈልጋቸውን እሴቶችን አስበን መደበኛም ኢመደበኛም ውይይት በማድረግ ብንጠቀምበት መዓቶሙ በከረቶሙ የሚለውን ተገበርነው ማለት ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉ለምሳሌ በዚህ የውይይት ጊዜ እናትና አባት በእውነትና በግልጽ ከልጆቻቸው ጋር ልጆች እኛን እንዴት ያዩናል የሚለውን ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡በአንድ ወቅት በሲቪል ምሕንድስና ሙያ የተሰማራ አንድ አባት ልጁ የሚማርበት ትምህርት ቤት ግብረ ገብ ትምህርት ስለነበረው ምን እንደተማረ ሲጠይቀው ስለሙሴ ታሪክ ተማርን ይለዋል፡፡ ታሪኩን ንገረኝ እኔ አላውቀውም ይለዋል፡፡ ልጁ የሙሴን ታሪክ እየተረከ ፈርዖን እያባረራቸው ቀይ ባሕር ሲደርሱ ሙሴ ሕዝቡን ድልድይ ሠርቶ አሻገራቸው ይለዋል፡፡ አባት ተበሳጭቶ እንዴ ማነው እንደዚህ የነገራችሁ ሲለው ሚስ ናት ይላል፡፡ ልክ አደለም ድልድይ ሠርቶ አላሻገራቸውም ይልና የተሳሳተ ታሪክ ትምሀርት ቤቱ ለልጁ በመናገሩ ተናዶ ሙሴ ያሻገራቸው ድልድይ ሠርቶ ሳይሆን በተዓምራት በበትሩ ባህሩን ከፍሎ ነው ሲለው አባዬ ሚስ የነገረችን እኮ እንደዛ ነው ይለዋል፤ ታዲያ አንተ ለምን እንደዚህ ነገርከኝ ሲለው አታምንም ብዬ ነው አለው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉ልጆች ስለእኛ እኛ ከምናስበው በላይ ይረዱናል የረሳቸውም ግንዛቤ አላቸው፡፡ ስለዚህ ስለወላጆቻቸው የሚሰማቸውን እንዲናገሩ ጥፋት ብለው የሚያስቡትን እንዲናገሩ እድል መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ለልጅ ከሳቁለት … በሚል ተረት ለልጆች ፊት ማሳየት አይገባም ልጅ ደግሞ ከወላጅ እኩል ካወራ መታዘዝ እምቢ ይላል በሚል የከረመ ሥጋት በጉልበት ብቻ ለማሳደግ መሞከር የሚቻል አይደለም፡፡ ውጤታማም አይሆንም፡፡ በእውቀትና በጥበብ ፍቅርን ከምክርና ከተግሳጽ ጋር በማድረግ ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉በሌላ በኩል ወላጆች ለልጆቻቸው ሊሆኑ የሚገባው ትልቁ ነገር ምሳሌ መሆን ነው፡፡ ልጆቻችንን መሆን ያለባቸውን ልንመክራቸው እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን እነርሱ ከምንነግራቸው ይልቅ የምንሠራውን ያያሉ፡፡ በዚያ ይመራሉ፡፡ የምንሠራውና የምንናገረው ነገር ከተለያየ ደግሞ ትልቅ የሕሊና ግጭት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህንን ለማስታረቅ የራሳቸውን መንገድ ይጠቀሙና በወላጆቻቸው ፊት የሚኖራቸው ጠባይና በሌላ ቦታ የሚኖራቸው ጠባይ የተለያየ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ልጆች እኛ የምንላቸውን ዝም ብለው እንዲቀበሉ በማድረግ የምናሳዳግቸው ከሆነ ለሁሉ ነገር እሽ ባይ ይሆኑና በቀላሉ በሌሎች ተጽእኖ ውስጥ የሚወድቁ ይሆናሉ፡፡ በቤታችን ውስጥ በጥሩ ክርስትያናዊ ሥነምግባር ለማሳደግ የምንጥር ሆነን ነገር ግን የትምህርት ቤትና የውጭ ተጽእኖ ምን እያደረጋቸው እንደሆነ ለማወቅና ለመረዳት ጊዜ ያጠረን ስለትምህርታቸው ስለዝንባሌያቸው ወዘተ ትኩረት ሰጥተን ማሰብ ያልቻልን ወላጆች ይህ ጊ
ዜ መልካም አጋጣሚ ይሆናል፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
#ሠ_የንባብ_ጊዜ
••●◉ ✞ ◉●••
👉መጽሐፍ በመግዛት የበረታን ለማንበብ ግን ጊዜ የሌለን ብዙዎች ነን፡፡ አንድ ወዳጄ በአንድ ወቅት ያጫወተኝ ታሪክ ሰውየው የአንድ ድርጅት ባለቤት ሲሆን ጥሩ ክርስትያን ነው፡፡ የጸሎት መጽሐፍት የተባሉ ድርሳናት ገድላት መልክዓ መልክ ሁሉ ይዞ ይዞራል፡፡ቢሮው ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን አያነባቸውም፡፡ ቤተክርስትያን ጠዋት ደርሶ ትንሽ ጸሎት አድርጎ ወደ ቢሮ ይገባና ቁጭ ብሎ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ድርሳናቱን እና መልክዓ መልኩን ሁሉ አንድ በአንድ ይሳለማል፡፡ አንድ ቀን ይህ ወዳጄ ይህን ሲያደርግ ያገኘውና ምንድነው ጸሎት አልጨረስክም እንዴ ብሎ ቢጠይቀው የራሴን አድርሼ መጥቻለሁ እነዚህን ድርሳናት እና ገድላት አባቶቼ ያነቡልኛል እኔ እሳለማለሁ ይለዋል፡፡ ይህንን ሁል ቀን እንደሚያደርግ ይነግረዋል ይህ ትልቅ እምነት ቢሆንም ደሞ እንደዚህ ከሥራ በምክንያትም ቢሆን እረፍት ሲገኝ ያላነበብናቸውን ገድላት ድርሳናት መጽሐፍት ሁሉ የማንበብያ ወቅት ቢሆን ጥሩ ነው፡፡ ብዙዎች የተማርን የምንባለውም ካነበብን ብዙ ጊዜ ከመሆኑ የተነሳ ከእውቀት ነጻ ወደ መሆን ደርሰን በስሜት ብቻ የምንኖር ሆነናል፡፡ ማን ያውቃል አምላክ ይህንን አይቶ የማንበቢያ ጊዜ ሰጥቶን ቢሆንስ፡፡ ወደ እውቀት ወደ ማስተዋል ወደ ማመዛዘን እንድንመለስ ለማድረግ፡፡#ወደ_አንተ_እንዳይቀርቡ_ለማድረግ_በልባብና_በልጓም_ጉንጫቸውን_እንደሚለጉሙአቸው_ልብ_እንደሌላቸው_እንደ_ፈረስና_እንደ_በቅሎ_አትሁኑ መዝ 31፥14
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉በአጠቃላይ ሥላሴ መዓታቸው ምሕረት ነው እንደተባለ ይህንን ጊዜ ስለመጣው ነገር በማውራት ብቻ ወይም በመሰቀቅ ሳይሆን በሚገባ ብናሳልፈው የምናተርፍበት ይሆናል፡፡ መሐሪ ይቅርባይ አምላካችን ምኅቱን እንዲያደርግልንና በዚሁ እንዲያሳልፍልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ 🙏🙏🙏
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
የጽሑፉ አዘጋጅ፡- ቀሲስ ዶ/ር ደረጄ ሽፈራው
አስተባባሪ -፡ የኮቪድ 19 መከላከል ግብረ ኃል ኮሚቴ አ/አ ማዕከል

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ!!!
🙏ማራናታ🙏


💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
#ኦርቶዶክሳዊት_ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን

👉#ሰለቸኝ ሌላ እምነትና አዲስ ነገር ልፈልግ አታሰኘኝም። ሌሎች እንደሚቅበዘበዙት እንዳልቅበዘበዝ ዘወትር ቀዳማዊ፣ ሐዲስ፣ ጧፋጭ፣ ተናፋቂ፣ ተፈላጊ፣ ሰርክ አዲስ የሆነውን ምሥጢሯን በማስተማር ታስደምመኛለች።

👉 #በሰው ፈራጅና ሰዎችን ነቃፊ እንዳልሆን ታደርገኛለች። በደካማነቴ ያልጨረስኩትንና ያልደረስኩበትን እያሳየች ለሌሎች ከማዘን አልፌ ወደ ፍርድና ንቀት፣ ስድብና አድልዎ እዳልገባ ታግደኛለች።

👉 #በትዕቢት ተጠልፌና ከቅድስና ተለይቼ እንዳልቀር ታተጋኛለች። “እኔ ድኛለሁ በቃ” በሚል ግብዝነት ራሴን ከፍ፣ ሌሎችን ዝቅ እንዳላደርግ ዘወትር ቅዱሳንን ከፊቴ በማቆም ራስህን እይ ትለኛለች። እነርሱን ዓይቼ፣ በተጋድሏቸው ቀንቼ እንድከተላቸው፣ድል ለነሣው የሕይወትን አክሊል እሰጠዋለሁ እንዲባልልኝ ታስሮጠኛለች።

👉 #ወድቆ መነሣት መኖሩን በመንገር እንድነሣ ትደግፈኛለች። ወድቀው በሚንከባበለሉት ከመዘበት ይልቅ ራሴን እንዳይ ታደርገኛለች። አንተ ሰነፍ ዛሬ ሞት ቢወስድህ የአምላክህን ፊት በምን ሥራህ ታየዋለህ እያለች በትሩፋት ላይ ትሩፋት እንድሠራ ታተጋኛለች።

👉 #እንቅልፍ በማብዛት ከሚተኙት የበለጠ ዕረፍት እንዳገኝ ታደርገኛለች ። “ድነኃል” በቃ ተኛ፣ ተዝናና፣ ሳይሆን ባሕረ ኤርትራን ተሻገርክ እንጂ መች ከነዓንን ዓየኻት ትለኛለች። መሻገር መድረስ አለመሆኑን ደጋግማ ትነግረኛለች። በረሃው ረዥም በመሆኑ በርታ፣ ተራመድ፣ ከተቀመጥክበት ተነሥተህ በርትተህ ወደ ትሩፋት ተራመድ፣ ኃጢአት ይብቃህ ንስሐ ግባ፣ ዲያብሎስ ሳያሸብርህ ቅዱሳንን ጋሻ አድርገህ በጽናት ተጋደል፣ ቅጥረ ኢያርኮ እስከሚፈርስ ወደ አጸዴ መመላለስህን አታቋርጥ፣ ጣዖታትን ሰባብራቸው ትውክልትህ በአምላክህ ላይ ብቻ ይሁን ትለኛለች።

👉 #ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ስጦታዋ ጉድለት የሌለበት ምሉእ ነው። ረቂቁንና ግዙፉን፣ ምድራዊውንና ሰማያዊውን፣ ቍሳዊውንና መንፈሳዊውን፣ ሰውንና መላእክትን፣ በዚህ ዓለም መኖርንና በሞት የሚደረስበት ሕያውነትን፣ በመከራ ውስጥ ደስታን፣ በመስጠት ውስጥ መቀበልን አሳይታ የመንፈስ ልዕልና እንዳገኝ ታተጋኛለች።

👉 #ኦርቶዶክሳዊነት የሚኖሩት፣ የሚሞቱለት፣ የሚቀበሉትና የሚሰጡት እንጂ የሚያወሩት፣ የሚገድሉለት፣ የሚፈጥሩት አለመሆኗን በተግባር ታሳየኛለች።

👉 #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “እንደ ውሃ ፈሳሽ፣ እንደ እንግዳ ደራሽ” ሳትሆን በሐዋርያት የተተከለች፣ በሊቃውንት ለፍሬ የበቃች፣ በሰማዕታት ደም የለመለመች፣ በክርስቶስ ተዋጅታ በመንፈስ ቅዱስ የምትመራ መሆኗን አወቅሁ። ታሪክና ትውፊት ያላት መሆኗን ተረዳሁ። ደስ ይላል፣ ይመቻል፣ ዘመናዊ ነው፣ ከሌሎች አገር አየነው በሚል ንጥል፣ግንጥል፣ ብቸኝነት፣ በቃሁ፣ አየሁ፣ አደረግሁ በሚል ተለዋዋጭ ሰዋዊ አስተሳሰብ የምትመራ አይደለችም።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
#pray 🙏 #share

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
1
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያን_የመርሐ_ግብር_ተራ_በአራቱ_ጣቢያዎች
••●◉ ✞ ◉●••
📌ሰኞ፡ በ ETV ከምሽቱ 3፡00-4፡00
📌ማክሰኞ፡ በ FANA ከምሽቱ 3፡00-4፡00
📌ረቡዕ፡ በ ADDIS TV ከምሽቱ 3፡00-4፡00
📌ሐሙስ፡ በ WALTA ከምሽቱ 3፡00-4፡00
📌አርብ ፡ በ ETV ከምሽቱ 3፡00-4፡00
📌ቅዳሜ፡ በ FANA ከምሽቱ 3፡00-4፡00
📌እሑድ፡በADDIS ከምሽቱ 3፡00-4፡00
••●◉ ✞ ◉●••
#ለሰው_ሁሉ_ከሚሆነው_በቀር_ምንም_ፈተና_አልደረሰባችሁም_ነገር_ግን_ከሚቻላችሁ_መጠን_ይልቅ_ትፈተኑ_ዘንድ_የማይፈቅድ_እግዚአብሔር_የታመነ_ነው_ትታገሡም_ዘንድ_እንድትችሉ_ከፈተናው_ጋር_መውጫውን_ደግሞ_ያደርግላችኋል
••●◉ ✞ ◉●••
💌1ኛ ቆሮ 10፥13💌
••●◉ ✞ ◉●••
©EOTC TV
••●◉ ✞ ◉●••
#Share #Share #Share

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
👉ተወዳጆች ከዛሬ ጀምሮ በተጠናከረ መልኩ አገልግሎት የምንጀምር ሲሆን @geb19bot ላይ ጥያቄዎን እንዲጠይቁ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።
••●◉ ✞ ◉●••
#አንድ_ጌታ_አንድ_ሀይማኖት_አንዲት_ጥምቀት ኤፌ 4፥4-5
••●◉ ✞ ◉●••
👉 #ለሚጠይቁዋችሁ_ሁሉ_መልስ_ለመስጠት_ዘወትር_የተዘጋጃችሁ_ሁኑ_ነገር_ግን_በፍርሃትና_በየዋህነት_ይሁን።1ኛ ጴጥ፫፥፲፭

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
#ስራ_ወይስ_እምነት_ነው_የሚያጸድቀው? ተብሎ ብዙ ጊዜ ይጠየቃል።ጥያቄውን በአጭሩ ለመመለስ ያህል#የሚያጸድቀው_ሁለቱንም_በጥምረት_መያዝ_ነው።

#ሰው_ዳግመኛ_ከውሃና_ከመንፈስ_ካልተወለደ_በስተቀር_ወደ_መንግስተ_ሰማይት_አይገባም።ዮሐ 3፥5
👉 #ስጋዬንም_የሚበላ_ደሜንም_የሚጠጣ_የዘላለም_ህይወት_አለው።ዮሐ 6፥54 እንደተባለ በኋላ እምነቱን በስራው መግለጽ የግድ ነው።#ጌታም_በማቴዎስ_25 ላይ ስለሙሽራው፤ ዘይትና መብራት አጣምረው ስለያዙት ደናግላን በምሳሌ ያስተማረውን አንብበን መረዳት እንችላለን። በተጨማሪም #ወንድሞቼ_ሆይ_እምነት_አለኝ_የሚል_ስራ_ግን_የሌለው_ሰው_ቢኖር_ምን_ይጠቅመዋል_እምነቱስ_ሊያድነው_ይችላልን? ያዕ 2፥14 ብሎ አስቀምጦታል።
#ስራ_የሌለው_እምነት_ቢኖር_በራሱ_የሞተ_ነው።ያዕ 2፥17 ብሎ ገልጾልናል። ይህ ምእራፍ ስለ እምነትና ስራ በደምብ የሚያስረዳን ሲሆን መናፍቃኑ #አብርሃምም_አመነ_ጽድቅም_ሆኖ_ተቆጠረለት_ስለሚል መጽሀፍ_ቅዱስ_እምነት_ብቻ_በቂ ነው ብለው ለሚያስተምሩት ትምህርትም አጥጋቢ ምላሽ ይሰጣል።
══════◄✣••✥••✣►══════
#አባታችን_አብርሀም_ልጁን_ይስሀቅን_በመሰዊያው_ባቀረበ_ጊዜ_በስራ_የጸደቀ_አልነበረምን_እምነት_ከስራው_ጋር_ጋር_አብሮ_ያደርግ_እንደነበር_በስራም_እምነት_እንደተገለጸ_ትመለከታለህን_መጽሀፍም_አብርሀምም_አመነ_ጽድቅም_ሆኖ_ተቆጠረለት_ያለው_ተፈጸመ_የእግዚአብሄርም_ወዳጅ_ተባለ_ሰው_በእምነት_ብቻ_ሳይሆን_በስራ_እንዲጸድቅ_ታያላችሁ

👉ጽድቅ በእምነት ብቻ ቢሆን ኖሮ እነዚህ የእግዚአብሔር ቃላት ለምን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጻፉእውነት ነው የጽድቅ በር የተከፈተልን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የጽድቃችን መሰረትም በሩም እርሱ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን በማመን ብቻ መዳን እንደሚቻል ተደርጎ ሊወሰድ አይገባውም፡፡ መልካም ሥራ ካልሰራን የክርስቶስ መሆናችንስ በምን ይታወቃል፡፡ በማመናችን ብቻ ለእርሱ ልንሆን አንችልም፡፡ ማመን ብቻው አያድንም፡፡ መታመንን መጨመር አለብን፡፡ መታመን ማለት ደግሞ ላመኑት መገዛት፣ የታዘዙትን መፈጸም ማለት ነው፡፡ ይኸውም የሚገለጸው በመልካም ሥራ ነው እንጅ አምናለሁ እያሉ በመናገር ብቻ አይደለም፡፡ ለማነኛውም የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡና ፍረዱ፡፡ እምነት ብቻውን ቢያድን ኖሮ እነዚህ ለምን ተጻፉ
══════◄✣••✥••✣►══════
👉 #ባሕርም_በእርሱ_ውስጥ_ያሉትን_ሙታን_ሰጠ_ሞትና_ሲኦልም_በእነርሱ_ዘንድ_ያሉትን_ሙታን_ሰጡ_እያንዳንዱም_እንደ_ሥራው_መጠን_ተከፈለ።ራዕ 20፥13
👉#እነሆ_በቶሎ_እመጣለሁ_ለእያንዳንዱም_እንደ_ሥራው_መጠን_እከፍል_ዘንድ_ዋጋዬ_ከእኔ_ጋር_አለ።ራዕ 22፥12
👉#ትዕግሥትም_ምንም_የሚጎድላችሁ_ሳይኖር_ፍጹማንና_ምሉዓን_ትሆኑ_ዘንድ_ሥራውን_ይፈጽም።ያዕ1፥4
👉#ነገር_ግን_ነጻ_የሚያወጣውን_ፍጹሙን_ሕግ_ተመልክቶ_የሚጸናበት_ሥራንም_የሚሠራ_እንጂ_ሰምቶ_የሚረሳ_ያልሆነው_በሥራው_የተባረከ_ይሆናል።ያዕ 1፥25
👉#ወንድሞቼ_ሆይ_እምነት_አለኝ_የሚል_ሥራ_ግን_የሌለው_ሰው_ቢኖር_ምን_ይጠቅመዋል_እምነቱስ_ሊያድነው_ይችላልን ያዕ 2፥14
══════◄✣••✥••✣►══════
👉እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።ያዕ 2፥17
👉#አንተ_ከንቱ_ሰው_እምነት_ከሥራ_ተለይቶ_የሞተ_መሆኑን_ልታውቅ_ትወዳለህን_አባታችን_አብርሃም_ልጁን_ይስሐቅን_በመሠዊያው_ባቀረበ_ጊዜ_በሥራ_የጸደቀ_አልነበረምን_እምነት_ከሥራው_ጋር_አብሮ_ያደርግ_እንደ_ነበረ_በሥራም_እምነት_እንደ_ተፈጸመ_ትመለከታለህን_ያዕ 2፥20
👉ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምንከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።ያዕ 2፥24
══════◄✣••✥••✣►══════
👉#እርስ_በርሳችሁ_በኃጢአታችሁ_ተናዘዙ_ትፈወሱም_ዘንድ_እያንዳንዱ_ስለ_ሌላው_ይጸልይ_የጻድቅ_ሰው_ጸሎት_በሥራዋ_እጅግ_ኃይል_ታደርጋለች።ያዕ 5፥16
👉እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፤ሮሜ 2፥6
👉 #የሰረቀ_ከእንግዲህ_ወዲህ_አይስረቅ፥ነገር_ግን_በዚያ_ፈንታ_ለጎደለው_የሚያካፍለው_እንዲኖርለት_በገዛ_እጆቹ_መልካምን_እየሠራ_ይድከም።ኤፌ4፥28
👉ባሪያ ቢሆን ወይም ጨዋ ሰው፥ እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት እንዲቀበለው ታውቃላችሁና።ኤፌ 6፥8
👉 #እንዲሁም_ደግሞ_ሴቶች_በሚገባ_ልብስ_ከእፍረትና_ራሳቸውን_ከመግዛት_ጋር_ሰውነታቸውን_ይሸልሙ_እግዚአብሔርን_እንፈራለን_ለሚሉት_ሴቶች_እንደሚገባ_መልካም_በማድረግ_እንጂ_በሽሩባና_በወርቅ_ወይም_በዕንቍ_ወይም_ዋጋው_እጅግ_በከበ_ልብስ_አይሸለሙ።1ኛ ጢሞ 2፥9-10
👉ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥2ኛ ጢሞ 3፥3
══════◄✣••✥••✣►══════
👉#የሚቃወም_ሰው_ስለ_እኛ_የሚናገረውን_መጥፎ_ነገር_ሲያጣ_እንዲያፍር_በነገር_ሁሉ_መልካምን_በማድረግህ_ምሳሌ_የሚሆን_ራስህን_አሳይ_በትምህርትህም_ደኅንነትን_ጭምትነትን_ጤናማና_የማይነቀፍ_ንግግርን_ግለጥ።ቲቶ 2፥7-8

👉በአጠቃላይ እምነት ብቻ ያድናል የሚለው አስተሳሰብ በፍጹም ትክክል ያልሆነ መሆኑን ከላይ በጥቂትና በትንሹ በተጠቀሱት የቅዱሱ መፅሐፍ ጥቅሶች እንረዳለን።ስለዚህ ማመን ብቻ ሳይሆን እምነታችን በስራ መገለፅ አለበት።

🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏

💒💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
የኦርቶዶክስ እና የካቶሊክ ልዩነት? በምን ምክንያት ተለያዩ
2025/10/28 09:42:42
Back to Top
HTML Embed Code: