Telegram Web Link
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
ሻሎም ቅዱሳን
ነገ እሁድ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ልዩ የትምህርት፣ የአምልኮ እና የጌታ እራት ጊዜ ይኖረናል። በአካል ተገኝተው አብረውን ጌታን እንዲያመልኩ በክብር እንጋብዛለን።
>>>>> ነጭ በነጭ ለብሰን በመገኘት ጌታን አብረን እናምልክ!!! <<<<<
ብሩካን ናችሁ!
53🔥5👍4🥰4
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)

.....እስቃለሁ!!!😂😂😂

“እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።”
— ኢሳይያስ 61፥3

✍️ ጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ በምድር ላይ ከተላከበት ተልእኮ መካከል አንዱ ደስታን ወደእኛ ሕይወት ማምጣት ነው። በሕይወታችን ከገጠሙን ማንኛውም ለቅሶ ፈንታ የደስታ ዘይት እንዲሁም ባሳለፍናቸው ኀዘኖች ፈንታ የምስጋናን መጎናጸፊያ ሊሰጠን ተልኳልናል።

— ዕብራውያን 1፥9

ጌታ ኢየሱስ ከተቀባበት ቅባት አንዱ የደስታ ቅባት ነው። ደስታ በዋነኝነት ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ በሳቅ ነው። ሳቅ መድኃኒት የሆነና ውስጣችን ያለውን የእግዚአብሔርን ደስታ የምንለማመድበት አንዱ መንገድ ነው።

— መዝሙር 59፥8

#መሳቅ_ጠላቶችህን_መናቅ_ነው!

እግዚአብሔር በብዙ ቦታ ጠላቶቹን ምላሽ የሚሰጠው በመሳለቅ እና በመሳለቅ ነው። አንዱ ለሁኔታ፣ ለችግር እና ለጠላቶቻችን መልስ የምንሰጠው እንደ እግዚአብሔር አባታችን በመሳቅ ነው። ይህም የሚያሳየው በእግዚአብሔር ላይ ያለንን መተማመን ነው።

ድብርት፣ ጭንቀት፣ በሽታ ወዘተ ሕይወታችንን አስረው በኀዘን እንዳይሞሉን የእግዚአብሔርን ደስታ በመሳቅ ልንለማመድ ይገባል። በመንፈስ ቅዱስ የሆነው ደስታ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ነገር ግን በጌታ ላይ የተመሠረተ የሕይወታችን ዘይቤ ነው።

ታዲያ በሰማይ ያለው እግዚአብሔር አባታችን ይስቃል፤ ምድር ያለነው እኛ ልጆቹ እንስቃለን! ጠላት ካመጣው ኀዘን ሁሉ እናመልጣለን!

— መዝሙር 2፥4

ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
05/12/2016
መልካም የደስታ ምሽት!!
94🥰12👍10🔥6
Forwarded from Abresh Yilma
ሻሎም ቅዱሳን! የዛሬውን የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው አብረውን ይሁኑ!
https://youtube.com/live/kk0t5kSgOMc?feature=share
30👍5🥰3
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)

.....እስቃለሁ!!!😂😂😂

“እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።”
— ኢሳይያስ 61፥3

✍️ ጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ በምድር ላይ ከተላከበት ተልእኮ መካከል አንዱ ደስታን ወደእኛ ሕይወት ማምጣት ነው። በሕይወታችን ከገጠሙን ማንኛውም ለቅሶ ፈንታ የደስታ ዘይት እንዲሁም ባሳለፍናቸው ኀዘኖች ፈንታ የምስጋናን መጎናጸፊያ ሊሰጠን ተልኳልናል።

— ዕብራውያን 1፥9

ጌታ ኢየሱስ ከተቀባበት ቅባት አንዱ የደስታ ቅባት ነው። ደስታ በዋነኝነት ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ በሳቅ ነው። ሳቅ መድኃኒት የሆነና ውስጣችን ያለውን የእግዚአብሔርን ደስታ የምንለማመድበት አንዱ መንገድ ነው።

— መዝሙር 59፥8

#መሳቅ_ጠላቶችህን_መናቅ_ነው!

እግዚአብሔር በብዙ ቦታ ጠላቶቹን ምላሽ የሚሰጠው በመሳለቅ እና በመሳለቅ ነው። አንዱ ለሁኔታ፣ ለችግር እና ለጠላቶቻችን መልስ የምንሰጠው እንደ እግዚአብሔር አባታችን በመሳቅ ነው። ይህም የሚያሳየው በእግዚአብሔር ላይ ያለንን መተማመን ነው።

ድብርት፣ ጭንቀት፣ በሽታ ወዘተ ሕይወታችንን አስረው በኀዘን እንዳይሞሉን የእግዚአብሔርን ደስታ በመሳቅ ልንለማመድ ይገባል። በመንፈስ ቅዱስ የሆነው ደስታ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ነገር ግን በጌታ ላይ የተመሠረተ የሕይወታችን ዘይቤ ነው።

ታዲያ በሰማይ ያለው እግዚአብሔር አባታችን ይስቃል፤ ምድር ያለነው እኛ ልጆቹ እንስቃለን! ጠላት ካመጣው ኀዘን ሁሉ እናመልጣለን!

— መዝሙር 2፥4

ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
05/12/2016
መልካም የደስታ ምሽት!!
50👍9🔥5🥰1
2025/10/31 11:58:39
Back to Top
HTML Embed Code: