Telegram Web Link
…..ሁሉም ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ!!!!

““እግዚአብሔር መልሶ እንዲሰጠው፣ ለእግዚአብሔር ያበደረ ከቶ ማን ነው?” ሁሉም ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ ነውና፤ ለርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን! አሜን።”
ሮሜ 11 : 35 - 36 NASV

በኛ ሕይወት የሆነው ሁሉ፣ ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ እንጂ ከእኛ በእኛ ለእኛ አይደለምና ክብር ለርሱ ይሁን በሉ!!!

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
117🔥18👍10🥰3
Blessing #78
Reverend Tezera Yared
ቡራኬ 🙌 Blessing

💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

“ከእግዚአብሔር ቤት ባረክናችሁ።”
  — መዝሙር 118፥26

“We have blessed you from the house of the Lord.”
  — Psalms 118:26

አድራሻችን: ከለም ሆቴል ወደ 24 ቀበሌ የሚወስደውን ሃይ ዌይ መንገድ እንደጨረሱ በስተ ግራ በኩል ያገኙናል፡፡

☆ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል ሕይወትዎ ለዘላለም ይለወጣል።

Share 👉🏼 @AgapeGLC
86🔥11👍4
…ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ ነው!!!

“የዚህ ዓለም ሰዎች በገዛ ጥበባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ እንዳይችሉ እግዚአብሔር በጥበቡ ዘጋባቸው፤ ነገር ግን እንደ ሞኝነት በሚቈጠረው እኛ በምናስተምረው ወንጌል የሚያምኑትን ለማዳን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል። መቼም አይሁድ ተአምር ማየትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎች ደግሞ ጥበብን ይሻሉ። እኛ ግን ክርስቶስ ስለ እኛ መሰቀሉን እናስተምራለን፤ ይህም ለአይሁድ መሰናከያ ነው፤ ለግሪክ ሰዎች ደግሞ ሞኝነት ነው። ለተጠሩት ግን ለአይሁድም ሆነ ለግሪክ ሰዎች፥ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ ነው። ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔር በጠራችሁ ጊዜ ምን ዐይነት ሰዎች እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፤ እንደ ሰው አስተሳሰብ ከእናንተ መካከል ብዙዎች ጥበበኞች ወይም ብርቱዎች ወይም ታላላቅ ሰዎች አልነበሩም።”
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 : 21 - 24 , 26 አማ05

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
124👍8👏5🔥3🥰1
…. “የሚመካ በጌታ ይመካ።””!!!!

“በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኗል። እንግዲህ፣ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፤ “የሚመካ በጌታ ይመካ።””
1 ቆሮንቶስ 1 : 30 - 31 NASV

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
115👍7🔥6
“እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።”
1ኛ ቆሮንቶስ 3 : 23 NASV

እኔ የክርስቶስ ነኝ! የሚል ካለ አሜን የክርስቶስ ነኝ ይበለኝ!!
I belong to Christ!!!
መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
205🔥20👏13
እጅግ የተወደድህ መንፈሳዊ አባታችን
ላለፉት ዓመታት በከፍተኛ ትጋት እና መሰጠት ትምህርትህን በመከታተል በከፍተኛ ውጤት የዶክትሬት ዲግሪህን በማግኘትህ እኛ በክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የምንገኝ ልጆችህ የተሰማንን ታላቅ ኩራት እና ደስታ ልንገልጽ እንወዳለን።

We are proud of you sir!
295👏32🥰22🔥16👍8
…..እግዚአብሔር!!!!

“እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም። በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያ ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ። እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤ እኛም ደስ አለን።”
መዝሙር 126 : 1 - 3

መልካም ቀን!!!
ሬቨ, ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
199🔥17🥰5
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
….ጕልበቴ እግዚአብሔር ሆይ፤ እወድድሃለሁ!!!

“ጕልበቴ እግዚአብሔር ሆይ፤ እወድድሃለሁ። እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤ እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ።”
መዝሙር 18 : 1 - 3 (አ.መ.ት.)

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
137🔥7🥰5👏3
…..ሶስት ዓይነት ሰዎች አሉ!!!

በሕይወታችን ውስጥ የሚመጡ ሶስት ዓይነት ሰዎች አሉ።
የትላንት፣ የዛሬ እና የነገ ሰዎች ናቸው።
እግዚአብሔር ትናንት የተጠቀመባቸው ሰዎች በወደፊታችን ላይ ቦታ ላይኖራቸው ይችላል። መተው ስለሄዱ ሰዎች አንጨነቅ እንደውም በፍጥነት ወደ እግዚአብሔር ተስፋዎች ይንሂድ ፤ ያለ ትናንት ሰዎች ወደ ፊታችን ለመግባት እንዘጋጅ።
“በተከሰስሁበት ነገር የመጀመሪያ መከላከያዬን ሳቀርብ ማንም ሊያግዘኝ አልመጣም፤ ነገር ግን ሁሉ ትተውኝ ሄዱ። ይህንም አይቍጠርባቸው። ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙላት እንዲሰበክና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳም መንጋጋ አዳነኝ። ጌታ ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ ወደ ሰማያዊው መንግሥቱም በሰላም ያደርሰኛል፤ ለርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።”
2 ጢሞቴዎስ 4 : 16 - 18 NASV

መልካም ቀን!!!
ሬቨ.ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
142🔥8🥰7👍3
Forwarded from A.R.M.Y. GLC
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🛑ራስን ማሳደግ II ክፍል 2 II እጅግ ድንቅ ትምህርት II በሬቨረንድ ዶክተር ተዘራ ያሬድ

ዛሬ ማታ ሙሉ ትምህርት on YouTube
81🔥4🥰4👏3
….ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ!!!

“ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙላት እንዲሰበክና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳም መንጋጋ አዳነኝ። ጌታ ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ ወደ ሰማያዊው መንግሥቱም በሰላም ያደርሰኛል፤ ለርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።”
2 ጢሞቴዎስ 4 : 17 - 18 NASV

ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ… ጌታ አሜን ብሎ ይህንን ቃል ለሚቀበል ሰው ብርታትን ይስጠው!!!
መልካም ቀን!!!

ሬቨ. ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
131🔥8👍6🥰5👏1
2025/10/20 10:17:34
Back to Top
HTML Embed Code: