Telegram Web Link
“አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፣ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤ በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም። እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ።”
ኢሳይያስ 43 : 1 - 3
124👍19
“‘ወደ እኔ ጩኽ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና የማይመረመር ነገር እገልጥልሃለሁ።’”
ኤርምያስ 33 : 3

"Through prayer, we can defeat our enemies and receive powerful blessings from the Lord."
Blessed day.
Rev Tezera Yared
83🔥32👏4👍2🥰1
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)

"... ክርስቶስ..."

የዮሐንስ ወንጌል 1:34 አማ05
እኔም ይህን አይቼአለሁ፤ ስለዚህ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እመሰክራለሁ።”

✍️ ኢየሱስ የሰራው ነገር ከኢየሱስ በላይ መሆን የለበትም። ማለትም የኢየሱስ ስራ ከኢየሱስ ማንነት አስታርቀን መማር እና ማወቅ አለብን። የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት የእግዚአብሔር ልጅነት ነው!

ክርስቶስ የኢየሱስ የአባቱ ስም አይደለም! ክርስቶስ ማለት በግሪክ "CHRISTOS" ሲሆን በዕብራይስጥ "MASHIYACH" or "Messiah" ማለት ሲሆን ትርጓሜውም የተቀባ ማለት ነው።

በመሆኑም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቶስ የሚለውን ቃል የእግዚአብሔር ልጅ ከሚለው ጋር በተለዋዋጭነት ይጠቀመዋል።

JESUS was Christ at His birth!

በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ለመቆየት እና ጸንተን ለመኖር የሚያስችለን ሌላ ነገር ሳይሆን ኢየሱስ ክርሰቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ማወቅና ማመን እንዲሁም ከእርሱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ማድረግ ነው።

የዮሐንስ ወንጌል 6:69 አማ54


የእግዚአብሔር ልጅ ማለት እና ክርስቶስ ማለት የሚያመለክተው የኢየሱስን መለኮትነት ማለትም እግዚአብሔር መሆኑን ነው።

ኢየሱስ ግን ክርስቶስ ነኝ ብሎ ሲናገር እግዚአብሔር እንደሆነ ወይም መለኮት እንደሆነ ማረጋገጡ ነበር።
በመጨረሻም ክርስቶስ ስንል እንዲሁም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ስንል መለኮትነቱን እንደሚያመለክት እንረዳለን።

ዮሐንስ 11:27
እርሷም፣ “አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አምናለሁ” አለችው።

ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 07/07/2017
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም ምሽት!
78🔥11👍6👏3🥰2
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
እግዚአብሔር ታማኝ ነው!!! ላንተ፣ ላንቺ ፣ለእኔ ለሁላችንም አሜን፤ አሁን እያለፍንበት ያለው የትኛውም አይነት ፈተና ማለፊያ እንጂ መስመጫ አይደለም አሜን።
መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
95👍23👏6🔥1
…ወደ ማን እንሄዳለን….?!!
“ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።”
የዮሐንስ ወንጌል 6 : 68 - 69 አማ54
95👍16🔥3
እርሱ መቷል!!!
“ሴትዮዋም፣ “ክርስቶስ የተባለ መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ነገር ይነግረናል” አለችው። ኢየሱስም፣ “የማነጋግርሽ እኮ እኔ እርሱ ነኝ” ሲል ገልጾ ነገራት።”
ዮሐንስ 4 : 25 - 26 NASV
74🔥13👏1
..ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን…!!!

“ሳውል (ዻውሎስ) ግን እየበረታ ሄደ፤ በደማስቆ ለሚኖሩትም አይሁድ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ማስረጃ እያቀረበ አፋቸውን ያስይዛቸው ነበር።”
ሐዋርያት ሥራ 9 : 22 NASV

መልካም ቀን!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
92👍9🔥9🥰4
2025/10/22 20:38:59
Back to Top
HTML Embed Code: