Telegram Web Link
💚💛❤️አድዋ💚💛❤️
.
.
እንዴት! ያውም አድዋን!?
(በድሉ ዋቅጅራ)
.
ምነው!?
አድዋን ያህል ታቦት!
ነጻነትን ያህል ጽዋ!
ምነው አጣ፣ አንጋሽ - ደጋሽ፣
የጀግና አባቱን፣ ድል ወራሽ?
ምነው?
.
ምነው?
ምነው! ጭር አለ ቀዬው፣ ዳዋ ዋጠው ደብሩ፤
ፎካሪ ናፈቀ ፈፋው፣ ሸላይ ጠፋ ባገሩ፡፡
ምነው?
.
ምነው?
በደም ቀለም፣ በአጥንት ብእር የተጻፈ ገድል፤
የጥቁር ህዝቦች፣ የነጻነት ውል፤
አድዋን ያህል ድል?
ምነው!?
.
ምነው!?
እንደመጥበትን ልቦና፣ እንናገርበትን ልሳን፣
አንከበርበትን ግርማ፣ እንከብድበት ሚዛን፣
ምነው! . . . . ያውም አድዋን!?
.
ምነው!?
በጎሰኝነት ችካል፣ በየጎጡ ጋጥ ታስረን፤
‹‹አድዋ!›› ማለት ከበደን፤
‹‹ኢትዮጵያ!›› ማለት ሸከከን፡፡
ባንባረክ ልንባርከው፣ ቅርጫ ʽናረገው አማረን፡፡
የአባቶቻችን ድል አሳከከን፤
ለትርክት አንደበት አጠረን!
ጀግንነትን አንውረስ - እንፍራ፣ እዳ አለው፣
ስንቀል ይከብዳል፤
ጀግንነት ጣር አለው ይቅር፣
እንዴት ድል መውረስ ያቅታል!?
.
ምንስ ድንቁርና ቢጎራበተን፤
ጎሰኝነት ቢያባትተን፤
እንዴት ድል መውረስ ያቅተን!
ያውም አድዋን! ከሀገር፣ ከሰንደቅ፣ ከነጻነትም በላይ፤
የሰው መሆንን ማተብ፣ የ‹‹ሳቬጅ›› ተረት ተርትን ስራይ፤
የአፍሪካን የነጻነት አዋይ፤
እንዴት!
.
ኧረ ወገኔ ውሉን ስቷል፤
አድዋ ተራራ መስሎታል!
ሸንሽኖ ሊከፋፈለው፣ ኮረብታ ሊያደርገው አምሮታል፡፡
አድዋ የአንድ ቀን ውሎ፣ አድዋ ተራራ መስሎታል፡፡
.
መንፈስ እኮ ነው አድዋ፣ . . . .
ፈለግ - ለመንገዳችን፣ ለታሪካችን - ልሳን፤
ዙፋን - የነጻነታችን፣ የአብሮነታችን ቁርባን፤
የመረዳዳት ፍሬ፣ የኢትዮጵያዊነት መልህቅ፤
የደገፈን - እንዳንወድቅ፤
ያጸናን - እንዳንዋዥቅ፡፡
እንዳንፈርስ ያጠነከረን፣ . . .
እንዳንጎድል - ቀድሞ የሰፈረን፡፡
. . . . . ምነው ዘመን አወረን!?
.
አድዋ እንደሁ መንፈስ ነው!
እንኳን ጎጥ - ሀገር ያልቻለው፤
ጽናት - አህጉር የጠበበው፤
አይገድቡት - ይፈሳል፤
አያቅቡት - ይዳረሳል፡፡
.
ታዲያ ምነው!?
ምንስ ድንቁርና ቢጎራበተን፤
ጎሰኝነት ቢያባትተን፤
እንዴት ድል መውረስ ያቅተን!
ያውም አድዋን!
-------------
የካቲት 23፣ 2009፤ አዲስ አበባ፡፡

ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራት ለሆነው ለታላቁ የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት የመታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ !አደረሰን ።🙏
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
ለ March 8
#Ezana Mesfin

@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
Join$share🙏😍
ሊያኖር እየሞተ
ገጣሚ ጃፒ
@Getem_lemitemaw
"ርዕሱን ለአድማጭ"
ርዕሱ ነው
( አምባዬ ጌታነህ )

እኔ የአንቺ ደሐብ-ብኩን ደግ አፍቃሪ፣
ለክብረሽ መግለጫ - ፊደልሽን ቆጣሪ፣
እየተቅለሰለስኩ በልጅሽ ፊት ስኖር፣
ከማዘን በስተቀር ስቄ አላቅም ከምር።
ያም ለዛ ያም ለዛ ሲያጋድል እያየሁ፣
በጊዜ ዳኛ ላይ ፍትህ እየተራብሁ፣
ሁሌ እንዳጉተመተምሁ
'ልጅ አሳድግ ብየ
ካገር እኖር ብየ
ለባሻ ዳርኩለት ሚስቴን 'ህቴ ብየ።'
እንዳለው ገበሬ፣
አለሁኝ እንዳለሁ
ግፍ ሆኖብኝ ክብሬ።

አባት ማጣት ሀዘን - እናት ማጣት ህመም፣
ሆኖ እንደ እግር እሳት እልፍ አመት ቢፈጅም፣
በተበዳይ ልብ ውስጥ ለምፅ እንደሚያሳርፍ ገዳይ አውቆ አያቅም፣
እኔ ያለ ወላጅ መቅረቴ አያመውም።

ሰማይ የግፍ እምባ ሊጥል አቀርዝዟል፣
ጋራ ሸንተረሩ በዝምታ ነግሷል፣
ሜዳ ወንዛ ወንዙ ቅጠሉ ጠንዝሏል፣
እናት ሞቅ አጥልቃ፣
ቁርንጮዋን ታጥቃ፣
ፊቷ ተነጫጭቷል፣
አባት ወደ ማታ ባዘን አጎንብሷል፣
የእኔም የነገ እጣ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።

ለዛሬ ያለምነው ቅዠት ሲሆን ተስፋ፣
አንተ የፍጥረት አምላክ
የምህረት ዝናብህን ባጥል እንኳ አካፋ።
ነፃ በሆነች ምድር ነፃ አውጪዎች ሞልተው ነፃ ህዝብ ጠፋ።
እኒህ ነፃ አውጪዎች
የለውጡ አምበሳዎች
በቀን አስር ጊዜ ' እመኑን 'የሚሉን፣
ከምናየው እውነት የተፃረረውን
' መሲህ ነን ' የሚሉን
ከእመኑን ባሻገር እንድናምን 'ሚሹት ውሸቱ ምን ይሆን፣

ባለሁለት ወንበር ምቾት ካልተሰማኝ፣
የምለውን ሰምቶ ሰርቶ ካልታዘዘኝ
አባወርነቴን ከተፈታተነኝ
የእሱ መኖር ለእኔ ..
መሄጃ መቆሚያ ማረፊያ ካሳጣኝ፣
እንዴት መላ አላስብ፣
እንዴት ሴራ አልሸርብ
የምን እያቀፉ እንደ ልጅ ማባበል፣
ሳለ ብልህ ዘዴ
በመፈንቅለ ስም መሪነትን መግደል።

እንዲህ ነው እንግዲህ የኛ ዘመን ጣጣ፣
የየዋህ እስትንፋስ የንፁህ እድል እጣ።
ያደለው በሰው ልብ እንደተናፈቀ በክብር ይሞታል፣
ያለደለው ደግሞ የራሱን ቁም ሙቶ ሊገድል ይኖራል፣
ምንድን ነው ሰው መሆን ያዘነ ማስመሰል፣
በውስጥ እየሳቁ ለቅሶ ምን ያደርጋል፣
ፍረድ አንተ ጌታ...
የኃጢያት እልፍኜን
ና ደብድብ ጣራዋን
ወየ ኡኡ ብየ ላቅልጠው ዋይታየን
ቅጣኝ ለክህደቴ
አርገው እውነት የምር የውሸት ለቅሶየን።

እናም በኔ ዘመን...
የእውነት ዘውድ ተጭኖ የሚታየው አሁን፣
ቀዳዳን በር አረጎ ሚያይ ልዩነትን
አንድነትን ትቶ የሚስብክ ጥልን።
በአንድ መንጋ ሚሄድ፣
ያለ ሀሳብ ሚነጉድ
ግን
እስከየት ድረስ ነው?
ጎዳናው ሚያዘልቀው
እስከ መቼ ድረስ በጎጥ አንድ መንገድ፣
በንፁሃን ደም ላይ..
ንፁሃንን ከሶ እያሰሩ መሄድ።
ነውስ?
'ውሻ በቀደደው ጅብ ሠፍቶ ይገባል
ፍየል በግ ቢያጣ እንኳ
ቋንጣውን ሸምጥጦ ይሮጣል እንዲባል
ሆነ በቃ እንግዲህ
የዚች አገር እጣ በተራ መበደል?!

ተው
እንተው
በዳይ ከተበዳይ እኩል ፍትህ ካለ ካልሰከነ ነገር፣
ቤትን ካላቆመ
አንደኛው ጭራሮ ሌላው ሆኖ ማገር፣
ምስጥ የበላት ጎጆ ትመስላለች ሀገር።
"
' ? '
በበረሀ ጋመን ጠውልጎ ያልረባው፣ማውጣት የተሳነው የማህፀንሽ ፍሬ፣
ለአርባ አምስት አመታት ንጉሥ ያልወጣብሽ ምን ኀጥያት ሰርተሽ ነው ንገሪኝ ሀገሬ?

ምንዱባን ኢትዮጵያ - ምትለምኝ ሰጥተሽ፣
ጥበብሽ ሳይቆሽሽ
የምታጥቢ ፈተሽ
ሩህሩኋ የኔ
ጥጥ ፈታይዋ እናቴ፣
ምን ልብ ነው ያለሽ
እኔ እየጠላሁሽ
አንቺ ምትሳሽልኝ ንገሪኝ በሞቴ?

' መደምደሚያ '
በአንድ ቋንቋ ዘየ የሰራነው መንደር፣
ምን ብንኩራራበት አይሆነንም ሀገር።
ይብቃን መጋደሉ፣
ይብቃን መላቀሱ፣
መርገምት ነው ይሄ
እንፀልይ ወደ እርሱ።
ደግሞ
ያሻው ቢከፋኝም፣
ያሻ ብቀየምም፣
ወንድምነትክን ግን
ለሰከንድ አልፍቅም
ሲነኩህ ያመኛል ይሰማዋል ጎኔ፣
ይህ ሁሉ ግፍ ይቁም በአንተ በእሷ በእኔ
ልዩነቱ ይብቃን አንድ እንሁን ወገኔ።


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
@Getemlemitemaw
#ከራስ ጋር ንግግር!
...(ሚካኤል አስጨናቂ)...
.
ውሾችን ሳትሰማ
ግመል ሆነህ ተጓዝ
አጥብቅ መንገድህን
የፊት የፊቱን ያዝ ።
.
አትችልም ሲሉህ
በእሾህ ትብታባቸው ወርውረው ሲዶሉህ
እችላለሁ ብለህ ትብታብህን በጥስ
እንባ ያራሳቸው
የአይኖችህን ቦይ ... በወኔህ ክንድ አብስ።
.
ነገህ ማልዶ ይንጋ
የፅልመት ታሪክህ
በአዲቷ ጀንበር ተማርኮ ይወጋ።
.
ትናንት ኖረህ ታልፏል
ዛሬ ላይ ለመዋል
ቀንበርህን ግን ጣል !
.
እንዲያ ነው ዘመዴ
ይቀነሳል ሸክም አቀበት ለመውጣት
ሸቅንም ይጣላል ከእድፍ ለመንፃት
ሀሳብ መታሻ ነው ልብ ነው ሳሙና
መንፈስም ጥምቀት ነው በአርሞሞህ ተቃና
.
እንዲያ ነው ወዳጄ ...
ጆሮ ሰጥተህ ስትኖር
ለወጪ ወራጁ...
ሁሉም ልንዳህ ይላል ያሾርሀል በ'ጁ።
.
የራስህ ሹፌር ሁን ሰልጥን በገላህ ላይ
ነፃነት ነው መናህ ... የተቸረህ ከላይ
ውስጥህን ማመን ነው ... የንግስና ውሉ
ያመነ ይድናል
ብሎ እንዲናገር .... የመፅሀፍ ቃሉ ።
.
እንዲያ ነው ዘመዴ ...
የንፋስ ወጀቡ
ላስቲክ ሆነህ አይቶ ... በዛው ይዞህ እንዳይቀር
አትችልም ሲሉህ...
እችላለሁ ብለህ ... አንተን አምነህ እደር።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
#ያቺ ሴት !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

በዛች ፍልቅልቅ ሴት ፣ የሳቅ መልዕክተኛ

ዓለም ተሸብበው ፣ ከበው 'ሚካድሟት

ከግብዣ በኋላ እንተኛሽ በሚሏት

እንስት.. .!

መልከ መልካም ንግስት.. .

በመልሷ እሺታ.. .

በቃሏ ይሁንታ.. .

ውል ጫፉን ሳይዙ 

ዘማዊ ናት ብለው ስድብ የሚመዙ 

ሰዎች...

የንፅህና እርካብ... አናት ላይ ወጭዎች

አዋቂ ነን ባዮች!

ያልተረዱት ነገር የማያውቁት እውነት

ከታሪኳ ጀርባ አለ የርሷ ህይወት።
.

ያቺ ፍልቅልቅ ሴት ሳቋ የውሸት ነው 

እንዲሁ ለይስሙላ ነበር የምትስቀው

.

ያቺ ሳቂታ ሴት ...

በውሸት ፈገግታ ከመሳቋ ቀድሞ

ነበር አንድ ደስታ ልቧ ላይ ታትሞ

.

የዛች ሳቂታ ሴት የእውነት ፈገግታ

ነጣቂው ወንድ ነው ነበር ባል አግብታ

እርሷ ቤቴን ስትል

ባሏ ወንድነቱን ለሀገር ሴት ሲያድል

ጨዋ ሴትነቷን አቅልሎ ሊበድል

ቅዱስ አልጋዋ ላይ ሀጥያት ዘርቶበት

ሳቋን ሰርቆ ጠፋ ነጥቋት የሷን እውነት።

.

ከባሏ በኋላ

እምነቷን ገደፈች

አቅል ቀልቧን ሳተች

ማስመሰልን ወዳ ከእልህ ጋር ወሸመች
ለአላፊ አግዳሚው ስንዴ ንፍሮ ሆና ለሁሉ ቀረበች ...

.

ከቁስሏ በኋላ

 ሀዘኗን ልትሸፍን አውቃ ትስቃለች 

ንፍር አንጅቷ ላይ አልኮል ታፈሳለች

ለጎተታት ሁሉ በለስ ትችራለች

ወይን እየጠጣች ጭኗን ትገልጣለች

ወንድ ሁሉ ከሀዲ አንድ ነው ትላለች
.

ሌሎች 

ሳቋን ተከትለው ... ታሪኳን ዘንግተው

እንደ አየር ላይ ፊኛ

በንፋስ አቅጣጫ መንጎዷን አስበው

አመንዝራ አሏት.. . ድንጋይ ተሸክመው

.

ያቺ ፍልቅልቅ ሴት ...

ህመሟን ልትሽር ስትስቅ ስትጫወት

በኮናኝ ቃላቶች ... ገላዋ ሲነረት 

የባሏ ክህደት.. . 

ውስጧን እሳት ሆኖ እቶን ሲለቅበት

በኒህ ሁሉ ፅንፎች መሀል ተወስና

ህመሟ ቢጠና

ብትውል ከአልጋዋ ላይ 

እግዜር ቀጣት አሉ ተመልክቶ ከላይ።

.

እንዲያ ነው !

ያቺ የቤት ባላ...

በጠባብ ዳሷ ውስጥ ብቻዋን ተንጋላ

አይኖቿን ከደነች ...ይስፋላቸው ብላ ።

.

ዛሬ ደረት እየደቃ መንደር ሲያለቅስላት

ጋቢ አገልድሞ ባሏ እሷን ሲጠራት

በእልቃሽ ሆይ ሆይታ

መንፈሷ ሲረታ...

ባስመሳይ አጃቢ ሬሳዋ ሲሸኝ

እኔ ሳቋን ሰማሁ ... ገረማት መሰለኝ! 

@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
ደማቅ ዕለተ ሰንበት ተመኘሁ!
🕋🕋🕋🕋🕋🕌🕌🕌🕌🕌

#ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ አባላቶቻችን በሙሉ እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ! እያልን መልካም የፆም ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። 🙏
ረመዳን ከሪም!

@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

መቅደላ አፋፋ ላይ ጩኸት በረከት
የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ።

በዘመነ መሳፍንት ተበታትና የነበረችውን ሀገር አንድ ለማድረግ በድንኳን እያደሩ አንድነቷን የመለሱት ታላቁ ንጉስ አፄ ቴውድሮስ በዛሬዋ ቀን ለጠላት እጅ ላለመስጠት በራሳቸው ሽጉጥ ተሰው።ከዛሬ 153 ዓመት በፊት በ1860
ዓ.ም።
#ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖቹ
ሀገር ጠብቀው ላስረከቡን አባቶቻችን ።💚💛❤️
ታሪክ እያወሳን ታሪክ እን'ስራ!🙏❤️
@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
#መኖር_እና_ማኖር


አለም ሁለት መንደር ፡ ሁለት ጎዳና ናት
ሰለ አንዱ ደስታ አንዱ የምኖርበት።

ለመኖር የመጣው ሞልቶለት ሕይወቱ
በደስታ ይኖራል በሀብት ንብረቱ።

ለማኖር የመጣም፣
በሌላ ጎዳና ያለው በምድሪቱ
መከራን ሸምቶ ይኖራል በከንቱ ።


ሕይወት እንደዚህ ናት፣
እንደ አንዷ ሳንቲም የሁለት ገፅታ
ኑሯችን በአንድ አለም ሕይወታችን መንታ።




#share_join
@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛💛

#ታላቅ_የምስራች

ሰላም እንዴት ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ገጣማያን እና የግጥም አፍቃሪያን#አሪፍ_ዜና ይዘንላችሁ መጥተናል#100ብርየሚያሸልምየግጥም ውድድር ይዘን መተና

አሪፍ ግጥም አለኝ የሚል ሁሉ ሊሳተፍበት የሚችል ለየት ያለውድድር ነው የተዘጋጀው እንዲሁም ለውድድር ይሆናል የምትሉት ግጥም ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በሚቀመጥላችሁ #አድራሻ የምትወዳደሩበትን በመላክ በውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ እያልን ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጠን ፈጠን ብላችሁ ተመዝገቡ።

#ውድድሩን ለየት የሚ ያረገው ሌለው ነገር 3ዙሮች ይኖሩታል

#1ኛው ዙር ራሳቹ በፈለጋቹት ዕርስ በፃፋቹት ግጥም ምትወዳደሩ ሲሆን

#2ተኛ ዙር ለይ ወደሁለተኛ ዙር ያለፈቹ ተወዳዳሪዎች ደሞ እኛ በምንሰጣቹ ዕርስ ትወዳደራላቹ

#3ተኛ ዙር ለይ ደግሞ ወደ3ተኛ
ዙር ያለፋቹ ተወዳዳሪዎች ድጋሚእኛ በምንሰጣቹ ዕርስ ትወዳደሩናባገኛቹት ነጥብ አሸናፊዉን ለይተን ውድድሩ እናጠናቅቃለን

-#ሽልማቱ ምንድነው ካለቹኝ በዚ ዙር አንድ ተሸለሚ ሲኖረን ይህም ማለት

#1ኛ የወጣውን ብቻ ስንሸልም ሽልማቱም #የ100 ብር ካርድ ነው

#የሽልማቱ መጠን የተወዳዳሪዎች ፉኩኩሩ እየታየ ሊጨመር ይችላል

#ሌላው ለየት የሚያረገው ነገር የሽልማቱ ወጪ ሙሉበሙሉ በእስፖንሰር ነው ሚሸፈነ

#ለመመዝገብ ከታች ያለውን #አድራሻ ይጠቀሙ👇

@jozmareyam @jozmareyam
ወይም
@Heyawbot @Heyawbot

ውድድሩ የሚካህድበት ቻናል
👇
@heyawubear @heyawubear @heyawubear @heyawubear
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ኢትዮጵያዊ ነኝ
.
በላሊበላ አስቀድሼ፣ ሸህ ሁሴን ባሌ የተገኘሁ፤
በአባ ገዳ ተመራርቄ፣ መካ ላይ እርዝቅ ያገኘሁ፡፡
ሀመር የቡርጆ አደራ
ፈጣሪ ከሰጠኝ በረከት፣ ዘመን አያነጥፈው ወረት፤
የሚገባኝን ለሰጠኝ፣ የሚገባውን የምገመድል፤
ለሞላልኝ የማላጎድል፡፡
በሲዳማ ጨንበለላ፣
በወላይት ጊይታ፣
ቢያሻኝ በቅዱስ ዮሀንስ፣
የዘመን ጥባት የምከትብ፣ አዲስ አመት የማወድስ፡፡
በጅምላ የማልቀመስ፤
በችርቻሮ የማልረክስ፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ሳነቴ ላይ ውርጭና ጉም፣ ዳሽን ጫፍ ግግር በረዶ፤
ደሎ መና የአዋራ ጭስ፣ ዳሎል ላይ የእሳት እርጎ፡፡
ይርጋለም ያጋጥኳትን ላም፣ ወለጋ ላይ አስጠቅቼ፤
ትኩስ እንገርዋን የጠጣሁ፣ አክሱም ጫፍ ጥገት አስሬ፤
ሰሜን ያለብኩትን ወተት፣ በአርሲ ጮጮ የሞላሁ፤
ጋምቤላ ወተቱን ንጬ፣ የሀረሪ ቆንጆ የቀባሁ፡፡
ወሰን የለሽ እግረ ፌንጣ፣
ሞተ ሲሉኝ ብን - ትር የምል፣ ሄደ ሲሉኝ የምመጣ፤
የቅዠት ምች፣ ህልም ፈቺ፣ ዳነው ሲሉኝ የማገረሽ፤
ወሰን አልባ እግረ ሞረሽ፡፡
ጎጥ አይበቃኝ - የሀገር ስፍር፤
ጎሳ አይገልጠኝ - የሰው ስእል፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ማሳዬ ላይ ገበሬ፣ ምድር አራሽ፣
ድንበሬ ላይ ወቶአደር፣ ጠላት ደምሳሽ፤
ከበሬዬ ቀንበር ከሞፈር፣
ከወገቤ ላይ ዝናር፣
ከጀርባዬ ላይ ዲሞትፈር፣
የማላጣ፤
ለወደደኝ እንዳወዳደዱ፣ ከማሳዬ ፍሬ የማልሰስት፤
ለጠላኝ እንደ ድርፈቱ፣ ከጀርባዬ ባሩድ የምግት፤
እልኸኛ!
እንደምስጥ በቁም የምጥል፤
ተበድዬ የማልተኛ፡፡
ለደፈሩኝ አድዋን ያህል ተራራ፣ ሀውልት ያቆምኩ በሀገሬ፤
ነጻነቴን - ሰንደቄን ያተምኩ፣ ሮም ላይ ተሻግሬ፤
ያውም እንደፈጠረኝ፣ በባዶ እግሬ፤
ኢትጵያዊ ነኝ!!
እንደ እየሱስ እንጂ በፍቅር፣
ለመርዘኛ የተንኮል ስፍር፣
የማልመች፣ አታጥልሉኝ ባይ፣
ክታብ የአብሮነት ሲሳይ.፣
በጅምላ የማልቀመስ፤
በችርቻሮ የማልረክስ፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ጃውሌ የደንጊያ እጣን፣ ከርቤ ከጊንር ቋጥሬ፤
አቦዳይ ጫት ተዘይሬ፤
ጂማ ካባጁፋር መንደር፣ ከአዎል - በረካ ጀባ፤
ሶዶ ዋዳ ተዘፍኖልኝ - ጎዴ ላይ ቃጢራ አድሬ፤
አፋር ላይ በግመል እንገር፣ ምርቃናዬን የሰበርኩ፤
የሀገሬን ባንዲራ፣ ለአፋር ግመል ማተብ ያሰርኩ፡፡
ወሰን የለሽ፣ እግረ ፌንጣ፣
ሞተ ሲሉኝ ብን - ትር የምል፣ ሄደ ሲሉኝ የምመጣ፤
የቅዠት ምች፣ ህልም ፈቺ፣ ዳነው ሲሉኝ የማገረሽ፤
ወሰን አልባ እግረ ሞረሽ፡፡
ጎጥ አይበቃኝ - የሀገር ስፍር፤
ጎሳ አይገልጠኝ - የሰው ስእል፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
------------------
ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
ቅኔ ቢጤ


***************
ሲያሳሳቸው ጊዜ ነገውን ሊሰቅሉት
ሮብ ርቧቸው አስቀድመው በሉት

ስቀለው ስቀለው ስቀለው ይላሉ
ጠርጴዛ ከበው ከጁ እንዳልበሉ

አጠገበው ህብስት አሰከረው ወይኑ?
በ3ተኛው ጩኸት ተገለጠን አይኑ

የፋሲካ ቂጣ ስንዴው ምን ምን አለክ?
ሰው ሰው ይላልን ወይስ አምላክ አምላክ?

ከየት በላህ ስጋ ደምስ ከምኑላይ
ከ'ኔ ትለፍ ብሎ በጽኑ ሲጸልይ
ጽዋ ነበረ ወይ የተራራው ድንጋይ
የወዝ ደም የሞላው የጠጣችሁት ማይ

የፋሲካው ወይን ምን ምን አለክ ደሙ?
የልጅ የልጅ ነውን? ያባት ያባት ጣ'ሙ

ስትቀባበሉት ስትቆርሱ ያየች ለታ
ልጄን ልጄን ነውን? አባቴን አባቴን
የናቲቱ ዋይታ?

ሃሙስ ጾሜን ልዋል አልፈልግም ንፍሮ
አርብ ስጋ አለልኝ ህዝብ ያልበላው አፍሮ

እጅ እጅ ይላል ምነ እማ ያነፈርሽው
የአይሁድን ሞያ መቼ በቀመስሽው

ምንአስቦ ይሆን በ ባዶ እሚለፋ
ቅጭጭት ከግራቸው ባጠባ ላይጠፋ።

አለም ለረገጣት እድፍ ነው ምንጣፏ
ላዘላት ነው እንጂ የሚበራ ጧፏ።



°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
መልካም ምሴተ ሃሙስ ይሁንልን
**********************
tomi

(Toma's tigistu)
@Getem_Lemitemaw
@Getemlemitemaw
ለሰንበታችን 💚!

ውቅያኖስ ሁን እዚህም እዛም ቢጨልፉህ
አንድ አይነት ጣዕም እንዲኖርህ !!

መልካም ዕለተ ሰንበት !

@Getemlemitemaw
@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
ⓜⓊⓛⓊⓖⓔⓣⓐ💚
የማይወዳደር …

የማይወዳደር እኩያ የሚያጣ
ከልቤ ግርጌ ሥር ጣፋጭ ስሜት ወጣ፡፡
ተሰማኝ፡ ወደድኩሽ፡፡ ያንቺን ጣም ለየኹኝ፤
ቈዳዬ ቀመሰሽ፡ ምላሴን ከዳኹኝ፡፡

ኬትኛው አካሌ ፍቅርሽ የወደቀው፡
የሚያርበተብተኝ ጥፍሬን የሚነዝረው?
አካልስ አለው ወይ የሚታይ፡ ሚቀመስ፡
ወንድነት ገላዬን ነክቶ ሚያጐለምስ?

ትንፋሼን ቋጠርኩት ፍቅርሽን ላደምጠው፡፡
የትኛው አካሌን ልሶ እንዳላመጠው
ንገሪኝ አንቺዬ …

‹‹ከደጅ እንዳያድር ዳስም ልጣልለት፤
እንዲህ ያለ ፍቅር አያድርም ከኔ ቤት፡፡
በአዳፋዬ ባያድፍ ንጹሕ፡ ጥሩ ፍቅርሽ፡
ከቆሸሸ ገላ፡ ከዚህ በድን ይሽሽ …››
እንዲ ያለ ልመና ሚዛን አያነሣም፤
የፍቅር ባሕርይ ዙፋንን አይሻም!

የት ጋ ነው ሚሰማኝ?
ምኔን ነው የያዝሺው?

የት ጋ ነውያጣኹሽ? ምኔን አገኘሺው?
ብቻ፡ ከልቤ ሥር ስሜቴ ይፈልቃል፡፡
የደረስሽበትን
ያልደረስሽበትን
ረቂቁ ፍቅርሽ፡ እርሱ ብቻ ያውቃል፡፡




ገጣሚ ረድኤት ተረፈ
የመጽሐፉ ርዕስ :- አንድ ኅሙስ
@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
📜📜ከመጽሐፍት አምድ📜📜
እመጓ ከዶ/ር አለማየሁ

አንድ ተመራማሪ ለአንድ መንፈሳዊ አባት እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረቡለት

አባ ለምንድ ነው ታሪካችሁ ምሥጢር ፤ መድኃኒቱን ምሥጢር ፤ ቅርሱን ሁሉ ምሥጢር ማድረግ ምን ይጠቅማል ።

እኛስ የክርስቶስ ፍቅር የለንምን የቃል ኪዳኑ በረከት አይገባንም እጅግ ምሥጢራዊ ከመሆናችሁ የተነሣ ከትውልዱ ጋር የሚያገናኝ የቅብብሎሽ ድልድይ መሥራት አልቻላችሁም ።

ሁሉ ነገር ምሥጢር ማድረግ ምን ይጠቅማችሁኋል ምን አለ ሁሉንም ነገር ትውልዱ ቢያውቀው ?

አባ መለሱ፦ በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተውታላችሁ ። ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ ፤ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ ፤ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ ፤ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ ።

ምኞታችሁ ልክ የለውም ፤ አምሮታችሁ ብዙ ነው።

የአማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰላቻችኃል። ተው የተባላችሁትን ትሽራላችሁ ፤ የተከልከላችሁትን ትደፍራላችሁ ፤ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ። ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ ፤ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም ። ሁሉ አላችሁ ፤ ግን ባዷችሁን ናችሁ። ሃይማኖት እንጂ (እምነት) የላችሁም ።

መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ መጀመሪያውን ብቻ ሞጭልፈህ ትተኸኝ ትሄዳለህ ። ጥበብን "ሀ ግእዝ ብዬ ላስተምርህ ብሞክር ፤ መንደር ውስጥ በቃረምካት ዕውቀት ተመክተህ በመሰልቸት "ሆ ሳብዕ ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ ።

የግል ታሪካችሁ ቢታይ ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተለከፈከፈ የተማሪ ኮፋዳ ውስጥ ያለ እህል ይመስላል።

ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ ፤ ሰርታችሁ ሀብት ስታፈሩ ፤ ከላይ የሆናችሁትን ሀገር ለቃችሁ ፤ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ፤ ትጀምራላችሁ ትቀጥላላችሁ ፤ በመጨረሻም ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ።

@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
😭 ሰማይ አለቀሰ 😭
ሰማይ አለቀሰ ምድሪትዋን ወደ ታች አይቶ
ቁልቁል ሲያንጋጥጥ ክፋት አንጂ ደግነት አጥቶ
ዝም ብሎ ሲመለከት ቆይቶ ።
ዛሬን ግን አልቻለም ሆድ ሆዱን ብሶታል
አልችል አለ ዉስጡ አንቧ ተናንቆታል
ወንድም ወንድሙን ገድሎ ለለቅሶ ሲቀመጥ
ሰው ሰዉን ጠልቶ ለክፋት ሲቋምጥ
ሰው ሰዉነቱን ረስቶ ስሜቱን ሳይቆጣጠር
አባት ለትንሽዋ ልጁ ሲሆንባት ችግር
ልጁን አስገድዶ ደፍሮ
ሲያመጣባት የዘመናት እሮሮ
እናት ምን ትበል ሆድዋ ዉስጥዋ አሮ
ሰማይ አለቀሰ ይህንን እያየ 😭
ምነው ይህንን ባላይ ምነዉ ባልሆንኩ ሰማይ
ምነው በቀረብኝ ይህንን ሁሉ ባላይ
አረ እኔስ ቀፈፈኝ አልችል አለ ሆዴ 😭😭
ምድርን ከፋፋልዋት ያንተ ያኔ እያሉ
ቆይ እንዴት ይረሳል የአምላክ አንድ ቃሉ
'ምድሪትዋን ሙልዋት' ነበር የሱ አባባሉ
በብሄር በጎሳ ተሞልታ ምድር

አንተ አዛ ነክ እኔ እዚያ እያሉ ድርድር
ድሮማ ነበር አንድነት መተባበር
መቻቻል እና ፍቅር
ታድያ ይሄን ሳጣ ይፈርድብኛል ባለቅስ ባማርር?
እያለ ሰማይ አለቀሰ የሰዉን ስራ አይቶ
ሀዘን ቢሰማው ጭንቁ በርትቶ
ሰማይ አለቀሰ በዝምታ ቆይቶ ።
😭😭😭😭😭😭😭😭

@TDtina
ተፃፈ በ 27/12/2012
እዉነታን መቀበል
..............................
በህይወታችን ውስጠ ከሚያልፉ ክስተቶች አንዱ ነው እዉነታን አለመቀበል ። ብዙ ግዜ አንድ ለረጅም ግዜ አብሮን የቆየን ነገር መሸኘት አለመቻል እዉነታን አለመቀበል ነው ባይ ነኝ። እንዴት? ለምሳሌ፦ ሁለት ለብዙ አመታት አብረው የኖሩ ጓደኛማቾች አንደኛው በስራ በትምህርት ወይም ሌላ ለህይወቱ ግብአት በሚሆኑት ነገሮች ካለበት ወደ ሌላ ስፍራ መሄድ ይኖርበታል። አንደኛው ይህንን እዉነታ መቀበል ስለሚከብደዉ ጓደኛዉ ከሚሄድበት ለማስቀረት አልያም እንቅፍት ለመሆን ይነሳል።
..................................
እንደዚህ አይነት ነገሮች የሚፈጠሩት ምናልባትም አብረውን የቆዩ ነገሮች ሁሉ የኛ ይመስሉናል። ሁሌም የማይለዩን የኛ ብቻ ነገር ግን ወደ ህይወታችን የገቡ ህይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ ለራሳቸውም ግዜ፣ ለኔ ግዜ እንደሰጡኝ ለሌሎችም ያስፈልጉ ይሆናል ብሎ ማሰብ አይከፋም። እና ምንም ነገር ሲፈጠር በስሜታዊነት ነገሮችን ከመረዳት ቆም ብሎ ማሰብ ጥቅም አለው።
..................................
እዉነታ ምንድነው? እንዴትስ ላዉቀዉ እችላለሁ? እና የመሳሰሉትን እራስ መጠየቅ እና ስህተት አንዴ ቢፈጠር በሁለተኛው ለማስተካከል መጣር "ስትሄድ የመታክ ድንጋይ/እንቅፋት/ ስትመለስም ከመታክ ድንጋዩ አንተ ነክ"
አንዴ ተሳስተክ በሁለተኛው ስህተቱን ከደገምክ የተፈጠረው ነገር ሳይሆን አንተ ነክ ስህተት።
......................................
በመጀመሪያ እንዳትሳሳት እዉነታን መርምር ተቀበል ። እሱን ሳታደርግ አንዱ ካመለጠክ እዉነታዉን በመቀበል አስተካክል።።

የዛሬን አበቃሁ!!
ትንቢት ዳንኤል/Tina
For any comment
@TDtina
Audio
😭ስለቃሌ ልሙት😭

ህይወት ግራ ገብታኝ በውሸት ታምቄ
ለመ ሳቅ ስጣጣር ህመሜን ደብቄ
ጥርሴ እንኳን እምቢ አለኝ ማስመሰል አቃተው
ስቀህ እለፍ ብለው ህመሙን እንዲተው
መድሀኒቴ ብሎ እየጠራህ ዳግም
እስኪ ንገረኛ ታድያ እንዴት ልታከም???????😰
Jerusalem
@Getem_lemitemaw
➴➴➴➴➴➴➴➴
ደሞ ምን አሉ 🤔🤔
➹➹➹➹➹➹
ደሞ ምን አሉ?
ምንስ ተወራ በሀገሩ
ሰው መገደል ወይስ መታሰሩ
⁰⁰⁰⁰⁰⁰⁰⁰⁰⁰
ሞቶ ተገኘ ወይስ ተገደለ
መቼም ዜና የለ ከዚህ የዘለለ
በጋዜጣ በመጽሄት
የሚሰማዉ ሁሉ ጭንቀት
⁰⁰⁰⁰⁰⁰
ዛሬስ ምን ተሰማ? ምንስ ተካሄደ
በምን ጉዳይ ምን ተፈረደ
ሞቶ ለተገኘው ተለያይቶ አካሉ
ምን ምክኒያት ሰጡ
ደሞ ምን አሉ ??

ትንቢት ዳንኤል/Tina
27/5/2013

@silasewoch
#ልብህ_ውስጥ_ምን_አለ?

አንድ ገበሬ፣ በረት ውስጥ ባለ የሳር ክምር ውስጥ የእጅ ሰዓቱ ጠፋበት። ሰዓቱ ለእሱ ተራ አልነበረም፤ የሚወደው አያቱም ማስታወሻም ነበር።

ክምሩ ውስጥም ላይ ታች ፈለገ፤ በኋላም ተስፋ ቆረጠ፡፡ ውጪ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ህጻናትን እንዲረዱት ጠራቸው።

ከእነሱም መሃል ሰዓቱን ላገኘ ሽልማት እንደሚሰጥ ቃል ገባ።

ልጆቹም ይህንን ሲሰሙ እየተሯሯጡ ወደ በረቱ ውስጥ ገቡ። ክምሩንም እየበታተኑ ፈለጉ። ሆኖም ሰዓቱን ሊያገኙት አልቻሉም። ገበሬው ተስፋ ቆርጦ ልጆቹን ይዟቸው ወደ ውጪ ወጣ፤ ከልጆቹ መሃል ያለ አንድ ብላቴና ሌላ እድል እንዲሰጠው ጠየቀ።

ገበሬውም ብላቴናውን ወደታች እየተመለከተው፤ በቅሬታ ፈገግታ “አይ ምን ጥቅም አለው ብለህ ነው፤ የሚገኝም አይመስለኝም” አለና ጉንጩን ቆንጠጥ አድርጎ የእጅ ሰዓቱን እንዲፈልግ ፈቀደለት።

ብላቴናው ወደ በረቱ ገባ፤ ከበረቱ ተመልሶ ሲወጣም በእጁ ሰዓት ይዞ ነበር!

ገበሬው ተደሰተም ተገረመም። ብላቴናውንም፤ “እኛ ፈልገን ያጣነውን አንተ ብቻህን እንዴት አገኘኸው?” ብሎ ጠየቀው።

ህጻኑም መለሰ፣ “ምንም አላደረኩም፤ በጸጥታ መሬት ላይ ተቀምጬ መስማት ጀመርኩኝ። ሰዓቱም ቲክ ቲክ… ሲል ሰማሁት። በድምጹም ተመርቼ አገኘሁት”

አንተ እና እኔ ስንሯሯጥ እንውላለን፤ በጸጥታ እና በስክነት ውስጥ ከማሰብም ይልቅ፤ ምስቅልቅል ያለ እና ማሰርያ አልባ ቀንን እናሳልፋለን።
በጩኸት እና በግርግር ውስጥስ ማን ራሱን ያዳምጣል?
ሰላም ያለው፣ ጸጥ ያለ እና የተረጋጋ አእምሮ፤ ምስቅልቅል ውስጥ ከገባ እና ጥድፊያ ውስጥ ካለ አእምሮ በተሻለ ያስባል። ለደቂቃዎች አእምሮህን ጸጥ አሰኘው፤ የልብህንም ድምጽ … አድምጥ… ድው ድው .ልብህ ውስጥ ምን አለ? ልብህ ምን ይፈልጋል?

🌃መልካም አዳር።❤️
Share&join👇
@Getemlemitemaw
@Getem_lemitemaw
2024/05/13 02:17:41
Back to Top
HTML Embed Code: