Telegram Web Link
Forwarded from Ashruka InfoTainmet (AIT) (Asres)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በስዊድን ፖርላማ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እንዲቆም ተጠየቀ::


ስዊድን በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እንዲቆም ወንጀለኞች እንዲጠየቁ እና ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ አቅርባለች::

በተለይ ድምጻችንን በማሰማት የሚታወቁት የፓርላማ ተወካይዋ አሌክሳንድራ ቮልከር ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጥያቄ እና ማብራርያ አቅርበዋል::

በስዊድን ያለንም በቦታው ተገኝተን ስብሰባው ተከታትለናል::

💚💛❤️🇸🇪
(ሙሉ ትርጉም እስኪለቀቅ ዋናው መልክት ተከታተሉ🙏🏽)

የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ በስዊድን እና አሽሩካ ኢንፎቴንመንት

ሚያዝያ 18, 2016 ዓ.ም

@ashrukamedia
🌿 🌴 ሥርዓተ ዋዜማ ወማኅሌት ዘሆሣዕና 🌿 🌴

ሥርዓተ ዋዜማ

በእምርት ዕለት በዓልነ ንፍሑ ቀርነ በጽዮን፤
ወስብኩ በደብረ መቅደስየ፤
እስመ ይቤ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር፤
ሆሣዕና በአርያም፤
ቡሩክ አንተ ንጉሠ እሥራኤል።

አመላለስ፦

ቡሩክ አንተ ንጉሠ እሥራኤል፤/2/
ቡሩክ አንተ ንጉሠ እሥራኤል/4/

ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ (መዝ: ፳፫)

ይብሉ ሆሣዕና በአርያም፤
ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት፤
ይብሉ ሆሣዕና በአርያም።

እግዚአብሔር ነግሠ (መዝ: ፺፪)

ተፈሥሑ በእግዚአብሔር ዘርድአነ፤
ወየብቡ ለአምላከ ያዕቆብ፤
ንፍሑ ቀርነ በጽዮን በዕለተ ሠርቅ፤
በዕምርት ዕለት በዓልነ።

በ፭ እግዚኦ ጸራሕኩ ኃቤከ (መዝ: ፻፵)

ደቂቅኒ እንዘ ይጸርሑ፤
ወሕዝብኒ ኪያሁ ይሴብሑ፤
ደቂቅኒ እንዘ ይጽርሑ።

ይትባረክ (ጸሎተ ፫ቱ ደቂቅ: ፱)

ሆሣዕና በአርያም ለወልደ ዳዊት ለንጉሠ እሥራኤል፤
ዘይሁብ ዝናመ ተወን ከመ ትካት ይመልአ ዓውደ እክል፤
በረከተ ምክያዳተ ወይን።

ሰላም

ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ዓርገ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም፤
ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን፤
ወበልዋ ለወለተ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ ጻድቅ ወየዋህ ዘእሤቱ ምስሌሁ፤ ወምግባሩ ቅድመ ገጹ፤
ወይከውን ሰላም በመዋዕሊሁ

።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሥርዓተ ማኅሌት

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤
በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤
ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤
ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤
ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ

ሰላም ዕብል ለዘዚአክሙ ቆም፤
ዓለማተ ዓለም ሥላሴ ዘአልብክሙ ዓለም፤
እምኔክሙ ፩ በእንተ ፩ አዳም፤
እመኒ በምድር ተወክፎ ለነግደ ጲላጦስ ሕማም፤
ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም።

ዚቅ፦

እምሆሣዕናሁ አርአየ ተአምረ ወመንክረ፤
ዘኢተገብረ እምቅድመዝ፤
ወኢይከውን እምድኅረዝ።

በዐቢየ እግዚዕ ዚቅ፦

ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ምስለ አቡሁ አሐደ ፈቃድ፤
ቅድመ ገፀ ጸላዒ ጽኑዕ ማህፈድ፤
ተፅዕነ ዲበ ዕዋል ዘእሳት ነድ፤
ያጹ ሆሳዕና ዘአብ ወልድ

በዐቢየ እግዚዕ ፦

ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ፦

ዘበእንቲአሃ ኢሳይያስ ጸርሐ፤
እንዘ ይብል አብርሂ አብርሂ ተፈስሒ በንጉሥኪ በጽሐ፤
ኢየሩሳሌም ዜነዋ ፍስሐ

መልክአ ኢየሱስ፦

ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሃላ ዘኢይሔሱ፤
ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤
አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቌጸል በርእሱ፤
አህጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ።

ዚቅ፦

ሆሣዕና በአርያም ለወልደ ዳዊት ለንጉሠ ፳ኤል፤
ዘይሁብ ዝናመ ተወን ከመ ትካት ይመልአ ዓውደ እክል፤
በረከተ ምክያዳተ ወይን።

በዐቢየ እግዚዕ ዚቅ ፦

ይብሉ ሆሣዕና በአርያም፤
ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት፤
ይብሉ ሆሣዕና በአርያም።

መልክአ ኢየሱስ፦

ሰላም ለመትከፍትከ ከመ ልብሰ ክህነት ሎግዮ፤
ጊዜ ጸዓተ ፍትሕ ዘፆረ አርዑተ መስቀል በቀራንዮ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ በግዓ መድኃኒት ወአስተሥርዮ፤
አስተዳሎከ ለርእስከ ውስተ ዓፀደ ግፍዕ ተርእዮ፤
ወኲሎ በዘይደሉ አቅደምከ ሀልዮ።

ዚቅ፦

ኢይብከያ ዘከልአ ደናግለ፤
አርዑተ መስቀል ፆረ፤
እስከ ቀራንዮሰ ሖረ፤
ኢይብከያ ዘከልአ ደናግለ።

መልክአ ኢየሱስ፦

ሰላምን ለአእጋሪከ እለ ጠብዐ ለቀዊም፤
ቅድመ ጲላጦስ ፈታሒ መስፍነ ይሁዳ ወሮም ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘትማልም ወዮም፤
ኀበ ወረደ ወነጠበ ዝናመ አእጋሪከ ደም፤
ለመስቀልከ በሰጊድ ሰላም።

ዚቅ፦

ኦ አእጋር እለ አንሶሰዋ ውስተ ገነት፤
ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል።

በዐቢየ እግዚዕ፦ መልክአ ኢየሱስ፦

ሰላም ለአፅፋረ እግርከ በደመ ቅንዋት እለ ተጠምዐ፤
እስከ ጽዕዳዌዎን ለብሰ ልብሰተ ጠባይዕ ካልዐ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተሰቅልከ በአፍዐ፤
ከመ ይዜኑ ሂሩትከ ወእከውዕን ስምዐ፤
መምህረ ረሰይኩከ ረስየኒ ረድዐ ።

ዚቅ፦

አስተይዎ ብሂዓ ዘምስለ ሐሞት ለዘያዳ ሆሳዕና በክብር ሰቀልዎ ዲበ ዕፀ መስቀል፤ አይሁድ ዐማፅያን

መዝሙር፦

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ፤
ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ፤
ሀገረ እግዚአብሔር፤
ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን፤
አዕሩግ ወሕፃናት፤
ነሢኦሙ አዕጹቀ በቀልት፤ እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም፤
ተጽኢኖ ዲበ ዕዋል፤
ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም፤
በትፍሥሕት ወበኃሤት ይሁቦሙ ሃይለ ወሥልጣነ።

አመላለስ፦

በትፍሥሕት ወበኃሤት/፪/
ይሁቦሙ ሃይለ ወሥልጣነ/፬/
እንኳን አደረሳችሁ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ 🙋

👇
https://youtu.be/ewOJtK7f8vs?si=1MDETyky4_KRXE_4
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት
+++++++
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

U/ ኪርያላይሶን **
—------
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡

ለ/ ናይናን
—--------
** የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡

ሐ/ እብኖዲ
—---
** የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው

መ/ ታኦስ
—--------
** የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡

ሠ/ ማስያስ
—--------
** የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው

ረ/ ትስቡጣ
—--------

** «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው

ሰ/ አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ
—--------

** Em-nees the-tee mo-ki-riey enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡

ሸ/ አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
—--------

** Em-nees the-tee mo-a-geh-e enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው

ቀ/ አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
—--------

** Em-nees the-tee mo-zess-pota enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

(ምንጭ፦ መምህር እንዳለ )


share
ልሳነ ግእዝ
🔤🔤'🔤🔤
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በሰሙነ ሕማማት 👇

፩.ቅዳሴ የለም (ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር)
፪.የ ቡራኬ አገልግሎት የለም
፫.ሰው ቢሞት ጸሎተ ፍትሐት አይደረግም
፬.መስቀል መሳለም የለም
፭.የትኛውም የጸበል አገልግሎት የለም
፮.እልልታም ሆነ ጭብጨባ የለም
፯.ሩካቤ አይፈቀድም የቀደሙት ሳምታትም የለም።
፰.አመጋገብን በተመለከተ ኮከብ እስከሚወጣ (እስከ ምሽት 1:00) ድረስ መጾም የታዘዘ ነው
፱.ሰላምታን በተመለከተ በጸሎተ ሐሙስ "የይሁዳን የሽንገላ ሰላምታ" ለማስታወስ ሰላምታ ይከለከላል ወይም ተዐቅቦ ይደረጋል (ረስተዉት ንጹሕ ሰላምታ የተለዋወጡ ሰዎች ግን ኃጢአት ሠርተዋል ማለት አይደለም)
፲.በሰሙነ ሕማማት የሚውል ማንኛውም በዓል የሚከበረው በስግደት ነው

እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ጻማ ወድካም፤ አመ ከመዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ፤ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም።


ሼር
share...

https://www.tg-me.com/geeztheancient
ኪርያላይሶን አማኑኤል ናይን
ጴጥሮስ አሸናፊ


ክህደተ ይሁዳ ወምክረ አይሁድ ፤ የመልካም መዓዛና የእንባ ዕለት
ሰሙነ ሕማማት ዘረቡዕ

❖ ምክረ አይሁድ

ወእምዝ ተጋብኡ ሊቃነ ካህናት ወሊቃናት ሕዝብ ውስተ ዐጸደ ሊቀ ካህናት ዘስሙ ቀያፋ። ወተማከሩ ከመ ኢየሱስሃ በሕብል የአኀዝዎ ወይቅትልዎ። ወይቤሉ ባሕቱ አኮኬ በበዓል ከመ ሀከከ ኢይኩን ውስተ ሕዝብ።
በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው ሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥ ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ። የማቴዎስ ወንጌል 26:3-4

የአይሁድ ሊቃነ ካህናት እና ጸሐፍት ተሰብስበው ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን በመሆኑ ዕለቱ ምክረ አይሁድ ተብሏል፡፡
አይሁድ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡
"ወእምዝ ሖረ አሐዱ እምዐሠርቱ ወክልኤቱ አርዳኢሁ ዘስሙ ይሁዳ አሰቆሮታዊ ኀበ ሊቃነ ካህናት ወይቤሎሙ ሚመጠነ ትሁበኒ ወአነ ለክሙ አገብኦ። ወወሀብዎ ሠላሳ ብሩረ ። ወእምአሜሃ ይፈቅድ ይርከብ ሣኅተ ከመ ያግብኦ ።"
በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸውበጌታ መያዝ ተስማምተዋል።
[ማቴ. ፳፮፥፩፡፲፬ ፣ ማር. ፲፬፥፩፡፪ ቁ ፲.፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፥ ፩፡፮]

❖ የመልካም መዓዛ ቀን

ወበጺሖ ኢየሱስ ቢታንያ ቤተ ስምዖን ዘለምጽ መጽአት ኀቤሁ ብእሲት እንዘ ባቲ ብረሌ ዘምሉእ ዕፍረተ ውስቴቱ ዘብዙኅ ሤጡ ወሶጠት ዲበ ርእሱ ለኢየሱስ እንዘ ይረፍቅ ።
ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ (በለምጻሙ ሰምዖን) ቤት ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ዕለተ ረቡዕ የመዓዛ ቀን ተብሏል። ማቴ ፳፮፥፮-፯

❖ የእንባ ቀን

ይህም ይህቸው ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡
[ማቴ.፳፮፥፮፡፲፫ ፣ ማር.፲፬፥፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፥፩፡፰]
ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡
ማር ፲፬፥፱

እንበለ ደዌ ወሕማም ፤ እንበለ ጻማ ወድካም
ዓመ ከመ ዮም ፤ ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ
እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ
በፍስሓ ወበሰላም
ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ስለማጠቡ የሊቃውንት ትርጓሜ]


(በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)

በዕለተ ዐርብ የዓለምን ኀጢአት በደሙ የሚያጥበው ከጎኑ በሚፈሰው ውሃ ዓለምን የሚቀድሰው ጌታችን አስቀድሞ በዕለተ ኀሙስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በውሃ በማጠብ ትሕትናን የገለጸበት አስደናቂ ምስጢር የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በመገረም እንዲኽ ብለዋል፡-

ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዲኽ አለ፡-
“በመንክር ትሕትና ወረደ እግዚአብሔር ቃል…” (እግዚአብሔር ቃል በሚያስደንቅ ትሕትና ሰው ኾነ፤ የማይታዩ ረቂቃን መላእክት አደነቁ በልዑል ዙፋኑ ለደቀ መዛርቱ ሲያገለግል ባዩት ጊዜ አገልጋዮች መላእክት ደነገጡ፤ ትሕትና ወደ አለበት ፍቅር የአሕዛብን እግረ ልቡና ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ ብርሃናት ደነገጡ፤ አገልጋይ ይኾን ዘንድ እዚኽ ዓለም ከመጣ ከወልድ የተነሣ የአባቱ አገልጋዮች መላእክት እጅግ አደነቁ።

በመለኮቱ ግን ማገልገል የለበትም፤ በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው) (ሃይ. አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ ክፍል 9)



የቁስጥንጥንያው ፓትሪያርክ የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ይኽነን አለ፡-

“ልዑለ ባሕርይ የሚኾን ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳ የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበ፣ ከዚህ በላይ ደግሞ የይሁዳን እግር፥ የሌባውን እግር፥ ከክፋቱ መፈወስ የማይችለውን ሰው ካጠበ፥ ከማዕዱ እንዲካፈል ካደረገ እኛማ እንዴታ? እኛማ እንዴት ይህን ከማድረግ እንከለከላለን? የሠራተኞቻችንን እግር ብናጥብ ምንድነው ክፋቱ? የአሠሪና የሠራተኛ ልዩነት የቃላት ልዩነት ብቻ አይደለምን? እኛስ ሁላችን ዕሩቅ ብእሲዎች ነን፡፡ እርሱ ግን የባሕርይ አምላክ ነው፤ ኾኖም የባሮቹን እግር ዝቅ ብሎ ከማጠብ ምንም አልተጠየፈም፡፡

ለዚህም ነው ‘እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ስኾን እግራችሁን ካጠብኳችሁ፥ እናንተም የወንድማችሁን እግር ልታጥቡ ይገባችኋል’ ያለን፡፡ … ጌታችን እንዲህ ራሱ አድርጐ ካሳየን በኋላ እኛ አናደርግም ብንል በዚያች ቀን የምንመልሰው መልስ ምን ይኾን? … ይህን ከማድረግ ተከልክለን በትዕቢት የምንያዘውስ እኛ ምንድነን? እንደምን ያለ ስንፍናስ ቢይዘን ነው? ሰው ሆይ! በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው እርሱ ዝቅ ብሎ የይሁዳን እግር ካጠበ፥ አፈርና ትቢያ የምትኾን አንተ ራስክን ከፍ ከፍ ታደርጋለህን? ለዚህ ትዕቢትህስ እንደምን ያለ ፍዳ ይጠብቅህ ይኾን? ወዳጄ ሆይ! ከፍ ከፍ ማለትን ትወዳለህን? እንኪያስ ና! እንዴት ከፍ ከፍ እንደምትልም አሳይሃለሁ፡፡ እንደ ጌታህና እንደ መምህርህ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ራስህን ዝቅ አድርግ፤ የዚያን ጊዜም ከፍ ከፍ ትላለህ” /St. John Chrysostom, Homily LXXI/፡፡


ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ይኽነን አለ፡-
“ሐዋርያቲሁ ከበበ
እግረ አርዳኢሁ ሐጸበ
ኮኖሙ አበ ወእመ
ወመሀሮሙ ጥበበ”
(ሐዋርያቱን ሰበሰበ፤ የደቀ መዛሙርቱንም እግር አጠበ፤ እንደ አባትና እናት ኾናቸው የትሕትና ጥበብን አስተማራቸው)፡፡


አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምስጢር ይኽነን አለ፡-
“ዘያቀንቶሙ ለአድባር በኀይሉ ቀነተ ለንጸ ለተልእኮ…” (ተራሮችን በኀይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፤ የባሕርን ውሃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በወንዞች መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውሃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ ኩስኩስት አፈሰሰ፤ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን እንዲታጠቡ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በኦሪቷ ድንኳን ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውሃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ)


318ቱ ሊቃውንት በሕንጻ መነኮሳት እንዲኽ አሉን፡-
“ኢትትሐከይ ኀጺበ እግረ አኃው ሶበ መጽኡ ኀቤከ...”
(ወንድሞች ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እግራቸውን ማጠብን ቸል አትበል፥ ይህችን ሥራ ቸል የሚልዋትን ስለዚህ ትእዛዝ ሥላሴ በፍዳ ይመረምሯቸዋልና፤ ምንም ኤጲስ ቆጶሳትም እንኳ ቢኾኑ እግዚአብሔር አስቀድሞ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቦ እንዲሁ ያደርጉ ዘንድ አዝዟቸዋልና” ብለው አስተምረዋል) (ሃይ.አበ. ዘሠለስቱ ምዕት 20፡29)፡፡


ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱሳን ሐዋርያትን እግራቸውን ብታጥባቸው በዚኽ በታጠበና በተባረከ ባማረ እግራቸው ዓለምን ዙረው ወንጌልን እንዳስተማሩ የእኛንም እግሮቻችን እንደነሡ የሕይወት ውሃ የሚሰጥባት፤ የዓለምን ኀጢአት ያጠበ ቅዱስ ደምኽ ወደሚቀዳባት፤ ቅዱስ ሥጋኽ ለመድኀኒት ወደሚፈተትባት ወደ ቤትኽ ዘወትር የሚገሠግሡ አድርጋቸው፡፡

© ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ባለፈው ዓመት የጻፉት ላይ የተወሰደ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጌታ ተመረመረ
ዲያብሎስ 👿 👈 ታስረ


እንኳን አደረሳችሁ 🙏
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ 🙏
ዲያቆን ዘማርያም ዘለቀ እንኳን ለዚህ ክብር አበቃህ መምህር 🙏
ቅኔ ከሊቃውንት አንደበት


👇
https://youtu.be/Y5YoZIyvROE?si=Zo9PMNKmUbHpOV_n
ዜና ምንፍቅና

ዲያቆን የሚባል ማእረግ አለኝ ሲል የነበረው አፋም ልጅ ጰነጠጠ ...

አስኪ ዜማ በልልን ተብሎ
ለምሳሌ ብሎ ለጥምአ ሥጋከ ንስትዮ ወለነቅዐ ደምከ ንበልኦ ሲል የነበረ አውደልዳይ በይፋ ሜንጤ ( የአያቴ አነጋገር ) ሆነ አሉ😂
2024/05/18 05:24:59
Back to Top
HTML Embed Code: