።።።።።ፍቅር በሁለት ትርጉም።።።።።
የአንድ ትልቅ ነገር ሁለት ትርጉም
ፍቅር ለሁለት ተተንትኖ ሲተረጎም
አንዱ ፍቅርን አጥቶ ፍቅርን ይሻል
ሌላው ፍቅርን ትቶ በፍቅር ይቀልዳል
#Alazar
@Gitemenlenante
🌿እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሰን!🌿
መልካም የትንሳኤ በዓል
*ያልታደለ*

ባይረዳው እንጂ ፣ሰው ጠላሁ እያለ ፣
ሚያወራ ለቀሪ ፤
ያጣ 'ለት ያውቀዋል ፣አቤት ለማለትም ፣
ያስፈልጋል ጠሪ ።
..........//........
ቀለም እና ውበት

#Helen Fantahun
@Gitemenlenante
ሰላም ውድ የግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች 👥 እንደሚታወቀው ቻናላችን ለእናንተ ለቤተሰቦቻችን ግጥምን እንዲሁም ጠቃሚ የሆኑ አባባሎችና ግጥሞችን እንለቅ እንደነበር ይታወሳል እንዲሁም የቻናላችን ቤተሰቦች የራሳቸውን የግጥም ስራዎቻቸውን ለቻናላችን ቤተሰቦች እንዲደርስላቸው እናደርግ ነበር ሆኖም ከጊዜያት ቦሀላ በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት ከቻናላችን ጠፍተን ነበር ለዛም ይቅርታ እንጠይቃለን 🙏 ከዚህ ቦሀላ ይህ ስህተት እንደማይደገም ቃል እንገባለን እናም በትዕግስት ለጠበቃችሁን የቻናላችን ቤተሰቦች ምስጋናን እያቀረብን አሁንም አብሮነታችን አይለየን ከነገ ጀምሮም ስራችንን የምንጀምር ይሆናል እናመሰግናለን።

#ግጥምን #ለናንተ
አንድ ሰው የሞላ!

ብሎ የሚጣራ...

ኑሮ ያባተለው ጨብራራ ወያላ

አንዱን ሰው ያወርዳል ሊተካ በሌላ

እልፍ ተጓዥ እግሮች መድረስ የቋመጡ

ለመድረስ ሲሮጡ

እድል የቀናለት ገዱ ያማረለት

መንገድ ይጀምራል በዚች ታክሲ ህይወት።

ሹፌሩ ፈጣሪ

ህላዌን አብራሪ 

እስትንፋስን ዘርቶ መንገድ እየለየ

ተጓዥ ይቀበላል

ግፊያውን የረታ የማህፀን ፍሬ

መንገድ ይጀምራል።

ወያላው ሙት መ'ላክ የፈጣሪ ረዳት

መለከቱን ነፍቶ ቆሞ ይለፍፋል

ህይወት ያባከነው ተጓዥ ይሳፈራል

አንድ ሰው የሞላ ...!

ለህይወት ሁለት መልኮች

ለችግር ለተድላ 

መሳፈር ... መሳፈር ...

መጓዝ ...መሄድ ... መብረር.. .

መድረሻን መማተር ...

ከዚህ ጉዞ ላይ ነው 

የደረሰ መስሎት አውርዱኝ የሚለው

ወራጅ የሚፈጠር!


ሚካኤል .አስጨናቂ
@Gitemenlenante
#ጅብ እና ዘንድሮ

የድሮ ጅብ ትህትናው
ከማያውቁት ሄዶ፣<<ቁርበት አንጥፉልኝ ?>>
ነበረ ልመናው ።

የዛሬ ጅብ ድፍረቱ
ባለቤቱ እያየው ፣ ባይኑ በብረቱ
ይሰለቅጥና ፣ ላሚቱን ዘርግፎ
እበረቱ ያድራል ፣ ቁርበቷን አንጥፎ።

@Gitemenlenante
#የእረኛ_ማዕረግ
.
.
ከወዲያ ከጨፌ ከውድማ ከመስኩ፣
ሺህ በግ መጠበቅ ነው የእረኛ ልኩ።
ቀበሮ ቢለፋ ተኩላ ቢነፋፋ፤
ጅብ ጥላውን ቢጥል ቢያጓራ ቢጀነን፣
ለበጎቹ መንጋ፤
መልካ አዋቂ ብልህ እረኛ ነው ደጀን።

ከጥንትም ከወንዙ፤
ተኩላ ያልበጠሰው ጅብ ያላፈረሰው፣
የቀትር ቀማኛ ቀበሮ ያልዳሰው።
የተቆላለፈ የተጠላለፈ፤
ዕጣ ያስተሳሰረው የመዋደድ ሀረግ፣
ተኩላዎች ሲራቡ፤
በኩር በግ መሆን ነው የእረኛው ማረግ።

ለዘመኔ ጥበብ፤
ለዘመንህ ኩታ፤
"ቀን ያልፋል" ላሉት ቃል፤
ጥለቱ እስኪቋጭ እኔ ችዬም አልደርስ፣
እረኛም ልሁን በግ፤
መሰሪም ልሁን ደግ፤
ተኩላው ከሚበላኝ በልቼው ልቀደስ።

"ዐብይ"
@Gitemenlenante
እኔ የምወድሽ እንደ ኮከብ ብዛት
ብዬ ላንቺ ፍቅሬን የነገርኩሽ እለት
የማፍቀሬን ብዛት ለማወቅ ስትጥሪ
የሰማይ ከዋክብትን ስትቆጥሪ እንዳታድሪ።😁

#Alazar#አልአዛር#

ግጥም ለመላክ 👉 @AS_CJman
@Gitemenlenante
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ተመስገን፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በረሀ መሀል ላይ አንድ ሰው ነበረ
ረሀብ ጠንቶበት ብዙ ያማረረ
ፊቱን ካረጠበው የእንባ ጎርፍ ጋራ እየተናነቀ
ምግብ እንዲሰጠው ፈጣሪን ጠየቀ
ፈጣሪም ሳይዘገይ ምላሽ አሳወቀ
በሰማይ የሚበር አንድ ቆቅ ወደቀ
ተመስገንም ሳይል እየተጀነነ
ቆቅ ትንሽ ነው ብሎ ሰውየው አዘነ
በግ ባለመውደቁ ፈጣሪን ኮነነ

#ኤደን #ወልዴ
(እውነትን ፍለጋ)
@Gitemenlenante
አኩርፈሽ አትሂጂ
ከእግሮችሽ መውጣት ጋር ንጋቴ ይመሻል
'ረፍት እንቅልፌ - ካ'ይኖቼ ይሸሻል
ሰላም ፍስሀዬ - እመኚኝ ይሟሻል።
.
ብጠም አትጥመሚ
ተይ አትነሽብኝ - ድንገት አትሟሚ!
.
አኩርፈሽ አትሂጂ
ተይ አትራመጂ
ይወናበደኛል
ወበቅ ቁር ኾኖ ፥ ያንዘረዝረኛል
ብርድ እንደነበልባል ፥ ይለበልበኛል፤
.
ጎጆዬን ለይቶ
ስጉ ወኔዬ ላይ፣ መብረቅ ይባርቃል
በስስ ካፊያ ፈንታ፣ ነጎድጓድ ይወድቃል!
..
አትሒጅ እንደሰው . . .
ከመኖርሽ ሌላ መኖሬ ምን ያውቃል?
ጥቂት ሳልናፍቅሽ
ጥቂት ሳልጠብቅሽ ... ዘመኔ ያበቃል።

@Gitemenlenante
/// ሰፈሩ ቀመሰሽ ///

የእናትሽን ሙያ አትርሽ የጥንቱን
ጠጅን ጥሎ ጠላ ዶሮ መበለቱን
ቆጥረሽ አስረክቢ ይለካ ሴትነት
ስንት ነው ዘንድሮስ ያ የዶሮ ብልት
ድፎ ዳቦ ደፍተሽ ሲጠራ ጎረቢት
ባልሽ እንዲቆርሰው አቅርቢ በኩራት
የጠላውን ማማር ተማርሽ ወይ ከናትሽ
ጠጅ አጣጣሉ ነው ዘንድሮስ ያቃተሽ
በውድ የተገዛው ማሩን አበላሽተሽ
ስኳር ስኳር ስትይ ሰፈሩ ቀመሰሽ

@Gitemenlenante
ለስላሳ ሸክላ

(በረከት ለማ)

የጊዮን ወንዝ ዉሃ ከምድር አፈር ተማስሎ
ንፋስ እየተቀባ አካሉ ተድበልብሎ
የተሰራ ሸክላ ነዉ፣
ሰዉ የደም ጅረት የሚፈስበት
ገል የሚሆን ገላ ነዉ!

ወፎቹ ነግቷል ሲሉት ነቃሁ ብሎ ይነሳል
ከጉም የተሸመነ የዕለት ዕድሉን ይለብሳል
ሞፈር ያቀባብላል የኑሮን ሜዳ ለማረስ
በለስ ከቀናዉ አዱኛ ካልቀናዉ አመድ ለማፈስ፤

ሲታገል ይዉልና ገላዉ ላብ እያነባ
የጥሪት አዝመራዉን ወደ ኪሱ እያስገባ
ያለፈበትን መንገድ ሲያስብ ተመልሶ
ለቀኑ ማሳረጊያ ጎምዛዛ ዉሃ ልሶ
ለምን? ብሎ ሲጠይቅ ለምን ዞሮ ሲመጣ
ለላቡ መነሻ ሚሆን ትርጉም ፈልጎ ሲያጣ፤

ምዕራቡን ሲያስስ በምስራቅ እያደረገ
ከበቀለበት እርቆ ስሩን እየፈለገ
ፍለጋዉ ሲታክተዉ ምሽቱ ሲሄድበት
በፈቃዱ ጭንቀትን መሸመት ሲሆንበት
እራሱን ያወዳጃል ካገኘዉ ተጠልሎ
ክንፎቹን ከዘረጋ 'ትርጉም እኔ' ነኝ ብሎ፤

@Gitemenlenante
ከግጥም አታልፊም

🌓
🌓1

መጣሽም :አልመጣሽ
ኮራሽም: አልኮራሽ
ደመቅሽም ፡አልደመቅሽ
አወቅሽም ፡አላወቅሽ
ብትሽኮረመሚ፡ ብትኮሳተሪ
ዝም ፡ጭጭ ፡ብትይ ፡ደሞም፡ ብታወሪ
ብትገላመጪ ፡ብትንቀባረሪ
መፅሐፍ ፡ብትደግሚ፡ ቁርአን ፡ብትቀሪ
መሐይም፡ ብቶኚ፡ አልያ ፡ብትማሪ
ያሻሽን፡ ቢያረግሽ፡ ያሻሽን ፡ብቶኚ
,ልብሽ ፡ቢርገበገብ፡ አልቅሰሽ፡ ብታዝኚ
ብትንከራተቺም እኔን አታገኚ!
ምናልባት!
አንጀቴ፡ እንኳን ፡ሳስቶ፡ ልቤ ፡ቢወድሽም
አድናቆት፡ ካለው፡ ቃል፡ ከግጥም፡ አታልፊም

#በዳዊት ጥዑማይ
@Gitemenlenante
Channel photo updated
🌼🌼🌼🌼እንኳን ለ 2014 አዲስ አመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ/ን በአሉ የሰላም የፍቅር የጤና የአንድነት የመተሳሰብ ይሁንልን🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼 መልካም አዲስ አመት🌼🌼🌼
Live stream finished (24 seconds)
2024/06/16 09:57:52
Back to Top
HTML Embed Code: